የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.15K subscribers
1.94K photos
5 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
"ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " በሚል መሪ ቃል የህዝብ ውይይት ተካሄደ

19/12/ 2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " በሚል መሪ ነከተማው ነዋሪዎች የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ።

በውይይቱ 2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙንና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዱን እና የመልካም አስተዳደር ችግር በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

‎ባለስልጣኑ በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸው የደንብ ጥሰቶችን ከመከላከል አንጻር ሰፊ ስራ መሰራቱንና ህገ ወጥ ተግባራትን ከመከላከል፣የጎዳና ላይ ንግድ፣ ህገወጥ ንግድ ፣ የፍሳሽ አወጋገድ፣ ህገ ወጥ እርድ ፣ ማስታወቂያና የመሬት ወረራን ከመከላከል አንጻር ሰፊ የግንዛቤ ስራዎችን መስራቱ ተገልጿል።

በበጀት ዓመቱ በሰላምና ጸጥታ ግባችን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ እንደሆነ ገልጸው ለዚህም የሰላም ባለቤት ለማድረግ አንዱ መንገድ ህገ-ወጦችን መከላከል፣ መቆጠጠርና በጋራ እርምጃ መዉሰድ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሻለና ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተመላክቷል፡፡

ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባለስልጣኑ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ ከብሎክ ጀምሮ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ምላሽ እንዲያገኙ በትብብረሸ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
👍94👏2
ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

20/ 11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት አገልግሎት አሰጣጣችንን ምቹ ቀልጣፋ እና ፍትሀዊ እናደርጋለን" በሚል መሪ ቃል በክፍለ ከተማዎች የህዝብ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኮቹ የክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ለህብረተሰቡ ለውይይት መነሻ እንዲሆን ቀርቧል።

የህዝብ ንቅናቄ ማድረግ አስፈላጊነቱ ባለስልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተግባር እና ኃላፊነት በተሟላ ሁኔታ ለመፈፀም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከከተማው ህብረተሰቦች ጋር በሚደረጉ በህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በመለየት እና ችግሮችን በእቅድ ለመፍታት እንደሆነ ተገልጿል ፡፡

በመድረኩ በ2017 በጀት ዓመት ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣትና በርካታ ሰው ተኮር ሰራዎች በመስራት ያስመዘገብነውን ድል በላቀ ደረጃ ለማሰቀጠልና በ2018 የያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ እንዲሁም ለአገልግሎት አሰጣጥ ፍትሀዊነት የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ገልጸዋል ፡፡

የምናገለግለው የህብረተሰብ ክፍል በተቋማችን ከአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያና የተፈቱበት አግባቦችን በጋራ በመምከር በቀጣይ መፈታት የሚገባቸውን ችግሮች ለመለየትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መድረኩ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅና የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅት በማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4
የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

20/ 11/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት እቅድ ከክፍለ ከተሞችና ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ከተማችንን ከወንጀል ነጻ በማድረግ ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ እንቅስቃሴዎችን በማክሸፍ እና የግጭት አዝማሚያዎችን በመቀልበስ፣ ተቋማችንን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም የተለያዩ ጠንካራ የጸጥታ አደረጃጀቶች አንዲኖሩ በማድረግ የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል ።

አክለውም ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ለማድረግ በየደረጃው ጠንካራ የህዝብ ተሳትፎ ስራዎችን በመስራት የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ የህዝቡን የሰላም ባለቤትነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2017 በጀት ዓመት የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ የተቻለበት ፣ ሀገራዊና ሀይማኖታዊ የአደባባይ በዓላትና ፕሮግራሞች በሰላም ተከበረው የተጠናቀቀበት እንዲሁም በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ እንዲቀንስ ማድረግ በመቻሉ በአፈጻጸም ውጤታማ መሆን መቻሉን ገልጸዋል።

አክለውም ያስመዘገብነው ድል በላቀ ደረጃ ለማሰቀጠልና በ2018 የተያዘውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል ።

በመድረኩ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የ2018 በጀት ዓመት ካስኬዲንግ ዕቅድ ከዘርፍ ኃላፊዎችና ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል ።

በእለቱ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ በተደረገው ምዘና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ፣ ለማዕከል ዳይሬክተሮችና ፈጻሚዎች የእዉቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር አካሄደ።

በእውቅናና ሽልማት መድረኩ ተሸላሚ የሆኑ ክፍለ ከተሞች
1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ አራዳ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
3ኛ ጉለሌ ክፍለ ከተማ እና የካ ክ/ከተማ

በሽልማቱ ከአንድ እስከ 3ተኛ ደረጃ ላገኙ ክፍለ ከተሞች የሞተር ሳይክልና የክርስቲያል ዋንጫ ፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች የሞተር ሳይክልና ላፕቶፕ ከነፕሪንተሩ ፣ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድኖች እና ፈፃሚዎች የላፕቶፕና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።