ጨ'ረቃ
94 subscribers
5 photos
1 link
ጨረቃ ተስፋ ናት።
Download Telegram
Channel created
Channel photo updated
ሰኔ 25/2015 ጨረቃችን ተወለደች

እሁድ ሰኔ 25 በ ጎባ ዋቤ ሸበሌ ሆቴል የመጀመርያ መድረኳን በተሳካ መልኩ ጨረቃ አሰናድታ ነበር። ታዳምያንም አሰላፊያንም ተስፋን ሰቅለን የተለያየንበትም መድረክ ነበር።

ጨረቃ በየወሩ መድረኳን ማዘጋጀቷን ትቀጥላለች።

የጨረቃ ደቀመዝሙር ለመሆን የምትፈልጉ መገኛችን እነሆ
👉 +251985490581

ግጥ'ም የሚያረግ
ጥዑም ዜማን የሚያሰማ
ወገኛ አንደበት ያለው
ስሜትን የሚተውን

ጨረቃን ማጀብ ትችላላችሁ።

ጨረቃ ተስፋ ናት። ኑ ጨረቃን እንስቀል!
@cherekapoetry
2
የጨረቃ የመጀመሪያ ክፍት መድረኳ እሁድ (09/11/15) በዮና ላውንጅ ይሆኗል።

በዚህ ነፃ መድረክ
የምገጥሙ ፣ ወግ የምታሰሙን ፣ ጥዑም ዜማ የምታቀርቡልን ፤ ድምፅ ማጉያው ተሰክቶ እናንተን ይጠብቃል። እድሉን ተጠቀሙበት።

የስነጥበብ አፍቃሪያን የጨረቃን ማዕድ ተጋብዛቹሀል።


ጨረቃ ተስፋ ናት።
#cherekapoetry
#cherekaopenmic
@cherekapoetry

ለበለጠ መረጃ +251985490581
ማስታወቂያ
-------------

የጨረቃ የስነጥበብ ቡድንን መቀላቀል ለምትፈልጉ በሙሉ

🌕 በግጥም
🌕 በወግ
🌕 በተውኔት
🌕 በአዘጋጅነት
እንዲሁም
🌕 በሙዚቃ

በስልክ ቁጥራችን +251985490581

አልያም በቴሌግራም @cherekachat

ሊያናግሩን ይችላሉ።
-------------------
ቋሚ መገኛ ቦታችንን በቅርቡ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

#cherekapoetry
#cherekaopenmic
@cherekapoetry

ጨረቃ ተስፋ ናት።
👍3
"ጨረቃ poetry"

ጨረቃ poetry በወጣት የስነ-ጥበብ አፍቃሪያን የተጀመረ የስነ-ጥበብ መድረክ ነው::
~አላማችን ምንድነው?~
-በተለይም ባለንበት አካባቢ (ባሌ ጎባ እና ባሌ ሮቤ) እንደውም በግልፅ የማይታየው የስነ-ጥበብ እንቅስቃሴ ላይ አብዮት ማስነሳት
-አቅም አለን ብለው የሚያስቡ ልጆችን
~ አቅማቸውን የሚያሳዩበትን መድረክ ማዘጋጀት
~ከሌሎች አቻቸው ጋር መገናኛ ድልድይ መሆን
~ለታናናሾቻቸው አርአያ እንዲሆኑ ማብቃት
~ከታላላቆቻቸው እንዲማሩ ማመቻቸት

-ስነ-ፅሁፍን በተለይም ስነ-ግጥምን እና ወግን አንዱ የመዝናኛ አማራጭ ማድረግ
-ለእኩዮቻችን የማጉትን የዋጡትን አየር እንዲተነፍሱት ምክንያት መሆን
-ተስፋን እና ፍቅርን ቃል ማልበስ
ከምንም አይነት ፖለቲካዊ እና ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ በፀዳ መልኩ ሰውነትን መስበክ ሰውነትን ከፍ ከፍ ማድረግ

*በምን መልኩ*

-*ወርሀዊ የስነ- ጥበብ ምሽት በደማቅ ዝግጅት ተከፍቶ ወርሀዊ ቀጣይነት ይኖረዋል
~ የአካባቢው የስነ-ጥበብ ባለሞያዎች የሚሳተፉበት
~ተጋባዥ እንግዶች የሚታደሙበት እና ንግግር የሚያረጉበት
~አላማችንን እና ግባችንን የምናስተዋውቅበት
~ድጋፍ የምናሰባብበት
-* ቡሃላ በየ 15 ቀኑ open mic መድረክ ይኖረናል::
~ችሎታ ያላቸው ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡበት
~ግጥም
~ሙዚቃ
~ወግ
~አጠር ያለ ተውኔት
~የመማሪያ ፕሮግራሞች ያሉበት (ችሎታ ማዳበሪያ)
~ልምድ መለዋወጭያ
~ለዋናው ወርሓዊ መድረክ አቅራቢ ሊሆኑ የሚችሉ ባለተሰጥኦዎች የሚመመረጡበት
~ከሰአልያን ጋር በመጣመር ስነፅሁፍ እና ስእልን ያዋደዱ መርሀግብሮች ሚኖሩበት

*ለምን ጨረቃ ተብሎ ተሰየመ?*

-ምናልባት በፀሀፊያን ዘንድ ተወዳጅ ርእስ እና ሃሳብ በመሆኗ ተብሎ ሊገመት ይችላል::ሊሆንም ይችላል:: ከዛ ባለፈ ግን ልናንፀባርቅ የፈለግነውን ብርሃነ ሃሳብ ይገልፅልናል ብለን ስለተስማማን ነው::ጨረቃ ሯሷም አንፀባራቂ ስለሆነች::
-አብዛኛው ሰው አለምን በጨለማ ይመስላል::በጨለማ መደናበር ደግሞ የማንም በጎ መሻት አደለም::በጭለማ ውስጥ ብርሃን እንዳለ ለማወቅ እንደ ጨረቃ አይነት አብነት ያስፈልጋል::ከተንጣለለው ጨለማ ይልቅ ብትናንሾቹ ከዋከብት እና ጨረቃ የሚማረክ ተስፈኛ ሰው የሞላበት ዓለም ቢሆን ኖሮ ጨለማንም ባላወቅን ነበር::"ጨረቃ ጀንበር ናት ማታ" እንዲል Rophnan የማታ ጀንበር የሆኑ ሃሳቦችን ሰማይ ላይ መሰቀል እንፈልጋለን::

#cherekapoetry
#cherekaopenmic
@cherekapoetry

ጨረቃ ተስፋ ናት
👍53
እዚ ማዶ አንድ ድግስ!

እሁድ 10:30 ዮና ላውንጅ እንገናኝ።
መገቢያ 50 ብር
ቲኬቶን ከ 2025 studio አልያም በራፍ ላይ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ 0985490581

ጨረቃ ተስፋ ናት።
#cherekapoetry
#cherekaopenmic
@cherekapoetry
🔥41👍1
ጨረቃችን በአራተኛ የስነጥበብ መድረኳ ስለተስፋ የምለው አለኝ ትለናለች።



እሁድ መስከረም 13 ፤ 10:30 ዮና ላውንጅ እንገናኝ።
መገቢያ 50 ብር
ቲኬቶን ከ 2025 studio አልያም በራፍ ላይ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ 0985490581

ጨረቃ ተስፋ ናት።
#cherekapoetry
#cherekaopenmic
@cherekapoetry
👍2
ጨ'ረቃ
ጨረቃችን በአራተኛ የስነጥበብ መድረኳ ስለተስፋ የምለው አለኝ ትለናለች። እሁድ መስከረም 13 ፤ 10:30 ዮና ላውንጅ እንገናኝ። መገቢያ 50 ብር ቲኬቶን ከ 2025 studio አልያም በራፍ ላይ ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ 0985490581 ጨረቃ ተስፋ ናት። #cherekapoetry #cherekaopenmic @cherekapoetry
ክብሯን ቤተሰቦቻችን በአስገዳጅ ምክንያት የሰዓት ለውጥ እንዳረግን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

10:30 ይጀምር የነበረው መርሀግብራችን
ወደ እሁድ መስከረም 13 ከቀኑ 7 :30 እንደተለወጠ በትህትና እንገልፃለን።

@cherekapoetry
👍2
👍5