የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ የክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የ6 ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ ።
25/04/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከማዕከል አስከ ወረዳ ካሉ የዘርፋ ኦፊሰሮች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በዘርፉ ከማዕከል አስከ ወረዳ የተሰራው ሰራ አበረታች ቢሆንም የሚታዪ ክፍተቶችን በማረም ስራዎች ጠንክሮ በመሰራት የደንብ መተላለፍ የቀነሰ ማድረግ አንደሚገባ ገልፀዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ አንደተናገሩት በ2016 በጀት ዓመት በስድት ወር ውስጥ ባቀድነው እቅድ መሰረት ያከናወናቸው ተግባራት በጋራ በማየት ጥንካሬዎች ለማስቀጠል የታዪ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ክፍተቶችን ለማረምና ያለንን አቅምና እውቀት ተጠቅመን የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የዛሬው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ የቁጥጥር እና አርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ቀርቧል።
በሪፖርቱ በ6ወር እቅድ አፈጻጸሙ መሬት ወረራን በማስቆም ፣ ህገወጥ ማስፋፋት አና ህገወጥ ግንባታን ቀደም ሲል ከነበረው እየቀነስ መምጣቱን ተገልጿል ።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ በተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው ፦የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

"የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ልክ እየተገነባ ነው።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ታህሰስ 26/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
“ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የወል ትርክት ለሀገር አንድነት” በሚል ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ።
በፓናል መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ከክልሎች የመጡ የስራ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን እና የኪነ ህንጸ ባለሞያዎች እንዲሁም የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።
የዓድዋ ድል በደም እና አጥንት የተገኘ ታላቅ ድል መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ነገር ግን ይህ ታላቅ ድል ላለፉት ዓመታት በሚገባው ልክ አለመዘከሩን ገልጸዋል።
ዓድዋ የነጻነት አርማ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ልክ መገንባቱንም ተናግረዋል።
የዓድዋን ሙዚየም ገነባን ስንል ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ታሪክም ጭምር ነው የገነባነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ገራዊ የጋራ ታሪካችንን እኩል ልንናገረው፣ እኩል ልንኮራበትም ይገባል ብለዋል።
በፓናል ውይይቱ የክልሎች ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ ስነ-ህንፃ ባለሞያዎች እና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።

የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ለአቅመ ደካሞች፣ ለሃገር ባለውለታ አረጋዊያን፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞችና ምንም ገቢ ሌላቸው ከ263 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ ብለን ማዕድ አጋርተናል። በዚህ የበጎነት ተግባር ላይ የተሳተፋችሁ የከተማችን ባለ ሀብቶች፣ በጋራ ሆነን እምባ እያበስን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን ለህዝባችን መግለጽ ስለቻልን አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ በወጣ እጥፍ አድርጎ ይመልስላችሁ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዋሬ አካባቢ በ1523.3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤትች ግንባታ መርቀዋል።
የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የ’መደመር ትውልድ መጽሃፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው። ህንፃዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም እታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው።
በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች የተካተቱባቸው ናቸው። ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ፣ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ ተገጥሞላቸዋል።
ክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕን አርዓያነት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።
#PMOEthiopia

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የገና በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!
''ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
የገናን በዓል ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ በመወለዱ ሰውና መላዕክት በአንድ ላይ ፈጣሪአቸውን ያመሰገኑበት እለት በማሰብ በደስታና በፍቅር ልደቱን በማሰብ በድምቀት ያከብሩታል።
ከዚህም በመነሳት በዓለ ልደቱ የፍቅር፣ የአብሮነትና የሰላም እንደመሆኑ መጠን ሁላችንም በጋራ ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት ያለንን ለሌላቸው በማካፈል ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በማጎልበት ሊናከብረው ይገባል።
በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡
በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘሁ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ እላለሁ።''
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ
ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱ ያስተላልፋል።

👍1
ባለስልጣኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
30/04/2016 ዓ.ም
*ቢሾፍቱ*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ አመራሮች ከታህሳስ 30/2016 እስከ 03/05/2016 ዓ/ም ድረስ በአመራር ክህሎት፣ በእስትራቴጅክ እቅድ አስተቃቀድ፣ በጊዜ አጠቃቀም እና በከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጡ ተጨማሪ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ስልጠናው በ2016 በጀት ዓመት ከያዝናቸው እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑንና ከተማዋን የሚመጥንና ለውጥ አምጪ አመራር ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ የከተማዋን የደንብ መተላለፍ ለመከላከልና ስርዓት ለማስያዝ በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የአመራሩን ብቃት ይበልጥ ለማጎልበት በሚያበቁ ዕውቀቶች በኢንስቲትዩቱ ሙሁራንና ለቀጣይ ሶስት ቀናት ስልጠናው እንደሚሰጥ አስታውቋል።
Leadership and time management ርዕስ ያደረገ ስልጠና የሰጡት የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት አማካሪ እና አሰልጣኝ አቶ ጀማል አህመድ ሲሆኑ፤ ስልጠናውም አሳታፊና አነቃቂ የሆነ እንደነበረ ከተሳታፊዎች ተገልጿል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

❤1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አባቶች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል::
በውይይቱ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አባቶቹ የገለፁ ሲሆን ቤተ-ክርስቲያኒቷን የማይወክሉ ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ፈፅሞ እንደማይቀበሉና እንደሚያወግዙ ይህንንም ለምዕመናቸው ግልፅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በዩኒስኮ በቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል አከባበር ሃገራዊ ቅርስ እንደመሆኑ በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶቹ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::
የሃይማኖት አባቶቹ የከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ አከባበር የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል::

ባለስልጣኑ የበጀት ዓመቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን ከተቋሙ አመራሮች ጋር ገመገመ።
ጥር 03/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ጋር ገመገመ።
ተቋሙ በግማሽ ዓመቱ ለማሳካት ያቀዳቸውን ስራዎች በውጤት ያጠናቀቀበትና ካለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ብዙ ውጤቶች ያሳካበት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሪፖርቱ በጋራ መገምገሙ ሁሉም የራሱን ክፍተት በማየት ለማረም እና በሪፖርቱ ያልተገለፁ ስራዎች ለማስተካከል አንደሚረዳ በመድረኩ ተገልጿል።
የተጠመረውን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርቱን ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ ሲሆኑ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ ትግበራው ድረስ ታቅደው የተከናወኑ ስራዎች እና ና ከዕቅድ ውጭ የተከናወኑ ተግባሮች በሪፖርቱ ቀርበዋል።
የተቋሙ አመራሮች በሪፖርቱ ላይ ሳይካተቱ የቀሩ ነጥቦች በማንሳት በቀጣይ ተካተው እንዲቀርቡ እና በሪፖርቱላይ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተገኝተው ሪፖርቱ ከክፍለ ከተማና ወረዳ ተግባራት ጋር ተናቦ በተሰጠው ሀሳብና አስተያየት መሠረት በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ገልፀዋል።