የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.23K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ጥቅምት 5/2018
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና የክፍለ ከተማ የስልጠና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የባለስልጣኑ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት በተለያዩ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ጥናቶች መስራቱን ጠቁመው በ9ኙ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ምንጮች ለማወቅ እና ችግር ፈች ጥናት ወሳኝ በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ችግሮችን በመለየት ወደ መፍትሄ መግባት እንደሚችል አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ተፈራ ሙሉነህ ተሰጥቷል።

በስልጠናው ጥናት እንዴት እንደሚዘጋጅ፣ ስለ ጥናት አይነቶች ፣ ሰለ አጠናን ዘዴዎች፣ ጥናት ችግርን ለመፍታትና የችግሩን ዋና ምንጭ ለማወቅ እንደሚረዳ፣ ሰለ ጥናት አዘገጃጀት ቅደም ተከተል ዳራ ፣አለማ፣ወሰን ፣የተዛማጅ ጥናት ቅኝት እና ስለ ጥናት መሰረታዊ ባህሪ በመሳሰሉት ዙርያ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ጥናቶች በማዕከል ደረጃ ብቻ ሳይሆን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ መጠናትና ስላለባቸው ሰልጣኞች የወሰዱት ስልጠና እስከታች እንዲወርዱ እና ጥናቶች እንዲሰሩ አቅጣጫ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦ የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍41
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

5/02/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻና ኬሚካል የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ኢትዮ ሌዘር ፋብረ‍ኢካ ኬሚካል ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 800,000 ብር ፣8 የመኖሪያ ቤትና 1 ድርጅት ባመነጩት ቆሻሻ አወጋገዳቸው ደንብን በመተላለፉ ወንዞች በመበከላቸው በድምሩ 592,000/አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ተቀጥተዋል።

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ረጲ ኮምዶሚኒዮም እና ግራር ሆቴል ፍሳሽ ቆሻሻን ከወንዝ በማገናኘታቸው በድምሩ 600,000 ብር፤በቂርቆስ ክ/ከተማ ዲሊኦፖል እንተርናሽናል ሆቴል 300,000 ብር ሲቀጣ በጉለሌ ክ/ከተማ አቶ ሙሉጌታ መንጋ እና አቶ ናትናኤል ገበያው ድርጅት 300,000 ብር ብር ተቀጥተዋል።

በባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለህብረተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ የመጣ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የደንብ መተላለፍ በፈፀሙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶች እርምጃዎችን በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት በድምሩ 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር ቀጥቷል።

ባለስልጣን መረጃ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍7
የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በሁለቱ ተቋም ጠቅላላ ካውንስል ተገመገመ::

ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዲሁም የሁለቱ ተቋማት የማእከል አመራሮች በተገኙበት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የግምገማ መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመክፈቻ ንግግራቸው በሩብ አመቱ መጀመሪያ ዓለም አቀፍም ሆነ ሀገር አቀፍ የሆኑት የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማከናወን መቻሉ የሁለቱ ተቋማት ጥምር ውጤት መሆኑን በማንሳት ከ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በመነሳት ለቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች መዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በግምገማው ላይ የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

በሪፖርቱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ተቋማቱ ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጋር በጥምረት በማያያዝ ክፍተቶችን በመለየት ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ እንደግብአት በመጠቀም በ1ኛ ሩብ አመት ተፈጻሚ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸው በሪፖርቶቹ ተገልጿል።

ከሪፖርቶቹ በመነሳት የተቋማቱ አመራሮች ከተቋም ግንባታ አንጻር ስለሚገኙበት ደረጃ፣ ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ከመግታት አንጻር እየተሰሩ ስለሚገኙ ተግባራት እና ሌሎች በሂደት ላይ ስለሚገኙ ስራዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በማንሳትና የመፍትሄ ሀሳብ በማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በግምገማዊ ውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 2017 በጀት ዓመት ሁለቱም ተቋማት ስኬትን ያስመዘገብንበት ዓመት መሆኑ የተለየ መነቃቃት የመጣበት ነው ያሉት ኃላፊው በ2018 በጀት ዓመትም ይህን ስኬት አስቀጥሎ መሄድ ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።

ከቀረበው የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እንደ ክፍተት የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብአት በመውሰድ በቀጣይ በላቀ መነሳሳት ውጤታማ ስራዎችን የምንሰራበት መንገዶች መፍጠር እና እንደክፍተት ለታዩት ነጥቦችም አዳዲስ አሰራርና የመፍትሄ ሀሳብ በመዘርጋት ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ በግምገማዊ ውይይቱ ማጠቃለያ ተመላክቷል።

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ለቀጣይ የትግበራ መርሀ-ግብር የሚሆን ቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመስጠት ግምገማዊ ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍41
የባለስልጣኑ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸሙ
ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር እየገመገመ ነው

06/02 /2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር እየገመገመ ይገኛል።

መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የተከፈተሲሆን የሁለቱ ተቋማት ሪፖርት ቀርቦ እንደሚገመገም ተመላክቷል።

ዝርዝር ዜናውን መድረኩ እንደተጠናቀቀ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍8👏3