የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ
20/ 11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት እቅድ ከክፍለ ከተሞችና ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ከተማችንን ከወንጀል ነጻ በማድረግ ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን በማክሸፍ እና የግጭት አዝማሚያዎችን በመቀልበስ፣ ተቋማችንን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም የተለያዩ ጠንካራ የጸጥታ አደረጃጀቶች አንዲኖሩ በማድረግ የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።
አክለውም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ በየደረጃው ጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ ስራዎችን በመስራት የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ የህዝቡን የሰላም ባለቤትነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2017 በጀት ዓመት የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ የተቻለበት ፣ ሀገራዊና ሀይማኖታዊ የአደባባይ በዓላትና ፕሮግራሞች በሰላም ተከበረው የተጠናቀቀበት እንዲሁም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲቀንስ ማድረግ በመቻሉ በአፈጻጸም ውጤታማ መሆን መቻሉን ገልጸዋል።
አክለውም ያስመዘገብነው ድል በላቀ ደረጃ ለማሰቀጠልና በ2018 የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።
በመድረኩ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የ2018 በጀት ዓመት ካስኬዲንግ ዕቅድ ከዘርፍ ኃላፊዎችና ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል ።
በእለቱ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በተደረገው ምዘና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ፣ ለማዕከል ዳይሬክተሮችና ፈጻሚዎች የእዉቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሄደ።
በእውቅናና ሽልማት መድረኩ ተሸላሚ የሆኑ ክፍለ ከተሞች
1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ አራዳ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
3ኛ ጉለሌ ክፍለ ከተማ እና የካ ክ/ከተማ
በሽልማቱ ከአንድ እስከ 3ተኛ ደረጃ ላገኙ ክፍለ ከተሞች የሞተር ሳይክልና የክርስቲያል ዋንጫ ፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች የሞተር ሳይክልና ላፕቶፕ ከነፕሪንተሩ ፣ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድኖች እና ፈፃሚዎች የላፕቶፕና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የደንብ መተላለፍ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች እንደሚያከናውን ገለፀ
ነሀሴ 22/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል፣ ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድና ዘርፋ በ2018 በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የደንብ መተላለፍ የክትትልና የቁጥጥር እና የሰርቪላንስ ስራዎች እንደሚያከናውን ገለፀ
ዘርፉ የበጀት አመት እቅድ ካስኬድ በማድረግ ለዳይሬክተሩ እና ዳይሬክተሩ በስሩ ከሚገኙ ቡድኖቹ ጋር እቅዱካስኬድ በማድረግ የተሰጣቸውን ተግባር በሀላፊነት እንዲያከናው በመግለፅ የፊርማ ስነ-ስርዓት አካሂዷል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ሰርቪላንስ ዘርፋ የተቋሙ ስኬት ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ አመራሩና ሰራተኛው በመተባበር ሚናውን በመወጣት ባለስልጣኑን የገፅታና ግንባታና የስራው ውጤታማነት ከፍ ማድረግ እንደሚገባ መልክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በ2017 በጀት ያስመዘገብነው ውጤት በ2018 በጀትም ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን በመወጣት ውጤቱን ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ጠንካራ የደንብ መተላለፍ የክትትል፣ የቁጥጥርና የሰርቪላንስ ስራዎች በመስራት ለመቀነስ መታቀዱ አቶ ከፋያለው ታደሰ ገልፀዋል።
መረጃው ፦የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍3