CODE CRACKER ET
18.5K subscribers
7 photos
4 links
In a world of digital shadows be the one who controls the light Decoding the secrets of cybersecurity Not just breaking codes but mastering systems.
Educational purposes only
Stay alert Stay ahead
Download Telegram
Channel created
በየቀኑ የምትጠቀምባቸው አፕሊኬሽኖች፣ የምትገባባቸው ድረ-ገጾች እና የምትይዛቸው የይለፍ ቃሎች (Passwords) ሁሉም የራሳቸው ደካማ ነጥብ አላቸው። ብዙዎች ቴክኖሎጂን እንደ ተጠቃሚ ብቻ ነው የሚያዩት፤ እኛ ግን ከቴክኖሎጂው ጀርባ ያለውን ምስጢር እንፈታለን።
CODE CRACKER ላይ የምናቀርባቸው ይዘቶች፡
Cyber Security: መረጃህን ከሳይበር ጥቃቶች እንዴት እንደምትጠብቅ።
System Mastery: ሲስተሞች እንዴት እንደሚሰሩ እና ክፍተታቸውን እንዴት እንደምንቆጣጠር።
Tech Intel: በየሳምንቱ በዓለም ላይ የሚከሰቱ የሳይበር አደጋዎችን እና መከላከያዎቻቸውን።
ይህ ቻናል ለትምህርታዊ ዓላማ (Educational Purposes) ብቻ የተከፈተ ነው። መረጃ ኃይል ነው፤ ኃይሉን ለመቆጣጠር ዝግጁ ከሆንክ ወደ CODE CRACKER እንኳን ደህና መጣህ።
እኛ የምንሰብረው ኮድን ብቻ አይደለም፤ የዲጂታል ደህንነትህን እንገነባለን።
#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤‍🔥3❤2👨‍💻1
ኤቲካል ሃኪንግ ወይም ደግሞ ስነ ምግባራዊ ሃኪንግ ማለት የኮምፒውተር ሲስተሞችን ከወንጀለኞች ለመጠበቅ ሲባል በፈቃደኝነት እና በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ የደህንነት ክፍተቶችን መፈተሽ ነው
ኢንጅነሪንግ ሶሻል ሃኪንግ የሚባለው ዘዴ የቴክኖሎጂ ችሎታን ከመጠቀም ይልቅ የሰዎችን ስሜት እና ድክመት በመጠቀም የይለፍ ቃል ወይም ሚስጥራዊ መረጃዎችን ማግኘት ነው
የቀለም ሃኪንግ አይነቶች እንደ ዋና አላማቸው በነጭ ጥቁር እና ግራጫ ሃኪንግ ተብለው ይከፈላሉ ይህም ለጥቅም ሲባል የሚደረግ ወይስ ለጥበቃ የሚደረግ መሆኑን ይለያል
ማንኛውም ሃከር ሲስተም ውስጥ ለመግባት መጀመሪያ የሚያደርገው ነገር ኢነመሬሽን ወይም ስለ ሲስተሙ ዝርዝር መረጃ መሰብሰብ ነው ይህም ለአንድ ፕሮግራመር የሲስተሙን ደህንነት ለማጠናከር በጣም ወሳኝ የሆነ ጥናት ነው
የኢንክሪፕሽን ቴክኖሎጂ መረጃን ከሃከሮች ለመጠበቅ የሚያስችል በጣም ጠንካራ መከላከያ ሲሆን ይህም መረጃ ወደማይነበብ ምስጢራዊ ኮድ በመቀየር በባለቤቱ ብቻ እንዲከፈት ማድረግ ነው

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
👍4❤1
Cyber Cross የሳይበር ደህንነት እና የሃኪንግ መማሪያ መድረኮች

TryHackMe በተግባር የተደገፈ የሃኪንግ ትምህርት ለመጀመር ምርጥ የሆነ ድረገጽ ሲሆን በድር አድራሻው tryhackme.com በመግባት መጀመር ይቻላል

Cybrary ለሳይበር ደህንነት እና ለኢቲካል ሃኪንግ ሙያዊ ስልጠናዎችን የሚሰጥ መድረክ ሲሆን cybrary.it ላይ በመግባት በነጻ ኮርሶችን መከታተል ይቻላል

OWASP Top 10 የደህንነት ክፍተቶችን ለመለየት እና ለመረዳት ዋናው መመሪያ ሲሆን owasp.org ላይ በመግባት ማንበብ ይቻላል

Termux ለአንድሮይድ ስልክ የሚሆን በጣም ጠንካራ የሊኑክስ ተርሚናል ኢምዩሌተር ሲሆን በአንድሮይድ ፕሌይ ስቶር ወይም f-droid.org ላይ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል

Kali Linux በሃኪንግ እና በሳይበር ደህንነት ሙያተኞች ዘንድ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሲሆን kali.org ላይ በመግባት ሙሉ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል

HackerOne የደህንነት ክፍተቶችን በመፈለግ ሽልማት ማግኘት የሚቻልበት የታወቀ ድረገጽ ሲሆን hackerone.com በመጠቀም ስለ ሃኪንግ ተግባራት በዝርዝር መማር ይቻላል

ለወደፊቱ ቻናላችንን ይበልጥ ጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ የሃኪንግ ትምህርታዊ ኮርሶችን እና ለጀማሪዎች የሚመቹ አጠር ያሉ የሃኪንግ ቪዲዮዎችን በራሳችን አዘጋጅተን የምናቀርብ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
Cyber Cross የታዋቂው ሀከር ኬቪን ሚትኒክ የሕይወት ታሪክ

ኬቪን ሚትኒክ በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ ዝነኛ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ሀከሮች መካከል በአንደኛ ደረጃ የሚቀመጥ ስም ነው

ገና በወጣትነቱ የሰዎችን ስሜት እና ድክመት በመጠቀም መረጃ የማግኘትን ጥበብ ወይም ሶሻል ኢንጂነሪንግ የተባለውን የሃኪንግ ስልት በሚገባ በመለማመድ ትላልቅ ተቋማትን ሰብሮ መግባት ችሏል

የአሜሪካን ትላልቅ የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎችን እና የቴክኖሎጂ ተቋማትን ሲስተም በመስበር ሚስጥራዊ ኮዶችን በማግኘቱ በኤፍቢአይ (FBI) ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንጀለኛ ተብሎ ለአመታት ሲታደስ ቆይቷል
በመጨረሻም እጅግ አስገራሚ በሆነ አደን በቁጥጥር ስር ውሎ ለአምስት አመታት ያህል በእስር ቤት የቆየ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የኮምፒውተር መረቦችን በስልክ ጥሪ ብቻ ማዘዝ ይችላል በሚል ስጋት ስልክ እንኳን እንዳይነካ ከልክሎት ነበር
ከእስር ከተፈታ በኋላ ግን እውቀቱን ወደ መልካም ነገር በመቀየር ትልልቅ ኩባንያዎችን ከጥቃት የሚከላከል ስመ ጥር የሳይበር ደህንነት አማካሪ እና ኢቲካል ሀከር በመሆን ህይወቱን ሙሉ በሙሉ ለውጧል

ይህ የኬቪን ሚትኒክ ታሪክ ለብዙዎች የሃኪንግ ችሎታን ለጥፋት ሳይሆን ለጥበቃ ማዋል እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ሆኖ የሚጠቀስ ነው

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤1
Cyber Cross አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የሳይበር ደህንነት ተጽእኖ
በአሁኑ ሰዓት ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI በሳይበር ጥበቃ ዘርፍ ውስጥ አዲስ አብዮት እየፈጠረ ይገኛል
አጥቂዎች AIን በመጠቀም እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የፊሺንግ ወይም የማጭበርበር መልእክቶችን በማዘጋጀት ተጠቃሚዎችን በቀላሉ ለማታለል እየሞከሩ ነው
በአንጻሩ ደግሞ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ተመሳሳይ የ AI ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥቃቶችን ገና ከመድረሳቸው በፊት መለየት እና መከላከል ችለዋል
ይህ የቴክኖሎጂ ፍልሚያ ለወደፊቱ የትኛው ወገን የላቀ አቅም እንዳለው የሚወስን ትልቅ የሳይበር ጦርነት ሆኖ ቀጥሏል
የእኛ የ Cyber Cross ቻናል ዓላማ ተከታዮቻችንን ከእነዚህ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስጋቶች በበለጠ ግንዛቤ እንዲጠበቁ እና የ AIን አቅም ለጥበቃ እንዲያውሉት ማገዝ ነው
ለወደፊቱ የምናቀርባቸው የሃኪንግ ኮርሶች እነዚህን አዳዲስ የ AI መከላከያ ዘዴዎችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በጥልቀት የሚያስረዱ ይሆናሉ
በዲጂታል አለም ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ ተጠቃሚ ለመሆን የቻናላችንን መረጃዎች በየቀኑ ይከታተሉ

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤1
CODE CRACKER ET pinned a photo
ዛሬ ለእናንተ የማስተዋውቃችሁ OverTheWire የሚባል ድረገጽ ሲሆን ይህም በዓለም ላይ ያሉ የሳይበር ደህንነት ተማሪዎች ችሎታቸውን የሚፈትኑበት ምርጥ መድረክ ነው

ይህ ድረገጽ እንደ ጨዋታ በሚታይ መንገድ ደረጃ በደረጃ ሃኪንግን የሚያስተምር ሲሆን እያንዳንዱን ደረጃ ለማለፍ የሊኑክስ ትዕዛዞችን እና የደህንነት ክፍተቶችን መፍታት ይጠበቅብዎታል

በዚህ ድረገጽ ውስጥ የሚያገኙት Bandit የተባለው የጨዋታ አይነት ለጀማሪዎች የሊኑክስ ሲስተምን እና የሃኪንግ መሰረቶችን ለመማር እጅግ በጣም ተመራጭ ነው
ተጠቃሚዎች ከዚህ ድረገጽ የሚማሩት ነገር በቀጥታ በገሃዱ ዓለም የሳይበር ደህንነት ስራዎች ላይ የሚውል እውቀት ነው

መማር ለመጀመር ወደ overthewire.org ድረገጽ በመግባት የWargames ክፍልን በመምረጥ የራሳችሁን የሃኪንግ ጉዞ ዛሬውኑ መጀመር ትችላላችሁ

እኛ በ Cyber Cross ቻናላችን እነዚህን ደረጃዎች እንዴት በቀላሉ ማለፍ እንደሚቻል የሚያሳዩ አጠር ያሉ ቪዲዮዎችን እና ማብራሪያዎችን በቅርቡ በየቀኑ የምናቀርብ ይሆናል

የሳይበር አለሙን በጨዋታ መልክ ለመማር እና ችሎታችሁን ለማዳበር የቻናላችንን መረጃዎች በየቀኑ ተከታተሉ
#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤3
CODE CRACKER ET pinned a photo
በሳይበር ደህንነት ዘርፍ እውቀትዎን ለማሳደግ የራሶን የግል ላብራቶሪ ማቋቋም ከመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች አንዱ ነው
ለዚህ ተግባር የቨርቹዋል ማሽን (Virtual Machine) ቴክኖሎጂን መጠቀም አለብዎት ይህም በኮምፒውተርዎ ውስጥ ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እንዲፈጥሩ ይፈቅድልዎታል
በመጀመሪያ VirtualBox የተባለውን ሶፍትዌር ኮምፒውተርዎ ላይ በመጫን ይጀምሩ ይህም የተለያዩ የኮምፒውተር አካባቢዎችን በአንድ ላይ ለማስተናገድ ይረዳዎታል
በመቀጠል Kali Linux የተባለውን ለሃኪንግ የተዘጋጀ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከኦፊሴላዊው ድረገጽ kali.org በማውረድ በቨርቹዋል ማሽንዎ ውስጥ ይጫኑት
ከዛ በኋላ Metasploitable የተባለውን ሆን ተብሎ የደህንነት ክፍተት ያለበትን የሙከራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይጫኑ
ይህ Metasploitable ሲስተም የእርስዎ መለማመጃ ኢላማ ይሆናል ስለዚህ እሱን በመጠቀም የተሰሩ የደህንነት ክፍተቶችን ለመለየት እና ለመሞከር ይችላሉ
ይህ ሂደት የራስዎን የዲጂታል ደህንነት እና የሃኪንግ ላብራቶሪ በመፍጠር ከቀላል እስከ ውስብስብ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን እንዲለማመዱ ያደርግዎታል
እኛ በ Cyber Cross ቻናላችን እነዚህን ሂደቶች ደረጃ በደረጃ የሚያሳዩ የቪዲዮ ትምህርቶችን እያዘጋጀን በመሆኑ ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር ማወቅ ይችላሉ
የሳይበር ደህንነት እና የሃኪንግ ጉዞዎን በራስዎ ላብራቶሪ ለመጀመር ዝግጁ ከሆኑ ቻናላችንን በመቀላቀል አዳዲስ መረጃዎችን ይከታተሉ

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤1
አንድ ልነግራቹ የምፈልገው ነገር ሃኪንግን እና ሳይበር ደህንነትን ለመለማመድ ትልቅ የኮምፒውተር ሃይል የሚጠይቁ አፕሊኬሽኖችን እና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ማሄድ የግድ ነው

ለዚህ ስራ የሚመከር ላፕቶፕ ቢያንስ 16GB ራም RAM ሊኖረው ይገባል ምክንያቱም በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ ቨርቹዋል ማሽኖችን ለማሄድ ይህ መጠን ወሳኝ ነው

ፕሮሰሰርን በተመለከተ Intel Core i5 ወይም i7 የቅርብ ጊዜ ትውልድ እንዲሁም AMD Ryzen 5 ወይም 7 የሆኑ ላፕቶፖች ለሃኪንግ ስራዎች በጣም ፈጣን እና አስተማማኝ ናቸው
የማከማቻ መጠንን በተመለከተ ቢያንስ 512GB SSD መያዙ ለፈጣን ዳታ ንባብ እና ለስርዓት መጫን ትልቅ ጥቅም ይሰጣል
ከስም ዝርዝር ውስጥ Lenovo ThinkPad ተከታታዮች በሃኪንግ እና በሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑት ለረጅም ጊዜ ስራ በመቆየታቸው እና ለመጠገን ቀላል በመሆናቸው ነው
Dell XPS እና Apple MacBook Pro ደግሞ ለተንቀሳቃሽነት እና ለስራ አፈጻጸም በጣም ጥሩ አማራጮች ሲሆኑ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለመስራት ይረዳሉ
ላፕቶፕ ስትገዙ ሁልጊዜም ቢሆን ሊኑክስ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በቀላሉ መቀበል የሚችሉ እና ክፍሎቹን ማሻሻል የምትችሉባቸውን ሞዴሎች መምረጥ ለወደፊቱ ትልቅ ፋይዳ አለው

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤1
የኢቲካል ሃኪንግ እና የሳይበር ደህንነት ጉዞዎን በአስተማማኝ ላፕቶፖቻችን እንዲጀምሩ HP LAPTOP በተመጣጣኝ ዋጋ ይዤላቹ መጥቻለሁ ያሉኝ 4 ስለሆኖ ቀድመው ለመጡት በተመጣጣኝ ዋጋ እሸጣለሁ

Processor: Intel Core i7 (Fast
multitasking

RAM: 16GB Optimized for multiple virtual machines

Storage: 256GB SSD Lightning-fast boot and data access

Display: 15.6 Clear and comfortable for long coding sessions

Full details
☎️ 0921951433 call
Tg user @skatf
Location wello
በቅርቡ "Loki" በተባለ አፕሊኬሽን ስም እየተከናወኑ ያሉ የባንክ ማጭበርበሮች እየተበራከቱ ነው። ይህ አፕሊኬሽን የባንክ የክፍያ መልእክቶችን SMS በማጭበርበር ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረገ ይገኛል።

አንድ ቅርብ ጓደኛዬ ልብስ ነጋዴ በዚህ ዘዴ ተታሎ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል።

ይህንን መልእክት ያካፈልኳችሁ አፑን እንድትጠቀሙበት ሳይሆን እንደዚህ አይነት አደገኛ የማጭበርበር ዘዴዎች እንዳሉ አውቃችሁ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ነው።


እንዴት እንጠንቀቅ
በ SMS አትመኑ ከባንክ ተላከ የተባለ ማንኛውም መልእክት SMS ላይ ብቻ አትመኑ። ገንዘብ እንደገባ ወይም እንደተላከ የሚያረጋግጠው የባንክዎን ኦፊሴላዊ አፕ App ወይም የባንክ መግለጫ Statementበመፈተሽ ብቻ ነው
ያልታወቁ አፖችን አትጫ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ያልታወቁ አፖችን በስልካችሁ ላይ አትጫኑ
OTP እና ሚስጥርን ጠብቁ የባንክ መረጃችሁን ወይም የOTP ኮድ ለማንም አትስጡ።
የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቁ ስለሆነ ሁሌም ነቅተን እንጠብቅ !

ይህንን መልእክት ለሌሎችም በማጋራት ከማጭበርበር እንዲታቀቡ ያድርጉ።
#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤2
ደረጃ 1፡ የኔትወርክ መሰረታዊ እውቀት Networking Essentials
ምን መማር አለበት? IP Address, DNS, DHCP, HTTP/HTTPS እና እንዴት ዳታ ከኮምፒውተር ወደ ኮምፒውተር እንደሚተላለፍ።

ተግባር: ping, traceroute, እና ifconfig ትእዛዞችን በራስህ ኮምፒውተር ሞክር።

ደረጃ 2፡
ሊኑክስን መቆጣጠር (Mastering Linux)
ምን መማር አለበት? ሊኑክስ የሃኪንግ ቋንቋ ነው። Terminal-ን መጠቀም፣ ፋይሎችን መቆጣጠር እና Permission ማስተካከልን።

ተግባር: Kali Linux-ን በቨርቹዋል ማሽን ጭነህ ከዊንዶውስ ይልቅ በሊኑክስ ብቻ ለ3 ቀናት ለመስራት ሞክር።

ደረጃ 3፡ የደህንነት መሳሪያዎች Security Tools
ምን መማር አለበት? Nmap (ኔትወርክ ለመቃኘትWireshark ዳታ ለማየትMetasploit ክፍተቶችን ለመሞከር
ተግባር: በኔትወርክህ ውስጥ ያሉ ክፍት የሆኑ Ports -ን በ Nmap በመቃኘት እወቅ።

ደረጃ 4፡ የድረ-ገጽ ሃኪንግ (Web Application Hacking)
ምን መማር አለበት? SQL Injection XSS, እና እንዴት ድረ-ገጾች እንደሚጠለፉ

ተግባር OWASP Juice Shop የተባለውን ለትምህርት የተዘጋጀ ድረገፅ በመጫን እሱን ለመጥለፍ ሞክር።

ደረጃ 5 እውነተኛ የሃኪንግ ላብራቶሪ (Capture The Flag - CTF)
ምን መማር አለበት? የተማርከውን ሁሉ በአንድ ላይ በማቀናጀት ነገሮችን መፍታት።

ተግባር TryHackMe ወይም HackTheBox በተባሉ ድረገጾች ላይ በመመዝገብ የመጀመሪያውን Room አጠናቅቅ።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ስለ አንድ የተወሰነ የትምህርት ክፍል ለምሳሌ Nmap እንዴት እንደሚሰራ ወይም ሊኑክስ ላይ ፋይል እንዴት እንደሚቀየር እንማራለን

ከዛሬ ጀምሮ የጽሁፍ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ ደረጃ የምንሰራቸውን Lab Tasks እንጀምራለን የትኛው ደረጃ ላይ እንደሆናቹ ኮሜንት ላይ ጻፍፉኝ ።

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤2
ብዙ ሰው ይጠይቃል እንደ ጀማሪ የሳይበር ደህንነትን እንደ ሙያ ስንመለከት፣ ትላልቅ ሲስተሞችን የተለያዩ የሰዎች አካውት አፖች ዌብ እንደ ጎግል ያሉትን መጥለፍ ፈጽሞ ቀላል አይደለም።

እነዚህ ኩባንያዎች በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን በደህንነት ላይ ስለሚያፈሱ፣ የሃኪንግ ጥረቶች ትኩረት የሚያደርጉት ሲስተሙን "በኃይል ለመስበር" ሳይሆን፣ ስርዓቱን በዘዴ ለመፈተሽ ነው።

አንድ የደህንነት ተመራማሪ ጎግልን ወይም መሰል ትላልቅ ድረ-ገጾችን ሲፈትሽ የሚከተሉትን አካሄዶች ይከተላል፦
በመጀመሪያ፣ ሃከሮች በኩባንያው የተፈቀደ የ"Bug Bounty" ፕሮግራም ውስጥ በመመዝገብ ህጋዊ ፈቃድ ያገኛሉ። ይህ ፕሮግራም እንደ ጎግል ያሉት ተቋማት የራሳቸውን ሲስተም ደህንነት ለማረጋገጥ የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ ክፍተቶችን ለሚያገኙ ተመራማሪዎች ሽልማት ይሰጣሉ። ይህ የሚያሳየው ጥበብ በህግ መዋቅሮች ውስጥ ሲከናወን ከፍተኛ ተቀባይነት እንዳለው ነው።

በመቀጠል፣ የጥበብ ሂደቱ የሚጀምረው በ"Reconnaissance" ወይም የመረጃ አሰባሰብ ደረጃ ነው። ሃከሩ የኩባንያውን የኢንተርኔት መሠረተ ልማት፣ የጎራ ስሞች (Subdomains)፣ እና የሶፍትዌር አይነቶችን በጥልቀት ያጠናል። ትኩረቱ በኩባንያው ዋና መግቢያ ላይ ሳይሆን፣ በኩባንያው ውስጥ ባሉ ትናንሽ እና ብዙም ትኩረት ባላገኙ የውስጥ መተግበሪያዎች ወይም የAPI መገናኛዎች ላይ ነው። ትላልቅ ኩባንያዎች ዋና የደህንነት በራቸውን በጥብቅ ቢቆልፉም፣ በየቀኑ በሚለቀቁ አዳዲስ ኮዶች እና አፕሊኬሽኖች ምክንያት ትናንሽ የደህንነት ክፍተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።
በመጨረሻም፣ የተገኘውን ክፍተት በጥንቃቄ በመሞከር የሲስተሙን ደህንነት ይገመግማሉ።

ለምሳሌ፣ የድር ጣቢያ ክፍተቶችን የሚፈትሹ እንደ Cross-Site Scripting (XSS) ወይም SQL Injection ያሉ ቴክኒኮችን በመጠቀም፣ በሲስተሙ ውስጥ ያለውን የውሂብ አያያዝ ይፈትሻሉ። ዋናው አላማ ሲስተሙን መጉዳት ሳይሆን፣ ክፍተቱን ለኩባንያው በግልጽ በማሳወቅ እና የደህንነት ማሻሻያ እንዲደረግ ማድረግ ነው።
በአጠቃላይ፣ ትላልቅ ሲስተሞችን የመፈተሽ ጥበብ ማለት የአንድን ትልቅ መዋቅር እያንዳንዱን ክፍል እንደ እንቆቅልሽ በመቁጠር፣ የትኛው ክፍል ደካማ እንደሆነ በስልት መለየት ነው። ይህ የሚያሳየው የሃኪንግ ጥበብ ከጥፋት ይልቅ በችግር አፈታት እና በስርዓት ግንባታ ላይ የሚያተኩር የዘመናችን ትልቅ የቴክኖሎጂ ክህሎት መሆኑን ነው።

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤4
የመጀመሪያ ስራችሁ TryHackMe የሚባለውን website መክፈት ነው ይህ የላብራቶሪ ማዕከላችሁ ነው እዚያ ስትገቡ Pre-Security የሚለውን መንገድ ምረጡ ይሄ ክፍል ኮምፒውተራችሁ እንዴት ከኔትወርክ ጋር እንደሚገናኝ አይፒ አድራሻ ምን እንደሆነ እና ሰርቨር እንዴት እንደሚሰራ የሚያስተምር ነው ምንም ነገር በኮምፒውተራችሁ ላይ መጫን አያስፈልጋችሁም ሁሉም ነገር በብሮውዘር ውስጥ ነው የሚሰራው

2: የሊኑክስ ትዕዛዝ ማዕከል ሃኪንግን የምትማሩት በዊንዶውስ አይደለም በሊኑክስ ተርሚናል ነው ስለዚህ TryHackMe ላይ Linux Fundamentals የሚለውን ክፍል ጨርሱ እዚያ ስትገቡ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይነግራችኋል ለምሳሌ ፋይል እንዴት መክፈት የት እንዳላችሁ ማወቅ pwd እና ፋይሎችን እንዴት ማየት እንደሚቻል ls ትለማመዳላችሁ ይሄን ስትጨርሱ ኮምፒውተርን በደንብ መቆጣጠር ትጀምራላቹ

3:የመሳሪያዎች መተግበሪያ አንዴ የሊኑክስን መሰረት ከያዛችሁ በኋላ ወደ Nmap እና Wireshark ትገባላችሁ እነዚህ የሃከሮች መነጽር ናቸው በ TryHackMe ላይ እነዚህን መሳሪያዎች ተጠቅማችሁ የተደበቁ የኔትወርክ ክፍተቶችን እንዴት እንደምታገኙ ትለማመዳላችሁ። በዩቲዩብ The Cyber Mentor የተባለውን ቻናል በመክፈት Practical Ethical Hacking የሚለውን ቪዲዮ ስታዩ የጠቀስኳቸውን መሳሪያዎች በእጅ ስራ እንዴት እንደምትጠቀሙ በግልጽ ታያላችሁ

4:እውነተኛ የጥቃት ሙከራ በመጨረሻም የተማራችሁትን ሁሉ በአንድ ላይ የምትፈትሹበት ጊዜ ነወ OWASP Juice Shop የሚባለውን web በመጠቀም እውነተኛ የኢ ኮሜርስ web ን እንዴት እንደምትሰበሩ በህጋዊ መንገድ ትለማመዳላችሁ ይሄ web በተለይ የደህንነት ክፍተቶችን ለመለማመድ ተብሎ የተሰራ ስለሆነ ምንም አይነት ህግ አትጥሱመ
ወደ ተግባር ለመግባት የምትወስዷቸው እርምጃዎች
ወደ TryHackMe ግቡና አካውንት keftu
በየቀኑ ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ በዚያ web ላይ ላብራቶሪ ስሩ
ያጋጠማችሁን ችግር ኮሜንት ላይ አብረን እንፈታዋለን።🤞

#CodeCracker #CyberSecurity #TechSavage #StaySecure #EthiopiaTech

@CODE_CRACKER_ET
@CODE_CRACKER_ET
❤1