የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 820,000(ስምንት መቶ ሀያ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

6/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሽንት ቤት ፍሳሽ ቆሻሻ ከድሬኔጅ ጋር አገናኝቶ የለቀቀ ቱሉዲምቱ ማህበር ቤት 300,000 ብር ተቀጥቷል።

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት አሳማ እርባታ ድርጅት በካይ ፍሳሽ ቆሻሻን ከጎርፍ መውረጃ ቦይ ወደ ወንዝ በማገናኛት 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል።

በእለቱ በደንብ ቆሻሻን በአግባብ አለመያዝና በአይነት ባለመለየትና ወደ ወንዝ በመጣል ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች 120,000 ( አንድ መቶ ሃያ ሺህ) ብር አስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ እርምጃ ተወስዷል።

ተቋሙ መረጃውን ለባለስልጣኑ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍71👏1
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከለ ድርጅት 400,000(አራትት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

07/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በካይ ቆሻሻ ከከፍሳሽ ማስወገጃ ያገናኘው ድርጅት ሳውዝ ጌት ፕላዛ ድርጅት 400,000 ብር የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ድርጊቱ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ኤድናሞል አካባቢ ሳውዝ ጌት ፕላዛ/South Gate plaza/ ፍሳሽ ቆሻሻን ከሽንት ቤት ፍሳሽ ጋር ከ drainage ጋር በማገናኘት ወደ ወንዝ እየለቀቀ መሆኑ ተደርሶበት ተቀጥተዋል ።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍21
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎች ግንዛቤ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር እና ከበጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከር ወጣቶች ጋር ተወያየ

07/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎች ግንዛቤ ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር እና ከበጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከር ወጣቶች ጋር በተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት ዙሪያ ለግንዛቤ የሚሆን እና አብሮ መስራት የሚያስችል የውይይ መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ ከተማዋን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑ ገልፀዋል።

የሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደመሆናቹ፤ የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የተለያዩ የሚያከናውናቸውን ሰው ተኮር በጎ ተግባራትን ለህብረተሰቡ በማሳወቅ የበኩላችሁን ሀላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከተቋሙ ጎን ሆናችሁ አንዳንድ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሀሳብና አስተያየቶችን እየሰጣችሁ ከተማችን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ውብ ጽዱና፣ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶች ምቹ የማድረግ ተግባርን በጋራ እንድንወጣ እናንተም የዜግነት ግዴታችሁን የበኩላችሁን በማድረግ ልታግዙ ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከየት ወዴት ? በሚል የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክተር ወ/ሮ ስርካለም ጌታሁን ቀርቧል ።

በሰነዱ ባለስልጣኑ ከተመሰረተበት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አስከ አሁን ድረስ ያለው ነባራዊ ሁኔታና ያከናወናቸው ተግባራት ፣ መዋቅራዊ አደረጃጀቶቹ በዝርዝር ተገልጿል ።

ከተማችንን ከደንብ መተላለፍ የጸዳች የጸጥታ ችግር የሌለበት ለማድረግ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ያለው ጠቀሜታ ሰፊ በመሆኑ ወጣት የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከተቋሙ ጋር ተቀናጅተው መሰራት እንደሚገባ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል ።

አክለውም የዛሬው መድረክ በጋራ ስራዎችን ለመስራትና የመጀመሪያ የምክክር ፕሮግራም መሆኑንና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ።

በመድረኩ የተገኙት ተሳታፊዎቹ ስለ ተቋሙ ተግባርና ኃላፊነት የተደረገላቸው ገለጻ ከዚህ በፊት ስለ ደንብ ማስከበር የነበራቸው አላስፈላጊ ግንዛቤ የቀየረና መቅጣት ብቻ ሳይሆን በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችንን የሚሰራ እና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በሰፊው በመስራት የደንብ መተላለፍን የሚከላከል መሆኑን በመገንዘብ በቀጣይም የተቋሙ አምባሳደር በመሆን በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸው ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር ሰብሳቢ ጋር በቀጣይ አብሮ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዎል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
1👏1😎1