Channel 1 TV Ethiopia
171 subscribers
292 photos
📺 Channel 1 Ethiopia
Welcome to the official Telegram channel of Channel 1 Ethiopia – your trusted source for news, entertainment, culture, and lifestyle programs.

✅ Stay updated with:
• Breaking news & current affairs
• Exclusive interviews & document
Download Telegram
በሕንድ ለኢትዮጵያዊ የኤች.አይ.ቪ. ታማሚ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተከናወነ።


በሕንድ ዴልሂ የሚገኘው 'ማክስ ሱፐር ስፔሻሊቲ' ሆስፒታል ኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ በደሙ ውስጥ ለሚገኝ የ43 ዓመት ኢትዮጵያዊ እጅግ ስኬታማ የሆነ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጉን አስታውቋል።


ይህ የህክምና ሂደት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሰዎች ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ በመሆኑ በዘርፉ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል፡፡


ለንቅለ ተከላው ስኬታማነት ዘመናዊ የፀረ-ሬትሮ ቫይረስ ህክምናዎችና በጥንቃቄ የተመራ የበርካታ የህክምና ባለሙያዎች ቅንጅት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ስፑትኒክ ዘግቧል።


ይህ ስኬት በኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ የተያዙና የኩላሊት ህመም ያለባቸው ታማሚዎች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑ ተገልጿል።
እስራኤል ለኢራን ሲሰልል ነበር ያለችው ታዳጊ ላይ ክስ መሰረተች፡፡

ቴህራን በበኩሏ ከእስራኤልና ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን 466 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውላለች።

አልጀዚራ እንደዘገበው፤ በቴል አቪቭ አንድ የ14 አመት ታዳጊ ለኢራን መረጃ ሲያቀብል ነበር በሚል የስለላ ተግባር ወንጀል ተጠርጥሮ በታዳጊዎች ፍርድ ቤት ቀርቧል።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተልና በመኖሪያ ቤታቸው የአጥር ግንብ ላይ የዛቻ መልእክቶችን መጻፍ ከቀረቡት የክስ ዝርዝሮች መካከል ተጠቅሰዋል።

በዚህም ለሚፈፅማቸው ተልዕኮዎች ከ1,170 ዶላር በላይ ክፍያን በየጊዜው በክሪፕቶከረንሲ አማካኝነት ተቀብሏል ሲል አልጀዚራ የፍርድ ቤት ውሎውን የተከታተለውን ጀሩሳሌም ፖስት ዋቢ አድርጎ ፅፏል።

ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን እያደረገ መሆኑን በማመላከት ተቀያሪ ቀጠሮ መሰጠቱም ታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ቴህራን ከእስራኤልና ከአሜሪካ ጋር ግንኙነት አላቸው ያለቻቸውን 466 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውላለች።

አሳሳች መረጃዎችን ለህዝብ ማሰራጨት፣ ፍርሃትና ጭንቀት እንዲፈጠር በማድረግ "የስነ-ልቦና ደህንነትን" ማሳጣት የሚሉት ክሶች በ466'ቱ ግለሰቦች ላይ መቅረባቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።
❤1
ከአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተውጣጡ ወጣቶች፣ ዲፕሎማቶችና ፖሊሲ አውጪዎች የተሳተፉበት 6ኛው የአፍሪካ ወጣቶች የዲፕሎማሲ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

“ከፖሊሲ ወደ ትግበራ ለቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት አፍሪካዊ መፍትሔዎችን በአፍሪካውያን መሪነት ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ወጣቶች በአህጉሪቱ የሰላምና የልማት አጀንዳዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል ።

የጉባኤው ዋና ዓላማ ወጣቶች በአህጉራዊ የሰላም ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ውህደትና በፈጠራ ሥራዎች ላይ ያላቸውን ሚና ወደ ላቀ ተግባራዊ ደረጃ ማሸጋገር እንደሆነ ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ወጣቶች ለዛሬውም ሆነ ለነገው የአህጉሪቱ ብልጽግና የማይተኩ አጋሮች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አክለውም አፍሪካ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ተወዳዳሪ እንድትሆን የዲጂታል ፈጠራ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አጀንዳ 2063ትም ይሁን ሌሎች የዘላቂ የልማት ግቦች የወጣቶች ጉልበትና ራዕይ ከሌለበት ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም ያሉት ሚኒስትሯ፣ ወጣቶች የቀደሙ ትውልዶችን ጥበብ በመጠቀም የምንመኛት አፍሪካን የመገንባት ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ጉባኤው ከመጋቢት 16-20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይዘልቃል።
ጃፓን ለክፉ ቀን ብላ ያስቀመጠችውን ነዳጅ ወደ ገበያ አወጣች::


ውሳኔው ህዝቡ በነዳጅ እጦት ቅሬታ እንዳያሰማ ያደርጋል ተብሎለታል።


የጃፓን የኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ በመካከለኛው ምስራቅ በሚካሄደው ጦርነት ምክንያት የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ለመቋቋምና በዜጎች ላይም ጫና እንዳይፈጠር ለመጠባበቂያነት ከተከማቸው ነዳጅ አንድ ክፍል መልቀቅ ጀምሯል።

አዣንስ ፍራንስ ፕረስ የሚኒስቴሩን ውሳኔ ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፤ ከዛሬ ጠዋት አንስቶ ከብሔራዊ ክምችቱ ወደ ነዳጅ ጣቢያዎች መጓጓዝ ጀምሯል።


እንደ ዘገባው፤ ከክምችት ጣቢያዎች ግማሽ ያህሉ የነዳጅ መጠን ወደ አራት የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያዎች ተልኳል።
ይህ ውሳኔ ቶክዮ ከመንግስት የነዳጅ ክምችት ላይ ለአንድ ወር የሚቆይ መጠን ያለው ነዳጅ እንዲለቀቅ ካስታወቀ በኋላ የተወሰደ እርምጃ ነው።


ጃፓን፤ በዓለም ላይ 5ኛዋ ትልቅ የነዳጅ አስመጪ ሀገር ስትሆን ከ90 በመቶ በላይ የምታስገባው ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ነው።
"ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እየተደራደሩ ያሉት ከራሳቸው ጋር ነው" ስትል ኢራን ትራምፕን ወረፈች፡፡

ዎል ስትሪት ጆርናል በበኩሉ፤ ኢራን ለአሜሪካ ያቀረበቻቸው ጠንካራ ጥያቄዎች እጄ ገብተዋል ብሏል።

አሜሪካና ኢራን አሁን ላይ ከወታደራዊ እንቅስቃሴና ከጥቃት ልውውጥ ወደ ቃላት ጦርነትም ገብተዋል።

አሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ከኢራን ጋር እየተደራደርን ነው ማለታቸውን ተከትሎ የቴህራን ከፍተኛ ባለስልጣናት በየፊናቸው መልስ እየሰጡ ይገኛሉ።
አማራ ባንክ እና ቪዛ የዲጂታል ክፍያን ለማዘመንና የሚያስችል ስምምነት ፈፀሙ።


አማራ ባንክ እና በዲጂታል ክፍያ የዓለም መሪ የሆነው ቪዛ የፈፀሙት ስልታዊ አጋርነት አማራ ባንክ የቪዛን ዓለም አቀፍ አውታረ መረብና የቴክኖሎጂ ተሞክሮ በመጠቀም የካርድ አቅርቦቱን እንዲያስፋፋ የሚያስችለው ነው።
ዘንድሮ በሐረሪ ክልል የሚከበረው የሹዋሊድ በአል "ሹዋሊድ ለሕብረብሄራዊ አንድነታችንና ለቱሪዝም እድገታችን" በሚል መሪ ሀሳብ መጋቢት 17ና 18 በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ በድምቀት እንደሚከበር የክልሉ ባህል ቅርሰና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

የሹዋሊድ በዓል አከባበር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰስ አለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበ ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በአትላንቲክ ዙሪያ የተካሄደውን የባሪያ ንግድና የአፍሪካውያንን ባርነት "ሰብአዊነትን የሚጣረስ እጅግ ከፍተኛ ወንጀል" ሲል እውቅና ሰጥቷል።

ጉባኤውም አባል ሀገራት ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ለካሳ ፈንድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን፤ በውሳኔው 123 ሀገራት ድጋፍ ሲሰጡ፣ አሜሪካ፣ እስራኤል እና አርጀንቲና ግን የተቃውሞ ድምጽ ሰጥተዋል።
የኔዘርላንድስ ትምህርት ቤቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘመናዊ ስልኮች እና ሌሎች የግል መሳሪያዎች ላይ የተጣለዉን እገዳ ተግባራዊ ካደረጉ ከሁለት አመታት በኋላ፣ በመንግስት የተሰጠ መረጃ እንደሚያሳየው በግምት ሶስት አራተኛው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሻሻለ የተማሪዎችን የትምህርት ትኩረት መዝግበዉ ተገኝተዋል።

ኔዘርላንድስ ከመደበኛ ህግ ይልቅ የትብብር አካሄድን በመምረጥ ሞባይል ስልኮችን፣ ዘመናዊ ሰዓቶችን እና ታብሌቶችን ከትምህርት ቤት ግቢ የሚከለክል ብሔራዊ ስምምነት ከሁለት አመት በፊት አጽድቃለች።
እስራኤል የኢራን የባህር ኃይል አዛዥን ገደልኩ አለች፡፡

የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ፤ ዓሊረዛ ታንግሲሪ የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋትን በበላይነት የሚመራ ሰው ነበር ብላለች፡፡

ዓሊረዛ የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባህር ኃይል አዛዥ ሆነው የተሾሙት በ2018 ሲሆን ከ2010 ጀምሮ ምክትል አዛዥ ነበሩ፡፡

አልጃዚራ እንደዘገበው ኢራን ጦርነቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በተከታታይ በርካታ ልምድ ያላቸው የጦር መሪዎች ተገድለውባታል የዓሊረዛ ግድያ ሌላው የኢራን ትልቅ ኪሳራ ነው ብሏል::
ኬንያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ጣቢያ ልትገነባ እንደሆነ ተገለፀ።


የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ በተካሄደው አለም አቀፍ የኒውክሌር ኢነርጂ ኮንፈረንስ ላይ ኬንያ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ ጣቢያ እንደምትገነባ ገልፀዋል።

ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሲያያ ካውንቲ በ2027 መገንባት ትጀምራለች።


ይህ 2,000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም የሚኖረው ግዙፍ ፕሮጀክት በ2034 ሥራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የኬንያን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አሁን ካለበት 3,300 ሜጋ ዋት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ወደ 10,000 ሜጋ ዋት ለማሳደግ ለተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኔቶን በድጋሚ ወቀሱ፡፡

ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ዛሬ ባሰፈሩት ወቀሳ ኔቶ ጭራሽ ያደረገው ድጋፍ የለም ጉዳዩ ፈጽሞ የማይረሳ ክስተት ነው ብለዋል፡፡

በስም ያልጠቀሷቸው አንዳንድ ያሏቸው ሃገራት በሆርሙዝ ወሽመጥ መርከቦችን ለማጀብ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
በተጨባጭ ያገኘነው ወታደራዊ ስኬት የኔቶ ሃገራት ድጋፍ እንደማያስፈልገን አመላካች ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
የኔቶ አባላትን ፈሪዎች ሲሉም ደግመው ወርፈዋል
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር በተገናኘ ከጋዜጠኞች በቀረበላቸው ጥያቄ ተበሳጩ።

በትናንትናው ዕለት የተካሄደውን የካቢኔ ስብሰባ ተከትሎ በቦታው የተገኙ ጋዜጠኞች ለፕሬዝደንቱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን አቅርበው ነበር።

በተለይም የአሜሪካና ኢራን የሳምንታት ወታደራዊ ውጥረትን ተከትሎ ጋዜጠኞች ትኩረታቸውን እዚሁ ጉዳይ ላይ አድርገው ነበር።

ነገር ግን ከአንዲት ጋዜጠኛ የቀረበላቸው ጥያቄ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕንና የካቢኔ አባላቶቻቸውን ፈገግ ከማሰኘት ባለፈ ብስጭት ያጫረም ነበር።

ጋዜጠኛዋ "ዩራኒየሙን ለመውሰድ ወደ ኢራን ይገባሉ ወይ?" ስትል ነበር ጥያቄዋን ያቀረበችው።

ትራምፕ ጥያቄውን ተከትሎ ፌዝ በተሞላበት ሁናቴ "ልገባም ላልገባም እችላለሁ፤ ለዚህ ጥያቄ ግን መልስ የመስጠትም ያለመስጠትም መብት አለኝ" ሲሉ መልሰዋል፤ አክለውም ነገ በዘጠኝ ሰዓት ቴህራን እንገባለን የሚል ምላሽን በፌዝ አጅበው ሰጥተዋል።

የጋዜጠኛዋ ጥያቄ ያበሳጫቸው ትራምፕ "እንዴት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ጠይቀሽ መልስ ትጠብቂያለሽ ?" ሲሉም ወርፈዋታል።
የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ቢያንስ 2 ሴት የቦርድ አባላት እንዲኖራቸው የሚያስገድድ መመሪያ ወጣ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚጸና በኢንሹራንስ ኩባንያ ውስጥ ተፅዕኖ ያላቸው ግለሰቦች መመዘኛ መመሪያ ቁጥር SIB/63/2026 ተብሎ የሚጠራ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

አዲሱ መመሪያ በኢንሹራንስ ዘርፉ ላይ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና የተጠናከረ የኮርፖሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያለመ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሠረት፤ ማንኛውም የኢንሹራንስ ኩባንያ የቦርድ አባላት ስብጥር አንድን ጾታ ብቻ የያዘ መሆን የለበትም። እያንዳንዱ የኢንሹራንስ ኩባንያ ቢያንስ ሁለት ሴት የቦርድ አባላት ሊኖሩት እንደሚገባ መመሪያው የግዴታ መስፈርት አስቀምጧል።

የቦርድ አባል ለመሆን ዝቅተኛው የዕድሜ ገደብ 30 ዓመት መሆን እንዳለበት በዚሁ አዲስ መመሪያ ተደንግጓል።

እያንዳንዱ የኢንሹራንስ ኩባንያ ሦስት ገለልተኛ የቦርድ አባላት ሊኖሩት ይገባል። እነዚህ ግለሰቦች የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና በፋይናንስ ዘርፍ ወይም ተያያዥ መስኮች የ10 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል ተብሏል።

በዚህ ገለልተኛ የቦርድ አባልነት ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ሊመረጡ እንደሚችሉ የብሄራዊ ባንክ መረጃ ያሳያል።
አለማችን በኮረና ወረርሽኝ ወቅት ካጋጠማት ቀውስ ያልተናነሰ መከራ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ሰበብ እየጠበቃት ነው ሲሉ የሩሲያው መሪ ተናገሩ፡፡

ቀውሱ በዋናነት በሶስት የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነውም ብለዋል።

እየተባባሰ የመጣው ግጭት አለማችን ላይ ይዞት የሚመጣው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ከዚህ ቀደም ዓለምን ካናጋው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የማይተናነስ ሊሆን ይችላል ሲሉ ነው ያስጠነቀቁት።

እንደ ፑቲን ስጋት፤ የግጭቱ መዳረሻና መጫወቻ ሜዳው መካከለኛው ምስራቅ ቢሆንም፤ ምን ያህል ሊሰፋ እንደሚችል ለመገመት ቢያዳግትም፤ በትክክል እየታዩ ያሉ ምልክቶች ግን የወረርሽኙን ወቅት የሚያስታውሱና ከዛም ወቅት ጋር የሚመሳሰሉ ግዙፍ መናጋቶችን የሚፈጥር ስለመሆኑ እሙን ነው ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ መስመሮች መዘጋት፣ የምርት ሂደት እና የአቅርቦት ሰንሰለቶች መቆራረጥ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነውም ብለዋል።

እንደ ፑቲን ገለፃ ይህ ቀውስ በተለይ በነዳጅና ጋዝ ዘርፍ፣ በማዕድንና የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዘርፍና በማዳበሪያ ምርትና ስርጭት ዘርፎች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።