Code Biruh©
4.59K subscribers
179 photos
70 links
Welcome 🤗

➢ For #TechEnthusiasts, #Programmers & #Learners
Discover insights on coding, projects, and networks.

💻 Need a custom software solution? Let’s build something powerful together!

Empowering Minds

📩 Contact us: @CodeBiruhSupport
Download Telegram
Multimodal AI 2.0 ምንድን ነው?

AI አሁን ማየት፣ መስማት እና መናገር ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉንም በአንድ ላይ አቀናጅቶ እንደ ሰው ማሰብ ወደሚችልበት ደረጃ ተሸጋግሯል! ይህ የቴክኖሎጂ እድገት Multimodal AI 2.0 ይባላል።

የመጀመሪያው ትውልድ (1.0) AI ሞዴሎች አንድን መረጃ (ለምሳሌ ጽሑፍን) ወደ ሌላ (ለምሳሌ ምስል) ለመቀየር የተለያዩ ሞዴሎችን ይጠቀሙ ነበር። በ 2.0 ግን፣ አንድ ነጠላ ሞዴል ጽሑፍን፣ ምስልን፣ ድምጽን እና ቪዲዮን በአንድ ጊዜ ተረድቶ ምላሽ ይሰጣል።

ለምሳሌ ያህል፦
በስልካችሁ ካሜራ አንድን የተበላሸ ዕቃ እያሳያችሁት፤
Multimodal 1.0: ፎቶ አንስታችሁ ትልካላችሁ፣ እሱም ፎቶውን አይቶ በጽሑፍ ይነግራችኋል።
Multimodal 2.0: ልክ እንደ ሰው በቪዲዮ እያየው፣ እናንተ በድምፅ ስታወሩት እሱም በድምፅ "እዚህ ጋር ያለችውን ብሎን አጥብቃት" እያለ ቅጽበታዊ (Real-time) መመሪያ ይሰጣችኋል።

የMultimodal 2.0 ዋና ዋና ጥቅሞች፦
ቅጽበታዊ ግንኙነት (Native Reasoning): መረጃዎችን ለመተርጎም ጊዜ አይወስድም፤ ልክ እንደ ሰው በፍጥነት ስሜትንና ሁኔታዎችን ይረዳል።
ሁለንተናዊ ግንዛቤ: አንድን ቪዲዮ አይቶ በውስጡ ያለውን ድምፅ፣ እንቅስቃሴና ጽሑፍ በአንድ ላይ አቀናጅቶ ትርጉም ይሰጣል።
More accuracy: መረጃዎችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች (Multi-sensory) ስለሚያገኝ የሚሰጠው ውሳኔ እጅግ አስተማማኝ ነው።

ባጭሩ Multimodal AI 2.0 ማለት AI " ዓይኑን ገልጦ " ዓለምን እንደ እኛ ማየትና መስማት የጀመረበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ነው።

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊

✍️ @codebiruh

#MultimodalAI #GenerativeAI #TechTrends #AI2.0
4👍3