በክርስቶስ ( in christ)
708 subscribers
98 photos
33 videos
40 files
38 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
በሩ አንተ ነህ ኢየሱስ
ወደ አብ ዘንድ ለመፍለስ
ከላይ መወለድ
(ዩሀንስ 3:1)

ያለ ዳግም ውልደት የእግዚአብሔር መንግት (መንግስተ ሰማይ) አይታሰብም !!!

በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
የክርስቶስ ደቀመዛሙርት በደስታ ይታዘዙታል ፤መምህሩ ራሱ ያስገኛቸው በመታዘዙ ነውና !!!
የእግዚአብሔር ፅድቅ ተገልጦ የእግዚአብሔር ወንጌል ደረሰልን ከዛም የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሆንን..የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ጋር ቀላቅሎን አካል አደረገን ።
እግዚአብሔር ወደ ዘላለማዊ መንግስቱ ልጁን ኢየሱስ ልኮ ጠራን !!!
#ፀጋው በእምነት አድኖኝ ....
#ኢየሱስ ፅድቁን አልብሶኝ...
#ስለእኔ በአብ ፊት ታይቶ ....
#ፈፅሞታል ስራዬን ጨርሶ..
መልህቅ⚓️ሶስት ጎን ያለው የሚመስል ብረት ነው ። አገልግሎት ለመርከብ ወይም ለጀልባ ነው ። መርከበኞች ብዙ ጊዜ አድማቸው እና ምልክታቸው መልህቅ ነው ። የመርከበኞች እና የመርከብ ህይወት ከመልህቅ ጋር የተቆራኘ ነው ።

መልህቅ መርከቡ እንዲቆም ሲፈለግ ከደረሰበት ቦታ ወይም አደጋ ሲደርስ ወጀብ ማዕበል ሲነሳ ለማረጋጋት አገልግሎት ላይ ይውላል ። ወጀብ ሲነሳ መልህቁ ወደ መሬት ይጣላል .. ብረቱ ስለሆነ ወሃ ስር መሬት ይይዛል ያኔ መርከቡን ይቆማል ..ማዕበሉ ምን ቢገፉው መርከቡን ይነቃነቃል እንጂ ጉዳት አይደርስበትም መልህቁ አንቆ ይዞታላ።

እኛም ክርስቶስ የነፍሳችን መልህቅ ነው ። ከዚህ ምድር ለሚደርስብን እንግልት መከራ የሚታደገን እንደ መልህቁ ወደ ውሃ ውስጥ ሳይሆን ወደ ላይ ወደ አባቱ ዘንድ ወደ ሰማይ ገብቷል ።አሁን መልህቃችን ሰማይ ገብቶ አስገብቶናል መከራ ቢመጣ ይገፋናል እንጂ አያጠፋንም መልህቃችን ኢየሱስ ከሰማይ ጋር አገናኝቶናል !!⚓️

መልህቄ ⚓️ መልህቄ
ኢየሱስ መልህቄ
ላትለቀኝ የያዝከኝ
የእግዚአብሔር ልጅ ፅድቄ
⚓️⚓️⚓️⚓️⚓️⚓️⚓️⚓️

.............


መርከቢቷ አቅቷት
ሚዛኗ ሲዛባ
የነፍስ መልህቅ ⚓️
ሊቁ ቀድሞን ገባ

@ownkin
@cgfsd
በክርስቶስ ያለ ስሙ በኢየሱስ መዝገብ ስር ከህይወት መፀሀፍ ላይ ተፅፆፏል!!
ትኩረት ወደ ኢየሱስ !!
ስርየት
(1ዩሀ 2:12)



በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
#የአብን ቁጣ አበረድክልኝ #የቅጣቱን እጁን ተቀበልክልኝ #ለእኔ የተገባውን ሆኖ በአንተ ላይ #ሆንክልኝ ፅድቄ አብ ፊቱን እንዳይ


ዘማሪ አስቴር አበበ
#በስራ ብዛት ላይ ደምቅ ቤቱ #ያንዴም ለሁሌም ረክቷል አባቱ #የአንድኛ ልጁ ንፅሁ ደም ቀርቦ #ደምቋል ህይወቴ ታይቷል ተውቦ


ዘማሪ አስቴር አበበ
( ከማስታወሻዬ ማስታወሻ)

ከሰሞኑን በተደጋጋሚ የሰማኋቸውን የክርስቶስን የመዋጀት ስራ ላይ በማተኮር የተዘመሩን መዝሙሮች በማስታወሻዬ ፅፌ ነበር ።
................

( አስቴር አበበ)

#የአብን ቁጣ አበረድክልኝ #የቅጣቱን እጁን ተቀበልክልኝ #ለእኔ የተገባውን ሆኖ በአንተ ላይ #ሆንክልኝ ፅድቄ አብ ፊቱን እንዳይ
................
(ሰላም ደስታ)

#ፀጋው በእምነት አድኖኝ ....
#ኢየሱስ ፅድቁን አልብሶኝ...
#ስለእኔ በአብ ፊት ታይቶ ....
#ፈፅሞታል ስራዬን ጨርሶ..
..........

(ሰላም ደስታ)

........ #የበግ ደም አይደለም ያነፃኝ
#አብን እንዳየው ፀጋው ነው የረዳኝ

..............
(ህሊና ዳዊት )

#እኔም ኢየሱስን ለብሼ #አብ ፊት ሞገስ አገኘው !!
.................
(መስከረም ጌቱ)

#ኢየሱስ ያድናል #አዎን አድኖናል
ከፊት እየመራ 😍
ወደ ፅዮን ያደርሰናል

..............
(ዘመናይ ጎሳዬ)

#አባትነት ከሚሰየምበት #ከአብ ፊት እንበረከካለሁ #በልጁ ለሚያየኝ የልቤን አስታወቀዋለሁ
...................
( አዲሱ ወርቁ )

#እኔ በበኩሌ ከእኔ ነው የምለው
ምንም ታሪክ የለኝ
#በመስቀል ላይ ሁኖ ተጠማሁኝ
ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ

.........................
(በረከት መገርሳ)

#ከህይወቱ ብዙ መማሬ ሳያንሰኝ
#ትንሳኤ ድጋሚ ወደድኩት አነፀኝ
አቤት የኔ ረቡኒ .....

@ownkin
@cgfsd
ሕይወት ተገልጧል እኔ አይቻለሁ
#በአንድ ልጁ ሞት ተዋጅቻለሁ #ስለ አብ ፍቅር ተሰልፊያለሁ !!

(ሀዋዝ)
የመጀመሪያው አዳም ምድርን እንዲገዛ ተስጥቶት ነበር ቢሆንም በውድቀት ሳቢያ በፍፅምና ሊገዛ አልተቻለው !!! የኋለኛው አዳም (ክርስቶስ) ግን በማያልፍ ሃይል በማይገረሰስ ጉልበት ድል በመንሳቱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይገዛል እኛም እንገዛለታለን!!!
ህብረትን ማጣጣም
መዝ133

ክርስቶስ የመሰረተው ህብረት ግሩም መአዛ እና የሚያወድ ጠረን አለው ።እሱን እናጣጥም !!!

በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
#መልካሙን የእምነት ገድል ተጋድዬ🏃‍♂ #እንዳልፍ እርዳኝ ኢየሱስ ጌታዬ🙏
ክርስቶስ ገብቶበት ትርጉም የማይሰጥ የህይወት እንቆቅልሽ የለም ።

Aman shalom
ደቀመዛሙርትነት ዘወትር በመምህሩ ኢየሱስ ክርስቶስ እየተገረሙ እና እየተደነቁ መኖር !!
ክርስቶስ ማለት የተቀባ ማለት ነው ስለዚህ የተቀባውን ክርስቶስ ስንጠራ ቀቢውን አብን.. ቅባቱን መንፈስ ቅዱስም እያነሳን መሆኑን ማወቅ አለብን ።

(ሙሽሪትን ለሙሽራ በሔኖክ ኢሳይያስ )
ክርስቶስ ወደ እራሱ አደረሰን !!!እሰይ እሰይ ራሱ ክርስቶስ በራሱ ስራ ፣በራሱ ደም፣ በራሱ ፀጋ፣ በራሱ አቅም ፣በራሱ ምህረት ፣ በራሱ ፍቅር ወደ ራሱ አደረሰን !!!

ዕብራውያን 12 (Hebrews)
24፤ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


@ownkin
@cgfsd