የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ውይይት እያካሄደ ይገኛል

11/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በዉይይቱም የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፤ የክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣የባለድርሻ አካላት ኃላፊዎችና የማዕከሉ ዳይሬክተሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የመረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡
👍2
ከባለድርሻ ተቋመት ጋር የቅንጅት ተግባራት በማጠናከር ከተማችን ውብ፣ ጽዱና የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

11/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከልና የህግ ማስከበር ስራን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመናበብ በመስራት በከተማችን የደንብ መተላለፍ 83% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።

አክለውም ደንብ ማስከበር በከተማዋ አስተዳደር የተሰጠዎን ተልዕኮ ለመወጣት የቅንጅት ስራዎች ከፍተኛ ሚና ያላቸው እንደመሆኑ በጋራ የመስራት ባህልን በማጠናከር ከተማችን ውብ ጽዱ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ፣ የምሽት ንግድን በመደገፍ ፣ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለትን በመከላከል እንዲሁም የኮሪደር ልማቶች ደህንነት በመጠበቅ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ ውጤታማ ስራዎች መስራት መቻሉን በመድረኩ ተገልጸዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ እና በጉድለት በሰነድ ተለይተው በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል ።

በሪፖርቱ ተቋሙ ከ20 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት በሰነድ በተፈራረመው ልክ ወደ ስራ በመግባት በጋራ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

የመረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡
👍2