Code Biruh©
Photo
GraphQL ምንድን ነው?
ከዚህ ቀደም ስለ REST API ተነጋግረን ነበር። ነገር ግን በቴክኖሎጂው ዓለም መረጃን ይበልጥ በብቃት ለማምጣት አዲስና የተሻለ አማራጭ መጥቷል 👉 GraphQL.
GraphQL በ 2012 በ Facebook (Meta) develop የሆነ እና በ 2015 Open-source የሆነ የዳታ መጠየቂያ ቋንቋ (Query Language) ነው። እንደ REST API ሁሉ መረጃን ከሰርቨር ለማምጣት ያገለግላል፤ ልዩነቱ ግን አጠቃቀሙ ላይ ነው።
በ REST API ጊዜ ሰርቨሩ የሰጠንን ዳታ በሙሉ ለመቀበል እንገደዳለን። በ GraphQL ግን የምንፈልገውን መረጃ ብቻ ለይተን መጠየቅ እንችላለን።
ለምሳሌ፦ የአንድን ተጠቃሚ ስም ብቻ ከፈለጋችሁ፣ ሰርቨሩ ስሙን ብቻ ይልክላችኋል። በ REST ቢሆን ኖሮ ግን ስሙን፣ ስልኩን፣ አድራሻውን እና የማይፈለጉ ብዙ መረጃዎችን አብሮ ይልክ ነበር።
GraphQL ለምን ልዩ ነው?
➤ Over-fetchingን ያስቀራል: የማንፈልገውን ዳታ አናመጣም።
➤ Under-fetchingን ይከላከላል: በአንድ ጥያቄ (Query) ብቻ ከተለያዩ ቦታዎች መረጃን መሰብሰብ ይችላል።
➤ ፍጥነት: ለሞባይል አፕሊኬሽኖች እና ዝቅተኛ ኢንተርኔት ላላቸው ተጠቃሚዎች በጣም ፈጣን ነው።
➤ አንድ Endpoint: እንደ REST ብዙ URL አያስፈልገውም፤ ሁሉንም ነገር በአንድ
ዛሬ እንደ GitHub, Pinterest, እና Shopify ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ GraphQL ተቀይረዋል። ለአንድ ዘመናዊ Full-stack ደቨሎፐር GraphQLን ማወቅ ትልቅ ብቃት ነው።
ባጭሩ GraphQL ማለት "የምትፈልገውን ብቻ ጠይቅ፣ የጠየቅከውን ብቻ አግኝ" የሚል መርህ ያለው ቴክኖሎጂ ነው።
ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊
📌 እስኪ እናንተ ደግሞ GraphQLን ሞክራችሁታል? ከ REST API የትኛው ይበልጥ ይመቻችኋል? Comment ላይ አስተያየታችሁን ጻፉልን! 👇
✍️ @codebiruh
#GraphQL #API #Frontend #Backend
ከዚህ ቀደም ስለ REST API ተነጋግረን ነበር። ነገር ግን በቴክኖሎጂው ዓለም መረጃን ይበልጥ በብቃት ለማምጣት አዲስና የተሻለ አማራጭ መጥቷል 👉 GraphQL.
GraphQL በ 2012 በ Facebook (Meta) develop የሆነ እና በ 2015 Open-source የሆነ የዳታ መጠየቂያ ቋንቋ (Query Language) ነው። እንደ REST API ሁሉ መረጃን ከሰርቨር ለማምጣት ያገለግላል፤ ልዩነቱ ግን አጠቃቀሙ ላይ ነው።
በ REST API ጊዜ ሰርቨሩ የሰጠንን ዳታ በሙሉ ለመቀበል እንገደዳለን። በ GraphQL ግን የምንፈልገውን መረጃ ብቻ ለይተን መጠየቅ እንችላለን።
ለምሳሌ፦ የአንድን ተጠቃሚ ስም ብቻ ከፈለጋችሁ፣ ሰርቨሩ ስሙን ብቻ ይልክላችኋል። በ REST ቢሆን ኖሮ ግን ስሙን፣ ስልኩን፣ አድራሻውን እና የማይፈለጉ ብዙ መረጃዎችን አብሮ ይልክ ነበር።
GraphQL ለምን ልዩ ነው?
➤ Over-fetchingን ያስቀራል: የማንፈልገውን ዳታ አናመጣም።
➤ Under-fetchingን ይከላከላል: በአንድ ጥያቄ (Query) ብቻ ከተለያዩ ቦታዎች መረጃን መሰብሰብ ይችላል።
➤ ፍጥነት: ለሞባይል አፕሊኬሽኖች እና ዝቅተኛ ኢንተርኔት ላላቸው ተጠቃሚዎች በጣም ፈጣን ነው።
➤ አንድ Endpoint: እንደ REST ብዙ URL አያስፈልገውም፤ ሁሉንም ነገር በአንድ
/graphql በኩል መጨረስ ይቻላል።ዛሬ እንደ GitHub, Pinterest, እና Shopify ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ወደ GraphQL ተቀይረዋል። ለአንድ ዘመናዊ Full-stack ደቨሎፐር GraphQLን ማወቅ ትልቅ ብቃት ነው።

❤12👍1🔥1