ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የውል ስምምነት አካሄደ ።
25/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለአመራሮችና ለኦፊሰሮች የአጭር ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርስቲው አመራሮች በተገኙበት የውል ስምምነት ፊርማ አካሄደ ።
በስምምነቱ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ አመራሩና ኦፊሰሩ አቅም ለማሳደግ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ዩንቨርስቲው ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ በበኩላቸው ተቋሙ እና ከተማው የሰጣቸው ተልዕኮ መወጣት የሚያስችል ስልጠና ልምድና እውቀቱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍10❤2
ባለስልጣኑ በሶስት ዙር ሲሰጥ የቆየውን የዲጅታል የመስክ ስራ አስተዳደር ስልጠነና ተጠናቀቀ
26/02 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች ፣ቡድን መሪዎች እና ሰራተኞች በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማስጀመር በሶስት ዙር የመስክ አስተዳደር /Field managmet system/ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
የባለስልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ስልጠናው መጠናቀቁን አስመልክቶ በቀጣይ ቀናት እንደሚጀመር ገልፀው አሰራሩ ተግባራዊ በማያደርግ ባለሙያ ተጠያቂነት እንደሚኖር አመላክተዋል ።
በቀጣይም የቅሬታ አስተዳደር ሲስተም /complain managnment system / እና የስማርት ቢሮ ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍4