ቅጥሬ አልፈረሰም መጠበቂያዬ
አለሁ ይለኛል ደጉ ጌታዬ
ቀና ብዬ ሳይ ቀለላት ነፍሴን
ፍቅሩ ስጠራኝ አየሁት እራሴን።
🎶 ደረጄ ከበደ🙏
አለሁ ይለኛል ደጉ ጌታዬ
ቀና ብዬ ሳይ ቀለላት ነፍሴን
ፍቅሩ ስጠራኝ አየሁት እራሴን።
🎶 ደረጄ ከበደ🙏
❤22🥰5
የሰው ልጅ ታማኝነትና ውለታ እንደ ደመና ተለዋዋጭ ቢሆንም፣ የእግዚአብሔር ኪዳን ግን እንደ ዐለት የጸና ነው። እኛ በጉዞአችን ብንደክም፣ መንገዳችንም ቢጠባብ እንኳ፣ እርሱ ስለ ታላቅ ስሙና ስለ ታማኝነቱ ሲል በሕይወታችን የጀመረውን መልካም ሥራ በድል ይፈጽመዋል።
“በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤”
— ፊልጵስዩስ 1፥6
የሕይወታችንና የዘላለም መዳናችን ዋስትና የራሳችን ጥንካሬ ወይም መልካምነት ሳይሆን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው የማይለወጠው የእግዚአብሔር ታማኝነትና ጸጋ ብቻ ነው።
ይህ ደግሞ ብርታታችን ነው 🙏

❤🔥23🥰7❤3🔥3🙏2
ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ የቤተክርስቲያን ትልቁ መሠረት የእርሱ ፍጹም መለኮትነትና ፍጹም ሰውነት ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹምም ሰው ሆኖ ወደ ምድር የመጣው፣ ቅዱሱን አምላክና በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቶ የነበረውን ሰው በመስቀል ላይ በከፈለው መስዋዕትነት ለማስታረቅና ለማገናኘት ነው (1 ጢሞቴዎስ 2:5)።
👉 በሰውነቱ (ፍጹም ሰው) እንደ እኛ መከራን፣ ሕመምን፣ ፈተናንና ጭንቀትን የቀመሰ በመሆኑ አቅማችንንና የልባችንን ስብራት በደንብ ይረዳል (ዕብራውያን 2:18፤ 4:15)።
ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን መስሎ በመመላለሱ፣ በሕይወታችን የምናልፍበትን ማንኛውንም ፈተና የሚረዳ ርኅሩኅ ሊቀ ካህናችን ነው።
👉 በአምላክነቱ (ፍጹም አምላክ) ደግሞ የኃጢአታችንን ዕዳ የመክፈል፣ የሞትንና የዲያብሎስን ሥልጣን የማሸነፍ፣ እንዲሁም ለተሰበረው ልባችን እውነተኛ ሰላምንና የዘላለም ሕይወትን የመስጠት ሙሉ ሥልጣን አለው (ቆላስይስ 2:9-10፤ ዮሐንስ 14:27)።
የልባችንን ስብራትና ጭንቀት የሚረዳ፣ በሰውነቱ መከራችንን የተካፈለ፣ በአምላክነቱ ደግሞ ከኃጢአትና ከጭንቀት እስራት ሊገላግለን የሚችል አንድ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እርሱ የነፍሳችን አዳኝ፣ የታመነው ወዳጃችንና ብቸኛው መካከለኛችን ነው።

❤20🔥4👍2
በሕይወታችን ውስጥ ሁላችንም አልፎ አልፎ የኀዘን፣ የቁጭት እና የንስሐ ስሜቶች ያጋጥሙናል። ነገር ግን ሁሉም ኀዘን አንድ ዓይነት አይደለም፤ ፍሬውም ይለያያል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልእክቱ ላይ፦
“እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።”(2ኛ ቆሮንቶስ 7፥10)
በማለት ሁለት መሠረታዊ የኀዘን ዓይነቶችን እና የሚያስከትሏቸውን ውጤቶች በግልጽ ያሳየናል።
1. እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን (መንፈሳዊ ኀዘን)
ይህ ዓይነቱ ኀዘን ሰው በራሱ ጥረት የሚያመጣው ሳይሆን፣ መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ በሚሰራው የመታደስ ሥራ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው። ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት በመበላሸቱ፣ በፍቅሩ ላይ በመበደሉ ወይም ሕጉን በመጣሱ ምክንያት በልቡ ውስጥ የሚሰማው ጥልቅ እውነተኛ የልብ ስብራት ነው።
👉ባሕርዩም የራስን ጥፋት አምኖ መቀበልን፣ ትህትናን እና የመንፈስ ቅዱስን የልብ መታደስ ያመጣል።
👉ውጤቱም የእውነተኛ መዳን እና የልብ መታደስ ፍሬ የሆነውን ንስሐን ያስገኛል። ንስሐ የመዳናችን ምክንያት ወይም ሥራ ሳይሆን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ላገኘነው ነጻ የመዳን ጸጋ የሚሰጥ ትክክለኛ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ነው። የእግዚአብሔርን ይቅርታ እና ሰላም ስለሚያስገኝ በኋለኛው ጊዜ ምንም የሚያስጸጽት ነገር አይተውም።
👉ምሳሌ፡ “ሐዋርያው ጴጥሮስ ጌታን ሶስት ጊዜ ከካደ በኋላ፣ ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ ስለ እምነቱ በጸለየለትና በሰጠው የመታደስ ጸጋ ምክንያት አልቅሶ ወደ ቀደመው አገልግሎቱና ፍቅሩ ተመለሰ (ማቴ. 26፥75፤ ሉቃ. 22፥32)።”
2. የዓለም ኀዘን (ሥጋዊ ኀዘን)
የዓለም ኀዘን የሚመነጨው ከትዕቢት፣ ከራስ ወዳድነት ወይም ደግሞ ጥፋት በመሰራቱ ከሚመጣው ውርደት እና ቅጣት ከመፍራት ነው።
👉ባሕርዩም ሰዎች ምን ይሉኛል?፣ ስሜ ጠፋ፣ ወይም ጥቅሜ ቀረ ከሚል ስጋት የሚወለድ ነው፤ በኃጢአቱ የተነሳ እግዚአብሔርን በመበደሉ አይቆጭም።
👉ውጤቱም ተስፋ መቁረጥን፣ ጭንቀትን፣ ምሬትን እና የመንፈስ ሞትን (አንዳንድ ጊዜም አካላዊ ሞትን) ያመጣል።
👉ምሳሌ፡ ይሁዳ ጌታን አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ተጸጸተ፤ ነገር ግን ኀዘኑ እግዚአብሔርን ከማሳዘን የመነጨ ሳይሆን ከውርደት እና ከቅጣት ፍርሃት የመጣ የዓለም ኀዘን ስለነበረ፣ ወደ እግዚአብሔር ምሕረት ከመሮጥ ይልቅ ተስፋ ቆርጦ ራሱን ሰቀለ (ማቴ. 27፥3-5)።”
ውድቀት ወይም ስህተት በገጠመን ጊዜ የሚሰማን ኀዘን ወደ የትኛው መንገድ እየመራን እንደሆነ ማስተዋል አለብን። ኀዘናችን ወደ እግዚአብሔር ምሕረት የሚያቀርበን ከሆነ የእውነተኛ መዳን እና የጸጋው ፍሬ ነው፤ ነገር ግን ወደ ተስፋ መቁረጥ እና ራሳችንን ወደ መኮነን የሚወስደን ከሆነ የዓለም ኀዘን መሆኑን አውቀን፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በፈጸመው ሥራ ወደተከፈተልን ወደ እግዚአብሔር የጸጋ ዙፋን መሮጥ ይኖርብናል (ዕብ. 4፥16)።
እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሆነውን የተሰበረውን ልብ አይንቅም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው፦
“የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።”( መዝሙር 51፥17)
በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ሥራ በተከፈተው መንገድ፣ ኀዘናችን በጸጸት የሚቀር ሳይሆን ወደ ትክክለኛ ንስሐና ወደ እግዚአብሔር እቅፍ የሚመልሰን መንፈሳዊ መንገድ እንዲሆን ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ጸጋና እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል።
@christcentered7

❤🔥13❤4👍2😭1
ምድራዊ ሕይወታችን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጸጋ ያገኘነውን የዘላለም ሕይወት፤ በቅድስናና ለእግዚአብሔር ክብር የምንገልጥበት አጭር ምዕራፍ ናት። በክርስቶስ የተመረጥን አማኞች በምድር ላይ የምናደርገው እያንዳንዱ የታዛዥነት ምርጫ በዘላለም አክሊላችንና ዋጋችን ላይ ፍሬ ያፈራል።
ጊዜያዊውን የዓለም ጥቅም ለማተርፍ ሲሉ ዘላለማዊውን የእግዚአብሔርን ክብር ንቆ መተው የታላቁን ሀብት ዋጋ አለማወቅ ነው። ዘላለምንና የእግዚአብሔርን ክብር ታሳቢ ያደረገ ሕይወት፤ የዛሬን ፈተና በደስታ የመሻገር አቅም አለው።
“የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 4፥17-18

❤19🔥6🥰2👌1
ኢሳይያስ 41
⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥
⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፦ አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥
¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
¹¹ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፉማል።
¹² የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
¹³ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፦ አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
አሜን አሜን 🙏🙌

🙏25❤10👍2
08 ምህረትህ-Mihreth/Yosef Aschalew
አሐዱ ዜማ Tube
መጸለይ ስከብዳኝ፣ ነፍሴ እጅግ ደክማ፤
ደግሞ ስትበራታ፣ ጸንታ በፈተና፤
ካንታ ንጽህና ስታይ ከውበትህ፤
ደክሜም በረትቼ፣ አልመጥንህም ፊትህ....
ምህርትህ/ቸርነትህ
አኖረኝ በቤትህ
✍Yosef Aschalew
@christcentered7
❤16🙏2
Christ-centered
አሐዱ ዜማ Tube – 08 ምህረትህ-Mihreth/Yosef Aschalew
እረመድበት ዘንድ፣ ከምርግጣው መሬት
እጅግ ይታመናል የአንታ፤ ምህረት
ከምታነፍሰው ከዚህ ንጽሁ አየር
ቸርነትህ ላኔ ብዙ ነው እግዚአብሔር🥰
እጅግ ይታመናል የአንታ፤ ምህረት
ከምታነፍሰው ከዚህ ንጽሁ አየር
ቸርነትህ ላኔ ብዙ ነው እግዚአብሔር🥰
❤24
ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል የሚታወጅባት፣ ጸጋው የሚገለጥባትና የ አካሉ መገለጫ ናት። እሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ የተነሣበት የጌታ ቀን ነው!
በዚህ ታላቅ ቀን ሕያው ቃሉን ልንሰማ፣ ከቅዱሳን ኅብረት ጋር ልንደመር፣ እናም በቃሉና በመንፈሱ በመታደስ አምልኳችንን ለጌታ ልናቀርብ ወደ ቅዱሳን ህብራት (ቤተክርስቲያን) እንሂድ🥰

❤23🔥4👍2🙏1
በእኛ ወንጌል አማኞች ማህበረሰብ ውስጥ ለአማኙ መንፈሳዊ እድገት፣ ለቤተክርስቲያን አንድነትና ለወንጌል ምስክርነት ሲባል ሊታረሙና ሊስተካከሉ የሚገባቸው ብዬ የማስባቸው ሀሳቦችና ድርጊቶች፦
1. የብልጽግና ወንጌል አመለካከት፦ እምነትንና መንፈሳዊነትን ቁሳዊ ሀብት፣ ገንዘብና የዚህ ዓለም ስኬት ማግኛ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ። ክርስቲያናዊ ሕይወት በመስቀሉ መንገድ፣ በትግስቱና በመከራውም ውስጥ ክርስቶስን መከተል እንደሆነ አስተምህሮውን ማመጣጠን ያስፈልጋል።
2. መጽሐፍ ቅዱስን ከተቆራረጡ ጥቅሶች ብቻ መረዳት (Proof-Texting)፦ ጥቅሶችን ከቀደም ተከተላቸውና ከተጻፉበት ታሪካዊ/መንፈሳዊ context ውጭ በመውሰድ ለግል ፍላጎት ወይም ለስሜት ማስማማት። መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀትና በስርዓት የማንበብ ባህል ሊጎለብት ይገባል።
3.አገልጋዮችን ከተገቢው በላይ ማላቀቅ (Hero Worship)፦ ሰዎችን ወይም አገልጋዮችን እንደ እግዚአብሔር ምትክ አድርጎ የመመልከትና የማምለክ ያህል የማክበር አዝማሚያ። ትኩረቱና ክብሩ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ብቻ መመለስ አለበት።
4.ትንቢትንና ተአምራትን ያለመመርመር፦ የሚነገሩ ትንቢቶችንና ተአምራትን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር ሳያመዛዝኑ በየዋህነት መቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ” እንደሚል የመንፈስን አመጣጥ የመመርመር ልምድ ያስፈልጋል።
5.የጸሎትና የአምልኮ አቀራረብ፦ ጸሎትና አምልኮ መንፈሳዊና ግላዊ ግንኙነት እንደመሆኑ መጠን፣ ሌሎች ሰዎችን በሚረብሽ ወይም ከልክ ባለፈ ጫጫታና ግርግር የሚደረጉ ድርጊቶችን መቀነስ።
6.የፋይናንስ ግልጽነት ማነስ፦ በቤተክርስቲያናትና በአገልግሎት ድርጅቶች ውስጥ የሚሰበሰቡ አስራት፣ በኩራትና ስጦታዎች አጠቃቀም ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት ማነስ።
7.ለማህበራዊና ለሀገራዊ ጉዳዮች ትኩረት አለመስጠት፦ መንፈሳዊነትን ከዕለት ተዕለት ማህበራዊ ሕይወት፣ ከስራ ባህል፣ ከታማኝነትና ከሀገር እድገት ነጥሎ ማየት። አማኞች በሙያቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን መሆን አለባቸው።
8.ሌሎችን የመፍረድና የመንቀፍ አመለካከት፦ ከእኛ እምነት ወይም አሰራር ውጭ ያሉትን ማህበረሰቦች ወይም የሌሎች እምነት ተከታዮችን በፍቅርና በክብር ከመቅረብ ይልቅ የመኮነንና የማግለል አቀራረብ።
9.የይስሙላ መንፈሳዊነት፦ በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም መንፈሳዊ መስሎ መታየት፣ ነገር ግን በቤት፣ በስራ ቦታና በግል ህይወት የክርስቶስን አምሳል አለማሳየት።
10. የህብረትና የአንድነት መሸርሸር፦ በትንሽ ልዩነቶችና በጥቅም ምክንያት የመለያየትና አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን የመክፈት አዝማሚያ። የመንፈስን አንድነት በሰላም ማሰሪያ ለመጠበቅ መጋደል ይገባል።
ሌሎችን እያያን እንጨምራለን 🙌

💯15🤝4❤3❤🔥2⚡1🙏1
ዛሬ በደካማ ሥጋ ውስጥ ሆነን፣ በኃጢአት ደመናና በሰይጣን ፈተና መካከል ስንጓዝ የጌታ ፍቅር ትንሽ ጠብታ እንኳ በልባችን ሲያርፍ ዓለምን የሚያስረሳ ከሆነ፣ ነገ በትንሣኤ ቀን በክብር ስንነሳ የሚጠብቀን ደስታ ምን ያህል ግዙፍ ይሆን?
በዚያን ቀን፡
➙የሚከብድ ሥጋ፣ የሚያታልል ሕሊና ወይም የሚስብ ኃጢአት አይኖርም።
➙ዛሬ በእምነትና በምሳሌ የምናየውን፣ በዚያን ቀን ፊት ለፊት እያየነው በፍቅሩ ባህር እንዋኛለን።
ስለዚህ፤ ዓለምና ምኞቷ አላፊ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ለዘላለም ይኖራል። እግዚአብሔር በጸጋው ልባችንን ለዚህ የክርስቶስ ፍቅር ሲከፍተው፣ የሞት ጥላ ሳይጋርደን የዘላለም ሕይወትን መዓዛና ዘላለማዊውን ሰላም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ከወዲሁ መለማመድ እንጀምራለን።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:12 (NASV)
¹² ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

❤🔥23❤6🔥2
"እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።"
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1 (NASV)
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1 (NASV)
❤19🔥5
እውነተኛ አገልጋይ በራሱ ችሎታ፣ እውቀት ወይም ጥረት አይመካም። በህይወቱ ላከናወነው መልካም ነገር ሁሉ ምስጋናውን ለሰጠው ጸጋ ያቀርባል። በገዛ ጉልበቱ አልፎ የተሻገረ መስሎት አይታበይም፤ ይልቁንም "ዛሬ ባለሁበት ማንነቴ በእግዚአብሔር ጸጋ እኔ ነኝ" ብሎ በትህትና ይንበረከካል። ይህ ትህትና እና የጸጋ ጥገኝነት ህይወቱንና አገልግሎቱን የሚያንፀባርቅ እውነተኛ ውበት ይሰጠዋል።
❤🔥29❤4🔥4🥰4
“ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።” — ሮሜ 4: 8
በዚህ ዓለም ላይ ትልቁ ደስታና ዕረፍት ምንድን ነው? ብዙዎች ሀብት፣ ሥልጣን ወይም ዝና ሊመስላቸው ይችላል። ነገር ግን ቅዱሱ መጽሐፍ እውነተኛውን ብፅዕና (ደስታ) የሚያያይዘው ከውስጥ ማንነታችንና ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ግንኙነት ጋር ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በመዝሙረኛው ዳዊት ቃል ተደግፎ እንደነገረን፣ እውነተኛ ብፁዕ ሰው ማለት "ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው" ነው።
የማይቆጠር ኃጢአት ማለት ምን ማለት ነው?
በሒሳብ ስሌት ወይም በሕግ መዝገብ ውስጥ እዳ እንደሚመዘገብ ሁሉ፣ ኃጢአትም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ትልቅ እዳ ነው። ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ በተከፈለልን ዋጋ ምክንያት፣ በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ እዳቸው ተደምስሷል። እግዚአብሔር ኃጢአታችንን "አይቆጥርብንም" ሲባል፣ ኃጢአት አልሰራንም ማለት ሳይሆን፣ የኃጢአታችን ፍርድና ቅጣት በክርስቶስ ላይ ተጭኗል (ኃጢአታችን ለክርስቶስ ተቆጠረ) እና የክርስቶስ ፍጹም ጽድቅ ደግሞ ወደ እኛ መዝገብ ተዛውሯል/ተቆጥሮልናል (2ኛ ቆሮንቶስ 5:21) ማለት ነው።
ይህ ብፅዕና በሰው መልካም ሥራ፣ በሥጋዊ ጥረት ወይም በራሳችን ጽድቅ የሚገኝ አይደለም። ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጥ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። እኛ ልንከፍለው ያልቻልነውን የኃጢአት እዳ ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ስለከፈለው፣ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሰውን ልብ ስያነቃቃ፤ በጸጋው ጥሪ በእምነትና ንስሐ ወደ እርሱ የሚመጡ ሁሉ የዚህ ነጻነትና ብፅዕና ተካፋዮች ይሆናሉ።
የኃጢአት በደለኝነት ስሜትና የፍርሃት ሕይወት የሰውን ውስጣዊ ሰላም ያጠፋል። ነገር ግን እግዚአብሔር ኃጢአታችንን እንደማይቆጥርብን ስንረዳ፦
➙ከበደለኝነትና ከኩነኔ ስሜት ነጻ እንወጣለን።
➙ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆን እውነተኛ ውስጣዊ ሰላም ይኖረናል።
➙በፍቅር ላይ የተመሠረተ አዲስ አኗኗር እንኖራለን።
"ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው" የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ለወደቀው የሰው ልጅ ሁሉ የተላከ የወንጌል የምስራች ነው። ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔር በጸጋው ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነው። የኃጢአትህ ብዛት ወይም የሕይወትህ ውድቀት ምንም ያህል ቢሆን፣ በክርስቶስ ደም ታጥበህ "ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ብፁዕ ሰው" የመሆን እድል አለህ። ይህንን የእግዚአብሔርን ያልተገባ ጸጋና ፍቅር በማሰብ ሁልጊዜ በደስታና በምስጋና እንኑር።
@christcentered7
❤15🔥6
የሁሉ ሰጪ የሆነውን የጌታን ታላቅነት እያሰብን፣ በቅዱሳን ህብረት መካከል የምንቀበለው በረከት እጥፍ ድርብ ነው። በቃሉ እንደተጻፈው "ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ መልካም ነው፤ እነሆ፥ እንዴት ያማረ ነው!" (መዝሙር 133:1)። ይህ ህብረት የቃሉን እውነት የምንካፈልበት፣ እርስ በርሳችን በወንድማማች ፍቅር የምንታነጽበትና እምነታችን የምታደስበት የጸጋ መድረክ ነው።
የነፍሳችንን ጥማት በሚያረካው፣ መንፈሳችንን በሚያደሰው በእግዚአብሔር ፊት ተገኝተን አምላካችንን በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እናመስግን፤ ሰላሙንም በልባችን እንቀበል።
እንግዲህ እግሮቻችንን ወደ ቤቱ እናቅና፤ ልባችንንም ለበረከቱ እናዘጋጅ!

❤24❤🔥4
በክርስትና መንገድ ላይ ትልቁ ስኬት ክርስቶስን መረዳት፣ ልብን በእርሱ ላይ መጣል።፣ በፍቅሩ መማረክ፣ እርሱን መከተልና የቅርብ ወዳጁ መሆን ነው።
የመልካም ፍሬያማ ሕይወት ምስጢር ደግሞ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር መጣበቅ፣ በክብሩና በሕልውናው መሸፈን፣ እንዲሁም ባልተቋረጠ ጸጋውና ፍቅሩ ውስጥ እለት እለት ማደግ ነው።

❤30👍2
ኑዛዜ(Confessions) — የቅዱስ አውግስጥኖስ የሕይወትና የእምነት ጉዞ፤
በ4ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ አውግስጥኖስ የተጻፈ፣ በዓለም ሥነ-ጽሑፍና በክርስቲያናዊ መንፈሳዊነት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ድንቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ደራሲው ከፈጣሪው ጋር ባደረገው ጥልቅ የግል ጸሎትና ንግግር መልክ የተዋቀረ ሲሆን፣ በውስጡ 13 ክፍሎችን (መጻሕፍትን) ይዟል።
የመጽሐፉ ዋና ዋና ጭብጦች
➙ አውግስጥኖስ ከወጣትነት እድሜው ጀምሮ በዓለማዊ ፍላጎት፣ በስጋ ፈተናና በተሳሳቱ ፍልስፍናዎች (እንደ ማኒካውያን እምነት) ውስጥ ያሳለፈውን ምስቅልቅል ሕይወት በግልጽ ያስቀምጣል።
➙ አእምሮው ዕረፍት ያጣበትንና እውነተኛውን አምላክ ለማወቅ ያደረገውን ረጅም የእውቀትና የፍልስፍና ፍለጋ ያቀርባል።
➙ እናቱ ቅድስት ሞኒካ በጸሎቷ ያፈሰሰችው እንባ፣ የቅዱስ አምብሮስ ትምህርትና በሚላን ከተማ ያጋጠመው ድንገተኛ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ አውግስጥኖስን እንዴት ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስቶስ እንዳመለሰው ይተርካል።
➙ በመጨረሻዎቹ ክፍሎች ስለ ጊዜ፣ ስለ ትውስታ (memory)፣ ስለ ፍጥረትና ስለ እግዚአብሔር ምስጢር ጥልቅ ስነ-መለኮታዊና ፍልስፍናዊ ትንተናዎችን ያቀርባል።
መጽሐፉ፤ የሰው ልጅ የቱንም ያህል ቢሳሳትና ከእግዚአብሔር ቢርቅ፣ በእውነተኛ ንስሐና በፈጣሪ ቸርነት ወደ ሕይወት መመለስ እንደሚችል የሚያሳይ የታሪክ ምስክርነት ነው።
የመጽሐፉ ዋና ማጠቃለያ የሚሆነው አውግስጥኖስ በታዋቂው አባባሉ የገለጸው እውነት ነው፦ "አቤቱ፥ አንተ ለራስህ ፈጥረኸናልና፣ ልባችንም በአንተ ውስጥ እስኪያርፍ ድረስ እረፍት የለውም"
በጥያቄያችሁ መሠረት መጽሐፉን ከታች አስቀምጬዋለሁ 👇👇

❤16👍2