የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.28K subscribers
2.48K photos
5 videos
1 file
57 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ እሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ወደስራ መግባቱ አስታወቀ

22/ዐ1/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበርና እንግዶች ለመቀበል እና በዓሉን ለማክበር የቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።

ለበዓሉ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን በዓሉ በሚከበርበት ቦታ የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር የተቋሙ አመራሮችና ኦፊሰሮች የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ስምሪት በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ በማድረግ ለእንግዶች ምቹነትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር አስፈላጊ አገልግሎቶች ለመስጠት መዘጋጀቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍9👏3
ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን እንኳን ለ2018 ዓ.ም የይቅርታ የመተሳሰብ ምሳሌ ለሆነው የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት በከተማዋ የሚፈጸሙ የደንብ መተላለፎችን እና ህ-ወጥ ተግባራት በመከላከል፣ መቆጣጠር እና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ማራኪና ሰላማዊ እንድትሆን የማድረግ ስራ አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ በክብረ በዓሉ ላይ ታዳሚዎች ለከተማችን መልካም ገጽታ ሲባል በልማት ኮሪደሮች፣ በፓርኮች እንዲሁም በተለያዩ አረንጓዴ ቦታዎች ጉዳት እንዳይደርስ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ እና በቦታው ላይ ለሚገኙ የጸጥታ አካላትና የበዓሉ አስተባባሪዎች በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተገቢውን ትብብር በማድረግ የሰላም፣ የፍቅርና የእርቅ መገለጫ የሆነውን የኢሬቻ በዓል በአንድነት እናክብር።

መልካም በዓል
ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፡፡
👍7🥰51😁1
ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሆራ ፊንፊኔ የእሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ለደንብ ማስከበር አመራሮችና ሰራተኞች ያስተላለፉት የምስጋና መልዕክት፦

መስከረም 24/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ወጥቶ ያለምንም የፀጥታ ችግር ዕሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች፣ኦፊሰሮች እና ሰራተኞች ከፍተኛ ምስጋና አቀረቡ።

ዋና ስራ-አስኪያጁ እንደተናገሩት "ከበዓሉ አስቀድም በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቀን እና በሌሊት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ስምሪት በመውሰድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የባለስልጣኑ ማኔጅመንት አባላት፣የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮች፣ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ዳይሬክተሮች እና የሲቪል ሰራተኞች ላደረጋችሁት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ እንደዚሁም የከተማው ነዋሪዎች በደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!"

በከተማው ከበዓሉ አስቀድሞ በዓሉ የሚከበርበት ቦታ በማስዋብ እና አካባቢውን በማፅዳት እንግዶቹን በየአካባቢው ባማረ መስተንግዶ በመቀበል፣ በዓሉ ሰላማዊ ድባቡን ይዞ እንዲጠናቀቅና የበዓል እሴቱንና ስርዓቱን ጠብቆ በከፍተኛ ድምቀትና በሰላማዊነት እንዲከበር ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ፡፡

በየደረጃው የምትገኙ አመራሮች ይህ በዓል ያለአንዳች እክል በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በትጋትና በንቃት በየተመደባችሁበት ሃላፊነታችሁን በአግባቡ ስለተወጣችሁ አመሰግናለመሁ!!

አሁንም ቢሆን እንግዶቻችን ወደ አካባቢው በሰላም እስኪመለሱ ድረስ በተጀመረው የእንግዳ ተቀባይነት ስሜት እስከመጨረሻው ድረስ በትጋት እና በቅንጅት መስራታችንን እንድንቀጥል እና በነገው እለት የሚከበረው የሆራ አርሰዴ በዓልም በሰላም እንዲጠናቀቅ ፣ ሁላችንም ይበልጥ ተጠናክረን በትብብርና በሃላፊነት ስሜት ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበር ያደረጋችሁት ጥረት የደንብ መተላለፎች በመከላከሉ እና በመቆጣጠሩ ላይ መቀጠል አለበት።

በድጋሚ መልካም የኢሬቻ በዓል!

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ
4
ባለስልጣኑ “ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና” በሚል ርዕስ ውይይት አካሄደ።

27/01/2018ዓ.ም
*አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሀገራችን ስላለችበት እንዲሁም ከህዝቡ ምን ይጠበቃል፤ ያለንበት የጂኦ ስትራቴጂ ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ የተቋሙ አመራሮች እና መላው ሰራተኞች ውይይት አካሂደዋል።

ከጂኦስትራቴጂ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና የሚለውን ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፍሁን አሉላ እንዳሉት ሀገራችን በተግዳሮቶች ውስጥ አልፋ ወሳኝ የሆነ ተጨባጭ ለውጥ አምጥታለች በዚህ ጊዜ አለም ከሉዓላዊነት ወደ አዲስ ጂኦስትራቴጂያዊ የበላይነት ላይ እየሄደች ነው ኢትዮጵያ ደግሞ በጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናቸው ከታደሉ ሀገሮች መካከል አንዷ መሆኖን ገልፀዋል።

አክለውም ከቁጭት ኩስመና ወጥተን እንበልፅግ ነገር ግን ይህን ለማድረግ የምናገለግለውን ህዝብ፣ የምንገነባውን ሀገር ፣የምናስከብረውን ብሔራዊ ጥቅም ታሳቢ ያደረገ ፅኑ አቋም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

መድረኩን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ሀገራችን ከታላላቅ ሀገራት መካከል የምትመደብ ነበረች የአክሱምን እና የላሊበላ አቢያተ ቤተክርስቲያንን እንደ ማሳያ ማየት እንደሚቻል እናወ ቀደመው ገናናነትዋ ለመመለስ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ይህንን ትልቅነታችንን ለመመለስ ኢትዮጲያዊ የሆነ ሰው በሙሉ የብሔር፣የሀይማኖት የባህል እንዲሁም የተለያዮ ልዮነቶች ቢኖረንም በሀገራችን ጉዳይ ግን አንድ ልንሆን ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ ሀሳብ አስተያየቶች ተሰተው ወይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
2👍1
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት አዋኪ ተግባራት መከላከል እንዳለበት ተገለፀ

27/ዐ1/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና በስነምግባር ና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት በዘጠኙም የደንብ መተላለፎች ላይ በመስራት በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም ትውልድ ገዳይ የሆነውን አዋኪ ድርጊት በመከላከል ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጋር በመቀናጀት የግንዛቤ ስራዎችን አጠናክረው መስራትና እርምጃ እንዲወሰድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
አክለውም ኃላፊዋ ወጣቱን ትውልድ እያጠፍ ከአላማው እያስቀረ ያለውን አዋኪ ድርጊት ተግባር በመቆጣጠር ምንም አይነት የደንብ መተላለፍ እንዳይከሰት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው ለቀጣይም በዘጠኙም የደንብ መተላለፍ ተግባራት ላይ ሰፊ ስራዎችን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

በመድረኩም አዋኪ ድርጊቶችን መከላከል በስነምግባር እና ብልሹ አሰራር መከላከል በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ቁምላቸው ቀርቧል አዋኪ ተግባራት በክፍለ ከተማው ምን እንደሚመስል ፣ አዋኪ ድርጊቶችን እንዴት መፍታት እና መከላከል እንደሚቻል በሰነዱ በዝርዝር ተገልፃል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱት ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።
👍2