Christocentric Pulpit
157 subscribers
17 photos
85 links
Christocentric Pulpit: A channel dedicated to sharing humble, passionate, and loving teachings centered on Christ. Join us for insightful sermons, Bible studies, and discussions that focus on deepening your walk with God and living out His word.
Download Telegram
ብዙ ጊዜ በእጮኛሞች ከተለመዱ ጥያቄዎች መካከል፡
ከትዳር በፊት በሁለት ጥንዶች መካከል እንደ መሣሣም እንዲሁም ሌሎች እንደ መተሻሸት፣ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን መነካካት ና የመሳሰሉት አይነት ድርቶችን መከወን ችግር አለው? እንደዚህ አይነት ድርጊቶችስ እንደ ወሲብ ሊቆጠሩ ይችላሉ?

ሁለት ሃሳቦችን ላስቀምጥላችሁ፡

1. ጥያቄው ከክርስትና አጠቃላይ መርህ አንፃር ሲታይ ችግር አለበት፡
👉 ክርስትና ''እንደዚህ ባደርግ ችግር አለው?'' በማለት ሳይሆን ''እንደዚህ ባደርግ ጥቅም አለው?'' ተብሎ የሚኖር ነው። ድርጊቶች ለሌሎች ሰዎች (ለራስ አይደለም) ጥቅም፤ ለእግዚአብሔር ደግሞ ክብር ካላመጡ መደረግ የለባቸውም።(1ቆሮ6:12) ስለዚህ ራሳችሁን ይሄን ጠይቁ፡ ሰዎች እንዲህ አይነት ነገር ስታደርጉ ቢያዩአችሁ ለእግዚአብሔር ክብር ያመጣሉ? (1ቆሮ10:31)

2. ወሲብ ማለት ምን ማለት ነው? ይህን ለመመለስ አንድ ጥያቄ እንጠይቅ፡ ''ወሲባዊ አካል (sexual organ) የሚባለው የሰውነት ክፍል የቱ ነው?'' ሰዎች ወሲባዊ አካል የቱ እንደሆነ ካላወቁ ወሲብ ምን እንደሆነ መተርጎም አይችሉምና ወሲብ ያድርጉ ወይም አያድርጉ አያውቁትም። ብዙዎች ''ወሲባዊ አካል የመራቢያ አካላት ናቸው'' ሲሉ መመለሳቸው የሚጠበቅ ነው። ይህ መልስ ግን ትክክል አይደለም። እንዲሁም ለብዙ ስህተቶችም ምክንያት ነው። እንደሚባለውም ወሲባዊ አካል መራቢያ አካላት ቢሆኑ ኖሮ እነዚህ አካላት እስካልተገናኙ ድረስ ወሲብ አልተፈፀመም ማለት ይቻል ነበር።

👉 ነገርግን ወሲባዊ አካል ተብሎ በሳይንሱ የሚጠራው መራቢያ አካላት ሳይሆኑ አዕምሮ (Brain) ነው። ሰዎች መራቢያ አካላቸውን ሳይጠቀሙ ወሲባዊ ሃሳቦችን በማሰብ ብቻ sexual climax ላይ የመድረሳቸውም ምስጢር ስራው በዋናነት የአዕምሮ ስለሆነ ነው።
👉 ወሲባዊ አካል አዕምሮ ከሆነ አዕምሮን ለወሲብ እንዲነሳሳ (ሆርሞኖች ና ኒውሮትራንስሚተርስ እንዲለቀቁ) የሚያደርጉ ነገሮች ሁሉ ወሲብ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ። ለዚህም ነው አንዳንድ ሳይንቲስቶች ከላይ ያስቀመጥናቸውን ድርጊቶች mini-sex ብለው የሚጠሯቸው።

* በአጠቃላይ ክርስቲያን ከሚኖርበት መርህ ና ከወሲብ ትርጓሜ አንፃር ከትዳር በፊት ቢደረጉ ተብለው የሚጠየቁ ድርጊቶች እጅግ አደገኛ ና ደግሞም ሐጢያት ናቸው። ስለዚህ በንሰሃ ተመልሶ ራስን ማደስ ና ማስተካከል ያስፈልጋል።
Courtesy :- Mere Protenstantism
አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይሆኑ?

የምትመለከቷት ወፍ Fire Hawks ትባላለች። አደገኛ ወፍ ናት። እንደአካሏ ማነስ እንዳትመስላችሁ። በሚሊየን ዶላር የሚገመት ንብረት በዚች ሚጢጢ ፍጥረት በየአመቱ ይወድማል። ስራዋ ማጥፋት ነው። ከየትም ፈልጋ የተቀጣጠለ እንጨት፣ ሰወች ሳያጠፉ የጣሉት ሲጋራ ወዘተ ታነሳና ደረቅ ጫካ ፈልጋ ትጥለዋለች ....እሳት ይነሳል። አንዳንዴ መንደር ወይም ለዘመናት የተጠበቀ ደን ይወድማል፣ ብርቅየ እንስሳት ይሞታሉ ይሰደዳሉ። ቅርሶች ይቃጠላሉ። ይሄን ሁሉ የምታደርገው ለምን ይመስላችኋል? ለሆዷ! ጫካው ውስጥ የተደበቁ በረሮወችና ትናንሽ ነፍሳት እሳቱን ፈርተው ሲውጡ እየለቀመች ትበላለች በቃ! ለዚሁ ነው አገር የምታወድመው!!
Courtesy :-Alex Abreham
ሌሰፌር (Laissez-faire) አመራር - ልቅ የአመራር “ስልት”

“አመራር A to Z” በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ አስር የአመራር ስልቶችን አብራራለሁ፡፡ እነዚህን ስለቶች በሚገባ መገንዘብ በግላችን የአመራር ብቃት ለማደግ ይጠቅመናል፡፡ ምክንያቱም በተመሪነትም ሆነ በመሪነት ከአመራር ሂደት ስለማናመልጥ ማለት ነው፡፡ ለበለጠ ግንዛቤ ወደመጽሐፉ ጎራ እንድትሉ እየጠቆምኩኝ የዛሬውን መልእክቴን ላስተላልፍ፡፡

ከአስሩ ስልቶች መካከል ሶስቱን “ጥንታዊ ስልቶች” እንላቸዋለን፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡-
1. አውቶክራቲክ (Autocratic) አመራር - ገደብ የለሽ ስልጣን ያለው የአመራር ስልት
2. ዴሞክራቲክ (Democratic) አመራር - መብት ሰጪ የአመራር ስልት
3. ሌሰፌር (Laissez-faire) አመራር - ልቅ የአመራር “ስልት”

የተቀሩት ሰባቱ ስልቶችም ቢሆኑ በዘመናችን በተለያዩ መሪዎች በተግባር ላይ ሲውሉ የሚታዩ ዘይቤዎች ናቸው፤ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ቢውሮክራቲክ (Bureaucratic) አመራር
2. ካሪዝማቲክ (Charismatic) አመራር
3. ለውጥ-ተኮር (Transformational) አመራር
4. ሰው-ተኮር (People-oriented) አመራር
5. ተግባር-ተኮር (Task-oriented) አመራር
6. ልውውጥ-ተኮር (Transactional) አመራር
7. ሁኔታዊ (Situational) አመራር

አሁን ባለንበት ዘመን የቤተሰብን አመራር፣ የተቋምን አመራር፣ የሕብረተሰብ (የሃገር) አመራር እየሞገተ ያለው ሁኔታ መሪዎች ሌሰፌር (Laissez-faire) የአመራር ስልትን እንዲከተሉ ሲያወርዳቸው ማየት የተለመደ ነው፡፡

ሌሰፌር (Laissez-faire) የአመራር ስልት ማለት ልቅ የአመራር “ስልት” ማለት ነው፡፡
ሌሰፌር የሚለው ቃል በፈረንሳይኛ፣ “ነገሮች በራሳቸው እንዲንከባለሉና እንዲሆኑ መልቀቅ” የሚለውን ሃሳብ የያዘ ነው፡፡ ይህ አይቱን የአመራር ስልት የሚከተል መሪ ተከታዮች፣ ሰራተኞች ወይም ሕዝቡ ካለምንም መታየትና ቁጥጥር በራሳቸው ስራውን እንዲያንቀሳቅሱ የሚለቅቅ መሪ ነው፡፡

የሌሰፌር አመራር፣ “አመራር-አልባ” የአመራር ስልት በመባልም ይታወቃል፡፡ ይህ አይነቱ አመራር ዘይቤ በባህሪያቸው፣ በዲሲፕሊናቸውና በብቃታቸው የተመሰከረላቸው ሰዎችን ለመምራት የሚጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ ከስሙ ትርጓሜ እንደምንረዳው ግን አመራሩ ልቅነትን፣ እንደፈለጉ መሆንንና ከቁጥጥር ውጪ የሆነን የመሪ-ተመሪ ግንኙነትን ስለሚያንጸባርቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል ቤተሰብ በስነ-ምግባር ብልሹ የሆኑ ልጆችን ያፈራል፡፡
• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል የተቋም መሪ ሰርአት የሌለው ስራ ሂደትና የሰራተኞች ባህሪይን ይፈለፍላል፡፡
• ሌሰፌር (Laissez-faire) ወይም ልቅ የአመራር “ስልት” የሚከተል የሕብረተሰብ (የሃገር) መሪ ለሕግ የማይገዛና ጋጥ-ወጥ ዜጋ ይፈጥራል፡፡

የበሰለ መሪ ምንም እንኳን ጨዋና ለስላሳ በመሆን ቢያምንም ከዚያም ጋር ግን አቅጣጫን የሚያሳይ፣ ስርአትንና ህግን በማስቀመጥ በትክክል መከበሩን የሚከታተልና ጠንካራ መሆን ሲገባው በጥንካሬው የሚታወቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡

By Dr Eyob Mamo