ጌታ ሆይ፤
አንዳንዴ በህይወት ጉዞዬ እጅግ ዝዬና ደክሜ፣ በድካሜ ውስጥ ተስገብግቤ፣ ስንፍናዬ ስንፍናን እየወለደ፣ እኔው ራሴ ወድቄ ሌሎች እንዲወድቁ ምክንያት ስሆን እገኛለሁ። ማበርታት ባልችል እንኳ፣ የበረታውንና በብርታት የቆመውን ወንድሜን በሚያቆስልና በሚያደክም ከንቱ ቃላት እንዳልሰብርህ እለምንሃለሁ።
ለስንፍናዬ፣ ለውድቀቴና ለሃጢአቴ ምክንያት እየደረደርኩ፣ የራሴን ስህተት ልክ ለማስመስልና ራሴን ለማጽደቅ ከምሮጥበት የልብ ጥማት አድነኝ። ጥፋቴን በምክንያት መሸፈን፣ ውድቀቴን ይበልጥ ማግዘፍ እንደሆነ አውቃለሁ።
ስለዚህ አሁን የከንቱነትን ካባ ጥዬ፣ ድካሜን ሳልሸሽግ፣ በፍጥነትና በልብ ሙሉነት ወደ ጸጋህ ዙፋን በደፍረት እቀርባለሁ። ሃጢአቴን፣ ስብራቴንና ውድቀቴን ሁሉ በፊህ ይዤ እገባለሁ፤ በማንም ፊት ሳይሆን በአንተ ፊት እበረከካለሁ፣ እቀርባለሁ፣ እወድቃለሁ።
አንተ በደሌን የምትደመስስ፣ በጸጋህ የምታድስ፣ በምህረትህም የምታቆም አምላክ ነህና ተቀበለኝ። ከውድቀቴ አንሳኝ፣ ከስንፍናዬ አላቀቀኝ፤ መንፈሴን አድስልኝ።
አሜን🙏🙌

🙏24❤13😢6
ቤተክርስቲያን የሕንጻ ስብስብ ሳትሆን፣ በክርስቶስ ደም የተዋጁ አማኞች የሚገናኙባት፣ የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን ለመሆን የምንታጠቅባት የሕያው እግዚአብሔር ማኅበር ናት።
ወደ ቅዱሳን ኅብረት መግባት ማለት ከዕለት ተዕለት የዓለም ጫጫታ ወጥቶ፣ በጌታ እራትና በአንድነት ጸሎት ከወንድሞች ጋር መታነጽ፣ የጌታንም ፍቅር ማክበር ማለት ነው። እውነተኛ ሥነ-መለኮት የሚኖረው በጉልበት መበርከክና ቃሉን በመታዘዝ ውስጥ ነው።
ቤተክርስቲያን የኃጥአን ሆስፒታል እንጂ የጻድቃን ሙዚየም አይደለችም። በጸጋው ለመታደስና በፍቅሩ ለመገንባት ዛሬም ወደ ቅዱሳኑ ኅብረት እንገሰግሳለን።
(ዕብራውያን 10፥ 24-25)
"ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።"
ከአማኞች ጋር በአንድነት ጌታን ማምለክ፤ የሳምንቱ ምርጥ ሰዓት፣ የነፍሳችን ታላቅ ደስታ ነው።
ዛሬ እሁድ ነውና ጉዞ ወደ አማኞች ኅብረት! 🚶♀➡️🚶➡️

❤28🥰3🔥2
Christ-centered
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 4 9. የዓለም ወቃሽ ነው። "እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል።" (ዮሐንስ 16:8) አንድ ሰው ጌታን ሳይቀበል በፊት ኃጢአቱን አይቶ እንዲጸጸትና ንስሐ እንዲገባ የሚያደርገው ማን ነው? የሰዎች ንግግር ወይም የሕግ ጫና ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ውግዘት (Conviction) ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ ዓለም የመጣው ሰዎችን…
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 5
12. የድካማችን ደጋፊና አማላጅ ነው።
“እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”( ሮሜ 8፥26)
አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በጣም ከባድ የጭንቅና የፈተና ጊዜያት ይመጣሉ። በዚያ ሰዓት አእምሯችን ይዝላል፣ የምንናገረው ቃል ይጠፋናል፣ ሌላው ቀርቶ "እንዴት ብዬ ልጸልይ?" ብለን የምንይዘው የምንጨብጠው እስኪጠፋን ድረስ እንሰበራለን።
በዚህ የድካም አቅጣጫችን ላይ መንፈስ ቅዱስ አጠገባችን ይቆማል። እኛ መናገር ያቃተንን፣ በልባችን ውስጥ የታመቀውን ጥልቅ ስብራትና ፍላጎት እርሱ በማይነገር መቃተት ወደ አብ ያደርሳል። ድካማችንን ተሸክሞ ይጸልይልናል፤ በጸሎትም ውስጥ እንድንበረታ መለኮታዊ ኃይልን ይሰጠናል። እኛ ስንደክም እርሱ አይደክምም።
John Calvin👇
"እኛ በተፈጥሯችን በጸሎት ረገድ እጅግ ደካሞችና ዓይነ ስውራን ነን፤ ምን መጸለይ እንዳለብን እንኳ አናውቅም። መንፈስ ቅዱስ ግን እንደ መሪና መምህር ሆኖ ወደ እኛ ይመጣል። እርሱ ትክክለኛውን የጸሎት ምኞት በልባችን ውስጥ ይዘራል፣ የልባችንን በር ይከፍታል፣ መናገር ያቃተንን ምስጢር ደግሞ በቅዱስ አቀራረብ ወደ እግዚአብሔር ያደርሰዋል። እርሱ የጸሎታችን ሞተር ነው"
13. ታላቁ አጽናኝ ነው።
“እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”( ዮሐንስ 14፥15)
በዚህ ምድር ላይ ስንኖር ሐዘን፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ፍርሃትና ጭንቀት ሊገጥሙን ይችላሉ። የሰዎች ማጽናናት አንዳንድ ጊዜ ላዩን ብቻ የሚነካና ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል፤ ልባችንን ግን ሙሉ በሙሉ ሊፈውሰው አይችልም።
ጌታ ኢየሱስ ግን እንደዛ አላደረገንም፤ "ሌላ አጽናኝ" (Paraclete) ሰጠን። መንፈስ ቅዱስ ወደ ተሰበረው ልባችን ዘልቆ በመግባት ማንም ሊሰጠን የማይችለውን ሰማያዊ ሰላምና መረጋጋት ይሰጠናል። በነገው ሕይወታችን ላይ ያለንን ፍርሃት አስወግዶ፣ ልባችን ከተጨነቀበት ሐዘን ፈጽሞ ያሳርፈዋል።
Charles Spurgeon👇
"የሰዎች ማጽናናት አንዳንድ ጊዜ ቁስላችንን ይጫረው ይሆናል፤ የመንፈስ ቅዱስ ማጽናናት ግን መለኮታዊ ቅባት ነው። እርሱ ወደ ተሰበረውና ወደ ታመመው የልባችን ክፍል ዘልቆ በመግባት ሰማያዊ ሰላምን ያፈስበታል። ዓለም ሁሉ ቢተወንና በሐዘን ብንዋጥ እንኳ፣ ታላቁ አጽናኝ አጠገባችን ሲቆም ፍርሃታችን ሁሉ ተረት ሆኖ ይበናል።"
ይቀጥላል....
@christcentered7

❤20
(መዝሙር 77፥6-10)
"በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት።
“ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን?
ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?
ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን?
የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን?
እግዚአብሔር ቸርነቱን ዘነጋ? ወይስ
ከቍጣው የተነሣ ርኅራኄውን ነፈገ?” ሴላ
እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።

❤23🥰9🙏4❤🔥3
የሰው ሐሳብና ፍልስፍና እንደ ዘመኑ ፋሽን ያልፋል፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ትውልድን አሻግሮ ይቆማል። ቃሉ በጨለማ ለሚጓዝ እግር መብራት፣ ግራ ለገባው ልብ ደግሞ ፍጹም ሰላምንና መመሪያን የሚሰጥ መለኮታዊ ኮምፓስ ነው።
❤🔥37❤2👏2🙏2
Audio
በደሙ አንፅቶሽ በቃሉ ቀድሶሽ
አሸናፊው ጌታ በሞቱ የገዛሽ
ክብርት እና ቅድስት ያለነውር ሆነሽ
የሙሽራሽን ቀን ለማየት የናፈቅሽ
ደስ ይበልሽ አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን
የጠላትን ግፊያ ችለሽ ብዙ ዘመን
አምናሽ ቆይተሻል እንደቃልኪዳንሽ
ቀኑ በደጅ ነው የአስደናቂው ሰርግሽ
ሙሽራሽ የዋህ ነው ተንኮል የሌለበት
ፍፁም እና ታማኝ ጉድለት ያልታየበት
ሙሽራሽ እየሱስ የሰላም አለቃ
አንዳንችም አይጎለው ለሁሉም ሚበቃ
የሀሰት ተቃራኒ የእውነት አምድ ነሽ
በእሳት የነጠሩ ፃድቃን የሞሉብሽ
የፅድቅሽ ስራ ነው የተልባ እግር ልብስሽ
ተጎናፅፈሽ ቆይው ጌታን ተሰናድተሽ
የፊት መጨማደድ ከቶ ማይታይብሽ
የህይወት ሽታ ያለሽ እድፈት የሌለብሽ
ሞትን የተጫማሽ ኗሪ ለዘለአለም
አንቺ የሄድሽ እለት ወዮ ለዚች አለም
ኧራ ይሄንን ድንቅ መዝሙር ስሙት
@christcentered7
አሸናፊው ጌታ በሞቱ የገዛሽ
ክብርት እና ቅድስት ያለነውር ሆነሽ
የሙሽራሽን ቀን ለማየት የናፈቅሽ
ደስ ይበልሽ አንቺ ቅድስት ቤተክርስቲያን
የጠላትን ግፊያ ችለሽ ብዙ ዘመን
አምናሽ ቆይተሻል እንደቃልኪዳንሽ
ቀኑ በደጅ ነው የአስደናቂው ሰርግሽ
ሙሽራሽ የዋህ ነው ተንኮል የሌለበት
ፍፁም እና ታማኝ ጉድለት ያልታየበት
ሙሽራሽ እየሱስ የሰላም አለቃ
አንዳንችም አይጎለው ለሁሉም ሚበቃ
የሀሰት ተቃራኒ የእውነት አምድ ነሽ
በእሳት የነጠሩ ፃድቃን የሞሉብሽ
የፅድቅሽ ስራ ነው የተልባ እግር ልብስሽ
ተጎናፅፈሽ ቆይው ጌታን ተሰናድተሽ
የፊት መጨማደድ ከቶ ማይታይብሽ
የህይወት ሽታ ያለሽ እድፈት የሌለብሽ
ሞትን የተጫማሽ ኗሪ ለዘለአለም
አንቺ የሄድሽ እለት ወዮ ለዚች አለም
ኧራ ይሄንን ድንቅ መዝሙር ስሙት
@christcentered7
❤🔥15❤3👏3👍2🙏1
ወንጌልን ከዘመኑ ፍልስፍናና ስሜት ጋር ለማስማማት መሞከር፣ ወንጌሉን ማዳን ሳይሆን ኃይሉን ማክሰም ነው። ወንጌል ዓለምን ሊሞግትና ሊለውጥ የመጣ መለኮታዊ እውነት እንጂ፣ ከዓለም ጫጫታና ፋሽን ጋር እኩል ለመራመድ የሚታጠፍ ሰብአዊ ድርሰት አይደለም። William Ralph Inge እንደምለው "ከዘመኑ ጋር ያገባች ቤተክርስቲያን፣ በሚቀጥለው ዘመን መበለታ ሆና ትቀራለች።"
ቤተክርስቲያን ለዘመኑ ሰዎች መልእክቱን የምታደርስበት ቋንቋና መንገድ ዘመኑን የዋጀ (Contextualized) ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የምታደርሰው እውነት ግን መለኮታዊና ፍጹም የማይለወጥ (Absolute) ነው። ዓለም ወደ ቤተክርስቲያን መጥታ መለወጥ እንጂ፣ ቤተክርስቲያን ወደ ዓለም ሄዳ መልክዋን ማጣት የለባትም።
“እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።”
— ቆላስይስ 2፥8
ይህንን ጥልቅ ማሳሰቢያ ለትውልድ ማስተማርና ማስታወስ የሁላችንም ጥሪ ነው!

❤14🔥4❤🔥3👏3
Christ-centered
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 5 12. የድካማችን ደጋፊና አማላጅ ነው። “እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”( ሮሜ 8፥26) አንዳንዴ በሕይወታችን ውስጥ በጣም ከባድ የጭንቅና የፈተና ጊዜያት ይመጣሉ። በዚያ ሰዓት አእምሯችን ይዝላል፣ የምንናገረው ቃል ይጠፋናል፣ ሌላው ቀርቶ "እንዴት…
የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች — ክፍል 6(የመጨረሻው ክፍል)
14. ታማኝ መሪ ነው።
“ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”
— ኢሳይያስ 30፥21
ሕይወት በብዙ ምርጫዎችና ውሳኔዎች የተሞላች ናት። የትኛውን መንገድ ልሂድ? ምን ዓይነት ውሳኔ ልወሰን? ብለን ግራ የምንጋባባቸው ብዙ ቀናት አሉ።
በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው (ሮሜ 8:14)። መንፈስ ቅዱስ በጉዟችን ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድናውቅ ትክክለኛውን መንገድ ይመራናል። በልባችን ውስጥ ረቂቅ ድምፅ በመሆን፣ በቃሉ በኩል ብርሃን በመፈንጠቅና በሁኔታዎች ውስጥ መለኮታዊ ምልክት በመስጠት ከመሳሳትና ከጥፋት መንገድ ይታደገናል።
John Calvin👇
"የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን የሚታወቀው በመንፈስ ቅዱስ መመራታችን ነው። እርሱ በሕይወታችን ውስጥ ዓይነ ስውራን እንዳንሆን በቃሉ ብርሃንነት ይመራናል። የመንፈስ ቅዱስ አመራር መለኮታዊ ኮምፓሳችን ነው፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እንዳናዘነብል የክርስቶስን ፈቃድ በልባችን እያበራ ወደ እውነት መንገድ በትዕግሥት ይመራናል።"
15. በመከራ ውስጥ የጽናት ብርታት ነው።
"በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።" (ሮሜ 5:5)
ክርስቲያናዊ ጉዞ ሁልጊዜ አልጋ በአልጋ አይደለም፤ መከራና ፈተናዎች አሉት። በእነዚህ አስቸጋሪ ወቅቶች ውስጥ እምነታችን እንዳይደክም፣ ተስፋ ቆርጠን ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ የሚያደርገን ምንድን ነው?
ምስጢሩ መንፈስ ቅዱስ ነው። በመከራና በፈተና ውስጥ ስንሆን፥ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ዘላለማዊና የማይለወጥ ፍቅር በልባችን ውስጥ አፍስሶ ያረሰርሰናል። "እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው" የሚለውን እውነት እያስታወሰን፣ በውስጣችን ሰማያዊ ጽናትንና ብርታትን ይተክላል። በአውሎ ነፋስ መካከልም እንኳ ቆመን እንድንዘምር የሚያደርገን እርሱ ነው።
John Flavel👇
"እግዚአብሔር አማኞችን ከመከራ ማዕበል ሙሉ በሙሉ አይጠብቃቸውም፤ ነገር ግን በማዕበሉ ውስጥ እንዳይሰምጡ በመንፈሱ ያጸናቸዋል። መንፈስ ቅዱስ በመከራ ውስጥ የጽናታችን መልሕቅ ነው። በዙሪያችን ያለው ነገር ሁሉ ሲናወጥ፣ እርሱ ግን በነፍሳችን ውስጥ የማይናወጥ የሰማይ ሰላም ያኖራል።"

❤12🔥2🙏1
የእግዚአብሔር ጸጋ ሙሉ ሕይወታችንን ለክርስቶስ እንድንሰጥ ይጠይቃል(ያበቃናል) ስንል፤ ሕይወታችንን ሰጥተን ጸጋውን እንገዛዋለን እያልን ሳይሆን፤ በነጻ የተሰጠን እውነተኛ ጸጋ በሕይወታችን ላይ ያለውን ፍጹም የክርስቶስን ጌትነት (Lordship of Christ) በእምነትና በታዛዥነት እንድንቀበል በውስጣችን በኃይል ይሠራል እያልን ነው።
❤🔥16🙏6🥰4❤2🔥1
Missio Dei (የእግዚአብሔር ተልዕኮ)
ታላቁ ተልዕኮ የቤተክርስቲያን ፈጠራ ሳይሆን የ Missio Dei (የእግዚአብሔር ተልዕኮ) ነጸብራቅ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ላኪ አምላክ ነው፤ አብ ወልድን ላከ፣ አብና ወልድ መንፈስ ቅዱስን ላኩ፣ አሁን ደግሞ ሥላሴ ቤተክርስቲያንን ወደ ዓለም ይልካታል።
እኛ በተልዕኮው ውስጥ ስንሰማራ፣ እግዚአብሔር ዓለምን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ በሚያደርገው መለኮታዊ ሥራ ውስጥ አብረን እየሠራን (የእግዚአብሔር አብሮ ሠራተኞች) ነን። እኛ የተልዕኮው ባለቤቶች ሳንሆን፣ የባለቤቱ ታማኝ ባለአደራዎች ነን። (ማቴ 28:19)
የታላቁ ተልዕኮ መሠረት የክርስቶስ ፍጹም ጌትነት (Lordship of Christ) እና በአጽናፈ ዓለም ላይ ያለው ፍጹም ሥልጣን ነው። እኛ የምንሄደው በራሳችን ብቃት ሳይሆን፣ በትንሣኤው ሥልጣንና በተሰጠን (በወረደው) በመንፈስ ቅዱስ ኃይል (የሐዋ 1:8) ነው።
ወንጌልን ማወጅ የክርስቶስን ሕጋዊና መለኮታዊ ንግሥና በስፍራው ሁሉ ማወጅ ነው።
ቤተክርስቲያን የተጠራችው ለራሷ እንድትኖር ሳይሆን፣ ለዓለም ምስክር እንድትሆን ነው። የታላቁ ተልዕኮ ዋና ማዕከል "ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" የሚለው ትእዛዝ ነው። ይህ ደግሞ ሰዎች በወንጌል አምነው እንዲድኑ ከማወጅ ባለፈ፣ በክርስቶስ እውነትና ጸጋ ውስጥ እንዲያድጉ የማድረግ ስነ-መለኮታዊ ኃላፊነትን ያካትታል።
እውነተኛ ደቀመዝሙርነት የክርስቶስን ፍጹም ጌትነት በደስታ መቀበልና በሕይወት መግለጥ ነው።
ታላቁ ተልዕኮ የስነ-መለኮታችን ተግባራዊ መግለጫ ነው። እግዚአብሔርን ማወቅና እርሱን ለዓለም ማሳወቅ የሕይወታችን ዋና ግብ (Chief End) ነው።
“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9

❤16❤🔥2👍1🔥1🥰1
ሁሉ ከአንተ፣ ለአንተ፣ በአንተ፣ የአንተ ነውና!
ሁሉ ከአንተ ነው!
በዚህች ምድር ላይ የምናየውና የማይታየው፣ የሚጨበጠውና የማይጨበጠው ነገር ሁሉ ምንጩ አንተ ነህ። ከሰማያት ከዋክብት እስከ ምድር ጠብታ፣ ከሰው ልጅ እስትንፋስ እስከ ረቂቅ ፍጥረታት ሕልውና... ሁሉም የአንተ የፈጠራ ጥበብ ውጤቶች ናቸው። እኛ ራሳችን ካልነበርንበት ወደ መኖር የመጣነው በአንተ ፈቃድና ጥበብ ነውና የሕይወታችን፣ የዕውቀታችን፣ የጤናችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ፍጹም አንተ ብቻ ነህ።
ሁሉ በአንተ ነው!
መኖር ብቻውን በቂ አይደለም፤ መኖር የሚቀጥለው ግን በአንተ ደጋፊነትና መጋቢነት ነው። እያንዳንዱን ቀን የምንሻገረው፣ ፈተናዎችን የምናልፈው፣ በውስጣችን ያለውን ተስፋ የምናድሰው በአንተ ኃይል ነው። ያለ አንተ መሪነት መንገዳችን ጨለማ፣ ያለ አንተ አጋዥነት ጥረታችን ሁሉ ከንቱ ነው። በውድቀታችን ውስጥ የምናንሰራራው፣ በስኬታችንም ውስጥ የምንጸናው በአንተ በጎነትና እቅድ ብቻ ነው።
ሁሉ ለአንተ ነው!
የፍጥረት ሁሉ መኖር፣ የሰው ልጅም በዚህች ምድር ላይ መመላለስ ያለ ዓላማ አይደለም። የመኖራችን ትልቁ ግብ ለአንተ ክብር፣ የአንተን በጎነትና ውበት ለመግለጥ ነው። በአንተ ጸጋ የምናደርገው በጎ ነገር ሁሉ፣ የምናሳየው ፍቅርና የምንፈጥረው ሰላም መጨረሻው አንተን ማክበርና የአንተን ታላቅነት ማወጅ ነው። ሕይወታችን ትርጉም የሚያገኘው ፊታችንን ወደ አንተ አዙረን፣ የአንተን ፈቃድ ስንፈጽም ብቻ ነው።
ሁሉ የአንተ ነው!
እኛ በዚህ ምድር ላይ ባለቤት አይደለንም፤ መጋቢዎችና እንግዶች እንጂ። የምንይዘው፣ የምንገነባው፣ የምንመኘውና የምንሰበስበው ነገር ሁሉ ውሎ አድሮ ወደ አንተ ይመለሳል። የእኛ የምንለው ሕይወት እንኳ የአንተ ነው። ሁሉ የአንተ ስለሆነ በነገሮች ላይ አንጨነቅም፤ ምክንያቱም ዋናው ባለቤት አንተ ፍጹምና ታማኝ ነህና።
አምላክ ሆይ! የነገሮች ሁሉ መጀመሪያ (ከአንተ)፣ የሕይወታችን መተኪያ የሌለው መሪ (በአንተ)፣ የጥረታችንና የህልማችን መድረሻ (ለአንተ)፣ እንዲሁም የሁሉም ነገር እውነተኛ ባለቤት (የአንተ) መሆንህን አምነን እንቀበላለን። ይህ እውነት በልባችን ሲቀረጽ ፍርሃት ይወገዳል፣ እውነተኛ ሰላምና ነጻነትም በውስጣችን ይነግሳል።
“ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
— ሮሜ 11፥36

❤16🔥2🥰1
ዕቅበተ እምነት (Apologetics) እንዲሁ ለክርክር መቅረብ ሳይሆን፤ የክርስቶስን ጌትነት በልብ በመቀደስ፣ ለሚያምኑበት ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቁ ሁሉ በየዋህነትና በፍርሃት መልስ መስጠት ነው (1ኛ ጴጥሮስ 3:15)።
በዚህ ዘመን በዕቅበተ እምነት ላይ የምታገለግሉ ቅዱሳን፣ መሣሪያችሁ የእግዚአብሔር ቃል፣ መንገዳችሁ ትሕትናና ፍቅር፣ ግባቸው ደግሞ የሰዎችን አእምሮ ለክርስቶስ መማረክ ሊሆን ይገባል። እውነትን ያለ ፍቅር ማቅረብ ጭካኔ ነው፤ ፍቅርን ደግሞ ያለ እውነት ማቅረብ ስምምነት (Compromise) ነው። ሁለቱን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ለዘመኑ አገልጋይ ወሳኝ ነው።

❤20🥰5
የልብ ጩኸት እና የንስሐ ጸሎት🤲
(የአንድ ወደጄ ጸሎት)
ጌታ ሆይ! ስለ አስመሳይነቴ፣ በኃጢአት ውስጥ እየኖርኩ አንተን ስላገለገልኩኝ፣ በሰዎች ጥላቻ ተከብቤ በመድረክህ ላይ ስለቆምኩኝ፣ ኃጢአትን ሳላቋርጥ ስለመሥራቴ፣ ደስታዬን ከአንተ ውጪ ስላደረግኩኝ፣ ትኩረቴን ከአንተ ላይ ስለነቀልኩኝና ተራ ነገሮችን ከአንተ ስላስቀደምኩኝ... ዛሬ በፊትህ እወድቃለሁ።
ከዚህ በኋላ እንኳን አልበድልህም ብዬ፣ ልቤ በበረታበት ቀናት ሁሉ ቃል ገብቼልህ ነበር። ነገር ግን ያ ቃል ኪዳኔ ሁለት ቀናትን እንኳ ሳይሻገር፣ ሳምንታት ሳይሞላው፣ እንደገና ተመልሼ በዚያው በለመድኩት የድካም ማዕበል ውስጥ ተዘፍቄ ተገኘሁ። እሁድን በመድረክህ ላይ የቃልህን እውነትና ኃይል አገልግዬ፣ ሰኞ ሲተካ ግን ያው የድሮ ድካሜ አቅፎ ይቀበለኛል።
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? ብዬ ግራ ተጋብቻለሁ። መለወጤስ ለምን እንዲህ ዘገየ? ጌታ ሆይ፤ ጸጋህ ለእኔም ጭምር በቂ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ነገር ግን እኔ በጸጋህ ላይ መደገፍና ሥጋዬን ለቃልህ ማስገዛት ለምን አቃተኝ? በማለት በሐሳብ ማዕበል እየተናወጥኩኝ ነው፤ ልቤም በብዙ ቆስሏል። ውስጤና ውጪዬ፣ መድረኬና ህይወቴ አንድ እንዲሆንልኝ እለምንሃለሁ።
ነገር ግን ጌታ ሆይ፤ እባክህን ይቅር በለኝ!
እንደ ጠፋው ልጅ ደግመህ በእቅፍህ ተቀበለኝ፤ ሕይወቴንና ማንነቴን የምታድስበትን የይቅርታ ዕድል ስጠኝ! እባክህን ወደ እኔ ተመልከት፤ ከአንተ ውጪ ምንም ተስፋ የለኝም። ከአንተ ውጪ የሚያስችለኝ፣ ከአንተ ውጪ የሚያድሰኝ፣ ከአንተ ውጪ ማንም የለኝም!
ገበናዬን የሸፈንክልኝ አንተ ብቻ ነህ፤ ምስጢሬንና ውድቀቴን ሰዎች ቢሰሙ ኖሮ ምን እሆን ነበር? አንተ ግን በምሕረትህ ሸፈንከኝ እንጂ አላሳፈርከኝም።
ጌታ ሆይ፣ እባክህን ከዚህ የድካም አረንቋ አውጣኝ፤ የተሰበረውንና የቆሰለውን ልቤንም ጠግንልኝ!

🙏22😭11❤5😢2
እውነተኛ ጸሎት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚደረግ፣ በእርሱ ታማኝነት ላይ በፍጹም እምነት የሚመሠረት፣ እኛን ከራሳችን ጠባብ ሐሳብ አውጥቶ ወደ ሰፊው የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚያመጣ፣ በፍቅር የተጋመደ ልዩ ቁርኝት ነው። በዚህ የልጅነት መንፈስ ወደ አባታችን እንቅረብ!
❤🔥32👌5❤3🔥3
ጸጋ፤ በራሳችን መቆም ለማንችል ለወደቅን ኃጢአተኞች፣ ምንም ሳይገባን በክርስቶስ ኢየሱስ በነጻ የተሰጠን መለኮታዊ ሞገስ፣ ይቅርታና በቅድስና እንድንኖር የሚያስችለን መለኮታዊ ኃይላችን ነው።
❤30🔥8🥰2👏2
የጸጋው ዋጋ፡ ርካሽ ጸጋ እና ውድ ጸጋ
በዘመናችን በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ ቀውስ እየታየ ነው። እምነት አለ፣ ስብከት አለ፣ የአምልኮ ፕሮግራሞች በየቀኑ ይካሄዳሉ፤ ነገር ግን በሰዎች ሕይወት ላይ የሚታየው መንፈሳዊ ለውጥና የቅድስና ኃይል እጅግ አናሳ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው? ታዋቂው የስነ-መለኮት ምሁር Dietrich Bonhoeffer ለዚህ ጥያቄ ሲመልስ፦ "የቤተክርስቲያን ትልቁ ጠላት 'ርካሽ ጸጋ' ነው" ይላል።
ርካሽ ጸጋ ማለት የእግዚአብሔርን ይቅርታና ፍቅር መሸጫ ሸቀጥ ማድረግ ማለት ነው። ንስሐ ሳይገቡ፣ ሕይወትን ሳይለውጡና ለኃጢአት ሳይሞቱ በጸጋ ድነናል እያሉ በድፍረት በኃጢአት መኖር ነው።
Bonhoeffer ይህንን አስመልክቶ ሲናገር፦
"ርካሽ ጸጋ ንስሐ የሌለበትን ምሕረት፣ ቤተክርስቲያናዊ ተግሣጽ የሌለባትን ጥምቀት፣ ኅብረት የሌለበትን ቅዱስ ቁርባን (ማዕድ)፣ እና መስቀል የሌለበትን፣ ሕያውና ሥጋ የለበሰውን ክርስቶስን መስበክ ነው።"
👉 ርካሽ ጸጋ ሰውን ደቀ-መዝሙር ሳያደርግ ስማ ክርስቲያን ለማድረግ ይሞክራል።
👉 እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚጠላና እንደሚፈርድ ይዘነጋል።
👉እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ ዝም ብሎ ይምረኛል በሚል ስንፍና ሰውን ያደነዝዛል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው እውነተኛው ጸጋ ግን "ውድ ጸጋ" ነው። ይህ ጸጋ በነፃ የተሰጠ ቢሆንም፣ በዋጋ ደረጃ ግን እጅግ ውድ ነው። ለአብ አንድያ ልጁን ያስከፈለ፣ ለወልድ ደግሞ ሕይወቱንና የመስቀል ላይ ሞትን የጠየቀ ስለሆነ ነው። ለእኛም ቢሆን ውድ ነው፤ ምክንያቱም ሕይወታችንን ሙሉ ለእግዚአብሔር ጌትነት እንድንሰጥና በደቀ-መዝሙርነት እንድንመላለስ በውስጣችን ይሠራል።
ይህንን ዋጋ እኛ መክፈል ስለማንችል ክርስቶስ ስለ እኛ ከፍሎታል። እኛም ስንቀበለው እውነተኛ ሕይወትን ስለሚሰጠን ነው።
እውነተኛ ጸጋ ሰውን ዝም ብሎ አይተወውም፤ ይለውጠዋል። ኃጢአትን እንዲጠላ፣ እግዚአብሔርን ደግሞ እንዲወድ ያደርገዋል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ወደ ራሱ ሲጠራ፤ የጥሪውን ምንነት በግልጽ አስቀምጧል፦"ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።" (ማቴዎስ 16፥24)
ዛሬ በየማኅበራዊ ሚዲያውና በየመድረኩ የሚሰበከው ስብከት እኛን ደስ የሚያሰኝ፣ ሥጋችንን የሚያባብልና ያለንበትን የኃጢአት ሕይወት የሚያጸድቅልን (ርካሽ ጸጋ) ነው? ወይንስ ለኃጢአታችን እንድንሰበር፣ መስቀላችንን እንድንሸከምና ክርስቶስን እንድንመስል የሚያደርገን (ውድ ጸጋ) ነው?
በነጻ በጸጋው ድነናል፤ አሁን ደግሞ የጸጋው ኃይል በቅድስና ሕይወታችን ይገለጥ!

❤30🥰3👏2
በክርስትና ሕይወት ውስጥ በራስ ጥረት የሚመጣ የባህሪ ማሻሻል (Self-improvement) የሚባል ነገር የለም፤ ለሥጋ ምኞት መሞት እንጂ። አሮጌው ማንነታችን በትምህርትና በልምምድ የሚስተካከል ሳይሆን፣ በክርስቶስ መስቀል ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተፈረደበትና የሞተ ማንነት ነው። ክርስቶስ ሊያድነን የመጣው የቆሸሸውን አሮጌ ሕይወታችንን አጥቦ ሊያሳምርልን ሳይሆን፣ እርሱ በሞተበት ሞት ውስጥ እኛንም አብሮ ቀብሮ፣ በአዲሱ የትንሣኤው ሕይወት ፍጹም አዲስ ፍጡር ሊያደርገን ነው። እኛም በየዕለቱ ይህንን አዲስ ማንነት እየለበስን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንለወጣለን።
❤🔥26❤9👏4🔥2🙏2
ቤተክርስቲያን የምንሄደው እግዚአብሔርን ለመጥቀም ወይም በሰዎች ዘንድ ጥሩ ሰው ለመባል ሳይሆን፣ እኛ ራሳችን መንፈሳዊ ሕክምናና ዕድሳት ስለሚያስፈልገን ነው። ቤተክርስቲያን የፍጹማን ቅዱሳን ማሳያ ሙዚየም ሳትሆን፣ በክርስቶስ ጸጋ የሚፈወሱ የኃጢአተኞችና የደካሞች ሕክምና ሆስፒታል ናት።
ስለዚህ ስንሄድ በልማድ ሳይሆን፣ ከፈጣሪዬ ጋር ለመገናኘት፣ ከቅዱሳን (ከአማኞች) ማኅበር ጋር ለመኅበር፣ ነፍሴ በክርስቶስ ቃልና መንፈስ እንድትታደስ፣ እኔም በጸጋዬ ሌላውን ለማነጽ በሚል ንቁ መንፈሳዊ ዝግጅት ይሁን። ይህ የመሰብሰብ መደበኛነት ለእግዚአብሔር ቤት ያለንን የልብ ጥማትና የታማኝነት መገለጫ ነው።
ዛሬ እሁድ ነውና ጉዞ ወደ አማኞች ኅብረት! 🚶♀➡️🚶➡️
ስለዚህ ስንሄድ በልማድ ሳይሆን፣ ከፈጣሪዬ ጋር ለመገናኘት፣ ከቅዱሳን (ከአማኞች) ማኅበር ጋር ለመኅበር፣ ነፍሴ በክርስቶስ ቃልና መንፈስ እንድትታደስ፣ እኔም በጸጋዬ ሌላውን ለማነጽ በሚል ንቁ መንፈሳዊ ዝግጅት ይሁን። ይህ የመሰብሰብ መደበኛነት ለእግዚአብሔር ቤት ያለንን የልብ ጥማትና የታማኝነት መገለጫ ነው።
ዛሬ እሁድ ነውና ጉዞ ወደ አማኞች ኅብረት! 🚶♀➡️🚶➡️
❤37🔥4👌4🙏3
የሰዎች ትከሻ ይዝላል፣ የራሴም ጉልበት ይደክማል፤ የእግዚአብሔር ታማኝነት ግን ሁልጊዜ ብርታቴ ነው።
❤28🥰12🙏8
እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ለመቀጠል የሰውን ልጅ ይሁንታ ወይም ድምፅ አይፈልግም። ሰው ባያመልከው እንኳ እርሱ ያው ዘላለማዊ ንጉሥ ነው። እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ሰውን ሲፈጥር ለመመካከር ሳይሆን ክብሩን ለመግለጥ ነው፤ የሰው ልጅ ምርጫ፣ ፈቃድና ፍላጎት ሁሉ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ቁጥጥር ስር በመሆኑ፣ የእርሱን ዘላለማዊ ዕቅድ ሊያደናቅፍ አይችልም፤ ታሪክን የሚጠቀልለው በገዛ ሉዓላዊ ሥልጣኑ ነው። እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ ሁሉ፣ ኃጢአትንና እምቢተኝነትን በጽድቅ ፍርዱ የሚቀጣ የሚበላ እሳትም ጭምር ነው።
❤23👌5❤🔥3👏1🙏1
የሰው ልጅ ትልቁ ኃጢአት በክፉ ሥራው ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ፊት በሚያቀርበው የራስ ጽድቅ ውስጥም ጭምር ነው። ያለ ክርስቶስ ደምና ያለ እምነት፣ ለመጽደቅ በሚደረግ ሃይማኖታዊ ትጋት የሚቀርብ ማንኛውም ምጽዋትና ጸሎት በቅዱሱ አምላክ ፊት እንደ ረከሰ ጨርቅ ነው። ሰብአዊ ጽድቅ ሰውን ከመለኮት ቁጣ ሊሸፍን የማይችል የተበሳ ጃንጥላ ነው፤ እግዚአብሔርን በሥራችን ልንደልለው መሞከር ራሱ የኩራት ሁሉ አክሊልና ሌላው የኃጢአት መልክ ነው።
ስለዚህ ንስሐ የሚያስፈልገው ለግልጽ ክፉ ሥራችን ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን ለመደለል በሞከርንበት በዚያ በራስ-ተኮሩ መልካም ሥራችንም ጭምር ነው። እውነተኛና በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ያለው መልካም ሥራ የሚጀምረው፣ በክርስቶስ የማዳን ሥራ አምነን ከጸደቅን በኋላ፣ እርሱን ለማስደሰትና ለመታዘዝ በቅዱስ መንፈስ የምናፈራው የእምነት ፍሬ ሲሆን ብቻ ነው።

❤🔥11❤4🔥2🥰1🙏1👌1