የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.13K subscribers
1.91K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በህገ-ወጥ መንገድ ሲሰሩ በነበሩ ስጋ ቤቶች እና ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ

      27/06/2016 ዓ.ም
      #አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፣ ንግድ ቢሮ እና ከከተማ ግብርና ኮሚሽን ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ ሲሰሩ በነበሩ ስጋ ቤቶች እና ግለሰቦች ላይ ከየካቲት 12 እስከ ከየካቲት 24 በተደረገው የክትትል ስራ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

በክትትል ስራው አጠቃላይ በከተማው ከ11 ክፍለ ከተሞች 226 ቤቶች ክትትል ተደረጎባቸው ከነዚህ  ውስጥ ከደረሰኝ እና በህገወጥ እርድ ጋር በተያያዘ 45 ስጋ ቤቶች የታሸጉ መሆኑ ተገልጿል።

በተደረገው የክትትል ስራው  የተለያዮ ለህገወጥ እርድ የተዘጋጁ እንስሳቶች የተወረሱ ሲሆን 5,293 ኪሎ ግራም ስጋ እንዲወገድ ለቄራዎች ድርጀት ገቢ በማድረግ ህግ በተላለፉት ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እንደ ጥፋታቸው የተቀጡ ሲሆን ከቅጣቱ 450,000 ብር ገቢ ማድረግ ተችሏል።

በህገ-ወጥ እርድ ስጋ ለማህበረሰቡ በማቅረብ የማህበረሰቡ ጤና አደጋ ላይ በሚጥሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ እርምጃው የሚቀጥል መሆኑ  በክትትል አባላቱ ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
የከተማዬን ጽዳት በመጠበቅ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ በሚል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

የካቲት 30/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች፣ዳይሬክተሮች እና ኦፊሰሮች የተሳተፉበት የጽዳት ዘመቻ "የከተማዬን ጽዳት በመጠበቅ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ" በሚል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ ።

በዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተማዋን የጽዳት ተምሳሌት ለማድረግ ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል አድርጎ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የከተማው እና የክፍለ ከተማዉ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ከንግግር ባለፈ ስራው በተግባር የምናሳይበት መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉም ህብረተሰቡ ጽዳትን የእለት ተእለት ተግባሩ እንዲያደርገዉ ጠይቀዋል፡፡

አዲስ አበባ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በአይን የሚታዩ ሁለንተናዊ ለዉጦችን እያስመዘገበች ትገኛለችና
ከነዚህ ለዉጦች ዉስጥ ደግሞ ጽዳት ተጠቃሽ ነው ተብሏል ።
👍6
የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መጋቢት 5/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ

የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማዕከሉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የሴቶች ፆታዊ እኩልነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ሴቶችን ማብቃት እና የእኩልነት መብታቸውን ማክበር እና ማስከበር እያረጋገጥን መሔድ እንደሚገባን በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ውስጥ የትኩረት አቅጣጫችን መሆኑን የምናሳይበት አንዱ ሥራ ነው ብለዋል።

ዛሬ ይህንን ማዕከል መርቀን ስንከፍት አዲስ የተገነባ ሕንፃን ሥራ ከማስጀመር ባለፈ የተሻለ ነገን፣ ብሩህ ተስፋን፣ ፅናትን እና ሰፊ ሠርቶ የመለወጥ ዕድልን በዘላዊ ፅኑ መሠረት ላይ እየተከልን መሆኑን በማነን ነው ሲሉም አክለዋል።

በርካታ ሴቶች በሚደርስባቸው ፆታዊ አድልኦ፣ ተፅዕኖ እና ጥቃት ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች እና በደሎች ከመጋለጥ በላይ በማኅበረሰባቸው እና ለሀገራቸው ዕድገት አቅማቸው የሚፈቅደውን አስተዋፀኦ ማድረግ እንዳይችሉ ከፍተኛ ውስንነት ውስጥ እንዲያልፉ እንደሚያደርጋቸው አንሥተዋል።

በሀገራችን ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለሴቶች ዕድልን ለማስፋት፣ ለማብቃት፣ እኩል ተጠቃሚ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን እና አበራታች ውጤቶችም መታየታቸውን ጠቁመዋል።

ዛሬም በርከታ እህቶቻችን እና ልጆቻችን ላይ በሚደርሰው የተወሳሰበ ፆታዊ አድልኦ የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ዕድል ጠባብ መሆን ተጨምሮበት ለኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ ለአካላዊ እና ፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

በመሆኑንም ይህ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ሁሉን ችግር የሚፈታ ባይሆንም ለጎዳና ሕይወት እና ለወሲብ ጥቃት እንዲሁም ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ የሆኑ እህቶቻችን አማራጭ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ የሚያበቃቸውን እና ብቁ የሚያደርጋቸውን የክህሎት፣ የሥነ-ምግባር፣ የሥራ ባህል፣ የሥራ ስምሪት ጭምር እንዲፈጠርላቸው በማድረግ ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ እንደሚያስችል እምነታቸውን መግለፃቸው AMN ዘግቧል።
#Ethiopia
#addisababa
🙏4👍2