Christ-centered
1.62K subscribers
18 photos
7 videos
13 files
3 links
​ጤናማ አስተምህሮ ለበሰለ ህይወት መሰረት ነው።
​እውነት ለአእምሮ፣ ጸጋም ለልብ ብርሃን ነው።
Download Telegram
በእኛ ወንጌል አማኞች ማህበረሰብ ውስጥ ለአማኙ መንፈሳዊ እድገት፣ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ለወንጌል ምስክርነት ሲባል ሊታረሙና ሊስተካከሉ የሚገባቸው ብዬ የማስባቸው ሀሳቦችና ድርጊቶች፦

1. ​የብልጽግና ወንጌል አመለካከት እምነትንና መንፈሳዊነትን ቁሳዊ ሀብት፣ ገንዘብና የዚህ ዓለም ስኬት ማግኛ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ። ክርስቲያናዊ ሕይወት በመስቀሉ መንገድ፣ በትግስቱና በመከራውም ውስጥ ክርስቶስን መከተል እንደሆነ አስተምህሮውን ማመጣጠን ያስፈልጋል።
2. ​መጽሐፍ ቅዱስን ከተቆራረጡ ጥቅሶች ብቻ መረዳት (Proof-Texting)፦ ጥቅሶችን ከቀደም ተከተላቸውና ከተጻፉበት ታሪካዊ/መንፈሳዊ context ውጭ በመውሰድ ለግል ፍላጎት ወይም ለስሜት ማስማማት። መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀትና በስርዓት የማንበብ ባህል ሊጎለብት ይገባል።
3.​አገልጋዮችን ከተገቢው በላይ ማላቀቅ (Hero Worship)፦ ሰዎችን ወይም አገልጋዮችን እንደ እግዚአብሔር ምትክ አድርጎ የመመልከትና የማምለክ ያህል የማክበር አዝማሚያ። ትኩረቱና ክብሩ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ብቻ መመለስ አለበት።
4.​ትንቢትንና ተአምራትን ያለመመርመር የሚነገሩ ትንቢቶችንና ተአምራትን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር ሳያመዛዝኑ በየዋህነት መቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ” እንደሚል የመንፈስን አመጣጥ የመመርመር ልምድ ያስፈልጋል።
5.​የጸሎትና የአምልኮ አቀራረብ ጸሎትና አምልኮ መንፈሳዊና ግላዊ ግንኙነት እንደመሆኑ መጠን፣ ሌሎች ሰዎችን በሚረብሽ ወይም ከልክ ባለፈ ጫጫታና ግርግር የሚደረጉ ድርጊቶችን መቀነስ።
6.​የፋይናንስ ግልጽነት ማነስ በቤተክርስቲያናትና በአገልግሎት ድርጅቶች ውስጥ የሚሰበሰቡ አስራት፣ በኩራትና ስጦታዎች አጠቃቀም ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ማነስ።
7.​ለማህበራዊና ለሀገራዊ ጉዳዮች ትኩረት አለመስጠት መንፈሳዊነትን ከዕለት ተዕለት ማህበራዊ ሕይወት፣ ከስራ ባህል፣ ከታማኝነትና ከሀገር እድገት ነጥሎ ማየት። አማኞች በሙያቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን መሆን አለባቸው።
8.​ሌሎችን የመፍረድና የመንቀፍ አመለካከት ከእኛ እምነት ወይም አሰራር ውጭ ያሉትን ማህበረሰቦች ወይም የሌሎች እምነት ተከታዮችን በፍቅርና በክብር ከመቅረብ ይልቅ የመኮነንና የማግለል አቀራረብ።
9.​የይስሙላ መንፈሳዊነት በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም መንፈሳዊ መስሎ መታየት፣ ነገር ግን በቤት፣ በስራ ቦታና በግል ህይወት የክርስቶስን አምሳል አለማሳየት።
10. ​የህብረትና የአንድነት መሸርሸር በትንሽ ልዩነቶችና በጥቅም ምክንያት የመለያየትና አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን የመክፈት አዝማሚያ። የመንፈስን አንድነት በሰላም ማሰሪያ ለመጠበቅ መጋደል ይገባል።

ሌሎችን እያያን እንጨምራለን 🙌
@christcentered7
💯15🤝43❤‍🔥21🙏1
​ዛሬ በደካማ ሥጋ ውስጥ ሆነን፣ በኃጢአት ደመናና በሰይጣን ፈተና መካከል ስንጓዝ የጌታ ፍቅር ትንሽ ጠብታ እንኳ በልባችን ሲያርፍ ዓለምን የሚያስረሳ ከሆነ፣ ነገ በትንሣኤ ቀን በክብር ስንነሳ የሚጠብቀን ደስታ ምን ያህል ግዙፍ ይሆን?

በዚያን ቀን፡
➙​የሚከብድ ሥጋ፣ የሚያታልል ሕሊና ወይም የሚስብ ኃጢአት አይኖርም።
➙​ዛሬ በእምነትና በምሳሌ የምናየውን፣ በዚያን ቀን ፊት ለፊት እያየነው በፍቅሩ ባህር እንዋኛለን።

​ስለዚህ፤ ዓለምና ምኞቷ አላፊ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ለዘላለም ይኖራል። እግዚአብሔር በጸጋው ልባችንን ለዚህ የክርስቶስ ፍቅር ሲከፍተው፣ የሞት ጥላ ሳይጋርደን የዘላለም ሕይወትን መዓዛና ዘላለማዊውን ሰላም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከወዲሁ መለማመድ እንጀምራለን።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:12 (NASV)
¹² ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።
❤‍🔥236🔥2
"እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።"
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1 (NASV)
19🔥5
እውነተኛ አገልጋይ በራሱ ችሎታ፣ እውቀት ወይም ጥረት አይመካም። በህይወቱ ላከናወነው መልካም ነገር ሁሉ ምስጋናውን ለሰጠው ጸጋ ያቀርባል። በገዛ ጉልበቱ አልፎ የተሻገረ መስሎት አይታበይም፤ ይልቁንም "ዛሬ ባለሁበት ማንነቴ በእግዚአብሔር ጸጋ እኔ ነኝ" ብሎ በትህትና ይንበረከካል። ይህ ትህትና እና የጸጋ ጥገኝነት ህይወቱንና አገልግሎቱን የሚያንፀባርቅ እውነተኛ ውበት ይሰጠዋል።
❤‍🔥294🔥4🥰4
“ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።” — ሮሜ 4: 8

​በዚህ ዓለም ላይ ትልቁ ደስታና ዕረፍት ምንድን ነው? ብዙዎች ሀብት፣ ሥልጣን ወይም ዝና ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ቅዱሱ መጽሐፍ እውነተኛውን ብፅዕና (ደስታ) የሚያያይዘው ከውስጥ ማንነታችንና ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ግንኙነት ጋር ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በመዝሙረኛው ዳዊት ቃል ተደግፎ እንደነገረን፣ እውነተኛ ብፁዕ ሰው ማለት "ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው" ነው።

የማይቆጠር ኃጢአት ማለት ምን ማለት ነው?
በሒሳብ ስሌት ወይም በሕግ መዝገብ ውስጥ እዳ እንደሚመዘገብ ሁሉ፣ ኃጢአትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ትልቅ እዳ ነው። ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ በተከፈለልን ዋጋ ምክንያት፣ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ እዳቸው ተደምስሷል። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን "አይቆጥርብንም" ሲባል፣ ኃጢአት አልሰራንም ማለት ሳይሆን፣ የኃጢአታችን ፍርድና ቅጣት በክርስቶስ ላይ ተጭኗል (ኃጢአታችን ለክርስቶስ ተቆጠረ) እና​ የክርስቶስ ፍጹም ጽድቅ ደግሞ ወደ እኛ መዝገብ ተዛውሯል/ተቆጥሮልናል (2ኛ ቆሮንቶስ 5:21) ማለት ነው።

ይህ ብፅዕና በሰው መልካም ሥራ፣ በሥጋዊ ጥረት ወይም በራሳችን ጽድቅ የሚገኝ አይደለም። ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። እኛ ልንከፍለው ያልቻልነውን የኃጢአት እዳ ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ስለከፈለው፣ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሰውን ልብ ስያነቃቃ፤ በጸጋው ጥሪ በእምነትና ንስሐ ወደ እርሱ የሚመጡ ሁሉ የዚህ ነጻነትና ብፅዕና ተካፋዮች ይሆናሉ።

የኃጢአት በደለኝነት ስሜትና የፍርሃት ሕይወት የሰውን ውስጣዊ ሰላም ያጠፋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ኃጢአታችንን እንደማይቆጥርብን ስንረዳ፦
➙​ከበደለኝነትና ከኩነኔ ስሜት ነጻ እንወጣለን።
➙​ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን እውነተኛ ውስጣዊ ሰላም ይኖረናል።
➙​በፍቅር ላይ የተመሠረተ አዲስ አኗኗር እንኖራለን።

"ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው" የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ለወደቀው የሰው ልጅ ሁሉ የተላከ የወንጌል የምስራች ነው። ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር በጸጋው ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነው። የኃጢአትህ ብዛት ወይም የሕይወትህ ውድቀት ምንም ያህል ቢሆን፣ በክርስቶስ ደም ታጥበህ "ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ብፁዕ ሰው" የመሆን እድል አለህ። ይህንን የእግዚአብሔርን ያልተገባ ጸጋና ፍቅር በማሰብ ሁልጊዜ በደስታና በምስጋና እንኑር።

@christcentered7
15🔥6
የሁሉ ሰጪ የሆነውን የጌታን ታላቅነት እያሰብን፣ በቅዱሳን ህብረት መካከል የምንቀበለው በረከት እጥፍ ድርብ ነው። በቃሉ እንደተጻፈው "ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፤ እነሆ፥ እንዴት ያማረ ነው!" (መዝሙር 133:1)። ይህ ህብረት የቃሉን እውነት የምንካፈልበት፣ እርስ በርሳችን በወንድማማች ፍቅር የምንታነጽበትና እምነታችን የምታደስበት የጸጋ መድረክ ነው።

​የነፍሳችንን ጥማት በሚያረካው፣ መንፈሳችንን በሚያደሰው በእግዚአብሔር ፊት ተገኝተን አምላካችንን በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እናመስግን፤ ሰላሙንም በልባችን እንቀበል።

እንግዲህ እግሮቻችንን ወደ ቤቱ እናቅና፤ ልባችንንም ለበረከቱ እናዘጋጅ!
24❤‍🔥4
በክርስትና መንገድ ላይ ትልቁ ስኬት ክርስቶስን መረዳት፣ ልብን በእርሱ ላይ መጣል።፣ በፍቅሩ መማረክ፣ እርሱን መከተልና የቅርብ ወዳጁ መሆን ነው።

​የመልካም ፍሬያማ ሕይወት ምስጢር ደግሞ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር መጣበቅ፣ በክብሩና በሕልውናው መሸፈን፣ እንዲሁም ባልተቋረጠ ጸጋውና ፍቅሩ ውስጥ እለት እለት ማደግ ነው።
30👍2
ኑዛዜ(Confessions) — የቅዱስ አውግስጥኖስ የሕይወትና የእምነት ጉዞ፤

በ4ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ አውግስጥኖስ የተጻፈ፣ በዓለም ሥነ-ጽሑፍና በክርስቲያናዊ መንፈሳዊነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ድንቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ደራሲው ከፈጣሪው ጋር ባደረገው ጥልቅ የግል ጸሎትና ንግግር መልክ የተዋቀረ ሲሆን፣ በውስጡ 13 ክፍሎችን (መጻሕፍትን) ይዟል።
​የመጽሐፉ ዋና ዋና ጭብጦች
➙​ አውግስጥኖስ ከወጣትነት እድሜው ጀምሮ በዓለማዊ ፍላጎት፣ በስጋ ፈተናና በተሳሳቱ ፍልስፍናዎች (እንደ ማኒካውያን እምነት) ውስጥ ያሳለፈውን ምስቅልቅል ሕይወት በግልጽ ያስቀምጣል።
➙​ አእምሮው ዕረፍት ያጣበትንና እውነተኛውን አምላክ ለማወቅ ያደረገውን ረጅም የእውቀትና የፍልስፍና ፍለጋ ያቀርባል።
➙​ እናቱ ቅድስት ሞኒካ በጸሎቷ ያፈሰሰችው እንባ፣ የቅዱስ አምብሮስ ትምህርትና በሚላን ከተማ ያጋጠመው ድንገተኛ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ አውግስጥኖስን እንዴት ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስቶስ እንዳመለሰው ይተርካል።
➙​ በመጨረሻዎቹ ክፍሎች ስለ ጊዜስለ ትውስታ (memory)፣ ስለ ፍጥረትና ስለ እግዚአብሔር ምስጢር ጥልቅ ስነ-መለኮታዊና ፍልስፍናዊ ትንተናዎችን ያቀርባል።

​መጽሐፉ፤ የሰው ልጅ የቱንም ያህል ቢሳሳትና ከእግዚአብሔር ቢርቅ፣ በእውነተኛ ንስሐና በፈጣሪ ቸርነት ወደ ሕይወት መመለስ እንደሚችል የሚያሳይ የታሪክ ምስክርነት ነው።
የመጽሐፉ ዋና ማጠቃለያ የሚሆነው አውግስጥኖስ በታዋቂው አባባሉ የገለጸው እውነት ነው፦ "አቤቱ፥ አንተ ለራስህ ፈጥረኸናልና፣ ልባችንም በአንተ ውስጥ እስኪያርፍ ድረስ እረፍት የለውም"

በጥያቄያችሁ መሠረት መጽሐፉን ከታች አስቀምጬዋለሁ 👇👇
16👍2
ኦሪት ዘዳግም 33:26-27 (NASV)

“አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣ በደመናትም ላይ በግርማው እንደሚገሠግሥ፣ እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።
ዘላለማዊ አምላክ (ኤሎሂም) መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከሥርህ ናቸ
🥰

ኧራ አሜን 🙏🙌
🙏285
የክርስትና ሕይወት በሁለት እውነታዎች መካከል የሚኖር መንፈሳዊ ጉዞ ነው፦ የተሰጠንን ማንነት እና የምንኖርበትን እውነታ የማስታረቅ ጉዞ።

​1. የታወጀው ማንነት (Position)
በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አስቀድሞ ስምና ስፍራ ሰጥቶናል። ይህ በፍጹም በሥራችን ያገኘነው ሳይሆን በጸጋው የተሰጠን ድንቅ ስጦታ ነው፦
➙​የእግዚአብሔር ልጆች ነን (1ኛ ዮሐንስ 3፥1)
➙​ቅዱሳን ነን (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥2)
➙​ተጠርተናል (ሮሜ 8፥30)
➙​ድነናል (ኤፌሶን 2፥8)

​2. የሚኖረው ማንነት (Practice)
ጉዞው የሚጀምረው እዚህ ጋር ነው። የተቀበልነውን የታወጀ ማንነት በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የመግለጥ እና የመኖር ሂደት ነው።
​ከተጠራንበት ጥሪ ጋር የሚመጥን አካሄድ እንድንንቀሳቀስ መጽሐፍ ቅዱስ ያሳስበናል (ኤፌሶን 4፥1)።

​ስለዚህ ክርስትና ያልሆንነውን አዲስ ነገር ለመሆን የምናደርገው የኃይል ግብግብ አይደለም፤ ይልቁንም በክርስቶስ የሆንነውን ማንነት በተግባር ወደ መሆን የምናደርገው የእድገት መስመር እንጂ።

​የሐዋርያው ጳውሎስ ጸሎት አስቀድሞ በተጠናቀቀው የእግዚአብሔር ሥራ ላይ የተመሠረተ ነው፦
​“...አምላካችን ለጥሪው የበቃችሁ አድርጎ እንዲቈጥራችሁ፣ ...እንጸልያለን።” — 2ኛ ተሰሎንቄ 1፥11
➙ ​ጥሪው የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ ጸሎቱ እንድንጠራ ሳይሆን፣ ከተጠራንበት ታላቅ ጥሪ ጋር የሚመጥን ስብዕና እና ፍሬ በሕይወታችን እንዲገለጥ ነው።
➙ ​ጥሪው ታላቅ እንደመሆኑ መጠን በራሳችን ጥረትና ሥጋዊ አቅም ብቻ ልንመላለስበት አንችልም። ስለዚህ የዘወትር ምልጃችን "አባት ሆይ! ለአንተ የተለየውን ማንነቴን በምድር ላይ እንድኖር በጸጋህ አቅም ሁነኝ" የሚል ይሁን።

@christcentered7
17❤‍🔥3👍2🔥1
እግዚአብሔርን መስማት የጸሎታችን መጀመሪያ ሲሆን፣ የሰማነውን መኖር፣ እግዚአብሔርን ማክበርና ለዘላለም በእርሱ ደስ መሰኘት የሕይወታችን ፍጻሜ ነው።
27🥰5💯2🔥1
ክርስቶስ ብቻ (Solus Christus)

​ማዕበል በናወጠውና ተስፋ በቆረጠው ዓለም ውስጥ፣ የሰው ልጅ ነፍስ የምትጠጋበትና የምታርፍበት ጽኑ መሠረት ትፈልጋለች። ለዚህም መሠረታዊና ብቸኛ መልስ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው!

​ይህ እውነት በሦስት ታላላቅ ምሶሶዎች ላይ ይቆማል፦

​1. የክርስቶስ ማዕከላዊነት ላይ
ኢየሱስ ክርስቶስ የክርስትና አስተምህሮ ማሟያ ሳይሆን ራሱ ማዕከሉና መሠረቱ ነው። ከእርሱ ውጭ ሌላ አማላጅ፣ ሌላ መንገድ፣ ወይም ሌላ የድኅነት በር የለም። ነፍሳችን የምትቆመው በሰዎች መልካም ሥራ ወይም በሃይማኖታዊ ትውፊቶች ላይ ሳይሆን፣ በሕያው የእግዚአብሔር ቃል ላይ በተገለጠው በኢየሱስ ማንነት ላይ ብቻ ነው።

​2. የነፍሳት እረፍት በተጠናቀቀው የመስቀሉ ሥራ ላይ
"ተፈጸመ!" (ዮሐንስ 19:30)
የነፍሳት ድነትን እረፍት የሚገኘው በስጋትና በትግል ሳይሆን በደኅንነት እርግጠኝነት ነው። ኢየሱስ መስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ሙሉና ፍጹም ስለሆነ፣ በእርሱ ያመነች ነፍስ ከኩነተ-ኃጢአትና ከሞት ፍርሃት ነፃ ትወጣለች። ይህ እረፍት የሰው ልጅ በገዛ ጥረቱ የሚገነባው ሳይሆን፣ በጸጋ (Sola Gratia) ተቀብሎ በእምነት (Sola Fide) የሚለማመደው ሰላም ነው።

​3. በማይናወጠው በቃሉ መሠረት ላይ
ዓለምና ሥርዓቶቿ ቢናወጡም፣ በክርስቶስ ላይ የተመሠረተች ነፍስ ግን ፈጽሞ አትናወጥም። መሠረታችን በየዕለቱ የሚለዋወጥ ስሜታችን ሳይሆን፣ የማይለወጠውና የማይታጠፈው የእግዚአብሔር ቃል ነው። "ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ..." (ዕብራውያን 6:19) እንደሚል፣ ክርስቶስ ማዕበሉን አልፎ ነፍሳችንን ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር ያቆራኛታል።

ነፍሴ ሆይ፤ ጸንተሽ የምትቆሚበትን ማዕበል የማይበግረውን ዐለት ፈልጊ፤ እርሱም የቀራንዮው ኢየሱስ ነው። የሰው ሥርዓት ይለዋወጣል፣ ምድርም ትናወጣለች፤ በኢየሱስ የተፈጸመው ሥራ ግን ለዘላለም የጸና ነው። ነፍሳችን ያረፈችው በሥራችን ሳይሆን በእርሱ ፍጹም ፍቅር ላይ ነው!

@christcentered7
12👍2🔥2
​ብዙዎቻችን በህይወታችን ውስጥ አሁንም ደስታን፣ ሰላምን እና የህይወት ትርጉምን በሌላ አቅጣጫ ለመፈለግ እንፈተን ይሆናል። በሃብት፣ በትምህርት፣ በሙያ ስኬት ወይም በሰዎች ዘንድ በሚገኝ እፎይታ ውስጥ ፍጹም እርካታን ለመፈለግ እንሮጣለን፤ ነገር ግን በክርስቶስ ካገኘነው እውነተኛ እርካታ ውጪ ያለው ነገር ሁሉ ውስጣዊ ክፍተታችንን ሊሞላው አይችልም። ምክንያቱም የሰው ልጅ ተፈጥሮ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ በመሆኑ፣ የልባችንን ጥልቅ ፍላጎት ሊያረካ የሚችለው ፈጣሪያችንና አባታችን ብቻ ነው።
​ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ህይወታችን የመጣው ህይወት እንዲሆንልንና እንዲበዛልንም ነው።

ዛሬም ቢሆን በህይወታችን የምንፈልገውን እውነተኛ ፍቅር፣ የማይናወጥ ሰላም እና ጽናት የሚሰጠን እርሱ ብቻ ነው። ስለዚህ አምነን የተቀበልነውን ጌታ አጥብቀን እንያዝ፤ ህይወታችንን በየቀኑ በሙሉ እሺታ ለጌታ አሳልፈን እንስጥ፤ በክርስቶስ ያለው ህይወታችንም በኃይልና በደስታ ይታደሳል።

"እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።" — ዮሐንስ 10:10
❤‍🔥155🥰5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብልጽግና ወንጌል አስተምህሮ ዳሰሳ || Prosperity Gospel
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምኦን ሙላት ያስተላለፉት ትምህርት ነው። መሪዎች የቃሉ አስተማሪዎች ሲኾኑ እንዲህ ነው።

ይህ የብልጽግና ወንጌል አስተምህሮ በመጽሀፍ ቅዱስ ሲመረመር የተሰኘው ዳሰሳ በሕይወት ቲቪ youtube ገጽ ላይ ተገኛለችሁ....መደመጥ ያለበት መልዕክት ነው። በዚህ link 👇👇 https://www.youtube.com/watch?v=zu2ZeWwsVzM
19❤‍🔥5
የዚህ(የ2018 ዓ.ም) አማት ጉዞዬ፡

በደሌ ከፍ ብሎ ሳለ
ምህረትህ በኔ ላይ ገናና
እኔ ነኝ እግዚአብሔር የረዳኝ
ከትቢያ ካመድ ላይ ያነሳኝ🥰
27🥰2🙏2
ይህ አማት የፈጣሪ ምሕረት፣ ታጋሽነትና ጥበቃ የጎላበት ትልቅ የመማሪያ መድረክ ነው። ጊዜ ሲያልፍ አብሮ የሚሸኘው የቀናት ቁጥር ብቻ ሳይሆን የእኛም ውጣ ውረድ፣ ደስታ፣ ፈተናና ውድቀትም ነው።

​ይህ ዓመት በሕይወታችን የተከሰቱትን ድካምና ኃጢአት እያየ ፈጣሪ ሳይፈርድብን እስከ ዛሬ የቆየንበት የችሎቱና የትዕግሥቱ ማሳያ ነው (ሰቆቃወ ኤርምያስ 3፥22-23)።

ያለፉት ፈተናዎች፣ ያጋጠሙ ውድቀቶችና ያልተሳኩ ዕቅዶች ሁሉ መንፈሳዊ ጥንካሬና እውነተኛ ጥበብ እንድናገኝ የተፈቀዱ መለኮታዊ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

​ያለፊትን ጊዜያት መለስ ብሎ ማየት የራስን ድካም ለመገምገም፣ በንስሐ ለመታደስ እና ከሰዎች ጋር የነበረን የበደል ሂሳብ ዘግቶ በሰላም ለመሻገር ወሳኝ እድል ይሰጣል።

ይህ ዓመት ምንም ይሁን ምንም በንስሐ፣ በይቅርታና በምስጋና አጠናቆ ወደ አዲሱ ምዕራፍ መሻገር የመንፈሳዊ ብስለትና የውስጥ ሰላም መሠረት ነው።

ጸጋ ይብዛላችሁ 🙏🙌
@christcentered7
13👍4
​አዲስ ዘመን ሲጠባ ምድር በደመቀ አበባ እንደምትሸለም፣ የእኛም ሕይወት በእውነተኛ ንስሐ፣ በወንድማማች ፍቅርና በመልካም ፍሬ እንዲሸለም አድርግ። የባከኑ ጊዜያቶችን፣ ያልተሳኩ ዕቅዶችንና የልብን ስብራት በጸጋህ ፈውሰው።

​በዚህ አዲስ ዓመት አእምሮአችንን በአዲስ አስተሳሰብ አድሰው፤ እግሮቻችንን በጽድቅ መንገድ ላይ አጽና። ዘመናችንን ሙሉ በብርሃንህ እንድንመላለስና ለሌሎች የምሕረትህ ማሳያ እንድንሆን እርዳን።

መልካም አድስ ዓመት!
@christcentered7
16🙏2