ባለስልጣኑ ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን ገለፀ
24/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በልደታ ክ/ከተማ 2 ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከሉ ሁለት ተቋማት እያንዳንዳቸው 1,000,000 ብር በድምሩ 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
ባለስልጣኑ ቢጂ አይ ኢትዮጲያ እና ሞሀ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ድርጅቶች የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
ወንዞችን ከብክለት የፀዱ ከማድረግ አንፃር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በስፋት እየሰጡ መሆኑ ገልፀዋል።
በግንዛቤው መሠረት ተቋማትና ግለሰቦች ከህገወጥ ተግባራቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተመላክቷል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን
ለተጨማሪ መረጃ፦
ዌብሳይት ገፃችን፦
https://www.aacea.gov.et/
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ለተቋማዊ የስራ ልምድ እና ተሞክሮ ለመውሰድ ድሬዳዋ ከተማ ገቡ
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
** ድሬዳዋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የባለስልጣኑና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የሚሳተፉበት የልዑካን ቡድን አባላት ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገብተዋል።
በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር ልማት ደህንነት አጠባበቅቅ አሰራር፣ ፤በሌሎች የደንብ መተላለፎችና የፀጥታ ጉዳዮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት ይሆናል፡፡
በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ዋና-ስራ አስኪያጅ ቃለቃ ዘሪሁን ተፈራ እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የባለስልጣኑ አመራሮችና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡
ለልዑካን ቡድን አባላቱ ደድሬዳዋ ከተማ ኤርፖርት እንደደረሱ በከተማ አስተዳደሩ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበርና ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የልምድ ልውውጥ አካሄደ
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
** ድሬዳዋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበርና ፍትህና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ።
በልምድ ልውውጡ በተቋም አደረጃጀት፣ በኮሪደር ልማት ደህንነት አጠባበቅ አሰራር፣የፀጥታና የግጭት አፈታት ፤ የደንብ መተላለፎች ግንዛቤና የቁጥጥር ስራዎች፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ከተማ አስተዳደሩ ያለውን ልምድና ተሞክሮው አጋርቷል፡፡
በልምድ ልውውጡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋሙ አደረጃጀት እና ያጋጠሙ ችግሮች ከሚመለከተው አካል በመነጋገር የተፈታበት ሂደት እና ተቋሙ በማጠናከር የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደቶች ገልፀዋል።
በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ አሰራሮች እና የተቋሙ ተሞክሮዎች የቀረበ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ የሁለቱም ከተማ አስተዳደር ተቋማት የስራ ተሞክሮ በሰነድ ቀርቦ ከአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

የባለስልጣኑ የልዑካን ቡድን አባላት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ጎበኙ
መጋቢት 25/2017 ዓ.ም
** ድሬዳዋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ጎበኙ።
በጉብኝቱ የከተማ አስተዳደሩ የሚገነባው ሲዲሲ/ኤግዜቢሽን ማዕከል/ ፣ የከተማ አስተዳደሩ የፖሊስ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ እና የወጣቶችና የፖሊስ ቅንጅታዊ ስራዎችና የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።