የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.27K subscribers
2.47K photos
5 videos
1 file
57 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አዋኪ ተግባራት መከላከል እንዳለበት ተገለፀ

27/ዐ1/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና በስነምግባር ና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት በዘጠኙም የደንብ መተላለፎች ላይ በመስራት በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም ትውልድ ገዳይ የሆነውን አዋኪ ድርጊት በመከላከል ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረው መስራትና እርምጃ እንዲወሰድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
አክለውም ኃላፊዋ ወጣቱን ትውልድ እያጠፍ ከአላማው እያስቀረ ያለውን አዋኪ ድርጊት ተግባር በመቆጣጠር ምንም አይነት የደንብ መተላለፍ እንዳይከሰት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው ለቀጣይም በዘጠኙም የደንብ መተላለፍ ተግባራት ላይ ሰፊ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

በመድረኩም አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል በስነምግባር እና ብልሹ አሰራር መከላከል በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ቁምላቸው ቀርቧል አዋኪ ተግባራት በክፍለ ከተማው ምን እንደሚመስል ፣ አዋኪ ድርጊቶችን እንዴት መፍታት እና መከላከል እንደሚቻል በሰነዱ በዝርዝር ተገልፃል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱት ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።
👍2
ባለስልጣኑ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙ ከጠቅላላ ካውንስል ጋር ገመገመ

27- 01 - 2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን ከባለሥልጣኑ ዳይሬክተሮች ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻው እንዳሉት በዚህ ውይይት በሩብ ዓመቱ በተቋማችን የታዩ ጠንካራ ጎኖች እና ክፍተቶችን ለመፈተሽ ያስችለናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 ዓ.ም በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ሰነድ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።

በሰነዱ እንደተገለጸው የተቋም የአቅም ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር፣የስራ አከባቢን ለሰራተኛውም ሆነ ለተገልጋይ ምቹ ለማድረግ የሚዲያ ሽፍንን በመጠቀም የተቋም ገፅታ በመገንባትና ከተገልጋይ ጋር መድረክ በመፍጠር ግብዓት ለማግኘት መሠራቱን ገልፀዋል።

ኮነሬል አድማሱ ተክሌ ከሪፖርቱ እንደገለፁት በባለስልጣኑ በቦታ 6808 እንዲሁም በካሬ 11,798,292.38 የሚያህል መሬት እየተጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
👍81
ባለስልጣኑ በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱን አስታወቀ

28/01/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እየተሰራ ባለው የአፍንጮ በር የወንዝ ዳርቻ ልማት በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀን የንግድ ተቋም (ጠጅ ቤት) 3 መቶ ሺ ብር መቅጣቱን አስታውቋል።

የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሀላፊ ዋና ሳጅን ውባለም ሽፈራው እንደገለፁት ድርጅቱ በተደጋጋሚ ወደ ወንዝ የሚለቀውን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻ እንዲያቆም ግንዛቤ ቢፈጠርለትም ከድርጊቱ መቆጠብ ባለመቻሉ ከክፍለ ከተማው የአካባቢ ጥበቃ ፅ/ቤት ጋር በመሆን የቅጣት እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ መሰል ደንብ መተላለፎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ገልፀው ደንብ ተላላፊዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል። እየሰሩም እንደሆነ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ድርሻ በመሆኑ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች 9995 ነፃ የስልክ መስመእንዲጠቀሙ ጥሪውን አቅርቧል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባልስልጣን ኮሙኒኬሽ ዳይሬክቶሬት ነው።
👍103
ባለስልጣኑ የመስከረም ወር መደበኛና ወቅታ ተግባራትን ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ

መስከረም 28/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስከረም ወር በእቅድ አፈፀፀምና ወቅታዊ ስራዎች በተመለከ ከክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አደረገ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የመስከረም ወር የአደባባይ በዓላት የነበሩበት ቢሆንም ከዚህ ጎን ለጎን በካስኬዲንግ የወረዱትን ተግባራት በጥራት መስራት መቻሉ ጠቁመዋል።

በውይይቱ የመስከረም ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ ያቀረበ ሲሆን በወሩ የአደባባይ ሁነቶች ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ፣ በ9ኙ የደንብ ጥሰቶች የመከላከል ፣የመቆጣጠር እና አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

በመድረኩ በድክመትና በጥንካሬ የታዩ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል።

በወሩ የተሰሩ ስራዎች ጠንካራ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች ላይ መረጃ በጥንቃቄ መሰራት እንዳለበት እና አስተዳደራዊ ቅጣቶች የቅጣት ደረሰኝ በትክክል መከፈላቸው መረጋገጥ እንደሚገባ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
6