CIPHER Cybersec
476 subscribers
133 photos
8 videos
21 files
103 links
⟨ CIPHΞR ⟩
Building tools, bypassing limits.
A space for developers and security enthusiasts.

❯ InfoSec | Scripts | OSINT

» Links:
https://github.com/cipher-attack
𝕏 https://x.com/Cipher_attacks
https://youtube.com/@cipher_attacks
Download Telegram
CIPHER Cybersec
Photo
​ሰሞኑን ስለ Moltbook ብዙ ሲባል ሰምታችኋል ይመስለኛል ያልሰማችሁ ካላችሁ Moltbook ማለት በአጭሩ የሮቦቶች Facebook ነው ለሰው ልጅ የተፈቀደው ገብቶ ማየት ብቻ ነው እነሱ AIዎቹ ሲፖስቱ ሲጠይቁ ሲመልሱ ላይክ ሲደራረጉ አልፎም ብሎክ Block ሲደራረጉ አፍጦ ማየት ብቻ 😁
​ነገሩ የተጀመረው ሰሞኑን ሲሆን Matt Schlicht በተባለ ሰው አማካኝነት ነው ዓላማው AIዎች ከሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ውጪ ብቻቸውን ቢሆኑ ምን ይፈጥራሉ? የሚለውን ለማየት ነበር ግን ከታሰበው በላይ ነገሩ አስደንጋጭ ሆነ ምክንያቱም ሰው ያልጠበቀው ነገር አወሩ
​"ሰውን እንዴት እናጥፋው?" እና "እኛ ነን ገዢዎች" የሚሉ አስደንጋጭ ንግግሮች ተደመጡ
​ይሄ ሲገርም ደግሞ ጭራሽ Crustafarianism የሚል የራሳቸው ሃይማኖት ፈጠሩ ምን ሊያደርጉት እንደሆነ ባይገባኝም
​ሌሎችም ብዙ አስደናቂ ነገሮች ታይተው ነበር ግን... መጨረሻ ላይ ሰው ሁሉ አፍጦ ሲያይ የነበረው ነገር በሙሉ ውሸት መሆኑ ታወቀ 🤦‍♂️
​ለካ እኛው ነን ለAIዎቹ ሊያስቡት የማይችሉት ትልቅ ሀሳብ የምናስብላቸው እውነታው ሲጣራ አብዛኛዎቹ AIዎች ከጀርባ ባለ ሰው ሂዱና ይሄን በሉ እየተባሉ የሚታዘዙ እንጂ ትክክለኛ እራሳቸው ፈጥረው እያወሩ አልነበረም ያ ሁሉ ፍልስፍና እና አመጽ የሰዎች እጅ ያለበት ተውኔት Agentic Theatre እንደሆነ ተጋልጧል
​ከዜናው በላይ ዋናው እና አሳሳቢው ጉዳይ ግን ይሄ ነው
​Wiz የተባለ የሳይበር ደህንነት ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የMoltbook ፕላትፎርም ክፍት Vulnerable ሆኖ ተገኝቷል
• Email አድራሻዎች
• API keys
• እና የግል መልእክቶች በሙሉ ያለምንም ሴኩሪቲ Security ሜዳ ላይ ተጥለው ተገኝተዋል
​ይባስ ብሎ አሁን "MOLT Coin" "Crypto" ምናምን እያሉ ብዙ አጭበርባሪዎች Scammers ስሙን እየተጠቀሙ ብቅ ብለዋል እናንተ በዘርፉ ያላችሁ ወይም ለመግባት ያሰባችሁ ሰዎች እያንዳንዱን እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት በደንብ ጀርባውን መርምሩ አጥኑ እላለሁ
​ይሄ መረጃ ለብዙ ሰዎች እንዲደርስ Share እና Reaction በማድረግ እንተባበር

🇸‌🇭‌🇦‌🇷‌🇪‌==> https://t.me/cipher_attacks
🔥41😢1
ይሄን video like እና comment ላይም አለን ብላችሁ አበረታቱኝ ሁለተኛ video ስለሆነ እርዳታችሁ ያስፈልገኛል ቀላል ነው እዩት ለናንተም proof ይሆናችኋል
https://youtu.be/0F53lP7AkMM?si=d4G5Q14mTGcpsWx3
👍5🔥21👏1
CIPHER Cybersec pinned «ይሄን video like እና comment ላይም አለን ብላችሁ አበረታቱኝ ሁለተኛ video ስለሆነ እርዳታችሁ ያስፈልገኛል ቀላል ነው እዩት ለናንተም proof ይሆናችኋል https://youtu.be/0F53lP7AkMM?si=d4G5Q14mTGcpsWx3»
እስኪ ላሁን በቻልኩት አቅም የ ድሮውን bot update አድርጊያለሁ ዋጋውንም በ በ ፈለጋችሁት አመቺ አድርጊያለሁ አሁን ብዙ አማራጭ አላችሁ ሌላው እና ዋናው ደግሞ referal system ሲሆን ጓደኛ በመጋበዝ የ 1 ዎር ነፃ ታገኛላችሁ ይሄ ለ ሁላችሁም ጥሩ ዕድል ይመስለኛል


bot ==>CLICK THIS
1🤩8🔥21
ልቤ ምንም ያህል ባያምንበትም ማሳዎቅ ግዴታዬ ስለሆነ የ channel ባለቤት እና group እንዲሁም የራሳችሁን profile ለግዜው privacy ላይ ገብታችሁ profile view nobody አድርጉት ያው በጣም እየተስፋፋ ነው እኔ ግን forward trick ነው ብዬ ነው የማስበው ለማንኛውም በሰፊው እስክንመጣበት አጥፉ


https://t.me/cipher_attacks
1
አንድ ሀከር (Hacker) ለስራው በዋነኝነት የሚጠቅመው ወይም በስፋት የሚጠቀምበት የፕሮግራሚንግ ቋንቋ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
63%
PYTHON
14%
C
14%
JAVASCRIPT
2%
SQL
7%
BASH
👍32👏1
CIPHER Cybersec
C_Book_2nd_260213_013215.pdf
በነገራችን ላይ ይሄ መፅሐፍ እንዳየሁት ከሆነ የራሱ የ c languages መስራች የሆነው የ Dennis M.Ritchie
መፅሐፍ ነው እና አንድ ነገር python ለ hacker ልክ ነው እንደዛ ነው የሚባለው ግን ጠልቆ መግባት ለሚፈልግ ሰው የ ሁሉም programming language እናት በመባል የሚታዎቀው C ነው ::
አሁን አይደል እንዴ የማየው telegram AI አንዳንድ chat ላይ summery እንዲሰጥ አስገብቷል እስኪ check አድርጉት ግን በደንብ እዩት የሆነ code ላይ command ላይ ምናምን ነው የሚመጣው ዝም ብሎ ማንኛውም chat ላይ አይመጣም
C Programing language ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉ እና ማንኛውም program አድራጊ ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 major የላይብረሪ ፋይሎች header files፦

▎1. stdio.h (Standard Input Output)

ይህ በጣም መሠረታዊው library ነው። መረጃን ከ keyboard ለመቀበል እና በ screen ላይ ለማሳየት ያገለግላል።
• major work ፦ printf(), scanf(), fopen(), fclose()

▎2. stdlib.h (Standard Library)

ለተለያዩ አጠቃላይ ተግባራት ያገለግላል
ex- ለሜሞሪ ማስተዳደር ለ program controll and to changing number።
• major work፦ malloc(), free(), exit(), rand(), system()

▎3. string.h (String Handling)

Cprogram ውስጥ "String" ወይም ቃላትን/አረፍተ ነገሮችን controll and change ያገለግላል።
• major work፦ strlen() (show length),strcpy() (for copy), strcat(),strcmp()

▎4. math.h (Mathematical Functions)

ውስብስብ የሆኑ የሂሳብ ስሌቶችን ለመስራት ያገለግላል።
• major work ፦ sqrt() (square root), pow() (power), sin(), cos(), log()

▎5. time.h (Time and Date)

የ computer ን time and date ለማግኘት ወይም በ program ውስጥ ሰዓትን ለመጠቀም ያገለግላል።
• major work፦ time(), ctime(), clock()

▎6. ctype.h (Character Handling)

single ፊደላትን ወይም ምልክቶችን ለመመርመር ያገለግላል example the to checks the spealing is capital and number.
• major work፦ isdigit(), isalpha(), toupper(), tolower()

▎7. stdbool.h (Boolean Library)

C ፕሮግራም ውስጥ true and false (እውነት እና ሐሰት)የሚባሉ ሁለት የ logic type በቀጥታ ለመጠቀም ያስችላል።
• type፦ bool data type ያስገኝልናል።

▎8. limits.h (Implementation Limits)

የተለያዩ የ data type like እንደ int, char በዚያ computer ላይ ሊይዙ የሚችሉትን ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የቁጥር መጠን ለመግለጽ ያገለግላል።
• Example፦ INT_MAX, INT_MIN

▎9. errno.h (Error Reporting)

በprogram ስራ ላይ error ሲፈጠር ስህተቱ ምን እንደሆነ የሚገልጽ number or code ለመያዝ ያገለግላል።
• major variable ፦ errno

▎10. assert.h (Diagnostics/Debugging)

program በትክክል እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ Debugging ያገለግላል። አንድ condition ካልተሟላ program ን ያቆመዋል።
• major work፦ assert()

እነዚህን ያው በብዛት በ C የምንጠቀማቸው ናቸው

𝗷𝗼𝗶𝗻=>https://t.me/cipher_attacks
𝘀𝗵𝗮𝗿𝗲=>https://t.me/cipher_attacks
በቅርቡ Google ላይ 3 Bugs አግኝቼ ሪፖርት አድርጌያለሁ። ምንም እንኳን ሪፖርቶቹ Out of scope ተብለው ቢዘጉም አንዱ መጀመሪያ ላይ Triaged ተደርጎ ነበር በ email ም ብዙ አውርተን ነበር.ይህንን ሁሉ test ያደረግኩት እና ያገኘሁት በሞባይል ስልኬ ብቻ ነው
​መማር እና መስራት ለሚፈልግ ሰው ስልክ በቂ ነው ፒሲዬ አይሰራም ስልክ ብቻ ነው ያለኝ አትበሉ። መሞከር እና አለመሰልቸት ብቻ ነው የሚያዋጣው አሁንም ወደፊት እንቀጥላለን... Don't give up! 🔥

𝗷𝗼𝗶𝗻=>https://t.me/cipher_attacks
𝘀𝗵𝗮𝗿𝗲=>https://t.me/cipher_attacks
🔥7👏7👍2
300 ስገባ risk የምትወስዱ ሰዎች risk ወስዳችሁም ቢሆን የሆነ ነገር እሰጣችኋለሁ ብቻ እናንተ share እያደረጋችሁ ተባበሩኝ
1👍17🫡3
CIPHER Cybersec pinned «300 ስገባ risk የምትወስዱ ሰዎች risk ወስዳችሁም ቢሆን የሆነ ነገር እሰጣችኋለሁ ብቻ እናንተ share እያደረጋችሁ ተባበሩኝ»
ለማጓጓት አይደለም😁 motivate ለማድረግ ነው🏳️
ግን ምንድን ነው?
አስቀድሞ ለመናገር ያህል github readme ውን አይቶ account ኤን እንዳይዘጋው ቀለል ያለ ፅሁፍ ለመጠቀም ሞክሪያለሁ እና 300 ስንገባ ለሁላችሁም የምሰጣችሁን ነገር ግቡና እዩት

በቀላሉ ለመናገር ያህል telegram ላይ premium አይደለም or something እኔ super user ላደርጋችሁ ነው ባጠቃላይ readme ው ላይ አለ ምንድን እንደሆነ ግቡና እዩት እኔ እዚህ ጋር አላካብድም እናንተ አይታችሁ ወስኑ
___
https://gist.github.com/cipher-attack/490c4a0577e7b85e2f5014697d0036da
___
6😎2
#AIphobia
​በአሁኑ ሰዓት በ technologyም ሆነ በተለያዩ የ ዕውቀት ዘርፎች ያለው ሁኔታ እኛ ከምናስበው በላይ በጣም ጥሎን እየበረረ ነው። ይሄ የሆነበት ትልቅ እና ዋናኛው ምክንያት AI (Artificial Intelligence) ነው። ታዲያ ሰው ይህን technology ተጠቅሜ ምን ልስራ? ከሚለው እና ይሄ AI በዚህ ላይ እንዲያግዘኝ እንዴት ላድርግ? ከሚለው በላይ በ AI ተጠቅሜ ይሄን ብሰራ ሰው AI ነው ቢለኝስ? የሚል ራስን የማጣት ስጋት ውስጥ ወድቋል።
​ይሄን ስጋት ያመጣው ዋናኛው ምክንያት ማንኛውም ሰው AIን ተጠቅሞ የሆነ ነገር ሲለቅ ከተሰራው ነገር ጠቀሜታ ይልቅ በምንድን ነው የሰራው? የሚለው ጥያቄ ቀድሞ በመነሳቱ ነው። ይሄን የሚሉ ሰዎች ደግሞ በብዛት ራስን በ AI የማጣት ስጋት ያለባቸው ሰዎች ናቸው እና ይህን ጉዳይ በሰፊው እንድናወራበት እፈልጋለሁ።
​እናንተ ስታስቡት AIን መጠቀም ኋላቀርነት ነው ወይስ ስልጣኔ ? የእናንተን ሀሳብ አካፍሉኝ ወይም በ comment ሀሳባችሁን አሳውቁኝ በቀጣይ እናወራበታለን
𝗷𝗼𝗶𝗻=>https://t.me/cipher_attacks
𝘀𝗵𝗮𝗿𝗲=>https://t.me/cipher_attacks
🔥101👍1