የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.15K subscribers
1.96K photos
5 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ታህሳስ 12//04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ለነበረው የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለመፈተን በስፍራው ለተገኛችሁ እና የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በመቀበል ውሳኔውን ላከበራችሁ ሰራተኞች በሙሉ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ጠይቋል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት በመስጠት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ቀን ማለትም በ 12/04/2016 ዓ.ም ፈተና ለመፈተን ሙሉ ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም ፈተናው የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባጋጠመው ቴክኒካል ችግር ምከንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በእለቱ ከረፋዱ 5:00-11:30 በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና በትእግስት የፈተናውን መሰጠት ስትጠባበቁ ለነበራችሁ የ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ነገር ግን በእለቱ በሰራተኛው ላይ ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ ይቅርታ ጠይቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች በተረጋገጠ ሰላም አና በተረጋጋ ስሜት ፈተናውን እንዲወስዱ የተለመደ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ላሳየው እና የሰላም አርበኛ ለሆነው የመንግስት ሰራተኛ በሙሉ ቢሮው ምስጋናን አቅርቧል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በመቀበል የትራንስፖርት አቅርቦት በማመቻቸት፣የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ እና ሰላም እና ፀጥታን በማስጠበቅ ሙሉ ድጋፍ ላደረጋቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ቢሮ ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያስታወቀ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በ ኦረንቴሽን ወቅት የተቀመጡ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተው ለፈተና እንዲገኙ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

በተመሳሳይም የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይቅርታ መጠየቁም አይዘነጋም።

መረጃው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነው።
ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

**አዲስ አበባ**
16/04/2016 ዓ.ም

"ከእዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ የፕብሊክ ሰርቪስ እና የፍትህ ልዩ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ለተካታተይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡

ስልጠናው በሃብት ፈጠራ፣ በገዢ ትርክቶች፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ በአገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ግንበታ እና የሰላም ባህልን አመለካከት የመገንባት እና የመምራት ክህሎት ጉዳዮች በተመለከተ ውጤታማ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የተኙ ሲሆን አባላቱ ከልዩነት ይልቅ የጋራ የሚያደርጉንን ገዥ ትርክቶችን በማንፀባረቅ ሕብረ-ብሔራዊ አንድናታችንና ሰላማችንን ማጽናት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የበሀገራች ብልጽግና ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች አየተሰሩ መሆኑ በመግለጽ በኢኮኖሚ የበለጸገች ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አባላቱ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበተ አሳስበዋል፡፡

የስልጠናው የተሳታፊ የሆኑ አባላት በበኩላቸው በስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግነታቸውን ገልጸው ሕብረ-ብሄራዊ አንድነትን ለመገንባትና ስልጡን እና ስነምግባር ያለው የሲቪል ሰራተኛ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉ በቁርጠንነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አባላቱ በተሰጠው ስልጠና መሠረት በቀጣይ ተግባራዊ የሚደረጉ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትና ለተግባራዊነቱ ቃል በመግባት ስልጠናው ተጠናቋል።

ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ አባላቱ አንድ ላይ በመሆን የኢትዮጵያ አንድነት ማሳያ የሆነው የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያንና የጥቁር ህዝብ ቅርስ እና የአንድነት የጀግንነት ማህተም መሆኑ እና ብ
ማሳያ መሆኑ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
በቅርቡ በህገ ወጥ መንገድ ሲሰሩ እርምጃ በተወሰደባቸው የቤቲንግ ቤቶችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካኔደ።

ታህሳስ 18/4/2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ )

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በቅርቡ በቤቲንግ ስፖርት ቤቶ ላይ የሚስተዋሉ አላግባብ ጸጥታን የሚያደፈርሱ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ጉዳዩን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በራስ አምባ ሆቴል ውይይት ተካኒዷል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፦አዲስ አበባ ከተማ በየግዜው የኢኮኖሚ ግብይትን በማዘመን የምትታወቅ ከተማ እንደ መሆኗ መጠን በንግድ ና ነጋዴው መካከል ባለው ስርዓት ውስጥ ሀገራዊ ፍይዳው የጎላ መሆኑን ጭምር በመጠቆም ከቅርብ ግዜ ጀምሮ ግን ህግና ስርዓትን ባልጠበቀ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ማህበረሰቡ ላይ ማህበራዊ ጫና በመፍጠር ተቀባይነት የሌላቸው እየተበራከቱ ከመምጣታቸው ባሻገር ከተማውን የሁከት ብጥብጥ የጸረ ሰላም ሀይሎች መሰብሰቢያ የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፍፊያ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል ።
ሀላፊዋ አያይዘውም ህጋዊ ሆነው ስርዓትን ባልጠበቀ መልኩ በሚሰሩ በቀጣይ እርምጃው እንደሚቀጥል በመጠቆም በቀጣይ እርምጃ የተወሰደባቸውን የቤቲንግ ቤቶቹን በተመለከተ መደረግ ስላለበት ጉዳይ አስፈጻሚው አባል የሚሰጠውን አቅጣጫ እናሳውቃለን ሲሉ ተደምጠዋል ።

በጉዳዩ ላይና በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎቹ ለቀረበው ሀሳብና አስተያየት ከሚመለከተው አካል ምላሽ ተሰቶበት ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባው፦የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ነው።
ባለስልጣኑ በመንግስት ንብረት አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

                 **አዲስ አበባ**
                   18/04/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለተወጣጡ የንብረት እና የፋይናንስ ባለሙያዎች በመንግስት ንብረት አያያዝ እና አወጋገድ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አዳነ ለገሰ እንደገለጹት ስልጠናው በአዲሱ በመንግስት ንብረት አያያዝና አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 2/2015 መሠረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

በስልጠናው የተገኙት የባለስልጣኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን በበኩላቸው ሰልጣኞች በሰለጠኑት መሠረት በመስራት ያለአግባብ የሚባክነው የመንግስት ሃብትና ንብረት ከብክነት ማዳን እንደሚገባ ተናግረዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች በበኩላቸው  የተሰጠው ስልጠና አስፈላጊ እና ጊዜውን መሠረት ያደረገ መሆኑ በመግለፅ በቀጣይ ህግንና መመሪያ ተከትለን እንድንሠራ በእጅጉ ይረዳናል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፡፡

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዳይሬክቶሬት ነው።
የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ የክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የ6 ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ ።

     25/04/2016 ዓ.ም
        አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ከማዕከል አስከ ወረዳ ካሉ የዘርፋ  ኦፊሰሮች ጋር  የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል ።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በዘርፉ ከማዕከል አስከ ወረዳ የተሰራው ሰራ አበረታች ቢሆንም የሚታዪ ክፍተቶችን በማረም ስራዎች ጠንክሮ በመሰራት የደንብ መተላለፍ የቀነሰ ማድረግ አንደሚገባ ገልፀዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ አንደተናገሩት  በ2016 በጀት ዓመት በስድት ወር ውስጥ ባቀድነው እቅድ መሰረት ያከናወናቸው ተግባራት በጋራ በማየት ጥንካሬዎች ለማስቀጠል  የታዪ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ክፍተቶችን ለማረምና ያለንን አቅምና እውቀት ተጠቅመን የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የዛሬው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።

የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ በባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ የቁጥጥር እና አርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል ቀርቧል።

በሪፖርቱ በ6ወር እቅድ አፈጻጸሙ መሬት ወረራን በማስቆም ፣ ህገወጥ ማስፋፋት አና ህገወጥ ግንባታን ቀደም ሲል ከነበረው እየቀነስ  መምጣቱን ተገልጿል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር  ሰፊ ውይይት  በማድረግ በተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው ፦የባለስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
"የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ልክ እየተገነባ ነው።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ታህሰስ 26/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

“ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የወል ትርክት ለሀገር አንድነት” በሚል ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

በፓናል መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ከክልሎች የመጡ የስራ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን እና የኪነ ህንጸ ባለሞያዎች እንዲሁም የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።

የዓድዋ ድል በደም እና አጥንት የተገኘ ታላቅ ድል መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ነገር ግን ይህ ታላቅ ድል ላለፉት ዓመታት በሚገባው ልክ አለመዘከሩን ገልጸዋል።

ዓድዋ የነጻነት አርማ የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ድል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች ታላቁ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ታሪኩን በሚመጥን ልክ መገንባቱንም ተናግረዋል።

የዓድዋን ሙዚየም ገነባን ስንል ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ታሪክም ጭምር ነው የገነባነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ገራዊ የጋራ ታሪካችንን እኩል ልንናገረው፣ እኩል ልንኮራበትም ይገባል ብለዋል።

በፓናል ውይይቱ የክልሎች ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ ስነ-ህንፃ ባለሞያዎች እና የሚዲያ አካላት ተሳትፈዋል።
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ለአቅመ ደካሞች፣ ለሃገር ባለውለታ አረጋዊያን፣ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሠራተኞችና ምንም ገቢ ሌላቸው ከ263 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ ብለን ማዕድ አጋርተናል። በዚህ የበጎነት ተግባር ላይ የተሳተፋችሁ የከተማችን ባለ ሀብቶች፣ በጋራ ሆነን እምባ እያበስን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን ለህዝባችን መግለጽ ስለቻልን አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ በወጣ እጥፍ አድርጎ ይመልስላችሁ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዋሬ አካባቢ በ1523.3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤትች ግንባታ መርቀዋል።

የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የ’መደመር ትውልድ መጽሃፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው። ህንፃዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም እታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው።

በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች የተካተቱባቸው ናቸው። ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ፣ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ ተገጥሞላቸዋል።

ክብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በንግግራቸው ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕን አርዓያነት እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

#PMOEthiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የገና በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!

''ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የገናን በዓል ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ በመወለዱ ሰውና መላዕክት በአንድ ላይ ፈጣሪአቸውን ያመሰገኑበት እለት በማሰብ በደስታና በፍቅር ልደቱን በማሰብ በድምቀት ያከብሩታል።

ከዚህም በመነሳት በዓለ ልደቱ የፍቅር፣ የአብሮነትና የሰላም እንደመሆኑ መጠን ሁላችንም በጋራ ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት ያለንን ለሌላቸው በማካፈል ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በማጎልበት ሊናከብረው ይገባል።

በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡

በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘሁ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ እላለሁ።''

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ
ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱ ያስተላልፋል።
👍1
ባለስልጣኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
30/04/2016 ዓ.ም
*ቢሾፍቱ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ አመራሮች ከታህሳስ 30/2016 እስከ 03/05/2016 ዓ/ም ድረስ በአመራር ክህሎት፣ በእስትራቴጅክ እቅድ አስተቃቀድ፣ በጊዜ አጠቃቀም እና በከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጡ ተጨማሪ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ስልጠናው በ2016 በጀት ዓመት ከያዝናቸው እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑንና ከተማዋን የሚመጥንና ለውጥ አምጪ አመራር ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ የከተማዋን የደንብ መተላለፍ ለመከላከልና ስርዓት ለማስያዝ በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የአመራሩን ብቃት ይበልጥ ለማጎልበት በሚያበቁ ዕውቀቶች በኢንስቲትዩቱ ሙሁራንና ለቀጣይ ሶስት ቀናት ስልጠናው እንደሚሰጥ አስታውቋል።

Leadership and time management ርዕስ ያደረገ ስልጠና የሰጡት የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት አማካሪ እና አሰልጣኝ አቶ ጀማል አህመድ ሲሆኑ፤ ስልጠናውም አሳታፊና አነቃቂ የሆነ እንደነበረ ከተሳታፊዎች ተገልጿል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አባቶች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል::

በውይይቱ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አባቶቹ የገለፁ ሲሆን ቤተ-ክርስቲያኒቷን የማይወክሉ ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ፈፅሞ እንደማይቀበሉና እንደሚያወግዙ ይህንንም ለምዕመናቸው ግልፅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በዩኒስኮ በቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል አከባበር ሃገራዊ ቅርስ እንደመሆኑ በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶቹ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::

የሃይማኖት አባቶቹ የከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ አከባበር የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል::