Classical Protestant
714 subscribers
318 photos
142 videos
60 files
83 links
The true heart of the classical Protestant Reformation is a return to the early Church faith grounded in the infallible authority of Scripture 📖 and Christ-centered doctrine ✝️ Anglican

Harmonic Heavens
Download Telegram
For 39 Article Commentaries from @Classical_Protestant.zip file: the names of the commentaries, authors, and the names of the PDF files
👍6❤1
"Protestant Dilemma" lol

አንዳንድ ጊዜ ከፕሮቴስታንት የወጡ ሰዎች የሚገርሙኝ እና የሚያሳዝኑኝ ነገር ለገቡት እንግዳ ሀሳብ በደንብ ጥናቱን ሳያረጉ ከማንኛውም ሰው በላይ ሲቃወሙ ወይ ሲደግፉ ማየታችን ነው። ለዚህም ጥሩ ምሳሌ Cleave to antiquity ነው። እንደው የሚያነሳው ሙግት ራሱ እዚህ ግባ የማይባል.... እስኪ በዚህ ላይቭ ሴሽን የ"Protestant Dilemma" ብሎ ላነሳው ሙግት የsean luke እና የPaulን ምላሾችን ልጋብዛችሁ።

https://youtube.com/live/32kDoj8_WQQ?si=MVFm9FsLI-Uua_TF
🔥6
ፕሮቴስታንት ሆኜ ለምን ቆያለሁ? እንዴት በተለያዩ ትራዲሽን ውስጥ ያለውን ክርስትና የቱን ልምረጥ?

አንዱና ብዙ ጊዜ ከተጠየኩት ጥያቄ ውስጥ እንዴት በተለያዩ ትራዲሽን ውስጥ ያለን ክርስትና ልክ የሆነውን የቱን ልምረጥ? በዚህ ክርስትና ትራዲሽን ውስጥ(ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስ) ለመምረጥ እና ለመሆን ሲቸገሩ አያለሁ። በዚህም ጥያቄ ምክንያት አብዛኛው ክርስቲያን ማህበረሰብ ከአንዱ ወደ አንዱ ሲሄድ ይስተዋላል። ይሄም ጽሑፍ ብዙ ጥልቀት ያለው ነገር ባይናገርም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች ግን ጥሩ ጥቆማ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

አንደኛ፦ በደንብ ሰዓት መውሰድ

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በዚህ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ በሙሉ ስሜትና በሙሉ ሰላም ማሰብ ትተው በብዙ ነገሮች ይጠመዳሉ። ይሄም ደግሞ ለነገሩ ሰዓት አለመውሰዳችን አንዱ ማሳያ ነው። ነገሩ በትክክል በእኛ ላይ በተፈጠረ ጊዜ እኛ ማድረግ ያለብን የሰከነ ሰላምና ለተፈጠረብን ጫና በደንብ ሰዓት መውሰድ አለብን።

ሁለተኛ፦ በደንብ ማንበብ

ይህ ሰው ሰዓት በሚወስድበት ጊዜ የሚያጠናውን መንገድ ማቀናጀት ይጠበቅበታል። ይህም በሰፊው ማንብብ አንዱ ግዴታው ሊሆንም ይገደዳል። በተቻለ አቅም ማንበብ ያሉበትን ነጥቦች መወሰን አለበት። ስለ ሚሥጢራት አንዱ ከሆነ በታሪካዊው ወይም በክላሲካል ፕሮቴስታንት ውስጥ ያለውን ምልከታ አበጥሮ ማንበብ ግዴታው ያድርግ። ይህም ለገጠመው ጫና ፍትሃዊ ፍልሚያም ለማድረግም ይሁን።

ሦስተኛ፦ የሚገጥሙት ችግሮች

በአጋጣሚዎች ሊሆን ይችላል ወይም ሌላም ከእርሱ ሰርክል ውጪ ባሉ አብያተ ክርስቲያናትን ንፅፅሮች ሊገጥሙት ይችላል። የሚያጠናው ሰው በቀድሞው ሚስጥራትን ዝም ብሎ ሚሞሪያሊስት ከሆነና በቀጥታ በሚያየው ነገር ሊደነግጥና ባደገበት ቤተክርስቲያን የሚሥጢራቱ ጉዳይ በቀላሉ የሚታይ ከሆነ በቀላሉ ሊሳብ ይችላል። ነገር ግን ይህ አይነቱ ችግር በታሪካዊ ፕሮቴስታንቲዝም ላይ ያጠላ አደጋ ግን ፈጽሞ አይደለም። ልክ አልነበርኩም ብሎ ካለበት ችግር በቀላሉ ከመሳቡ በፊት ሰፊ ጥናት ማድረግ አለበት። ምክንያቱም ይህን ችግር የተከሰተበት የክላሲካል ፕሮቴስታንቲዝሙን አመለካከት ባደገበት እና ባላጠናው ነገር ላይ ሰፍቶ መያዙ ነው።

➞ ሌላው በጓደኞቹ ጫና ምክንያት ፍለጋው ሊበላሽ ይችላል። ስለዚህ በሚመጡለት ድምጾች ሳይሆን በሚያስብበት አእምሮ መታገዝ እንዲችል መፍቀድ አለበት።(በቀናነት የሚያግዙት የሉም ማለት ግን ፈጽሞ አይደለም።)

አራተኛ፦ የሚመርጣት ቤተክርስቲያን ሚሥጢራትን እንዴት ታያለች?

ይሄን ጥያቄ በፕሮቴስታንቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ታሪካዊ ነን በሚሉ ቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ትላልቅ ልዩነቶች አጥርቶ ማየት አለበት። አብዛኛው ሰው ፕሮቴስታንቲዝሙን በዚህ ለቆ ይወጣና የሚመርጠውን አያውቅም። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ታሪካዊውን ፕሮቴስታንት ሊለቅ ይችል ይሆን? መልሱ በፍፁም ነው። ታሪካዊውን ፕሮቴስታንቲዝም ሳያዩ ሊወጡ/የወጡ ሰዎች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ወይም የበለጠ የቅዱስ ቁርባን አመለካከት እንደሚጎተቱ በተሰማቸው ጊዜ የታሪካዊው ፕሮቴስታንት (አንግሊካን፣ ሉትራን፣ ፕሪስትባይቴሪያን፣ ትራዲሽናል ባብቲስት...) ያለውን አመለካከት ማየቱ ጥሩ ነው። በቅዱስ ቁርባንና የጥምቀት ሥርዓቶችን በውብ ሊተርጂዎች መታገዛቸውን ሲያይ ከዚህ ጥያቄ የሚወጣ ይሆናል( በዚህም ላይ የታሪካዊው ፕሮቴስታንት አቋም እጅግ ጽኑ ነው።)

አምስተኛ፦ ከፕሮቴስታንት ዲኖሚኔሽን የቱን ልምረጥ?

ይህ ጥያቄ በሚያጠናበት ጊዜ ከላይ የተቀመጠለትን ተመሳሳይ መንገድ መከተል አንዱ መፍትሔ ነው። እንደ ተጨመሪ ነጥቦች ደግሞ ይህ ሰው አሁን እያነበበ ካለ አጭሩ እና የምነግረው ነገር ፕሮቴስታንት ማለት ቤተክርስቲያን አይደለም። አንድ ሙቭመንት መሆኑን አበክሮ ማወቅ አለበት። ጠቅልሎ ፕሮቴስታንት እንዲህ ነው ማለትና አንዲት ቤተክርስቲያን ነች ስለዚህ በመካከላችሁ ክፍፍል አለ ምናምን የሚል አቋም ከመያዙ በፊት የታሪካዊውን መሠረቶች እና አንድነቶች ማየት አንዱ መንገድ ነው።[በዚህች ርዕስ ላይ ሰፋ ባለ መልኩ የምንሄድበት ይሆናል።]

ሁለተኛው መፍትሄ ከእናተ የትኛውን ልምረጥ ካለ መስፈርቶቹን አልፎ የክላሲካል ፕሮቴስታንት ካታክዚሞች፣ ኮንፌሽኖችን፣ አርቲክሎችን እና መሠረታዊያኑን ማንበብ ይጠበቅበታል።

ስድስተኛ፦ ጸሎት

ከሁሉም አስቀድሞ መዝጊያውን ዘግቶ ይፀልይ። በዚህም እግዚአብሔር ጽኑ መንገዱንና ፍለጋውን ያገኝ ይረዳዋል።

በመጨረሻም፦ በዚህ ሁኔታ ላላችሁ ሰዎች በስድስቱ ነጥቦች ላይ ያሉትን አተኩሮ ላየ ሰው  የጽሑፉን ርዕስ የሚመልስ ይሆናል እላለሁ። በተጨማሪ 5ቱ ሶላዎች መሠረታዊ እና አንድ የሚያረገን ከሌሎች ቤተክርስቲያን ጋር የሚያለያየንን ነጥቦች ይመልከት ስል ጨርሳለሁ። ምናልባት ጥያቄ ያለው ሰው ካለ በውስጥ መጻፍ ይችላል። እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ፍለጋ ይረዳው ዘንድም እንጸልያለን።
------
@AnglicanFaith
@Classical_Protestant
❤12
የጥንቱን ሃይማኖት?

ጆን ኖክስ:፦

"በእግዚአብሔር ሃይማኖት ውስጥ የሰው አእምሮ የፈለሰፈው አምልኮ፣ ማክበር ወይም አገልግሎት ሁሉ ያለ እግዚአብሔር ግልጽ ትዕዛዝ ከሆነ ጣዖት አምልኮ ነው።"[1]


የዚህን ታላቅ ፕሮቴስታንት ሐዳሲ ንግግር ያስተዋለ የትኛውም በፕሮቴስታንት ጥላ ውስጥ ያለ ሰው በቀጣይ ሚያስተውለው ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የገቡበትን ችግር ታሪካዊነቱ ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የአምልኮ ስርአት ችግር ነው።[ይህ ችግር በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያን ጨምሮ የሚያካትት ነው።]

ይህን ችግር ግን በታሪካዊው ወይም በክላሲካል ፕሮቴስታንት መነጽር ስናየው የቀድሞው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ባለው በቤተክርስቲያናዊ አስተምህሮ የበለጠገ አምልኮ እንዲሁም ለእነዚህ ቅጥ ላጡ አካላት እጅግ የታመነ የእምነት አቋም እንዳለው ቢታወቅም ልንክድ ማንችለው እውነት ግን ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ውስጥ ሚታየው ስረአት አልባ የአምልኮ ስርአት አግባብ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን እጅግ ስህተት የሆነ ልምምድ መሆኑን ነው።(መታረምና መታየት ያለበት መሆኑን ይህ ጽሑፍ አጥብቆ ይናገራል)

እንዲያው የዚህን ጉዳይ ጉድለት ትኩረት ሰጥተን ብንመለከተው ችግር ሆኖ ምናገኘው የእውነት ጉድለት ሳይሆን፥ ለድህረ ዘመናዊነት እጅግ የተጋለጥን መሆናችን፣ ቃሉን ሳይረዱት "ሃይማኖት አያድንም" የሚሉና የአስተምህሮን አስፈላጊነት የጣሉ ሰባኪያንና መምህራንን በተሃድሶው ክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ ምስባክ ላይ ማቅረባችን፤ ይህንንም ተከትሎ አጥንትን ከመጋጥ ይልቅ ወተት መጋትን የሚወድ፣ በእምነቱ በቆየበት ልክ እውቀትንና ብስለትን ያጣ ምእመን ማፍራታችን ለዚህም የልጆች ፈንጠዝያ ሥርአተ አምልኮ መፍያና ማሟያ እንዲሆኑ ጆሮአችንን ለማከክ የፈቀዱን ሰዎች መሪዎችና እረኞች እንዲሁም መጋቢያን ዝም ማለታቸው ነው።(አጥብቀው የሚቃወሙና አጥብቀው የሚገስጹ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም)

መፍትሔ፦

መፍትሔው ሐዳሲያኑ የቆሙበትንና እኛም የተነሳንበትን እውነት አለመጣል ነው። ምክንያቱም ጌታን ለምን እንደተከተልነው እናውቅ ዘንድ á‹­áŒˆá‰ŁáŠ“áˆáŠ“á˘ ስለዚህ እውነትን በሙላት ልንካፈል እንጂ እምነትን አስታከን ለወደቀው አዳማዊ ማንነታችን ነፃነትን በመስጠት አለማዊነትን ልንለማመድ አይደለም።

መሰረታችና አስተምህሮአችን የሆነው
"የእግዚአብሔር ቃል ብቻ" "የእምነት መግለጫችንም" ብቻ ሳይሆኑ ምስባኮቻችንን፣ ልምምዶቻችንንና አምልኮአችንን የቆምንበት እውነት ሊገልጹ ይገባል። የዚህ ችግር ጉዳት "ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው" እንዲሉ አበው እንደ ምእራባዊያን áˆłá‹­á‰łá‹ˆá‰€áŠ• ቀስ እያልን ለዘብተኞች እንዳንሆን።

ወንድምና እህት ክርስቲያኖች ሁላችን ለምን እንደተጠራን ካወቅን እንግዲህ እንንቃ። ከራሳችን፣ ከቤተክርስቲያን ጣዕመ ዜማ ካለው አምልኮ፣ ከቅዱሳን ስብስብ(ማህበር) አስበልጠን የተሸከምነውን አለማዊነትንና ለአለማዊነት ያዘመመን ለዘብተኛ ክርስትናን ፈፅመን እናስወግድ፥ ማን እንደሆንን እናውቃለንና።

➠ የተሐድሶአችን ጥሪ ወደቀደመው እምነት እንመለስ እንደሆነ ሁሉ፥[2]

➠ እንደ ቀድሞው የአምልኮአችንን ማእከል፥ ቅዱሳት ምስጢራትንና የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታችን እናድርግ።

➠ ሥላሴያዊ የሆኑ መዝሙሮችና ስብከቶች ስርአትና ልምምድ ይሁኑልን፥

➠ እንደ እምነታችን እንዘምር፣ እንስበክ፣ እናስተምር።


ይህ ሁሉ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ሃይል፥ በልጁም በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ክብር ይሆን ዘንድ። ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሳርያ በእንተ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፉ ላይ፦

"...ቤተ ክርስቲያን የጠበቀችው ሐይማኖት በሐዋርያት የተላለፈውን ነው፣ የተቀበልነው እንዳናጠፋ ከአባቶች እምነት ጋር ጸንተን እንኑር !.."


በማለት የተሐድሶ አበው እንዳስቀመጡት ባስልዮስ ያስቅምጠዋል። ታዲያ ቤተክርስቲያን ከዚህች ወጥመድ ታመልጥ ዘንድ የተሐድሶውን ወቅት በማየት መነጽራችንን ወደ ቀደመው አምልኮዎቻን እንመለስ ስንል ይህን ጽሑፍ እንቋጫለን።

በአሚነ ሥላሴ ያጽናን። አሜን!


ማጣቀሻ

[1] The first book of discipline, Volume 3 page 34

[2] ተሐድሶ ማለት አዲስ ክርስትና መመሥረትና መቀጠል አይደለም። ይልቅ ወደ ቀደመው ውብ ክርስትና ቃሉ ብቻ የበላይ ወደ ሆነባት ክርስትና እንመለስ እንጂ።
@AnglicanFaith
❤4🔥3❤‍🔥2
W!🔥

አይ Orthobros....ዩቱዩብ ላይ ያሉ Apologistቶች አንዳንዴ ያስቁኛል ስፔሻሊ "Cleaved By Antiquity" ሚባል ልጅ lol videoው ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በAnglicanism ላይ ደግሞ የመለሳቸው መልሶች!🔥

https://youtu.be/1TLP2qKSpT4?si=ipl6_yoy3_LKtxC1
🔥3
እኛ የነገረ መለኮት ዲፕሎማ ሳንማር ወንድማችን ዳኒ እውነት ለሁሉ PHDኡን ሊጨርስ ነው🥰 እናም የዶክትሬት ትምህርቱን ለመጨረስ የሆነ የገንዘብ እርዳታ አስፈልጎታል። ለዚህ የሁላችንም ትብብር ይፈልጋል።
ምናልባት ዳኒ እውነት ለሁሉን ለማታውቁ ወዳጆች ዳኒ በእቀበተ እምነት አገልግሎት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየና የእውነት ለሁሉ ዌብሳይት መሥራችና አርታዒ ወንድማችን ነው። እስልምናና ሌሎች የኑፋቄ ትምህርቶችን በመመከት የሚታወቅ አመለ ሸጋ ወንድማችን ነው።

በዚህም ሁለት አማራጮችን ተከትላችሁ እርዳታችሁን ለወንድማችን ማድረስ ትችላላችሁ...
ውጪ ላላችሁ ወዳጆቻችን በዚህ የgofundme ገጽ በመግባት የምትችሉትን እንድታደርጉ በፍቅር እንጠይቃችኋለን....
https://gofund.me/e6a849d69
ሃገር ውስጥ ላላችሁ ወዳጆች ደግሞ በዚህ በጓደኛው አካውንት ልትረዱት ትችላላችሁ፤
1000784785207 አማኑኤል እንዳለ
በውስጥ ወንድማችን ዳንኤልን በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማነጋገር ትችላላችሁ @danit4all ተባረኩ....
❤4
ጥንታዊው የሥላሴ ትምህርት፡ ሥልታዊ እና ሜታፊዚካዊ ትንተና

https://youtube.com/watch?v=Y0o2YHLNfLs&si=jwCzpd8O2P1pAqjS
❤8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት (መታሰቢያ) ቀን ይከበራል። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ቀን ብፅዕት እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ መሆኑዋን በማስታወስ ይከበራል ፤ ይህም እግዚአብሔር በድኅነት ታሪክ ውስጥ እንዴት የክብር ማደሪያ አድርጎ እንደተጠቀመባት ለማስታወስ ነው።
በዋናነት ወንጌላት ላይ  በሚገኘው ፣ በተለይም ቅድስት ድንግል ማርያም ትንቢታዊ መዝሙር  (Magnificat) ውስጥ እንዲህ እንደዘመረችው ፦
⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
የሉቃስ ወንጌል 1:47-48

በተጨማሪም የጸሎት መጽሐፍ (Book of Common Prayer) በነሐሴ 9 / Aug 15 (እንደ አንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ቀን መቁጠሪያ) ቅድስት ማርያምን እንደ ታዛዥነት መልካም ምሳሌ አድርጎ ያቀርባል።
-----
የቀኑ ጸሎት

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥
የልጅህ እናት የሆነችውን ብፅህት ድንግል ማርያምን ፣
ወደ አንተ ወስደሃልና፤
በደሙ የተቤዥን እኛ ከእርሷ ጋር የዘላለም መንግሥትህን ክብር መካፈል ይሁንልን ፤
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣
ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ሆኖ የሚኖርና የሚነግሥ፣
አንድ አምላክ፣አሁንም ለዘላለምም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን
አሜን።

@anglicanfaith
@classical_Protestant #Anglican #mary #theotokos
❤‍🔥10😁1
Forwarded from Anglican faith (David Yeshua✠ )
Φῶς ἱλαρὸν/"ኦ ደስ የምታሰኝ ብርሃን"/[1]

ሰሞኑን የአንግሊካን የጸሎት መጽሐፍ ጥናት ላይ ነበርኩኝ። ከዛም BCBን በማነብበት ጊዜ አንድ እጅግ ጥንታዊ ዝማሬ "ኦ አቤቱ ደስ የምታሰኝ ብርሃን" በጽርኡ አገባብ Φῶς ἱλαρὸν/ፎስ ሂላሮን(“O Gladsome Light”) ይሉታል። በአንግሊካን ቤተክርስቲያን የቅዳሴና የጸሎት ሥርዓት ጊዜ በተለይም በታዋቂው Book of Common Prayer (BCP) ውስጥ "O Gladsome Light" የሚለው መዝሙር «Evening Prayer» ወይም «Evensong» በመባል በሚታወቀው የምሽት የቅዳሴ/የጸሎት ሥርዓት ላይ ይህ መዝሙር ልዩ ቦታ አለው። ፀሐይ ጠልቃ ጨለማ ሲተካ እና በመቅደሱ ውስጥ መብራቶች (ሻማዎች) ሲበሩ የሚዘመር «የምሽት ብርሃን ምስጋና» ነው። ይህ ሥርዓት የሻማው/የመብራቱ መበራት የሚያመለክተው የክርስቶስን ትንሣኤና ዘለዓለማዊ ብርሃን መሆኑን ነው። ይህም አካላዊው የፀሐይ ብርሃን ሲጠፋ፣ «ፈጣሪና ዘለዓለማዊ ብርሃን የሆነው ክርስቶስ በሕይወታችን አልጠፋም» የሚለውን እውነት ለማወጅ ጥቅም ላይ ስለሚውል ነው። መዝሙሩ የተጻፈው በ3ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ(ለምሳሌ በቅዱስ ባስልዮስ) በሰፊው ይታወቅ ነበር።

መጀመሪያ ሳነበው ምንም አልመሰለኝም ነበር። ነገር ግን ይህ ጥንታዊ መዝሙር መንፈሳዊ ትርጉሙ እጅጉን ጥልቅ ነው ከላይ እንዳልኳችኹ የምሽቷ ፀሐይ ስትጠልቅ የዓለም ብርሃን የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይታወሳል። ቁሳዊው ብርሃን ሲጠፋ፣ የማይጠፋው መለኮታዊ ብርሃን ክርስቶስ በምእመናን ልብ ውስጥ እንዲበራ የሚደረግ ምስጋና ነው። ቀጠል አድርገውም አብን፣ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን አንድ አምላክን በማመስገን ክርስቶስን «ደስ የሚያሰኝ/የደስታ ብርሃን» ብሎ ይጠራዋል።

አስባችሁታል በ3ተኛው ክፍለ ዘመን አባቶች በጨለማ ውስጥ ሆነው ጧፏቸውን ይዘው እንዴት እንደሚዘምሩት? እስኪ በስፋት መጣበታለሁ።.....
-----
1] በአማርኛ የመዝሙሩን ትርጓሜ በደንብ አጠናክሬ ሙሉ ግጥሙን ከእነ ዝማሬው ለቅላችኋለሁ
@anglicanfaith
❤‍🔥9
ቄስ ኮሊን ማንሰል- Rev Colin Mansell (1933-2005 እ.ኤ.አ)

ቄስ ማንሰል እንደ ኢትዮጵያ አቈጣጠር በ1926 ዓ.ም. በእንግሊዝ አገር የቤተሰባቸው አምስተኛ ልጅ ሆነው ተወለዱ። የዐሥራ አራት ዓመት ልጅ ሳሉ፥ ክርስቶስ በኀጢአታቸው ምክንያት በመስቀል ላይ እንደሞተ ተረድተው መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ የማንበብ ባህልን ተለማመዱ። በዐሥራ ስድስት ዓመታቸው ሚሲዮናዊ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ጠራቸው። በትምህርት ቤት ሳሉ ለኢትዮጵያና ለቤተ ክርስቲያኗ መጸለይ ጀመሩ። በእንግሊዝ መንግሥት ሕግ መሠረት የሁለት ዓመት ብሔራዊ አገልግሎት ግዳጅ ስለነበረ፥ ከነበሩበት ትምህርት ቤት ወጥተው ይህንኑ አገልግሎት ለመፈጸም በምክትል መቶ አለቅነት ማዕረግ ወደ ግብጽ ሂደው በመሐንዲስ ክፍል አንድ ዓመት ሠርተዋል። ከዚያም በኋላ በካምብርጅ ዩኒቨርሲቲ ገብተው የሦስት ዓመት የምሕንድስና ትምህርት ተከታትለው በዲግሪ ተመርቀዋል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ በመመራት ከዚህ ሙያ ወጥተው መንፈሳዊ ኮሌጅ በመግባት የሁለት ዓመት ትምህርት ከተከታተሉ በኋላ በተጠመቁባትና ባደጉባት በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ በ1950 የዲቁና፥ በ1951 ደግሞ የቅስና ማዕረግ ተቀብለው በቤተ ክርስቲያን እያገለገሉ ለተጠሩበት ተልእኮ ራሳቸውን ሲያዘጋጁ ቆዩ።

በ1953 ዓ.ም. በሠራዊተ ክርስቶስ ማኅበር ወደ ኢትዮጵያ በሚስዮናዊነት ተልከው በተለይ በጎንደር የአማርኛ ቋንቋ ማጥናት ጀመሩ። በቋንቋው ጥናት መጠነኛ ዕውቀት ካገኙ በኋላ ከሁለት ኢትዮጵያውያን ጋር በብዙ ጠቅላይ ግዛቶች በመዘዋወር፥ በተለይ በጎጃምና በጎንደር የመጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች መንፈሳውያን መጻሕፍትን ሽያጭ ማከናወን ጀመሩ። ከዚህም ሥራ ጋር በልዩ ልዩ ስፍራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኮርሶችን አስተምረዋል።

የሠራዊተ ክርስቶስ ኀላፊ ሚስተር እስቶክስ ጡረታ ሲወጡ፥ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ት/ቤት ከ6ኛ-11ኛ ክፍል፥ በሰንበት ት/ቤት መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማርና ልዩ ልዩ የካህናት ኮርሶችን በመስጠት ከ1963-1967 ዓ.ም. ድረስ ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል።

የሠራዊተ ክርስቶስ ማኅበር በጊዜው በነበረው መንግሥት ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ሲደረግ፥ ቄስ ማንሰል ወደ እንግሊዝ አገር ተመልሰው በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ረዳት ቄስ ሆነው ማገልገል ጀመሩ፤ እያገለገሉ ሳለም ከኢትዮጵያውያንና ከሌሎች እንግሊዛውያን ሊቃውንት ጋር በመተባበር የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትን በአማርኛ አዘጋጁ። በ1969 ዓ.ም. እንደገና ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በመጀመሪያ ከቸርች ሚሲዮን ቱ ጁውዝ ኀላፊ ከቄስ ሮጀር ካውሊ ጋር በጎንደር በተለይ በቤተ እስራኤል መካከል፥ በኋላም በብፁዕ አቡነ እንድርያስ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አመራር ሥር ለመነኰሳት፥ ለካህናትና ለዲያቆናት ልዩ ልዩ ኮርሶችን በመስጠት አሠልጥነዋል።

በደርግ መንግሥት ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ለጊዜው ከአገረ ስብከታቸው ሲነሡ፥ ቄስ ማንሰል የሥራ ፈቃድ ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ እንግሊዝ አገር ተመልሰው በመሄድ ባደጉባት ቤተ ክርስቲያን በረዳት ቄስነት እንደገና ማገልገል ጀመሩ። እዚያም እያገለገሉ ሳሉ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ በሚሲዮናዊነት ያገለግሉ የነበሩትን ሚስ ሄዘልን አገቡ። ከዚያም በኋላ በሠራዊተ ክርስቶስ ማኅበር ወደ ፖርቱጋል ከባለቤታቸው ጋር ተልከው ከአንግሊካን ቤተ ክርስቲያንና ከልዩ ልዩ መንፈሳዊ ድርጅቶች ጋር ሆነው አገልግለዋል።

የወንጌል በር ሲከፈትና ሁኔታዎች ሲመቻቹ ቄስ ማንሰልና ውድ ባለቤታቸው በ1983 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መጡ። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ዋና ሥራቸው መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዱ ልዩ ልዩ መጻሕፍትን ማዘጋጀት ሆነ። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ያሳተማቸው «በየዕለቱ ከእግዚእብሔርጋር» የተሰኙት የአራት ዓመት ምንባብ ፕሮግራም መግቢያና የየዓመቱ መጻሕፍት ከፍተኛውን ስፍራ የሚይዙ ናቸው። ቀደም ሲል ታትሞ የነበረውን የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ለማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፥ ቄስ ማንሰል የአዘጋጁ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኑ። በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ከባለቤታቸው ከሚስስ ሄዘል ጋር ልዩ ልዩ አዕማድ መጻሕፍትን ጽፈዋል። ቄስ ማንሰል እነዚህን ተግባራት ሁሉ ሲያከናውኑ ልዩ ልዩ መምህራንን ያማክራሉ፤ ከሊቃውንትም ጋር አብረው ይሠራሉ። ዓላማውም እግዚአብሔር እንዲከብርና የኢትዮጵያ ሕዝብ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት አምላኩን በይበልጥ እንዲያውቅ ነው።

በኢትዮጵያ ለሰጡት አገልግሎትና ላበረከቱት አስተዋፅኦ ሁሉ የካንተርበሪው ሊቀ ጳጳሳት ዶክተር ጆርጅ ኬሪ የቅዱስ አውግስጢኖስን መስቀል ለእርሳቸውና ለባለቤታቸው ሸልመዋቸዋል።

ከዛም ጊዜ በኋላ ቄስ ማንሰል በጡረታ ወጡ፥ በአንድ በኩል መጻሕፍትን እየጻፉ፥ በሌላ በኩል የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን አባል እንደመሆናቸው አዲስ አበባ በምትገኘው በቅዱስ ማቴዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተገለገሉና እያገለገሉ ህይወታቸውን ቀጠሉ። ኮሊን ማንሰል በትምህርተ እግዚአብሔር ሥነ መለኮታዊ መጽሐፋቸው የሚታወቁ የ አንግሊካን ቄስ ናቸው። ሥነ መለኮት ትምህርታቸውን በTyndale Hall ስነ መለኮት ትምህርት ቤት ከJI Paker ስር በመሆን ተምረው በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን በቅስና በሚሽነሪ አገልግሎትን ያገለገሉ ነበር። የኢትዮጵያ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤቶችን በአዲስ አበባና ፊቼ ሰላሌ ለማቋቋም ከDavid E. Stokes አገልግለዋል።(David E. Stokes ለብዙ የመካነ ኢየሱስ ቀደምት አገልጋዮች መካሪና አባት የነበሩ የአንግሊካን ሚሽነሪ ናቸው)

የቄስ ኮሊን ማንሰል መጽሐፎች

-የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት
-የመፅሐፍ ቅዱስ ማጥኛ
-በእየለቱ ከእግዚአብሔር ጋር(የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ለ4 አመት)
-እግዚአብሔር ወልድ
-ከባቢሎን ምርኮ መልስ
-የእግዚአብሔር ፀጋ አሰራር
-አስደናቂው ልውውጥ
-ትምህርተ እግዚአብሔር 2003 እ.ኤ.አ
-ትምህርተ ክርስቶስ 2006 እ.ኤ.አ
-ትምህርተ መንፈስ ቅዱስ

በአዕማደ መፅሐፍት ላይ (በእርማት የተሳተፉበት)

- ብሉይኪዳን
- አዲስ ኪዳን
- የክርስትና ትምህርተ
- የክርስትና ኑሮ አዕማድ

ስንቱ ተወርቶ? ድንቅ የአንግሊካን ቄስ ነበሩ። እኔም በጣም የምወዳቸውን መጽሐፍ ህይወቴን ካስተካከሉት ብዬ ከላይ Anglican Faith ቻናል ላይ አስቀምጬላችኋለሁ።
@AnglicanFaith
@Classical_Protestant
❤6
Audio
እስኪ ከእሁድ ዝማሬ መካከል ልጋብዛችኹ......

"....ሃሌሉያ/Hallelujah/,
praise the One
who set me free..."
@AnglicanFaith
@Classical_Protestant
❤4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
St Matthew Anglican Church
@AnglicanFaith
@Classical_Protestant
❤7❤‍🔥2👍1
Job 38:36 (ESV)
³⁜ Who has put wisdom in the inward parts or given understanding to the mind?

Verse of the Day
❤3
Forwarded from Classical Protestant (Ermias ✠)
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማታ ጸሎት

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
የመንግሥትህን ጣፋጭነት ከኔ አታርቅብኝ፤
ከዘላለም እሳትም አድነኝ፤
አቤቱ በአእምሮዬ በሀሳቤ በአንደበቴ ስበድል ይቅር በለኝ፤
ከዝንጉነት ከልቤ ድንዛዜ
ከቸልተኝነት ልቦናዬን ከመደንደን ጠብቀኝ፤
ጌታዬ ሆይ ወደ ፈተና አታግባኝ፤
ኃጢአት ባጨለመው ልቤ ላይ እውነተኛ ብርሃንን አብራልኝ፤
አቤቱ ሰው ነኝና በድያለሁ
አንተ ግን ምሕረትህ የበዛ ለቁጣ የዘገህ ጻድቅና ቸር ነህና
የነፍሴን ድካም ተመልክተህ አድነኝ፤
ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ ማድረግ እንድችል
ምህረትህን አብዛልኝ ፤
ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ!
ስሜን በሕይወት መጽሐፍ ጻፍ
መጨረሻዬንም አሳምርልኝ፤
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ!
እስከ ዛሬ ድረስ በፊትህ የሚቆጠር በጎ ሥራ የለኝም፤
ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ በጸጋህ መልካምን ማድረግ ልጀምር ፤
በቸርነትህ ጠል ልቦናዬን አንጻ፤
የሰማይና የምድር ንጉሥ ሆይ!
ኃጥያተኛውንና አሳፋሪ ርኩሱን ባሪያህን
መንግሥትህን በምትመጣበት ቀን አስበኝ፤
አሜን

#lent  #AbiyTsom #GreatLent #Anglican #bcp #Lutheran
@classical_Protestant
❤5
Forwarded from Classical Protestant (Ermias ✠)
The Invocation
The Invocation
The Invocations


O God the Father of heaven: have mercy upon us miserable sinners.
O God the Son, Redeemer of the world: have mercy upon us miserable sinners.
O God the Holy Ghost, proceeding from the Father and the Son: have mercy upon us miserable sinners.
O holy, blessed, and glorious Trinity, three Persons and one God: have mercy upon us miserable sinners.

#BCP #Litany #Anglican
@classical_Protestant
❤7
Lord's Prayer
Lord's Prayer
Our Father
which art in heaven
hallowed be thy name
Thy kingdom come
thy will be done
in earth as it is in heaven
Give us this day our daily bread
and forgive us our trespasses
as we forgive them that trespass against us,
and lead us not into temptation,
but deliver us from evil.
Amen.

#BCP #Litany #Anglican #lord #prayer
@classical_Protestant
@AnglicanFaith
❤4