ባለስልጣኑ በ6ወር ዕቅድ አፈጻጸሙ በርካታ የደንብ መተላለፎች እና ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን ገለጸ ።
ቀን 16/05/2016 ዓ.ም
* አዲስ አበባ *
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ የስድስት ወር የተከለሰ እቅድ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች እንዲሁም የማዕከል ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ውይይት አደረገ።
በዛሬው መድረክ ባሳለፍነው 6 ወር በነበረን የዕቅድ አፈፃፀም ጥንካሬያችንን እና ክፍተቶቻችንን የምንገመግምበትና ለቀጣይ 6 ወራት የምንሰራው ስራ የተከለሰው እቅድን የምንወያይበት መድረክ ነው ብለዋል።
የባለስልጣኑን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የቀጣይ የ6ወራት የተከለሰ እቅድ ያቀረቡት የእቅድ እና በጀት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ እንዳሉት በባለስልጣኑ በርካታ ስራዎች ታቅደው መከናወናቸውን ገልፀው።
በተለይም መሬትን በተመለከተ በካሬ 13,884,372 ካሬ የሆነና በቦታ 7,364 ቦታዎች በከተማችን የሚገኝ መሬት በተቋሙ እየተጠበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በዕለቱ የተመረጡ ሶስት ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣አዲስ ከተማ እና ጉለሌ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀማቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም በቀረቡት ሰነዶች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው የባለስልጣኑ ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍3
ባለስልጣኑ በ2016 ዓ.ም በስድስት ወር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ገመገመ ።
ጥር 21/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመሰራት የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረመው መሰረት በተያዘው በጀት ዓመት በ6ወር የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የቀሪ 6 ወራት የተከለሰ እቅድ ላይ የባለስልጣኑ አመራሮች የከተማው ምክር ቤት የፋትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ሙሉነህ ደሳለኝ በተገኙበት ከባለድርሻ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ከክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ እና የፖሊስ መምሪያ ሃላፊዎች፣ የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊዎች አንዲሁም የማዕከሉ ዳይሬክተሮች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል ።
የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አንደተናገሩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተፈራረምነው ስምምነት መሰረት በጋራ የሰራናቸውን ስራዎች በመገምገምና ጠንካራ ጎናችንን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችት በመሙላትና በማሻሻል ለቀጣይ እቅድ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል ።
በንግግራቸው በ2016 ዓ.ም በስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በከተማው ሲታዩ የነበሩ ህገወጥ የደንብ መተላለፎችን እንዲቀንሱ ማድረግ ተችሏል።
በተለይ ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን የሀገርና የህዝብ ሀብት እንደመሆናቸው በልዩ ትኩረት በመጠበቅ ሙሉ በመሉ በሚባል ሁኔታ መሬት ወረራን እንዳይፈጸም ማድረግ መቻሉን ዋና ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የአዲ

ዛሬ የጣልያን መንግሥት "ፀሐይ"ን ለኢትዮጵያ መንግሥት ያስረከቡበት የታሪካዊ ሁነት ቀን ሆኗል‼️
ጥር 21/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ላለፈው አንድ አመት ጊዜ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ጋር አውሮፕላኑ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚመለስበት ሁኔታ ትልቅ ጥረት እና ሰፊ ንግግር ሲያደርጉ ቆይተው ዛሬ በይፋ መረከብ ችለዋል።
ፀሐይ ባለሁለት መቀመጫ እና ሁለትዮሻዊ መቆጣጠሪያ ያለው ብሎም የባለከፍተኛ ኃይል ሞተር ባለቤት ተደርጎ የተሰራ አውሮፕላን ነበር። "ፀሐይ" ኮምፓስ፣ የአብራሪ መቆጣጠሪያዎች፣ ሁለት ያለ ፍሬን ማቆሚያ የተገጠሙ የማረፊያ ሽክርክሪቶች የነበሩትም ነበር።
ሞተሩ ባለሰባት ሲሊንደር ዋልተር ቪነስ ሲሆን የውሃ ማቀዝቀዣ ስርዓት የነበረው የ115 የፈረስ ጉልበት ባለቤትም ነበር።
"ፀሐይ" በ1935 ዓ.ም ሄር ሉድዊግ ዌበር የተባለው ጀርመናዊ ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት በወቅቱ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የተሰራ የመጀመሪያው አውሮፕላን ነው።
"ፀሐይ" ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በፊት በኢትዮጵያ የተሰራ ብቸኛ አውሮፕላን ነው።
ፀሐይ በውስን ሃብት እና ስፍራ በጊዜው የነበሩትን አናፂዎች እውቀት እና የእጅ ጥበብ በመጠቀም የተሰራ አውሮፕላን ሲሆን የ1930ዎቹ የአቪየሽን ጥረት ማሳያ ሆኖ የተረፈን አውሮፕላን ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ላለፈው አንድ ዓመት የአውሮፕላኑን መመለስ ስራ በማገዛቸው ለማመስገን እፈልጋለሁ” ሲሉም አመስግነዋል።

ባለስልጣኑ ለባህርዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ልምዱንና ተሞክሮውን አጋራ፡፡
ጥር 22/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን በተቋም አደረጃጀትና በአሰራር በመመሪያ ዙሪያ ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮውን አጋርቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በልምድ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማዋን እና የተቋሙ ገጽታ ለመቀየር በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ባለስልጣኑ ላደረገላቸው ቀና ትብብር አመስግነው በቀጣይነት በሚችለው ሁሉ ከጎናቸው እንዲቆም እና እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል።
ምክትል ስራ-አስኪያጅዋ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙ ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴዎች በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለጅማ፣ለድሬዳዋ እና ለሐረር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ያለውን ልምድና ተሞክሮ ማጋራቱ ይታወቃል፡፡
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

ባለስልጣኑ ከተጠሪ ተቋሙ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ።
ጥር 23/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን የክፍለ ከተማ እና የወረዳ የደንብ ማስከበርና የሰላምና ፀጥታና ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት የከተማው ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ፣ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበር በማድረግ እና የፀረሰላም ሃይሉ ተልዕኮ በማክሽፍና በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ በስድስት ወራት ውስጥ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱ ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን አያይዘው በጀት ዓመቱ 6 ወራት መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን ወረራን እንዳይፈጸም በመጠበቅ፣ በጎዳና ንግድ እና በሌሎች ተግባራቶች ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል ።
በመድረኩ የሁለቱም ተቋማት የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሁለቱም ተቋሞች በ6ወር ውስጥ የተሰሩ ሰራዎችን በጥንካሬና በክፋተት ተለይተው ቀርበዋል።
በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና በሻለቃ ዘሪሁን ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ።
24/05/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመንግስት ሰራተኞች ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በኤሊያና ሆቴል የተቋሞቹ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የመጀመሪያው ክፍል ስልጠና ተሰጠ።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በስልጠናው “ሀብት መፍጠር ማስተዳደር እና ገዥ ትርክት” የሚሉ ሁለት የስልጠናው ሰነዶችን ያቀረቡት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ግዛው ሀገራችን የውጭና የውስጥ ፈተናዎች የነበሩባት ነገር ግን አንድነቷን አስጠብቃ በመቀጠል በለውጥ ጎዳና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር ጥረት ማድረግ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ በበኩላቸው የአንዱን ክፍተት አንዱ እየሞላ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ በቀረቡት ሰነዶች ላይ በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን መድረኩን የመሩት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ግዛው እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።
መረጃው:-የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።