የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.14K subscribers
1.92K photos
4 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ፕሬስ ሪሊዝ
ባለስልጣኑ በደንብ መተላለፎችና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር የፊት ለፊት ውይይት እንደሚያካሄድ ገለፀ

22/12 /2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በደንብ መተላለፎችና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የፊት ለፊት ውይይት እንደሚያካሄድ ገለፀ።

በመድረኩ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል አስከ ወረዳ ያሉ የባለስልጣኑ አመራሮች ፣የአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ እና የ119 ወረዳ ከተወጣጡ የከተማው ነዋሪዎች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎችና መመዲያዎች እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍132
ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባለስልጣኑ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የትሀ2017 እቅድ አፈጻጸም ፣ የ2018 እቅድ ውይይት እና በደንብ መተላለፎችና በመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ከ1500 በላይ ከከተማው ነዋሪዎች ጋር የፊት ለፊት የውይይት መድረክ በአድዋ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከእቅድ አንጻር በርካታ የደንብ ጥሰቶችን የመከላከል እና የመቆጣጠር ተግባራት እንንደተሰሩና እነዚህ ተግባራት በህዝብ ተሳትፎ እና በባለድርሻ አካላት ትብብር የታጀቡ እንደነበር ጠቁመዋል ።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በጋራ ሆነን ደንብ መተላለፍን እና ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን በመቀጠል በስነ ምግባር የታነጸ ኦፊሰር በመገንባት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን እርካታ በማረጋገጥ ዓላማችንን ከግብ እናደርሳለን ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና አውት ሶርሲንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን አዲስ አበባ የምስራቅ አፍሪካ ፈርጥ እንድትሆንና ለዜጐቿ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በ7/24 የስራ ባህል በርካታ ፕሮጀክቶችን በመስራትና በአጭር ገዜ በማጠናቀቅ ፈጣን እድገት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

አክለውም ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና የከተማችንን ሰላም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመጠበቅ እንዲሁም በከማችን የተሰሩ የልማት ስራዎች የወንዝና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከላከል ንጽህናው የተጠበቀ ውብ ከተማ እንዲኖረን በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል ።

የአዲስአበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ አቅርበዋል።

በውይይቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና ምቹ የስራ አከባቢን የመፍጠር ተግባራት በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በዕቅዱ ተካቷል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባለስልጣኑ በትኩረት እንደሚሰራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና የአከባቢያችንን እንዲሁም የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍72
ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር አካሄደ

ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ዕቅድ አፈጻጸምላስመዘገቡ የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች፣ባለድርሻ አካላትና ሰራተኞች የእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር በክ/ከ አዳራሽ በዛሬው እለት አካሄደ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሙ ሙሄ ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሀመድ እና ሌሎችም የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

በእውቅናና ምስጋና መርሀግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠር በማስተማር ለህብረተሰቡ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑ ገልጸዋል

አክለውም በቀጣይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየደረጃው የተሰማራው ሰራተኛና ኦፊሰሮች የተጀመረው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሰፊ ስራ በቀጣይም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብሩ የመክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ጎንፋ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ተግባራትን በመከወን ህገወጥ ግንባታ 15%፣ህገወጥ ቆሻሻ አወጋገድ 70%፣ አዋኪ ድርጊት 4.7 ጨምሮ በጥቅሉ በክ/ከተማው 52.1% የደንብ ጥሰትን በመቀነስ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ዓመትመሆኑ ተናግረዋል።

ኃላፊው በቀጣይ 2018 ዓ.ም የተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ የጣለብንን ኃላፊነት ንቁ የሆነው የህብረተሰቡ አብሮነት ቀጣይነት እንዲኖረው አንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በእለቱ በበጀት ዓመቱ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በተቋሙ ጉልህ ተሳትፎ ለነበራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጽ/ቤቱ ምረጥ ፈጻሚ ባለሙያዎች ፣ ሴክተር ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት ፣ የጎልደን እና የአረንጓዴ ልዩ ተሸላሚ የሆኑ ወረዳዎች የምስጋና ሰርተፍኬትና እውቅና የመስጠት መርሀግብር ተከናውኗል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሙ ሙሄ በ2017 በጽ/ቤቱ የመጡት ለውጦች በቀጣይ አመትም በበለጠ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመግለጽ በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3