ባለስልጠኑ አዋኪ ድርጊቶችን በመከልከልና በስነ_ምግባር ብልሹ አሰራር ዙርያ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
15/1/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣኑ ከጉለሌ ፣ አራዳ ልደታ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከተወጣጡ የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አዋኪ ድርጊቶችን በመከልከልና በስነ_ምግባር ብልሹ አሰራር ዙርያ በጉለሌ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ።
መደርኩ በሀገር ሽማግሌዎች ፣ በሀይማኖት አባቶች እና በሀዴ ስንቄዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የከተማዋን ደንብ ጥሰቶች በመከላከል በመቆጣጠር ከተማዋን ውብና ፅዱ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ምክትል ሰራ አስኪያጁ አዋኪ ድርጊቶች ትውልድን የሚጓዳ የትውልድ ጠንቅ በመሆናቸው የከተማው ነዋሪ ከባለስልጣኑ ጋር በመስራት በአካባቢው የሚገኙ አዋኪ ድርጊቶችን መከለከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ከተማችን ውስጥ የሚሰሩ በርካታ የልማት ስራዎች ቢኖሩም ብልሹ አሰራሮችም ስለሚኖሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የማድረግ ሰራዎች በመስራት ህብረተሰቡን የማንቃት ስራ መሰራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በአዋኪ ድርጊቶችን በመከላከለ ዙርያ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ አሰልጣኝ በሆኑት ዶ/ር ዋና ኢኒስፔክተር ኤርሚያስ ከበደ እና ''ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለመከላከል የህብረተሰብ ሚና'' በሚል የተዘጋጀ ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ቀር ምክክር ተካሂዶበታል።
በሰነዱ የማህበረሰባዊ እሴቶች ምንነትና ጠቀሜታ፣ ከማህበረሰብ እሴቶች ስለማፈንገጥ፣ የማህበረሰብ ጠንቅ የሆነው አዋኪ ድርጊቶች በአዲስ አበባ ምን እነደሚመስል ፣ አዋኪ ድርጊቶችን እንዴት መፍታት እና መከላከል እንደሚቻልና ሙስና ስለሚያስከትለው ጉዳት ግንዛቤ ተፈጥሯል።
ስልጠናው በጣም ጠቃሚ በመሆኑ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መሰጠት እንደሚገባ እና የከተማው ነዋሪ ከባለስጣኑ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየታቸውን ተሰጥተዋል።
ዘገባው ፦ የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍7
ባለስልጣኑ የመስቀል ደመራ በዓል አፈጻጸም ገምግሞ መጪው የእሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት አካሄደ።
19/ዐ1/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር አፈጻጸም ሪፖርት እና የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር በተሳካ ሁኔታ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላምና በአብሮነት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጸዋል ።
በመስቀል ደመራ በዓል ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የታየውን ጥንካሬ በማስቀጠልና የታዩ አንዳንድ ክፍተቶችን በማረም መጪው የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅና የደንብ ጥሰት እንዳይፈጸም ከወዲሁ ዝግጅቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል ።
ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የተወሰዱ ተሞክሮዎች እና ለእሬቻ በዓል ግብዓት የሚሆኑትን ለመገምገም የተዘጋጀ አጭር ሰነድ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ቀርቧል።
የእሬቻ በዓል ለማክበር ወደ ከተማችን ከአራቱም አቅጣጫ የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደመኖራቸው እንግዳ ተቀባይነታችንን በማሳየትና በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ሁሉም አካል የድርሻውን ሚና መወጣት እንዳለበት የባለስልጣኑ ም/አስኪያጅ አቶ ንጋት ዳኛቸው ገልጸዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ም/ ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ስራዎችን በስኬት ለማጠናቀቅ ስራዎችን በየጊዜው መገምገም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ በመስቀል በዓል የታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል የእሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የተሰጠንን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ተቀምጧል ።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍4❤1