Christ-centered
1.62K subscribers
18 photos
7 videos
13 files
3 links
​ጤናማ አስተምህሮ ለበሰለ ህይወት መሰረት ነው።
​እውነት ለአእምሮ፣ ጸጋም ለልብ ብርሃን ነው።
Download Telegram
ወንጌልን ከዘመኑ ፍልስፍናና ስሜት ጋር ለማስማማት መሞከር፣ ወንጌሉን ማዳን ሳይሆን ኃይሉን ማክሰም ነው። ወንጌል ዓለምን ሊሞግትና ሊለውጥ የመጣ መለኮታዊ እውነት እንጂ፣ ከዓለም ጫጫታና ፋሽን ጋር እኩል ለመራመድ የሚታጠፍ ሰብአዊ ድርሰት አይደለም። William Ralph Inge እንደምለው "ከዘመኑ ጋር ያገባች ቤተክርስቲያን፣ በሚቀጥለው ዘመን መበለታ ሆና ትቀራለች።"

ቤተክርስቲያን ለዘመኑ ሰዎች መልእክቱን የምታደርስበት ቋንቋና መንገድ ዘመኑን የዋጀ (Contextualized) ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የምታደርሰው እውነት ግን መለኮታዊና ፍጹም የማይለወጥ (Absolute) ነው። ዓለም ወደ ቤተክርስቲያን መጥታ መለወጥ እንጂ፣ ቤተክርስቲያን ወደ ዓለም ሄዳ መልክዋን ማጣት የለባትም።

“እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።”
  — ቆላስይስ 2፥8


ይህንን ጥልቅ ማሳሰቢያ ለትውልድ ማስተማርና ማስታወስ የሁላችንም ጥሪ ነው!
14🔥4❤‍🔥3👏3
Christ-centered
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 5 ​12. የድካማችን ደጋፊና አማላጅ ነው። ​“እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”( ሮሜ 8፥26) ​አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በጣም ከባድ የጭንቅና የፈተና ጊዜያት ይመጣሉ። በዚያ ሰዓት አእምሯችን ይዝላል፣ የምንናገረው ቃል ይጠፋናል፣ ሌላው ቀርቶ "እንዴት…
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 6(የመጨረሻው ክፍል)

​ 14. ታማኝ መሪ ነው።
​“ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”
  — ኢሳይያስ 30፥21

​ሕይወት በብዙ ምርጫዎችና ውሳኔዎች የተሞላች ናት። የትኛውን መንገድ ልሂድ? ምን ዓይነት ውሳኔ ልወሰን? ብለን ግራ የምንጋባባቸው ብዙ ቀናት አሉ።
​በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው (ሮሜ 8:14)። መንፈስ ቅዱስ በጉዟችን ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናውቅ ትክክለኛውን መንገድ ይመራናል። በልባችን ውስጥ ረቂቅ ድምፅ በመሆን፣ በቃሉ በኩል ብርሃን በመፈንጠቅና በሁኔታዎች ውስጥ መለኮታዊ ምልክት በመስጠት ከመሳሳትና ከጥፋት መንገድ ይታደገናል።

John Calvin👇
"የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚታወቀው በመንፈስ ቅዱስ መመራታችን ነው። እርሱ በሕይወታችን ውስጥ ዓይነ ስውራን እንዳንሆን በቃሉ ብርሃንነት ይመራናል። የመንፈስ ቅዱስ አመራር መለኮታዊ ኮምፓሳችን ነው፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እንዳናዘነብል የክርስቶስን ፈቃድ በልባችን እያበራ ወደ እውነት መንገድ በትዕግሥት ይመራናል።"

​15. በመከራ ውስጥ የጽናት ብርታት ነው።
"በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።" (ሮሜ 5:5)

​ክርስቲያናዊ ጉዞ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለም፤ መከራና ፈተናዎች አሉት። በእነዚህ አስቸጋሪ ወቅቶች ውስጥ እምነታችን እንዳይደክም፣ ተስፋ ቆርጠን ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ የሚያደርገን ምንድን ነው?
​ምስጢሩ መንፈስ ቅዱስ ነው። በመከራና በፈተና ውስጥ ስንሆን፥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ዘላለማዊና የማይለወጥ ፍቅር በልባችን ውስጥ አፍስሶ ያረሰርሰናል። "እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው" የሚለውን እውነት እያስታወሰን፣ በውስጣችን ሰማያዊ ጽናትንና ብርታትን ይተክላል። በአውሎ ነፋስ መካከልም እንኳ ቆመን እንድንዘምር የሚያደርገን እርሱ ነው።

John Flavel👇
"እግዚአብሔር አማኞችን ከመከራ ማዕበል ሙሉ በሙሉ አይጠብቃቸውም፤ ነገር ግን በማዕበሉ ውስጥ እንዳይሰምጡ በመንፈሱ ያጸናቸዋል። መንፈስ ቅዱስ በመከራ ውስጥ የጽናታችን መልሕቅ ነው። በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ ሲናወጥ፣ እርሱ ግን በነፍሳችን ውስጥ የማይናወጥ የሰማይ ሰላም ያኖራል።"

@christcentered7
12🔥2🙏1
የእግዚአብሔር ጸጋ ሙሉ ሕይወታችንን ለክርስቶስ እንድንሰጥ ይጠይቃል(ያበቃናል) ስንል፤ ሕይወታችንን ሰጥተን ጸጋውን እንገዛዋለን እያልን ሳይሆን፤ በነጻ የተሰጠን እውነተኛ ጸጋ በሕይወታችን ላይ ያለውን ፍጹም የክርስቶስን ጌትነት (Lordship of Christ) በእምነትና በታዛዥነት እንድንቀበል በውስጣችን በኃይል ይሠራል እያልን ነው።
❤‍🔥16🙏6🥰42🔥1
Missio Dei (የእግዚአብሔር ተልዕኮ)

​ታላቁ ተልዕኮ የቤተክርስቲያን ፈጠራ ሳይሆን የ Missio Dei (የእግዚአብሔር ተልዕኮ) ነጸብራቅ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ላኪ አምላክ ነው፤ አብ ወልድን ላከ፣ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስን ላኩ፣ አሁን ደግሞ ሥላሴ ቤተክርስቲያንን ወደ ዓለም ይልካታል።
እኛ በተልዕኮው ውስጥ ስንሰማራ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ በሚያደርገው መለኮታዊ ሥራ ውስጥ አብረን እየሠራን (የእግዚአብሔር አብሮ ሠራተኞች) ነን። እኛ የተልዕኮው ባለቤቶች ሳንሆን፣ የባለቤቱ ታማኝ ባለአደራዎች ነን። (ማቴ 28:19)

የታላቁ ተልዕኮ መሠረት የክርስቶስ ፍጹም ጌትነት (Lordship of Christ) እና በአጽናፈ ዓለም ላይ ያለው ፍጹም ሥልጣን ነው። እኛ የምንሄደው በራሳችን ብቃት ሳይሆን፣ በትንሣኤው ሥልጣንና በተሰጠን (በወረደው) በመንፈስ ቅዱስ ኃይል (የሐዋ 1:8) ነው።
ወንጌልን ማወጅ የክርስቶስን ሕጋዊና መለኮታዊ ንግሥና በስፍራው ሁሉ ማወጅ ነው።

​ቤተክርስቲያን የተጠራችው ለራሷ እንድትኖር ሳይሆን፣ ለዓለም ምስክር እንድትሆን ነው። የታላቁ ተልዕኮ ዋና ማዕከል "ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" የሚለው ትእዛዝ ነው። ይህ ደግሞ ሰዎች በወንጌል አምነው እንዲድኑ ከማወጅ ባለፈ፣ በክርስቶስ እውነትና ጸጋ ውስጥ እንዲያድጉ የማድረግ ስነ-መለኮታዊ ኃላፊነትን ያካትታል።
እውነተኛ ደቀመዝሙርነት የክርስቶስን ፍጹም ጌትነት በደስታ መቀበልና በሕይወት መግለጥ ነው።

ታላቁ ተልዕኮ የስነ-መለኮታችን ተግባራዊ መግለጫ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅና እርሱን ለዓለም ማሳወቅ የሕይወታችን ዋና ግብ (Chief End) ነው።

“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9
16❤‍🔥2👍1🔥1🥰1
ሁሉ ከአንተ፣ ለአንተ፣ በአንተ፣ የአንተ ነውና!

ሁሉ ከአንተ ነው!
በዚህች ምድር ላይ የምናየውና የማይታየው፣ የሚጨበጠውና የማይጨበጠው ነገር ሁሉ ምንጩ አንተ ነህ። ከሰማያት ከዋክብት እስከ ምድር ጠብታ፣ ከሰው ልጅ እስትንፋስ እስከ ረቂቅ ፍጥረታት ሕልውና... ሁሉም የአንተ የፈጠራ ጥበብ ውጤቶች ናቸው። እኛ ራሳችን ካልነበርንበት ወደ መኖር የመጣነው በአንተ ፈቃድና ጥበብ ነውና የሕይወታችን፣ የዕውቀታችን፣ የጤናችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ፍጹም አንተ ብቻ ነህ።

ሁሉ በአንተ ነው!
መኖር ብቻውን በቂ አይደለም፤ መኖር የሚቀጥለው ግን በአንተ ደጋፊነትና መጋቢነት ነው። እያንዳንዱን ቀን የምንሻገረው፣ ፈተናዎችን የምናልፈው፣ በውስጣችን ያለውን ተስፋ የምናድሰው በአንተ ኃይል ነው። ያለ አንተ መሪነት መንገዳችን ጨለማ፣ ያለ አንተ አጋዥነት ጥረታችን ሁሉ ከንቱ ነው። በውድቀታችን ውስጥ የምናንሰራራው፣ በስኬታችንም ውስጥ የምንጸናው በአንተ በጎነትና እቅድ ብቻ ነው።

ሁሉ ለአንተ ነው!
የፍጥረት ሁሉ መኖር፣ የሰው ልጅም በዚህች ምድር ላይ መመላለስ ያለ ዓላማ አይደለም። የመኖራችን ትልቁ ግብ ለአንተ ክብር፣ የአንተን በጎነትና ውበት ለመግለጥ ነው። በአንተ ጸጋ የምናደርገው በጎ ነገር ሁሉ፣ የምናሳየው ፍቅርና የምንፈጥረው ሰላም መጨረሻው አንተን ማክበርና የአንተን ታላቅነት ማወጅ ነው። ሕይወታችን ትርጉም የሚያገኘው ፊታችንን ወደ አንተ አዙረን፣ የአንተን ፈቃድ ስንፈጽም ብቻ ነው።

ሁሉ የአንተ ነው!
እኛ በዚህ ምድር ላይ ባለቤት አይደለንም፤ መጋቢዎችና እንግዶች እንጂ። የምንይዘው፣ የምንገነባው፣ የምንመኘውና የምንሰበስበው ነገር ሁሉ ውሎ አድሮ ወደ አንተ ይመለሳል። የእኛ የምንለው ሕይወት እንኳ የአንተ ነው። ሁሉ የአንተ ስለሆነ በነገሮች ላይ አንጨነቅም፤ ምክንያቱም ዋናው ባለቤት አንተ ፍጹምና ታማኝ ነህና።

አምላክ ሆይ! የነገሮች ሁሉ መጀመሪያ (ከአንተ)፣ የሕይወታችን መተኪያ የሌለው መሪ (በአንተ)፣ የጥረታችንና የህልማችን መድረሻ (ለአንተ)፣ እንዲሁም የሁሉም ነገር እውነተኛ ባለቤት (የአንተ) መሆንህን አምነን እንቀበላለን። ይህ እውነት በልባችን ሲቀረጽ ፍርሃት ይወገዳል፣ እውነተኛ ሰላምና ነጻነትም በውስጣችን ይነግሳል።

​“ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
— ሮሜ 11፥36
16🔥2🥰1
ዕቅበተ እምነት (Apologetics) እንዲሁ ለክርክር መቅረብ ሳይሆን፤ የክርስቶስን ጌትነት በልብ በመቀደስ፣ ለሚያምኑበት ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቁ ሁሉ በየዋህነትና በፍርሃት መልስ መስጠት ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3:15)።

በዚህ ዘመን በዕቅበተ እምነት ላይ የምታገለግሉ ቅዱሳን፣ መሣሪያችሁ የእግዚአብሔር ቃል፣ መንገዳችሁ ትሕትናና ፍቅር፣ ግባቸው ደግሞ የሰዎችን አእምሮ ለክርስቶስ መማረክ ሊሆን ይገባል። እውነትን ያለ ፍቅር ማቅረብ ጭካኔ ነው፤ ፍቅርን ደግሞ ያለ እውነት ማቅረብ ስምምነት (Compromise) ነው። ሁለቱን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ለዘመኑ አገልጋይ ወሳኝ ነው።
20🥰5
የልብ ጩኸት እና የንስሐ ጸሎት🤲
(የአንድ ወደጄ ጸሎት)

​ጌታ ሆይ! ስለ አስመሳይነቴ፣ በኃጢአት ውስጥ እየኖርኩ አንተን ስላገለገልኩኝ፣ በሰዎች ጥላቻ ተከብቤ በመድረክህ ላይ ስለቆምኩኝ፣ ኃጢአትን ሳላቋርጥ ስለመሥራቴ፣ ደስታዬን ከአንተ ውጪ ስላደረግኩኝ፣ ትኩረቴን ከአንተ ላይ ስለነቀልኩኝና ተራ ነገሮችን ከአንተ ስላስቀደምኩኝ... ዛሬ በፊትህ እወድቃለሁ።

​ከዚህ በኋላ እንኳን አልበድልህም ብዬ፣ ልቤ በበረታበት ቀናት ሁሉ ቃል ገብቼልህ ነበር። ነገር ግን ያ ቃል ኪዳኔ ሁለት ቀናትን እንኳ ሳይሻገር፣ ሳምንታት ሳይሞላው፣ እንደገና ተመልሼ በዚያው በለመድኩት የድካም ማዕበል ውስጥ ተዘፍቄ ተገኘሁ። እሁድን በመድረክህ ላይ የቃልህን እውነትና ኃይል አገልግዬ፣ ሰኞ ሲተካ ግን ያው የድሮ ድካሜ አቅፎ ይቀበለኛል።

​አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? ብዬ ግራ ተጋብቻለሁ። መለወጤስ ለምን እንዲህ ዘገየ? ጌታ ሆይ፤ ጸጋህ ለእኔም ጭምር በቂ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን እኔ በጸጋህ ላይ መደገፍና ሥጋዬን ለቃልህ ማስገዛት ለምን አቃተኝ? በማለት በሐሳብ ማዕበል እየተናወጥኩኝ ነው፤ ልቤም በብዙ ቆስሏል። ውስጤና ውጪዬ፣ መድረኬና ህይወቴ አንድ እንዲሆንልኝ እለምንሃለሁ።

ነገር ግን ጌታ ሆይ፤ እባክህን ይቅር በለኝ!
​እንደ ጠፋው ልጅ ደግመህ በእቅፍህ ተቀበለኝ፤ ሕይወቴንና ማንነቴን የምታድስበትን የይቅርታ ዕድል ስጠኝ! እባክህን ወደ እኔ ተመልከት፤ ከአንተ ውጪ ምንም ተስፋ የለኝም። ከአንተ ውጪ የሚያስችለኝ፣ ከአንተ ውጪ የሚያድሰኝ፣ ከአንተ ውጪ ማንም የለኝም!
​ገበናዬን የሸፈንክልኝ አንተ ብቻ ነህ፤ ምስጢሬንና ውድቀቴን ሰዎች ቢሰሙ ኖሮ ምን እሆን ነበር? አንተ ግን በምሕረትህ ሸፈንከኝ እንጂ አላሳፈርከኝም።

ጌታ ሆይ፣ እባክህን ከዚህ የድካም አረንቋ አውጣኝ፤ የተሰበረውንና የቆሰለውን ልቤንም ጠግንልኝ!
🙏22😭115😢2
እውነተኛ ጸሎት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚደረግ፣ በእርሱ ታማኝነት ላይ በፍጹም እምነት የሚመሠረት፣ እኛን ከራሳችን ጠባብ ሐሳብ አውጥቶ ወደ ሰፊው የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚያመጣ፣ በፍቅር የተጋመደ ልዩ ቁርኝት ነው። በዚህ የልጅነት መንፈስ ወደ አባታችን እንቅረብ!
❤‍🔥32👌53🔥3
ጸጋ፤ በራሳችን መቆም ለማንችል ለወደቅን ኃጢአተኞች፣ ምንም ሳይገባን በክርስቶስ ኢየሱስ በነጻ የተሰጠን መለኮታዊ ሞገስ፣ ይቅርታና በቅድስና እንድንኖር የሚያስችለን መለኮታዊ ኃይላችን ነው።
30🔥8🥰2👏2
የጸጋው ዋጋ፡ ርካሽ ጸጋ እና ውድ ጸጋ

በዘመናችን በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ ቀውስ እየታየ ነው። እምነት አለ፣ ስብከት አለ፣ የአምልኮ ፕሮግራሞች በየቀኑ ይካሄዳሉ፤ ነገር ግን በሰዎች ሕይወት ላይ የሚታየው መንፈሳዊ ለውጥና የቅድስና ኃይል እጅግ አናሳ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ​ታዋቂው የስነ-መለኮት ምሁር Dietrich Bonhoeffer ለዚህ ጥያቄ ሲመልስ፦ "የቤተክርስቲያን ትልቁ ጠላት 'ርካሽ ጸጋ' ነው" ይላል።

ርካሽ ጸጋ ማለት የእግዚአብሔርን ይቅርታና ፍቅር መሸጫ ሸቀጥ ማድረግ ማለት ነው። ንስሐ ሳይገቡ፣ ሕይወትን ሳይለውጡና ለኃጢአት ሳይሞቱ በጸጋ ድነናል እያሉ በድፍረት በኃጢአት መኖር ነው።

Bonhoeffer​ ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፦
​"ርካሽ ጸጋ ንስሐ የሌለበትን ምሕረት፣ ቤተክርስቲያናዊ ተግሣጽ የሌለባትን ጥምቀት፣ ኅብረት የሌለበትን ቅዱስ ቁርባን (ማዕድ)፣ እና መስቀል የሌለበትን፣ ሕያውና ሥጋ የለበሰውን ክርስቶስን መስበክ ነው።"
👉 ርካሽ ጸጋ ሰውን ደቀ-መዝሙር ሳያደርግ ስማ ክርስቲያን ለማድረግ ይሞክራል።
👉 እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚጠላና እንደሚፈርድ ይዘነጋል።
👉እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ ዝም ብሎ ይምረኛል በሚል ስንፍና ሰውን ያደነዝዛል።

​በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው እውነተኛው ጸጋ ግን "ውድ ጸጋ" ነው። ይህ ጸጋ በነፃ የተሰጠ ቢሆንም፣ በዋጋ ደረጃ ግን እጅግ ውድ ነው። ለአብ አንድያ ልጁን ያስከፈለ፣ ለወልድ ደግሞ ሕይወቱንና የመስቀል ላይ ሞትን የጠየቀ ስለሆነ ነው። ለእኛም ቢሆን ውድ ነው፤ ምክንያቱም ሕይወታችንን ሙሉ ለእግዚአብሔር ጌትነት እንድንሰጥና በደቀ-መዝሙርነት እንድንመላለስ በውስጣችን ይሠራል።
​ ይህንን ዋጋ እኛ መክፈል ስለማንችል ክርስቶስ ስለ እኛ ከፍሎታል። እኛም ስንቀበለው እውነተኛ ሕይወትን ስለሚሰጠን ነው።
እውነተኛ ጸጋ ሰውን ዝም ብሎ አይተወውም፤ ይለውጠዋል። ኃጢአትን እንዲጠላ፣ እግዚአብሔርን ደግሞ እንዲወድ ያደርገዋል።

​ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ወደ ራሱ ሲጠራ፤ የጥሪውን ምንነት በግልጽ አስቀምጧል፦​"ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።" (ማቴዎስ 16፥24)

​ዛሬ በየማኅበራዊ ሚዲያውና በየመድረኩ የሚሰበከው ስብከት እኛን ደስ የሚያሰኝ፣ ሥጋችንን የሚያባብልና ያለንበትን የኃጢአት ሕይወት የሚያጸድቅልን (ርካሽ ጸጋ) ነው? ወይንስ ለኃጢአታችን እንድንሰበር፣ መስቀላችንን እንድንሸከምና ክርስቶስን እንድንመስል የሚያደርገን (ውድ ጸጋ) ነው?

በነጻ በጸጋው ድነናል፤ አሁን ደግሞ የጸጋው ኃይል በቅድስና ሕይወታችን ይገለጥ!

@christcentered7
30🥰3👏2
በክርስትና ሕይወት ውስጥ በራስ ጥረት የሚመጣ የባህሪ ማሻሻል (Self-improvement) የሚባል ነገር የለም፤ ለሥጋ ምኞት መሞት እንጂ። አሮጌው ማንነታችን በትምህርትና በልምምድ የሚስተካከል ሳይሆን፣ በክርስቶስ መስቀል ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተፈረደበትና የሞተ ማንነት ነው። ክርስቶስ ሊያድነን የመጣው የቆሸሸውን አሮጌ ሕይወታችንን አጥቦ ሊያሳምርልን ሳይሆን፣ እርሱ በሞተበት ሞት ውስጥ እኛንም አብሮ ቀብሮ፣ በአዲሱ የትንሣኤው ሕይወት ፍጹም አዲስ ፍጡር ሊያደርገን ነው። እኛም በየዕለቱ ይህንን አዲስ ማንነት እየለበስን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንለወጣለን።
❤‍🔥269👏4🔥2🙏2
ቤተክርስቲያን የምንሄደው እግዚአብሔርን ለመጥቀም ወይም በሰዎች ዘንድ ጥሩ ሰው ለመባል ሳይሆን፣ እኛ ራሳችን መንፈሳዊ ሕክምናና ዕድሳት ስለሚያስፈልገን ነው። ቤተክርስቲያን የፍጹማን ቅዱሳን ማሳያ ሙዚየም ሳትሆን፣ በክርስቶስ ጸጋ የሚፈወሱ የኃጢአተኞችና የደካሞች ሕክምና ሆስፒታል ናት።

​ስለዚህ ስንሄድ በልማድ ሳይሆን፣ ከፈጣሪዬ ጋር ለመገናኘት፣ ከቅዱሳን (ከአማኞች) ማኅበር ጋር ለመኅበር፣ ነፍሴ በክርስቶስ ቃልና መንፈስ እንድትታደስ፣ እኔም በጸጋዬ ሌላውን ለማነጽ በሚል ንቁ መንፈሳዊ ዝግጅት ይሁን። ይህ የመሰብሰብ መደበኛነት ለእግዚአብሔር ቤት ያለንን የልብ ጥማትና የታማኝነት መገለጫ ነው።

ዛሬ እሁድ ነውና ጉዞ ወደ አማኞች ኅብረት! 🚶‍♀‍➡️🚶‍➡️
37🔥4👌4🙏3
የሰዎች ትከሻ ይዝላል፣ የራሴም ጉልበት ይደክማል፤ የእግዚአብሔር ታማኝነት ግን ሁልጊዜ ብርታቴ ነው።
28🥰12🙏8
እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ለመቀጠል የሰውን ልጅ ይሁንታ ወይም ድምፅ አይፈልግም። ሰው ባያመልከው እንኳ እርሱ ያው ዘላለማዊ ንጉሥ ነው። እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ሰውን ሲፈጥር ለመመካከር ሳይሆን ክብሩን ለመግለጥ ነው፤ የሰው ልጅ ምርጫ፣ ፈቃድና ፍላጎት ሁሉ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ቁጥጥር ስር በመሆኑ፣ የእርሱን ዘላለማዊ ዕቅድ ሊያደናቅፍ አይችልም፤ ታሪክን የሚጠቀልለው በገዛ ሉዓላዊ ሥልጣኑ ነው። እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ ሁሉ፣ ኃጢአትንና እምቢተኝነትን በጽድቅ ፍርዱ የሚቀጣ የሚበላ እሳትም ጭምር ነው።
23👌5❤‍🔥3👏1🙏1
የሰው ልጅ ትልቁ ኃጢአት በክፉ ሥራው ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት በሚያቀርበው የራስ ጽድቅ ውስጥም ጭምር ነው። ያለ ክርስቶስ ደምና ያለ እምነት፣ ለመጽደቅ በሚደረግ ሃይማኖታዊ ትጋት የሚቀርብ ማንኛውም ምጽዋትና ጸሎት በቅዱሱ አምላክ ፊት እንደ ረከሰ ጨርቅ ነው። ሰብአዊ ጽድቅ ሰውን ከመለኮት ቁጣ ሊሸፍን የማይችል የተበሳ ጃንጥላ ነው፤ እግዚአብሔርን በሥራችን ልንደልለው መሞከር ራሱ የኩራት ሁሉ አክሊልና ሌላው የኃጢአት መልክ ነው።

​ስለዚህ ንስሐ የሚያስፈልገው ለግልጽ ክፉ ሥራችን ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን ለመደለል በሞከርንበት በዚያ በራስ-ተኮሩ መልካም ሥራችንም ጭምር ነው። እውነተኛና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው መልካም ሥራ የሚጀምረው፣ በክርስቶስ የማዳን ሥራ አምነን ከጸደቅን በኋላ፣ እርሱን ለማስደሰትና ለመታዘዝ በቅዱስ መንፈስ የምናፈራው የእምነት ፍሬ ሲሆን ብቻ ነው።
❤‍🔥114🔥2🥰1🙏1👌1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአንድ አገልጋይ እውነተኝነት የሚመዘነው ከገንዘብ ጋር በላው relationship ነው!

👉ዝና ላይ ያለን አቋም ምንድር ነው?
👉ገንዘብ ላይ ያለን motivation ምን ያህል በእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው?
👉ታዋቂነት ላይ ያን ልብ ምን ይመስላል?

“የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚሸቃቅጡት እንደ ብዙዎቹ አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።”
  — 2ኛ ቆሮ 2፥17


#ሳሚ_ቱራ
24👍2👏1
እውነተኛው ወንጌል ለዓለም ፍልስፍና ሞኝነት፣ ለሃይማኖተኞች ደግሞ ዕንቅፋት ነው። ዓለም ኃያልና በራሱ የሚተማመን አምላክን ትፈልጋለች፤ የመስቀሉ ሥነ-መለኮት ግን በመስቀል ላይ የተራቆተውን፣ የተተፋበትንና የተሰቀለውን ክርስቶስን ያሳያል። እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ያዋረደው በወታደራዊ ኃይል ሳይሆን፣ በዓለም ፊት ድክመትና ሞኝነት በሆነው በመስቀሉ ምስጢር ውስጥ ነው። ይህንን መለኮታዊ ምስጢር ለመቀበል ደግሞ በእግዚአብሔር ጸጋ ፊት ራስን ሙሉ በሙሉ መስበር የግድ ይላል።
19🔥10🙏4
“...የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው።”
  — ነሀምያ 8፥10
26
ክርስቶስ "ሊከተለኝ የሚወድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" ሲል፣ መስቀል ለእኛ በውጭ የሚታይ በወርቅ ተሰርቶ አንገት ላይ የሚታሰር ተራ የጌጥ ምልክት ሳይሆን፣ ተፈርዶብን የምንሞትበት የማስገደያ መሣሪያ ነበር። ክርስቶስን መከተል ማለት የራስን ፈቃድና ምኞት በእግዚአብሔር ጸጋና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አሳልፎ ለሞት መስጠት ማለት ነው። የድሮውን ማንነታችንን ለመቅበርና ለራሳችን ፈቃድ ለመሞት ራሳችንን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ስናስገዛ፣ የትንሣኤው ኃይል በሕይወታችን ውስጥ በክብር መሥራት ይጀምራል።
20🥰6
የእምነት ጉዞ

​ብዙዎቻችን ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እና እግዚአብሔርን በግል ሕይወት ማግኘት አንድ ይመስሉናል። ነገር ግን በሁለቱ መካከል የባሕርይ ልዩነት አለ።

👉ስለ እግዚአብሔር ማወቅ (Knowledge)፦ ይህ ደረጃ አእምሯዊ ነው። መጻሕፍትን ማንበብ፣ ታሪኮችን ማጥናት፣ ዶክትሪኖችን በቃል መያዝ እና በሃይማኖታዊ ክርክሮች ላይ ማሸነፍ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ እውቀት ወደ ልብ ካልወረደ የሃይማኖት "ሳይንስ" ወይም "ፍልስፍና" ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል።
👉እግዚአብሔርን ማግኘትና መለማመድ (Intimacy)፦ ይህ ደግሞ የልብና የሕይወት እውነተኛ ልምምድ ነው። መለኮታዊውን ፍቅር በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ በተግባር መለማመድ፣ በፈተናዎች መካከል የእርሱን እረኝነት ማየት እና ፈቃዱን በሕይወት መተርጎም ነው።

ስለዚህ፤ ​የእምነት እውነተኛው ውበትና ማራኪነት የሚገለጠው መረጃዎችን በማከማቸት ብቻ ሳይሆን፣ ያንን እውቀት ወደ ሕያው ግንኙነትና የሕይወት ለውጥ ማሸጋገር ሲቻል ብቻ ነው። ጉዟችን ከመጽሐፍት ገጾችና ከጭንቅላት እውቀት አልፎ ወደ ልባችን ጥልቀት የሚዘልቅ ይሁን!
❤‍🔥1710🔥3
የክርስትና ሕይወት ጉዞ ከሲኦል ፍርሃት ያወጣናል። የጸጋው ጥልቀት ግን ከዚያ በላይ ይወስደናል፤ ኃጢአትን ራሱን እንድንጸየፈው ያስተምረናል። ስለዚህ ኃጢአትን የምንሸሸው እኛን ወደ ሲኦል እንዳይወስድ በመፍራት ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ሰማይ የወሰደንን አምላክ ልብ ስለሚሰብር ነው። ያኔ ኃጢአት የቅጣት ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ የአምላክ እንባ ምክንያት መሆኑን እንረዳለን። የበሰለ ልብ የሲኦልን እሳት ሳይሆን፣ የመስቀሉን ፍቅር እያሰበ ኃጢአትን ይጠላል።
🥰146🔥6❤‍🔥1🙏1