በክርስቶስ ( in christ)
711 subscribers
98 photos
33 videos
40 files
38 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
ከቆላስይስ መልዕክት ጥናታችን ሁለት ቁጥሮችን አንስተን እንመልከት:-

“በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና። ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።” (ቆላ. 2:9-10)

1. “በእርሱ (በክርስቶስ) የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራል” ይላል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ማንነት በጥልቀት ካስተማረባቸው ክፍሎች አንዱ ይህ ክፍል ነው። የቤተልሄሙ ሕጻን የናዝሬቱ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም በገሊላና በቅፍርናሆም አካባቢዎች በእግሩ እየተመላለሰ በመቅደስና በምኩራቦች ሁሉ ሲያገለግል የነበረ ሰው ማን መሆኑን በደንብ ያብራራበት ክፍል ነው። ክርስቶስ በሥጋው ሰውነት የተገለጠ መለኮት ነው የሚል ትምህርት ነው። ክርስቶስ the true embodiment of the invisible God መሆኑን “እርሱ የማይታይ አምላክ ምሳሌ” ነው በማለት ከላይ በሚገኙ ክፍሎች ሲናገር ነበር “እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። … በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።” (1:15-16)። መንፈስ የሆነውን አምላክ በሰው ሰውነት የገለጠ አምላክ ነው ይለዋል ክርስቶስን።

ይህንን እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ራሱን በሙላት ለሰው ልጆች የገለጠበትን መንፈሳዊ ምስጢር መረዳት ለክርስትና እምነታችን አምድና መሠረት ነው። In Christ we find the fullness of God - ክርስቶስ የተገለጠለት ሰው ሌላ መገለጥ አያስፈልገውም ምክንያቱም ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ (በክርስቶስ) ነውና።” (ቆላ. 2:3) የሰውን ልጅ ለማዳን ክርስቶስ ብቻውን በቂ አለመሆኑን ለማስረዳት ለሚጋጋጠው የዘመኑ ከንቱ ፍልስፍና የሐዋርያው ጳውሎስ መልስ “በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦአል” የሚል ነው። ክርስቶስ በሥጋ የመጣ እግዚአብሔር (አምላክ) መሆኑን ማወጁ ሐሰተኞች ለሚያራምዱት ከንቱ ፍልስፍና ራስ ምታት ነው። ክርስቶስ የሰውን ዘር ከጨለማ ሥልጣን ማዳኑ፥ የኃጢአትን ስርየት ማስገኘቱ ሁሉ በዚህ ማንነቱ ላይ የተመሠረተ ነው። ሰው ብቻ ቢሆን ሰውን ማዳን (መዋጀት) አይችልም ነበርና።

የርሱን አምላክነት አሳንሰው ሲያቀርቡ የነበሩ እነዚያ የሐሰት መምህራን የቆላስይስ አማኞች በክርስቶስ ብቻ እንዳይረኩ (እንዳያርፉ) ሊያደርጉ ተጨማሪ ነገሮችን በማቅረብ ሊያስቱ ይሞክሩ ነበር። ጳውሎስ ግን “ማንም በሚያባብል ቃል እንዳያስታችሁ ይህን እላለሁ።” በማለት ክርስቶስ በቂ ሊሆን የቻለበትን ሁኔታ ሲያቀርብ እርሱ ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክን በሙላት የገለጠ ሰው ነው ይላቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ጉዳት የሌለባቸው የሚመስሉ የሰው ወጎችና ልምምዶች (ትምህርቶችና ፍልስፍናዎች) የክርስትና እምነት ዋና የሆነውን ነገር ለመናድ ሲሞክሩ ይስተዋላሉ። ይህ ዓይነት ሁኔታ ሲከሰት እንደ ጳውሎስ ግንባርን ሳያጥፉ ፈርጠም ብለው በመውጣት ይህንን ልምምድና ፍልስፍና ወግድ ማለት የወንጌሉን እውነት ከፍ አድርጎ ማሰማት ተገቢ ይሆናል። ሐዋርያው ይህንን የክርስቶስን እውነት በከንቱ ፍልስፍና ላለማስደፈር ካሳየው ብርቱ ጥረት ብዙ የምንማረው ነገር አለ። እርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ የሚኖርበት አምላክ መሆኑን ለመናገር አንዳች አላመነታም። ይህ ትምህርት ቸል መባል የሌለበት የክርስቲያን ዶክትሪኖች ሁሉ ቁንጮ ነው ባይ ነኝ።

2. “… በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል” ይላል።

ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቶስን ማንነት በሚመለከት በሥጋው መለኮትን በሙላት ለሰው ልጆች የገለጠ መሆኑን በማንሳት አላቆመም አማኞቹም በርሱ ምሉዕ መሆናቸውን አስከትሎ ተናግሯል። የቆላስይስ አማኞች ጉድለት (ባዶነት) እንዳይሰማቸው ከዚህም የተነሳ በክርስቶስ ላይ ሌላ ነገር ለመጨመር ሲንከራተቱ እንዳይገኙ ክርስቶስ በቂያቸው መሆኑን ለማስረዳት ይህንን ብሏል። በርሱ መሆን መሞላት ነው። ክርስትና ልዩ ጣዕም ያለው የመርካ (የማረፍ) ሕይወት የሚሆነው በክርስቶስ በቂነት ማመንና መተማመን ሲቻል ብቻ ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች በአይሁድ በኩል ለሚመጣው ኃይማኖታዊ ወግና ሥርዓት እንዲሁም ደግሞ በግሪክ በኩል ለሚመጣው ጥበብና ምርምር፣ ሌሎችም ከሌላ አቅጣጫ ለሚያመጡት መንፈሳዊ መሳይ ምስጢራዊ ልምምድ ሁሉ ልባቸውን ሰጥተው እንዳይዋከቡ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስቶስ መሆን ማለት መሞላት ማለት ነው ይላቸዋል። ይህ የዘላለም እውነት ነው።

እነዚያ ሐሰተኞች በትምህርታቸው ክርስቶስ የተወሰነውን አንተ ደግሞ ቀሪውን ስትፈጽም ነው ድነትህ ፍጹም የሚሆነው የሚል ዓይነት ጎዶሎ ወንጌል ነበር የሚሰብኩት። ለመዳን ያንንና ይህንን ማድረግ መሆን ይኖርባችኋል ይሏቸው ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ ግን ምን ይላቸዋል? “you are complete in Christ” ነው የሚላቸው። ፍጽምና ምሉዕነት በሰው ሥራ የሚገኝ አይደለም። ማንም የማንንም ጉድለት ሊሞላ አይችልም። በቀራኒዮ ስለ ሰዎች ልጆች ብሎ በመስቀል ላይ የሞተው ክርስቶስ በሠራው ሥራ ስናምን ያን ጊዜ በክርስቶስ ጉድለታችን ይሞላል fullness and completeness ይሆንልናል። ይህ የዘላለም እውነት ነው። መርጋትም መረጋጋትም የሚመጣው በክርስቶስ በመሆን ብቻ ነው። ምንም ማንም ሊሞላ የማይችለውን የሰውን ልጆች ክፍተት የሚሞላው በሥጋው መለኮትን በሙላት ገልጦ የሚኖረው ክርስቶስ ብቻ ነው። እርሱ የበላይ (supreme) ነው እርሱ በቂ (sufficient) ነው።

አንዳንድ ጊዜ በክርስቶስ ስላለን ማንነት በደንብ የማንረዳው በቅድሚያ ስለ ክርስቶስ ያለን መረዳት የተዛባ ስለሚሆን ነው። ክርስቶስን በማንነቱ በሙላት ቃሉ እንደሚለው ስንረዳ በክርስቶስ ያገኘነው ማንነት ከቶ አይጠፋንም መቼም አይቀልብንም። ለዚህ ይመስለኛል ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሙላት መሆኑን ከተናገረ በኋላ ወዲያው እናንተም በርሱ ተሞልታችኋል የሚለው። ክርስቲያኖች ስለራሳችን ያለን እይታ በእኛ በሚኖረው በክርስቶስ ማንነት ላይ ሳንመሠርት ስንቀርና (ስለራሳችን ያለን ግምት ዝቅ ሲል) ጉድለት ሲሰማን እረፍት የማይኖረን ያም ይህም እንደ ገለባ ተሸክሞ የሚወስደን ቀላሎች እንሆናለን። ለሐሰት ልምምዶችና ፍልስፍናዎች የተጋለጥን የሁሉንም ማታለያ የምናምን መዝነን አመዛዝነን ማየት ወደማንችልበት ደረጃ የወረድን እንሆናለን። “በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል” የሚለው ለአማኝ ሁሉ የሚሠራ የክርስቲያን ማንነትና ትርጉም ነው። እርሱ ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ ነው እኛም የተሞላነው በርሱ ነው።

Hallelujah….
የክርስትናን እምነት ልዩ የሚያደርገው ምንድነው? በክርስቶስ መሆናችንና ክርስቶስ በእኛ መሆኑ ነው።

ይህ እውነት ነው።

ክርስቶስ በኔ ሙሉ ነው።

ክርስቶስ በኔ ፍጹም ነው።

ጉድለት አይሰማኝም። ሌላ አልሻም።

አምኜዋለሁ ከቶ አልናወጥም።


workneh
ወልድ ተዛመደ ህዝቡን ተጠጋጋ
ገንዘቡ አደረገ  የሰውን ልጅ ስጋ

@ownkin
@cgfsd
ፍንትው አለ  አየነው ያየንን
የፅድቅ ፀሃዩ ኢየሱስ ወጥቶልን

@cgfsd
@ownkin
“የጸጋው ጅረት በትሕትና ዝቅ ወዳለ እንጂ ወደ ዕቡይ ልብ ሽቅብ አይወጣም።”
ቅዱስ በርናርድ
መልኬን በመልክህ ላይ ቀራንዮ አይቼ
እንዴት ዝም ልበል ፍቅርህን ጠጥቼ


🎼
@cgfsd
@ownkin
ግድ የለም ስለ ብዙ ነገር አይግባን እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሰራልን ስራ ግን በቅጡ እንረዳ ።

@ownkin
@cgfsd
Forwarded from Meareg Taye
filye.aac
27 MB
"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"

ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...።

የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል።

ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር።

እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት [ፍጹማን] ክርስቲያኖች ስለሆኑ አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም አስከባሪዎች ነበሩ።

አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!...

በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን።

ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ
አዲስ ኪዳን የአሮጌውን ኪዳን እንኳን የበለጠ እንድንረዳ የሚያደርገን መክፈቻ ቁልፍ ነው ።

(የክርስቶስ ትንሳኤ ገፅ 43)

@ownkin
@cgfsd
የእግዚአብሔር ልጅ ክፍል አንድ
<unknown>
ይሔ ድንቅ መፀሃፍ ነው በትረካ ብትሰሙት ታተርፋላችሁ ። ኢየሱስን በተመለከተ አስደናቂ ስራ ነው ። የኢየሱስ ማንነት ለፈለገ እጅግ ግሩም መፀሀፍት ነው ።

@cgfsd
ያበጃጁኝ እጆችህ እንዴት የተዋቡ ናቸው
የደሙልኝ እጆችህ እኔንም ያቀፉ ናቸው
ዛሬም መተህ በኔ ላይ ጌታ ሆይ ጫናቸው😭


🎼😍

@cgfsd
@ownkin
ኢየሱስን መውደድ የአንድ ጊዜ ውሳኔ ወይም ስሜት አይደለም።

ኢየሱስን መውደድ በየቀኑ በየሰዓቱ በየደቂቃው የምመርጠው ምርጫ ነው።

ለኢየሱስ ፍቅሬን ምገልጥለት እና ማሳየው በእያንዳንዱ ቀን እና ጉዳይ ላይ በምወስነው ውሳኔ ነው።

ለምንድንነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፍላጎት ብቻ ምታደርገው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!

ለምንድነው የራስህን ፈቃድ እና ፍላጎት ማታደርገው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!

ለምንድነው ለአባትህ ደስታ እና ሳቅ እንደዚህ ምትጨነቀው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!

ለምንድነው ደስ እንዳለህ ማትኖረው?
*ኢየሱስን ስለምወደው!!

ስለምወደው    ስለምወደው
ጌታ ኢየሱስን ስለምወደው

ለክርስቲያን ለምን ተብሎ ሲጠየቅ እጅግ ውብ የሆነ ምክንያቱ "የወደደኝን ኢየሱስ ስለምወደው ነው" ነው።


* ኢየሱስን ስለምወደው
Audio
የሰው ልጅ የሚያመጣው ፅድቅ የመርገም ጨርቅ ነው ።እግዚአብሔር ያመጣው ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።


@cgfsd
@ownkin
Forwarded from HUFELLOW
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የፌሎአችን ልጆች እንዴት ናቹ?

🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

እነሆ አዲስ ነገር ይዘንላችሁ መጥተናል በፌሎአችን ኳየር የተዘጋጀ ስምህ የሚል  ርዕስ ያለው የመዝሙር clip በቅርብ ቀን ይዘን እንቀርባለን!!! Stay tuned

Excited!! 💯
ስምህ | Hufellow choir new Gospel music video

View - Like - share

@HUfellow

#share_to_others
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ምግበ ስጋ ወምግበ ነፍስ

🎼

@ownkin
@cgfsd
ጌታ ኢየሱስ ደግመህ ደጋግመህ ነፍሴን በቤዛነትህ ጠረን እጠናት 😭!!

@ownkin
@cgfsd
አድራሻው እና ማንነቱ በክርስቶስ ሆኖ የተደላደለ ሰው የሚኖርበት የኑሮ መርህ የህይወት መንፈስ ህግ ይባላል እሱ መንፈስ ቅዱስ ነው ።   (ሮሜ 8:2)

@ownkin.
@cgfsd
ክርስቶስ የተጠማ ሁሉ ከእርሱ እንዲጠጣ እግዚአብሔር በዚህ ምድረ-በዳ ዓለም ያፈለቀው ምንጭ እንጂ የ 66 መጽሐፍ ጭምቅ ሐሳብ ብቻ ወይም እጣሬ አይደለም።
Christ is not a commentary.

Ylu

@cgfsd
@ownkin