የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክ የግጭት ማስተዳደር ስልትን እውቀት አጋራ

  10/02/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ግጭትን የማስተዳደር ስልት(conflict management styles) በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት እውቀትና ልምድ ተጋርቷል፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሰራተኛው ጤታማ ስራ በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን ምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበትና የተቋም ግንባታችን የምናጠናክርበት  መድረክ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል ።
በዕለቱ የባለስልጣኑ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ካላቸው ረጅም ልምድ በመነሳት የራሳቸውን የህይወት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሰራተኞች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

በተጨማሪም ኮለኔል አድማሱ ግጭትን የማስተዳደር ስልት ( conflict management styles )በሚል ለሰራተኛው በተዘጋጀ በሰነድ እውቀት አጋርተዋል ።

ግጭትን አንዱ በሌላው ድርጊት ወይም ግቦች የራሱን ጥቅም አደጋ ላይ ይጥላል ብሎ በሚያምንበት ጊዜ በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚፈጠር አለመጣጣም መሆኑ በሰነዱ ተገልጿል ።

ራስን ሁል ጊዜ በዕውቀት ማዳበር ፣ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጋር መልካም ግንኙኘት መኖር እንደሚገባና ስራን በትብብር  በአንድነት  መስራት ዉጤታማ እንደሚያደርግ በመድረኩ ገልጸዋል ፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ  የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍7
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1,750,000(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

10/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 1,750,000(አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታውቋል።

ቅጣቶቹ በቄርቆስ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ወደ ወንዝ በካይ ፍሳሾችን በመልቀቁ በድምሩ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር፣ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 400,000/አራት መቶ ሺህ/ ብርተቀጥተዋል።

በተጨማሪም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወንዝ በመበከል ፋፋ የምግብ ፋብሪካ 400,000/አራት መቶ ሺህ/ ብር በጉለሌና በየካ ክፍለ ከተማ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 150,000(ሀምሳ ሺህ) ብር እና 200,000(ሁለት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም እያሳሰበ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለባለስልጣኑ አመራር እና ኦፊሰሮች ስልጠና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ውይይት ተካሄደ

10/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለአመራሮች፣ ለባለሙያዎችና ኦፊሰሮች የአጭር ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት የባለስልጣኑ እና የዩኒቨርስቲው አመራሮች ውይይት አካሄዱ ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አመራሩና ባለሙያው የአፈጻጸም አቅሙ ጠንካራ እንዲሆን የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ እና መልካም አስተዳደርን በመረዳት የደንብ ማስከበር አገልግሎቶችን በሚገባ እንዲሰጡ ወቅቱን የጠበቀ ስልጠና ግንዛቤን ለማሳደግ አስፈለጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታምራት ሙሉጌታ ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ስራቸዉን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚችሉበትን በቂ ዕውቀት የሚያገኙበት ስልጠና ልምድና እውቀቱ ባላቸው አሰልጣኞች እንደሚያዘጋጁ ገልፀዋል፡፡

አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለሰልጣኞች አመቺ ቦታ እንዲሁም ከተቋሙ ጋር ተዛማጅነት ያለው ስልጠና ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ኦፊሰሮች ስልጠና የተዘጋጀ መነሻ ሀሳብ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ስልጠና አቅም ግንባታ ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል ።

በተቋሙ ተመድበው የሚሰሩ አመራሮች እና ኦፊሰሮች ወቅቱን መሰረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት የእውቀት ፣ክህሎት ፣አመለካከት ፣ የስነምግባር እና የስራ አፈጻጸማቸውን የላቀ በማድረግ ስለተቋማቸውና ስለሚሰጡት አገልግሎት ሁኔታ ልዩ ባህሪ በቂ ግንዛቤ ይዘው የህዝብ አገልጋይነት ስሜትን ተላብሰው የተቋሙን አላማ ለማሳካት በቀጣይ የሚሰጠው ስልጠና ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
4