Code Biruh©
4.6K subscribers
179 photos
70 links
Welcome 🤗

➢ For #TechEnthusiasts, #Programmers & #Learners
Discover insights on coding, projects, and networks.

💻 Need a custom software solution? Let’s build something powerful together!

Empowering Minds

📩 Contact us: @CodeBiruhSupport
Download Telegram
Code Biruh©
Photo
#DOCKER

ዛሬ ስለ Docker የሆነ ነገር ልንላችሁ ወደድን።

አብረን እንቆይ🥰

Docker ምንድን ነው?

በቀላሉ እንድንረዳው አንድ senario እንውሰድ።

እናንተ እቃወችን ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚያዘዋውር company ባለቤት ናችሁ እንበል። (እንበል ነው ያልን😊 ደግሞ ማን ያውቃል ብትሆኑስ💪)

💭 ድሮ container ከመምጣቱ በፊት
➢ የተለያዩ እቃወችን (like tv, pc, clothes, food...) ለብቻቸው ይታሸጉ ነበር።
➢ ማውረድ እና መጫን ከባድ ነበር።
➢ በtransport ጊዜም እቃወች ሊቀላቀሉም ሊሰበሩም ይችላሉ።
➢ ለእቃዎቹም የተለያዩ መኪናዎች ያስፈልጉ ነበር። እና ስራችሁ በጣም ከባድና አሰልቺ ነበር።

💭 አሁን ግን container የሚባል ሁሉንም ነገሮች ሊይዝልን የሚችል እቃ በመምጣቱ ሁሉንም እቃዎች standard-sized በሆነ አቅሙ እንዲይዛቸውና በቀላሉ transport እንድናደርግ ያስችላል።

የሚገርመው ግን ያን container ትልቅ መኪናም ውስጥ ጫኑት፣ የሆነ መርከብ የሚይዘው ቦታ ተመሳሳይ ነው።

Docker እነዚህ container-ኦች በአግባቡ መርከቡ ውስጥ እንዲጫኑና የተፈለጉበት ቦታ እንዲደርሱ የሚያደርግ system ነው።

ስለዚህ application-ኣችሁን እንደ እቃወቹ፤ Docker Container-ኦችን ደግሞ እንደ መርከቡ container-ኦች እና Dockerን ደግሞ እንደ system ማሰብ እንችላለን።

ለተለያዩ operating system-ኦች የምንሰራቸውን application-ኦች አንዴ ሰርተን በdocker container ካስቀመጥን በኋላ ድጋሜ መስራት ሳይጠበቅብን መጠቀም እንችላለን። container-ኡን መኪናም ላይ መርከብም ላይ ብንጭነው ተመሳሳይ እንደ ሆነ ሁሉ።

📌 የDocker ጥቅሞች በጣም ብዙ ሲሆኑ ለምሳሌ:-

➺ Application Packaging
➺ Simplified Development & Testing
➺ CI/CD Automation
➺ Microservices Architecture
➺ Environment Isolation
➺ Cloud Deployment
እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል።

📌 Docker እስካሁን ድረስ በsoftware development እና DevOps engineers ተወዳጅና ተመራጭ ነው።

ሙሉ installation የሚፈልግ ሰው ከ10 በላይ ከሆነ እንለቃለን። የምትፈልጉ comment ጋ እንፈልጋለን እያላችሁ ጻፉልን።

#Docker #Docker_Container #DevOps #Software #Code #codeBiruh
9👍4
Git & GitHub(Version Control) Insights
 
Part 1
#Git #Github #Version_control #DevOps #Code #codeBiruh
2🙏2
Git & GitHub(Version Control) Insights
 
Part 2
#Git #Github #Version_control #DevOps #Code #codeBiruh
💡 Tech Explained in Simple Words

🔹 Blockchain – A digital ledger that securely records transactions, making data tamper-proof and transparent.

🔹 Web3 – The next generation of the internet, built on decentralization, where users own their data and digital assets.

🔹 Cloud – Online servers that let you store, manage, and run applications without needing your own physical machines.

🔹 DevOps– A culture + set of tools that bring developers and operations teams together to deliver software faster and more reliably.

👉 These four pillars are shaping today’s tech world—understanding them gives you a strong foundation in modern development.

#CodeBiruh #Blockchain #Web3 #Cloud #DevOps
🚀 7 Free Websites to Learn Linux & DevOps! 💻

Whether you’re starting out or leveling up your skills, these 7 free resources will help you master Linux, DevOps, Cloud, and Container technologies:

1. Linuxhttps://linuxopsys.com/🐧
2. Bash Scriptingblog.sysxplore.com 🖋
3. AWShttps://explore.skillbuilder.aws/☁️
4. Azurelearn.microsoft.com 🔵
5. DevOpsedx.org/learn/devops🔧
6. Dockerhttps://docker-curriculum.com/🐳
7. Kuberneteskubernetes.io ☸️

#CodeBiruh #Linux #DevOps #AWS #Azure #Docker #Kubernetes #CloudComputing #TechLearning #ProgrammingJourney #LearnToCode
Code Biruh©
Photo
DevOps ምንድን ነው?

አንድን ሶፍትዌር ሰርቶ ለተጠቃሚ ለማድረስ በድሮ ጊዜ በሁለት ቡድኖች መካከል ትልቅ ቅራኔ ነበር። የሶፍትዌር አበልጻጊዎች (Developers) "እኛ ሰርተን ጨርሰናል" ይላሉ፤ የሲስተም አስተዳዳሪዎች (Operations) ደግሞ "ኮዱ አልሰራም" እያሉ ይጨቃጨቃሉ። ይህንን ችግር ለመፍታት አንድ አስደናቂ ነገር መጣ 👉 DevOps.

DevOps የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን Development (Dev) እና Operations (Ops) ማለት ነው።
በቀላል አገላለጽ DevOps ማለት አንድን ሶፍትዌር በፍጥነት፣ በጥራት እና ያለምንም መቆራረጥ ለተጠቃሚዎች ለማድረስ የሚያስችል የሥራ ባህል እና የቴክኖሎጂ ቅንጅት ነው።

DevOps በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው፦
Automation (ስራዎችን በራሳቸው እንዲሰሩ ማድረግ)
CI/CD (ኮድን በየጊዜው መፈተሽና ወደ ተጠቃሚ መላክ)
Monitoring (ሶፍትዌሩ በትክክል መስራቱን መከታተል)
Reliability (አስተማማኝ አገልግሎት መስጠት) ላይ ነው።

ለDevOps ስራ በብዛት የምንጠቀምባቸው Tools፦
Git (ለኮድ ቁጥጥር)
Docker & Kubernetes
Jenkins (ለኦቶሜሽን)
AWS / Azure (ለክላውድ አገልግሎት)

ባጭሩ DevOps ማለት አንድን አፕሊኬሽን የመገንባት፣ የመፈተሽ፣ ለተጠቃሚ የማድረስ እና የመቆጣጠር ሂደት ያለ እረፍት እንዲቀጥል የሚያደርግ "የቴክኖሎጂ ኢንጂን" ነው ማለት ይቻላል
በአሁኑ ሰዓት DevOps በዓለም አቀፍ ደረጃ እና በታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ እጅግ ተፈላጊ እና ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ዘርፍ ነው።

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊

📌 እስኪ እናንተ DevOpsን ለመማር ፍላጎቱ አላችሁ ወይስ እየተማራችሁ ነው? Comment ላይ ያሳውቁን! 👇

✍️ @codebiruh

#DevOps #CloudComputing #Automation #Programming
👍114
Linux ምንድን ነው?

ብዙዎቻችን ኮምፒውተር ስንጠቀም የምናውቀው Windows ወይም macOSን ነው። ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ጀርባ ዓለማችንን በዝምታ የሚመራ አንድ ግዙፍ ኃይል አለ 👉 Linux.

Linux በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰርቨሮችን፣ ሱፐር ኮምፒውተሮችን እና ስልኮችን (Androidን ጨምሮ የሚያንቀሳቅስ Open-source የሆነ Operating System ነው።

ከWindows ወይም ከmacOS የሚለየው ትልቁ ነገር፤ Linuxን በነጻ ማግኘት፣ እንደ ፍላጎታችን መቀየር (Modify) እና ለሌሎች ማጋራት መቻላችን ነው። ለዚህም ነው Developers እና በሲስተም አስተዳዳሪዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነው።

Linux በዋናነት ለምን ይጠቅማል?
ለዌብ ሰርቨሮች (Web servers)
ለክላውድ መሰረተ ልማቶች (Cloud infrastructure)
ለፕሮግራሚንግ እና ለሶፍትዌር ግንባታ
ለትንንሽ ዘመናዊ መሣሪያዎች (IoT devices)

Linux እንደየ ፍላጎታችን በተለያዩ አይነቶች (Distributions) ይከፈላል። ለምሳሌ፦ Ubuntu, Fedora, Debian, እና CentOS በብዛት የሚታወቁት ናቸው።

ባጭሩ Linux ጠንካራ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንደፈለጉት የሚመች ሲስተም ነው። እሱን ማወቅ በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ ብዙ የሥራ በሮችን ይከፍታል .

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊

📌 እስኪ እናንተ ደግሞ Linux ትጠቀማላችሁ? የምትወዱት የLinux አይነት (Distro) የትኛው ነው? Comment ላይ ንገሩን! 👇

✍️ @codebiruh

#Linux #OpenSource #Programming #DevOps
7👍4
Code Biruh©
Photo
CI/CD ምንድን ነው?

አንድን ሶፍትዌር
ሰርተን ለተጠቃሚ ለማድረስ (Deployment) ስንነሳ ብዙ ጊዜ የምንጨነቀው "ኮዱ ይሰራል ወይ? ስህተት ቢኖሮስ? ሲስተሙ ቢቆምስ?" ብለን ነው። ይህንን ጭንቀት ለማስወገድ የመጣ አንድ ድንቅ አሰራር አለ 👉 CI/CD.

CI/CD (Continuous Integration / Continuous Deployment) ዝም ብሎ ኦቶሜሽን ብቻ አይደለም፤ የሥራ ባህልና አስተሳሰብ ጭምር ነው ።

ባጭሩ CI/CD ማለት የጻፍነውን ኮድ በየጊዜው እርስ በርስ ማገናኘት፣ በራሱ ጊዜ እንዲፈተሽ (Testing) ማድረግ እና ያለምንም ስጋት ለተጠቃሚ እንዲደርስ ማድረግ ነው።

አብዛኛው ጀማሪ Programmers የማያውቃቸው የCI/CD ጥቅሞች፦

የሰውን ስህተት ይቀንሳል፦ ኮዱን ለተጠቃሚ ለማድረስ እኛ በእጃችን የምናደርገውን ጥረት ስለሚያስቀር ስህተቶች እንዳይፈጠሩ ያደርጋል።
Feature Flags፦ ኮዱን ዛሬ አፕሊኬሽኑ ላይ ጭነን (Deploy) ለተጠቃሚዎች ግን በፈለግንበት ሌላ ቀን እንዲታይ ማድረግ እንችላለን።
ፈጣን ርምጃ (Rollbacks)፦ አዲሱ ኮድ ችግር ቢፈጥር እንኳን፣ በቅጽበት ወደ ቀድሞው ወደሚሰራው ኮድ ያለምንም መደናገጥ መመለስ ያስችላል።

የCI/CD ስራን ለማቀልጠፍ እንደ GitHub Actions ወይም GitLab CI ያሉ መሣሪያዎችን መጠቀም ስራችንን እጅግ ያቃልሉልናል።

ባጭሩ CI/CD ማለት ለኮዳችሁ እንደ "Autopilot" ነው፤ እናንተ ኮዱን ትጽፋላችሁ፣ እሱ ደግሞ በሰላም ያደርሳል ።

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊

📌 እስኪ እናንተ ደግሞ ለCI/CD የምትጠቀሙትን Tool ወይም ማወቅ የምትፈልጉትን ጥያቄ comment ላይ ጻፉልን?

✍️ @codebiruh

#CICD #DevOps #Automation #Programming
11👍4
Code Biruh©
Photo
Kubernetes ምንድን ነው?

ባለፈው ስለ Microservices ስናወራ ሲስተሞችን መገንባት ጠቃሚ መሆኑን አይተናል። ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ሲስተሞች (Containers) ሲኖሩን እነሱን እንዴት በቀላሉ ማስተዳደር እንችላለን? ለዚህ መፍትሄው 👉 Kubernetes (K8s) ነው።

KubernetesGoogle develop የተደረገ እና አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል የContainer Orchestration መሣሪያ ነው። "Orchestration" ሲባል ልክ እንደ አንድ የሙዚቃ መሪ (Conductor) ሁሉንም የሙዚቃ መሣሪያዎች አስተባብሮ እንደሚመራው፣ Kubernetes ደግሞ ኮንቴይነሮችን (Containers) ያስተባብራል ማለት ነው።

በቀላል ምሳሌDockerን እንደ አንድ እቃ የያዘ ሳጥን (Container) ብንወስደው፣ Kubernetes ደግሞ እነዛን በሺዎች የሚቆጠሩ ሳጥኖችን የሚጭን፣ የሚያወርድ እና የት መቆም እንዳለባቸው የሚወስን ግዙፍ መርከብ ወይም ወደብ አስተዳዳሪ ነው ማለት ይቻላል።

Kubernetes ለምን እጅግ አስፈላጊ ሆነ?
ራስን ማከም (Self-healing): አንድ ኮንቴይነር ቢበላሽ ወይም ቢጠፋ፣ Kubernetes ወዲያውኑ አውቆ አዲስ ይተካለታል።
አውቶማቲክ ማሳደግ (Auto-scaling): ብዙ ተጠቃሚዎች ሲመጡ ኮንቴይነሮችን በራሱ ይጨምራል፣ ተጠቃሚ ሲቀንስ ደግሞ ይቀንሳል።
ጭነትን ማመጣጠን (Load Balancing): የኢንተርኔት ትራፊክ ሲበዛ ለሁሉም ኮንቴይነሮች እኩል እንዲዳረስ ያደርጋል።
ያለ መቋረጥ ማደስ (Rolling Updates): ሲስተሙን ሳይዘጉ አዳዲስ ለውጦችን (Updates) ለመጫን ያስችላል።

ዛሬ በ Cloud Computing ዓለም ውስጥ Kubernetes የማይታለፍ ቴክኖሎጂ ነው። እሱን ማወቅ ለ DevOps ኢንጂነሮች እና ለከፍተኛ Backend ደቨሎፐሮች ትልቅ የሥራ ዕድል ይፈጥራል።

ባጭሩ Kubernetes ማለት የኮንቴይነሮች አለቃ፣ ሲስተምዎ እንዳይወድቅና ሁልጊዜም በብቃት እንዲሠራ የሚያደርግ "ጥበበኛ" ነው!

ጽሑፉን ከወደዳችሁት 👍,❤️ አይረሳ። 😊

📌 እስኪ እናንተ ደግሞ Kubernetesን ተጠቅማችሁ ታውቃላችሁ? ወይስ አሁንም በ Docker ብቻ ነው የምትጠቀሙት? Comment ላይ ያጋሩን! 👇

✍️ @codebiruh

#Kubernetes #K8s #Docker #DevOps
17🖕1