ስነምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ
12/07/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች "ስነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በክ/ከተማው አዳራሽ ሰጠ።
ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግር ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዚህ ድርጊት በሚሳተፉ ላይ ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋትና በመከላከል ሁሉም አካል ብልሹ አሰራርን ሊጸየፍና ሊታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ስነ-ምግባር ለመልካም አስተዳደር መስፈን ያለዉ ፋይዳ የላቀ በመሆኑ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለሌሎች አርኣያ የሚሆን ስነ ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አቶ እዮብ ገልጸዋል ።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ኦፊሰሩ ከብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የተሰጠዉን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣትና ከዳር ማድረስ እንዳለበት ገልጸዋል።
በመድረኩም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍12
ባለስልጣኑ በካሳንቺስ አካባቢ የተሰራው አዲስ የኮሪደር ልማት በግዴለሽነት ጉዳት ያደረሰው ድርጅት 510 ሺህ ብር መቅጣቱ ገለፀ
15/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በካዛንቺስ የኮሪደር ልማት አዲስ በተሰራው የመንገድ መሠረተ ልማት ሜልኮን ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ጉዳት ያደረሰው ድርጅቱ 500 ሺህ ብር እና ሁለት ሹፌሮች እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር በድምሩ 510,000 ብር መቅጣቱ ገለፀ።
ድርጅቱ በቸልተኝነት የተሰራው የእግረኞች መንገድ ኮንክሪት ስታምፕ በማውደሙ ለፈጸመው ግዴየለሽነት ተግባር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል፡፡
ባለስልጣኑ ድርጅቱ ከገንዘብ ቅጣቱ በተጨማሪ ያወደመውን የእግረኞች መንገድ ከተቀጣበት ሰዓት ጀምሮ በራሱ ወጪ በመገንባት እንዲያስተካክል ውሳኔ የተሰጠው መሆኑንም አሳውቋል።
ህግ በማስከበሩ ሂደት የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ በማድረግ የአፍሪካ ብልጽግና ማዕከል ለማድረግ ቀንና ሌሊት በሚሰራበት በዚህ ሰዓት እንደዚህ አይነት ተግባር መፈፀም አሳፊሪ መሆኑ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ በከተማው በልማት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች መሠል ድርጊቶች ከመፈጸም እንዲቆጠቡ እያሳሰበ ደንብ በሚተላለፉት ላይ ደንብ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለደረቅ ቆሻሻ ሽርክና ጽዳት ማህበራት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ::
16/07 /2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለደረቅ ቆሻሻ ሽርክና ጽዳት ማህበራት አመራሮች የወንዝ ዳር ብክለትን ለመከላከል በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በባለስልጣኑ አዳራሽ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለህብረተሰቡና ማህበራት በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ከተማዋን ፅዱ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም የከተማዋን ፅዳት በመጠበቅና የደንብ መተላለፎች ሲመለከት በማውገዝ ከተቋሙ ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል የተደነገገው ደንብ ቁጥር 180/2017 እንዲሁም የቅጣት ሰንጠረዥ በባለስልጣኑ የቅድመ መከላከልና ኢንስፔክሽን ባለሙያ አቶ ናታን ታዬ በዝርዝር ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።
ህብረተሰቡ ወንዞችን እና የወንዝ ዳርቻ ብክለትን ለመከላከል የወጣውን ደንብ በመገንዘብ በየአካባቢው የሚገኙ ወንዞችን ከብክለት በመጠበቅ የእራሱን እና የሌሎችን ጤና ማስጠበቅ እንደሚገባ የደንብ መተላለፍ መከላከልና የግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታሁን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

👍15
ባለስልጣኑ በትላንትና በዛሬው እለት ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
16/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በድምሩ 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በየካ ክ/ከተማ 2,350,000 ብር፤ በቦሌ ክ/ከተማ 950,000 ብር ፤ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 1,050,000
ብር፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 600,000
ብር ቅጣት ተቀጥቷል።
በተያያዘ ዜና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 370,000 ብር ፤በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 300,000 ብር እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ 50,000 ብር ቅጣት በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡
ባለስልጣኑ በሁለት ቀናት በአጠቃላይ 14 ድርጅቶች እና 14 ግለሰቦች በድምሩ 5,670,000/ አምስት ሚሊየን ስድስት መቶ ሰባ ሺህ/ ብር ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ እንዳይበከሉ ለድርጅቶችና ለግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን በቀጣይ የግንዛቤና ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።

👍7❤1