በክርስቶስ ( in christ)
820 subscribers
99 photos
33 videos
40 files
38 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
( ውብ ትዕዛዙ 📖 )


1 ዮሐንስ 2 (1 John)
3፤ ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።

ዩሀንስ ትዕዛዝ ፣ትዕዛዙን የሚሉ ቃላት በወንጌልም በዚህም መልዕክት ውስጥ በተደጋጋሚ ይጠቀማል ።ትዕዛዝን ብቻ አይደለም እወቁ ፣ማወቅ፣እናውቀቃለን የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ፅፎታል ። ዕውቀትን የፃፈበት ምክኒያት ኖስቲዝም አስተማሪዎች እውቀት ብቻ ነው የሚያድነው ብለው ለሚያስተምሩ ነው ።ኖስቲዝም ማለት እራሱ ዕውቀት ማለት ነው ትርጉሙ ። ስለዚህ እነዚህን ቃላት ደጋግሟል በትክክል ለማስረዳት ነው ።እንደ ኖስቲዝም እግዚአብሔር ማወቅ የአይምሮ እውቀት የጠለቀቀ ማብራራት ፣ሀሳባዊነት ብቻ ሳይሆን ዩሀንስ የሚነግረን እግዚአብሔር ማወቅ ከውስጥ በመነጨ ትዕዛዙን በመጠበቅ ነው ።እግዚአብሔር ማወቅ ከንባብ ወይም ከመማር የሚመጣ "ፐ" የሚያስብል ምጥቀት አይደለም ። እግዚአብሔር ማወቅ ከህብረት (fellowship ) ነው የሚጀምረው ። ትዕዛዙን የጠበቀ በእርግጥ እግዚአብሔርን ያውቃል ።

እግዚአብሔር ማወቅ = ኢየሱስን ማመን + መታዘዝ + በፍቅር መመላለስ

ትዕዛዜን ጠብቁ ሲል ታዛዥ ሁኑ ታዘዙ እያለ ነው ። በእንደ ክርስቲያን መታዘዝ የእምነት ውጤት ነው ። ክርስቶስ እንደ ግል አዳኙ ያረገ ሰው እሱ እግዚአብሔርን ታዟል ። የመጀመሪያው የታዘዝነው ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን ያመንን ጊዜ ነው ።ያኔ በእምነት ለሚገኘው መታታዝ እጃችን ሰጠን ። ለእሱ ለመኖር ጀመርን ታዘዝን በእምነት ምክኒያት ።

አንድ ሰው በሚሰራበት መስሪያ ቤት ፣በሚማርበት ትምህርት ቤት፣ በሚኖርበት ቤት ..አለቃ ለሰራተኛው ፣አስተማሪ ለተማሪ ፣ ወላጅ ለልጆች የሚያዙት ትዕዛዝ አለ ያንን መፈፀም አለባቸው እንዲፈፅሙ የሚያስችላቸው እንዲታዘዙም የሚያደርጋቸው በመካከላቸው ያለው ህብረት ነው ያ ህብረት እና ግንኙነት እንዲታዘዙ ግድ ይላችኋል ። እኛም ከአባት ከልጁም ከኢየሱስ ጋር ህያው ህብረት ስላለን ወደደን እንታዘዛለን ።

ትዕዛዙ ግን ምንድን ነው ????

ትዕዛዝ ሲባል ቀድሞ የሚታወቀው መካከል 10ቱ ትዕዛዛት ነው ። እነዚህ ትዕዛዝ ለእስራኤል ሲሰጥ ከሰው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ለማረግ እነዚህን ትዕዛት እየፈፀመ ነው ።

አሁን ዩሀንስ ሊነግረን የፈለው ትዕዛዝ አለ !!!ያ ትዕዛዝ ፍቅር ነው !!!!!😍😍 ፍቅር ፣ፍቅር ፣ፍቅር ነው ትዕዛዙ ። እግዚአብሔር ግን ምን አይነት አምላክ ነው ያዘዘን ፍቅርን ነው ።
ዮሐንስ 15 (John)
12፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።

ዮሐንስ 13 (John)
34፤ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
35፤ እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።

ዮሐንስ 15 (John)
9፤ አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።
10፤ እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።

ጌታ የሰጠን ትዕዛዝ ይቺ ናት 👉 በፍቅሬ ኑሩ !!! በፍቅር ኑሩ ሲባል ሌላ ፍቅር እንዳንፈልግ እራሱን ፍቅሩን ሰጠን ፣ፍቅሩን አቀመሰን ወደ እኛ አስጠጋው እና በቀመሳችሁት በእኔው ፍቅር ኑሩ አለ ። ፍቅሬ ኑሩ አለ ይሔ ነው በቃ ትዕዛዙ ። አንድ ሰው እግዚአብሔር ማወቁ የሚተወቀው በእውቀት ጥልቁ ሳይሆን በፍቅር ስፋቱ ነው ። እግዚአብሔርን ይወዳል ወይ ??? ሰውን ይወዳል ወይ ??አዎ ከሆነ መልሱ እግዚአብሔርን ያውቃል ። ለምን ፍቅር እግዚአብሔር ማወቂያ መንገድ ሆነ??እግዚአብሔር ፍቅር ነዋ እኛን ያዳነን በፍቅሩ ነው ፍቅር ግድ ብሎት ነው ።

የእግዚአብሔር ፍቅር በደንብ ወደ እኛ ሊደርስ የቻለው ሁሉ በክርስቶስ መታዘዝ ነው ። ክርስቶስ የመታዘዝ ጥግ ነው ። መስቀል የመታዘዙ ወጤት ነው ...መዳናችን የመታዘዙ ውጤት ነው....ወደ ምድር መምጣቱ የመታዘዝ ውጤቱ ነው ...መሞቱ የመታዘዙ ውጤት ነው ። ኢየሱስ አባቱን አባ የታዘዘው ፍቅር ግድ ስላለው ነው። አባቱን ይወደዋል ደግሞም እኛም ይወደናል ። የመታዘዝ ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው። እኛም ትዕዙዙን(ፍቅሩ )እንታዘዛለን ደቀመዛሙርት ነን እና

10ቱ ትዕዛዝ ሆነም ሌላው ትዕዛዝ ህግ ዋና አለማቸው ፍቅር ነው ። አስርቱ ትዕዛዝ ሲጨመቁ የሚወጣቸው እንዲህ የሚል ነው ..

ማቴዎስ 22 (Matthew)
36፤ መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው።
37፤ ኢየሱስም እንዲህ አለው፡— ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።
38፤ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።
39፤ ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፡— ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።
40፤ በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።

#ትዕዛዙ ፍቅር ነው ያልነው በዚሁ አግባብ ነው ።

ሮሜ 13 (Romans)
8፤ እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።
9፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በውሸት አትመስክር፥ አትመኝ የሚለው ከሌላይቱ ትእዛዝ ሁሉ ጋር በዚህ፡— ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ፥ በሚለው ቃል ተጠቅልሎአል።
10፤ ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ አያደርግም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።

...እንዋደድ !!! ትዕዛዙም ያ ነው !!!
በፍቅሩ እንኑር🏃‍♂እንመላለስ🚶

@ownkin
@cgfsd
(ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን !!)
ዩሀ 12:20

ክርስትና ኢየሱስን በማየት የምንመላለስበት ህይወት ነው ።


በፊሊሞን ነጋ
@cgfsd
@ownkin
ያንተ ልታደርገን 🤗 እኛን ለመሰልከው🙏 ክበር
ለሰላም ፣ለፍቅር ፣ ለተስፋ ፣ለማዳን፣ ለማፅደቅ ፣የራሱ ለማረግ ፣ ወዳጅነት ለመፍጥር ደም የተቃባው አምላካችን እግዚአብሔር ብቻ ነው !!!
የትኛው ደም መፍትሔ ሲሆን አልታየም ። እንደው እርስ በእርስ መጠራጠሪያ ፣ እርስ በእርስ በበቀል ፣ ለመገዳደል የሚያነሳሳ ...የሚያቅበዘብዝ ፣ ሰውን ከሰው የሚያራርቅ ፣ በአንዱን ከሌላው የሚያናክስ ።
የመድሃኒታችን ኢየሱስ ደም በዘላለም መንፈስ የቀረበ ሰውን ከአምላኩ ጋር በሰላም ያወዳጀ ፣ የሰውን ኩነኔ ወደ ፅድቅ የለወጠ ፣ ኑ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበ ፣ ከሀጢያት የሚያነፃ ፣ መተማመኛ ዋስትና ያለው፣ ከወርቅ የከበረ ከብር የተወደደ፣ ንፁህ ደም ነው ።
ኢየሱስ ኢየሱሴ መገረሜ ነህ መደነቄ
መንፈስ ቅዱስ በውስጤም እያለህም ታስፈልገኛለህ !!
ፀረ ክርስቶስ በመጨረሻው ዘመን ተግዳሮት እንደሆነ ከቅዱሱ ቃሉ ከተገነዘብን ፤ እውነተኛው ክርስቶስ ምን ያህል የእግዚአብሔር መልዕክት እንደሆነ እንመለከታለን !!!!
ከክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ጋር መተባበር ማለት እርሱ እኛን ለማዳን ከእኛ ጎን እንደቆመ ሁሉ ከዚህ በኋላ ለራሳችን ላንኖር ከእርሱ ጎን የምንቆምበት ነው ።
የፀሎት ርዕስ :-

" ልባችን ይጓዝ"

2 ተሰሎንቄ 3:2 Thessalonians)
5፤ ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።

ይሔን ፀሎት ቅዱስ ጳውሎስ ነው የፀለየው !!ትልቅ ፀሎት ነው ከዚህ በላይ ምን ይፀለይ ይሆን ???ልባችን በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፣ ጥልቀት ፣ስፋት ፣ርዝመት ባለው ሀያል ፍቅር ከመረስረስ በላይ እና እንደተወደድን ከማወቅ እና ሌሎችን በዚህ ፍቅር እየወደድን ከመኖር በላይ ምንም የለም !!!ደግሞም ወደ ክርስቶስ ትግስት ልባችን ወደዛ ሲጠጋ ..ያ የክርስቶስ ግሩም ትዕግስት በመስቀል ላይ ነውርን ንቆ የታገሰልን ስለ እኛ መዳን የገለጠው እንዲህ ነው የማይባል ትዕግስት !!

ልባችን ወደ ፍቅሩ እና ወደ ትግስቱ ያቅናው
መስቀል ላይ ዋጋችን ተተምኗል እሱም ሞት ነው !! ሙተናል ከዚህ በኋላ ለራስ መኖር አበቃለት አሁን ላዳነን ፣ለተቤዥን፣ ለወደደን፣ ራሱን ለሰጠልን፣ ለሞተልን ክርስቶስ ፈቃድ፣ ዓለማ ፣ዕቅድ ነው የምንኖረው!!

ክርስቶስን ስንቀበል ለራሳችን መኖር እናቆማለን ..ለራሳችን የምንኖር ከሆንን የክርስቶስ መስቀል አልገባንም ማለት ነው !!!
ቤተክርስቲያን ከዘላለማዊ መንግስት ተካፋይ ናት ።ምክኒያቱም ኢየሱስ ራስ ነው ። ራስ የሆነው ጌታ ሲገዛ አካል አብሮ ነው ። ጌታ ኢየሱስ ሙሽራ ነው ።ባል ወይም ሙሽራ ሲገዛ ሚስት ወይም ሙሽሪት ትገዛለች ።

ኤርሚያስ መለሰ
የእግዚአብሔርን የትዕግስቱ ባለጠግነት በመስቀል በማይሸሸግ መልኩ ተገለጠ ።
* እግዚአብሔር የሀጢያትን ሂሳብ እና የቁጣውን በትር ለማወራረድ እስከ መስቀል ድረስ ታግሶ ቆየ (ሮሜ3:25-26)

* ክርስቶስ ነውር ንቆ በእንጨት ላይ ተሰቀለ፣ ለባህሪው ያልተገባው ሞት እና ቦታ ላይ ስለ ሰው መዳን ታግሶ ቅጣቱን ተቀበለ (ዕብ 12:2)
መንፈሳዊ ህይወት በራሱ በእግዚአብሔር ከመርካት የሚጀምር ህይወት ነው ።

(ከአየር የተዘገኑ)
በእግዚአብሔር ያልረካ ሰው በነገር ሁሉ ተቅበዝባዥ ነው ።

ስንታየሁ በቀለ
ስላም የተወደዳችሁ የዩሀንስ ወንጌል ጥናት በድምፅ (voice) እንጀምራለን !!በዚሁ አጋጣሚ ሀሳባችሁን comment ላይ ብትሰጡ እና መፀሀፍ ቅዱስ ማጥናት እየፈለጉ ግን እንዴት እንደሚጠና ላላወቁ በጌታ ፍቅር አድርሱልኝ !!!
ዮናስ ወደ ነነዌ ተልኮ እንቢ አሻፈረኝ አልታዘዝም ብሎ ወደ ጠርሴስ የሄደው እግዚአብሔርን በቸርነቱ፣በይቅር ባይነቱ ፣በበዛ ምህረቱ 👉 ጠርጥሮት ነበር ።
በበዛ ምህረቱ የሚጠረጠረው እና የሚታማው እግዚአብሔር ብቻ ነው !!!

ዮናስ 4 (Jonah)
2፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና፡— አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።

@ownkin
@cgfsd
( ሶሻል - ሚጥሚጣ )

ሶሻል ሚጥሚጣ ይቅርታ ማለቴ ሶሻል ሚዲያ !!! በተመለከተ ነበር የዛሬ ቀን አሰላስሎዬ ። የቀን ውሎህን መዝገብ ተብዬ በተሰጠኝ ሸንቋጭ ምክር መሰረት እንደወረደ እፅፋለሁ ..አሁንም ድጋሚ ይቅርታ እንደወረደ ለካ ለካፊቴሪያ ቡና ነው ።

ቅዳሜ ቀን ሲነሳ ምን ይነሳል ??? የማይዘነጉ ሁለት ነገሮች ናቸዋ ... ገበያ እና የወጣቶች ፕሮግራም ። የቅዳሜ የወጣቶች መርሃ ግብር ለመቋደስ ነበር ወደ መሪ ብርሃን መሰረተ ክርስቶስ አጥቢያ የከተምኩት ። በዝናብ ምክኒያት ያረፈድኩ በመሆኑ አምልኮ ሊጨረስ ሲል አካባቢ የደረስኩት ። የክፍሉ ተራ የስብከት ሆነና የሚያስተምረው ወንድም ምስባኩት ተረከበ ።እንደ ነገሩ ስለ መጣበት የአገልግሎት መስክ የወፍ በረር ገለፃ አድርጎ ። የዛሬው የሚያስተምረውን ቱባ ርዕሰ ጉዳይ ወደ ሸራው ደቅኖ ባዘጋጀው ፕሮክተር በኩል በቪዲዬ አሳየን እንዲህ ይላል " digital puberty " ስለ ማህበራዊ ድረ ገፅ አጠቃቀም እንደሆነ #ወዲያውኑ ገባኝ... ወዲያውኑ የሚለውን ቃል ከቅዱስ ማርቆስ ወይም ከማርቆስ ወንጌል ነው የተዋስኩት ማርቆስ ወንጌል ወዲያውኑ የሚለው ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል ። ብቻ ካስተዋወቀን በኋላ ስለምን ሊያወራን ይሆን በማለት ሀሳቤ ብዙ ቦታ ፋነነ(ተቅበዘዘ) ። ቀልቤ የገዛውን አንድ ነገር ብቻ ልናገር ....

ወደ ምዕመናኑ አነጣጥሮ በቀን ውስጥ አንድ ሰው ከስልኩ ጋር ፣ከቲቪ ፣ከላብቶፕ ፣ ታብ ፣ አይፓድ ብቻ ከዲጅታል ጋር 7 ሰአት ያሳልፋል አለ ። ከጉባኤ አንዱን ወንድም ስንት ቀን ቤተክርስቲያን ታሳልፋለህ በሳምንት በማለት ጠየቀው?? መልሱ 3 ቀን !!
እሺ ለስንት ሰአታት ?? ለ2 ወይም ለ3 ያክል ... ቀጠለ ይሔ ማለት በሳምንት 9 ሰአት ነው ። ለማህበራዊ ድረገፅ ደግሞ 49 ሰአት በሳምንት እናሳልፋለን ስለዚህ መንፈሳዊ ስራዎቻችን ከ49 ሰአቱ ምን ያህሉ ናቸው ?? ቤተክርስቲያን ዘመኑን አንድታይ የትዬለሌ ጉዳዬች ጠቁሟል ።

...............................

ከፕሮግራም በኋላ ቀኝ ወደ ኋላ ዙር ይላል ሰአቱ እኛ ወደ ቤት መሄድ ግድ ስለሚሆንም ወደ ኋላ ዙረናል ለመሄድ ። በአንድ talk show ፕሮግራም ላይ ሙግት ላይ እንደነበርን ከመካከላችን ሙግቱን ለመርታት አንድ ወዳጃች አንድ ጥያቄ ጠየቀን .." ከዚህ ፕሮግራም በኋላ ለምን ወደ ቤታችሁ ትሄዳለችሁ ?? በማለት ጠየቀ ። ብዙ ብዙ መለሱ አይደለም አለ ጠያቂው እናስ ሲባል ቤቱ ወደ እናንተ ስለማይመጣ ነው ወደዛ የምትሄዱት ብሎን ቁጭ አለ ። ብቻ ዛሬ ምንም ይሁን ምንም ወደ ቤታችን ለመሄድ መንገድ ጀምረናል ። እሰከ ተባበሩት (ይሰመርበት የተባበሩት ነጃጅ ያለበት ሰፈር ነው የተባበሩት መንግት እንዳልሆነ ይታወቅልኝ) ለመሄድ ከፓስተር አቤኒ እና ከአንዲት እህት ጋር ጉዞን ተያይዘናል ። የዛሬንውን ትምህርት አንስተን ማውጋት ጀመርን ..... ፓ/ር አቤኒ እንደዚህ ሀሳብ ሰነዘረ " ቤተክርስቲያን በማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ የለቀቀችው ተደምሮ የፓሮግራፊ ቪዲዬ ሩብን ካልሆነ ምን ያህል አሁንም መስራት ቪዲዬ መለቀቅ በድረገፅ መንሳቀስ በጣም ይጠበቅባታል !! የሚል ሀሳብ አጋራኝ እሱን ከተለየሁት በኋላ ከምናቤ ጋር እየተነጋገርኩ መንገዴን አዘገምኩ ......
...................
ሲሻል ሚጥሚጣን (ሶሻል ሚዲያን መዋጀት አለብን ። ሚጥሚጣ ሁለት አንኳር ጠቀሜታዎች አሉት ምንም ቢያቃለጥል ለምግብነት ይውላል በአግባቡ ከመጠን ሲያልፍ እና ካላወቁበት ይፋጃል የቃጠሎን መአት ያዘንባል ።

በቅርቡ የምንወደው ዘማሪ ጋሽ ታምራት ሀይሌ ወደ ሶሻል ሚዲያ በይፋ መቀላቀሉን አብስሮን ነበር ።የገባበትም ምክኒያት እንደዚህ ይገልፀዋል ።
" በሚመጣው ትውልድ ዘመን ከሶሻል ሚዲያ ውጭ መሆን ስለማይቻል " የሚል ገንቢ ምክኒያት ሰጥቷል ። እውነት ነው ቀጣይ ትውልድን ቤተክርስቲያን ስታስብ ሶሻል ሚጥሚጣን በመያዣው በኩል መያዝ አለባት ። መያዣ ማለት የሻይ ብርጭቆ ትኩስ እንዳይሆን በቤተሰብ ሲቀርብን ቀድመን የምንመርጠው መያዣ ያለው ..እንዳያቃጥለን ስለዚህ በመያዣው በኩል ቤተክርስቲያን መያዥ አለባት ።

መጋቢ አስፋው በቀለ ደግሞ እንዲህ ሀሳብ ይቸሩናል
"እነ ጳውሎስ ሮም በሰራው መንገድ እየሄዱ ወንጌል ሰብከዋል እኛም በተሰራው ቴክኖሎጂ ለወንጌል እናውለዋለን "
እኔ በመጋቢው ሀሳብ እስማማለሁ ። መንገድ ሁሉ ወደ ሮሜ ይወስዳል በተባለበት ዘመናት ሐዋሪያት ወንጌል ለማድረስ እንደሰሩ አለምን አንድ መንደር ባረገው ሶሻል ሚጥሚጣ እንዴት አንሰራ ??!

የዛሬ አሰላስሎ ይሔን ይመስላል ግን ተከታታት ፅሁፍ በዚህ ዙሪያ በክፍል (part) አዘጋጃለሁ !!ወሳኝ ነው እና

ይቀጥላል ........

ሁሉን ነገር ከእግዚአብሔር ክብር አንፃር መመዘን ..


ሰኔ 11 /2014 .ቅዳሜ


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እግዚአብሔር ለእኔ ያለውን የዘላለም ሀሳቡን በኢየሱስ ገለጠልኝ አሳየኝ ድንቅ ፍቅር !! .... አባቱ እንደወደደው ወደደኝ!!

(#ከእንዳውቅህ አልበም)

@ownkin
@cgfsd