የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.23K subscribers
2.37K photos
5 videos
1 file
57 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ወንዝና አካባቢ የበከሉ ተቋማትና ግለሰቦች 1.800,000 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ብር ተቀጡ

ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ከተማ እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ 9 ግለሰቦችና ተቋማት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ በመበከላቸው በደምብ ቁጥር 180/2017 መሰረት (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ሁሴኔ አብዳለ 150,000፣ ዳኞ አሞኔ 150,000፣ዝናሽ አሰፋ 100,000፣ኤ,ቲ,ኤ,ኤ ድርጅት 300,000፣ኦሮሚያ ግብርና ህብረት 300,000፣ገዛኸኝ ባዴ 50,000፣ሙላቱ አስረድ 50,000 በአጠቃላይ 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) ብር የቅጣት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በተመሳሳይ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሁለት ግለሰቦች የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ ወንዝና አካባቢውን በመበከላቸው ጌትዬ ነጋሽ እና እነ እሱባለው ማስረሻ እያንዳንዳቸው 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በድምሩ 300,000 (ሶትት መቶ ሺ ብር) ተቀጥተዋል።

ባለስልጣኑደ የተለያዩ ቆሻሻ በመልቀቅ ወንዝና አካባቢን የሚበክሉ ግለሰቦችና ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የሚበክሉ ግለሰቦችና ተቋማትን እንደማይታገስ አስታውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ መረጃ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታቸው የሚወጡ ነዋሪዎችን እያመሰገነ መላው የከተማው ነዋሪ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ 9995 ነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀሙ መልዕክቱን አስተላልፏል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4
ባለስልጣኑ በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ጥቅምት 5/2018
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጥናት አዘገጃጀት ዙርያ ለማዕከሉ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና የክፍለ ከተማ የስልጠና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለሥልጣኑ የጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የባለስልጣኑ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት በተለያዩ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ጥናቶች መስራቱን ጠቁመው በ9ኙ የደንብ መተላለፎች ዙርያ ምንጮች ለማወቅ እና ችግር ፈች ጥናት ወሳኝ በመሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ችግሮችን በመለየት ወደ መፍትሄ መግባት እንደሚችል አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ተፈራ ሙሉነህ ተሰጥቷል።

በስልጠናው ጥናት እንዴት እንደሚዘጋጅ፣ ስለ ጥናት አይነቶች ፣ ሰለ አጠናን ዘዴዎች፣ ጥናት ችግርን ለመፍታትና የችግሩን ዋና ምንጭ ለማወቅ እንደሚረዳ፣ ሰለ ጥናት አዘገጃጀት ቅደም ተከተል ዳራ ፣አለማ፣ወሰን ፣የተዛማጅ ጥናት ቅኝት እና ስለ ጥናት መሰረታዊ ባህሪ በመሳሰሉት ዙርያ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን ጥናቶች በማዕከል ደረጃ ብቻ ሳይሆን እስከታችኛው መዋቅር ድረስ መጠናትና ስላለባቸው ሰልጣኞች የወሰዱት ስልጠና እስከታች እንዲወርዱ እና ጥናቶች እንዲሰሩ አቅጣጫ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦ የባለሥልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍51
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ

5/02/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት በወንዞችና የወንዞች ዳርቻ በካይ ቆሻሻና ኬሚካል የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን መቅጣቱ አስታውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ኢትዮ ሌዘር ፋብረ‍ኢካ ኬሚካል ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቅ 800,000 ብር ፣8 የመኖሪያ ቤትና 1 ድርጅት ባመነጩት ቆሻሻ አወጋገዳቸው ደንብን በመተላለፉ ወንዞች በመበከላቸው በድምሩ 592,000/አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ ብር ተቀጥተዋል።

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ረጲ ኮምዶሚኒዮም እና ግራር ሆቴል ፍሳሽ ቆሻሻን ከወንዝ በማገናኘታቸው በድምሩ 600,000 ብር፤በቂርቆስ ክ/ከተማ ዲሊኦፖል እንተርናሽናል ሆቴል 300,000 ብር ሲቀጣ በጉለሌ ክ/ከተማ አቶ ሙሉጌታ መንጋ እና አቶ ናትናኤል ገበያው ድርጅት 300,000 ብር ብር ተቀጥተዋል።

በባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለህብረተሰቡ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ የመጣ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን የደንብ መተላለፍ በፈፀሙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶች እርምጃዎችን በደንብ ቁጥር 180 /2017 መሰረት በድምሩ 2,592,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ) ብር ቀጥቷል።

ባለስልጣን መረጃ በመስጠት የአካባቢ ብክለት መከላከል እንዲቻል የጠቆሙትን የህብረተሰብ ክፍሎችን እያመሰገነ በቀጣይ ህብረተሰቡና ተቋማት ከዚህ ዓይነት ድርጊት እንዲቆጠቡም አሳስቧል:

በተጨማሪም ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍8