በክርስቶስ ( in christ)
853 subscribers
99 photos
34 videos
40 files
40 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
(ኢየሱስ ያስቀናል )


የፈንሳዩ የጦር አበጋዝ ናፖሊዮ ቦናባርቴ በርከት ያሉ የውጊያ ድሎች አስመዝግቧል፣ ብዙዎች ማርኳል ነገር ግን ስለ ጌታ ኢየሱስ ማራኪነት ተደንቆ ያለ ጠብመንጃ ሚሊየኖች በፍቅር እንደሚከተሉት በአግራሞት ተናግሯል ። የክርስቶስ ማንነት በእጅጉ የሚገዛው በሰባአዊነቱ የሚጠቀሰው ማህተመ ጋንዲ የኢየሱስ ባህሪ ለዕድሜ ዘመኑ እንደጠቀመው ፣ ስብዕናው ውስጡ እንደሚገዛው አትቷል ።አለም በመዝገቧ ከትባ ያስቀመጠቻቸው ታላላቅ ሰዎች በናዝሬቱ ኢየሱስ የተነሳ እየተገረሙ ወቸው ጉድ በማለት እጃቸውን በአፋቸው አጣምረው ጭነዋል ። በአሜሪካን ለሰው ልጆች እኩልነት ወገቡን አስሮ በቀዳሚነት  ዘብ የቆመው ማርቲን ሉተር ኪንግ  እንዲህ ይላል "ኢየሱስ ለፍቅር ፣ ለእውነት ፣ ለመካምነት ፅንፈኛ ነበር "  በማለት ሀሳቡን አጋርቷል ። በዘመነ አብርሆት ለአለም መንቃት አስተፆ የተጫወተው ፈላስፋው ሩሶ ደግሞ በበኩሉ "ሶቅራጥስ እንደ ፈላስፋ ሞተ ኢየሱስ ግን እንደ እግዚአብሔር ሞተ " በማለት እይታውን አስቀምጧል ።

የቀጠናው አስተዳዳሪ ሔሮዶስ እልፍ እየተከተሉት እንደሆነ በተአምራቱ እና በትምህርቱ አካባቢውን አልፎ ዙሪያ ገባውን  የናዝሬቱ ኢየሱስ እንደሞላ ሲሰማ ስለ ስልጣኑ ስጋት ቢኖረው እሱን ሊሰማ ይናፍቅ ነበር ። መሲሁ ኢየሱስ ላይ ጥርስ የነከሱት የካህናት አለቆች ወታደር አሰማርተው ተጠፍንጎ እንዲመጣ ትዕዛዝ ቢሰጡም የተላኩት ወታደሮች ግን በማንነቱ ፣ በትምህርቱ እና በስራው ተመስጠው የተላኩበትን ረስተው  ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ስለ ንፅህናው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል ። የሸንጎ አባሉ ፈሪሳዊው ኒቆዲሞስ ኢየሱስን ለማወቅ በሌሊት ያለበት ድረስ አነፍንፎ መቷል ። ኢየሱስ ያስቀናል !! እንስማህ፣ እንይህ፣ እንንካህ ፣እንከተልህ ያስብላል ። 

በጨዋታችን መሃል አንድ የምቀርበው ወዳጄ በቤተክርስቲያን መሃል ስለተንሰራፋው ክርስቶስን ስለማይመስለው ልምምዳችን ሲያስብ እንዲህ ይለኛል " እኔ ግን አይገባኝም ክርስቶስን እንዲህ አለውቀውም  ኧረ እኔ ኢየሱስ እንደዚህ አላውቀውም ..ይገርምሃል ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝ አድርጌ የተቀበልኩት በመፀሀፍ ቅዱስ የዕለት ተለዕለት  ጥናት ወቅት ነበር ። በተለይም ደግሞ የወንጌል መፀሀፍት ማቴዎስ ፣ ማርቆስ ፣ሉቃስ እና ዩሀንስ ወንጌላት ላይ ያነበብኩት ጌታ ባህሪው፣ ትህትናው ፣ ፍቅሩ ፣ አላማው ፣ ታዛዥነቱ ያስቀናኝ ነበር  " በማለት አውግቶኛል ። በትክክል !! በተጨባጭ !!! ለዚህም ነው  የዕውቀት ቀንዲሉ  ሊቁ አልበርታን አንስታይል እንዲህ ያለው " ማንም የኢየሱስን እውነተኛነትን ሳይሰማ ወንጌልን ማንበብ አይችል " ያለው። ይሔው ነው !! የወንጌል መፀሀፍት ስናነብ የኢየሱስ የማንነት ውበት ይወረናል ፣ የባህሪው ማራኪነት ይማርከናል፣ አስደናቂነቱ ቀልባችንን ይገዛዋል ። የህይወት ታሪክ አይደለም አምላክ በስጋ የኖረው ህይወት እንጂ ። በቃ እንዲህ ነው የክርስትና ወጉ ኢየሱስን ከሰማበት ፣ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ መመረቅ ለሌለው ጊዜ ዘወትር በውስጥ እየተቃጠሉ ፣ እጅ እየነሱ መኖር ።

   ኢየሱስ ያስቀናል


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
እንጀራ ልንበላ አልተከተልህም ሀብት ብልጥግና ወደ አንተ አልጠራንም #ለምድር በረከት ታይቶ ለሚጠፋው #መች ደምህ ፈሰሰ ለሚያልፍ ተስፋ #የዘላለም ህይወት ማግኘታችን ጉዳይ ሁሌ ብርቃችን ነው #ህይወት ያካፈልከን #ኢየሱስ አንተ ነህ #ሌላ አላየንም በነፍሱ የጨከነ ...


🎼 መስኪ

@ownkin
@cgfsd
(ጌታ ኢየሱስ )



የራሴ ድምፅ ብዙ ጊዜ ረበሽኝ ፣ እኔነቴ ያለ ቅጥ  መፈናፋኛ አሳጣኝ ፣ ድካሜ ጉልበቴን ለግሞ ያዘኝ ፣ የምሰማው ነገር አስደነገጥ  በዚህ ሁሉ ግን ስምህ መማፀኛ ግንብ ሆነኝ ። በዙሪያ ካሉት ሁሉ ዘልዮ አመለጥኩበት ። ቃላት አጥቼ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ እያለኩ ለማምለጥ ጠራሁት ነገር ግን ማምለጡን ረስቼ የጠራሁት ስምህ ጣፈጠኝ ጌታ ኢየሱስ ብዬ ሳልጨርስ ከእንደገና ስሙን መጥራት ናፈቀኝ ። ጌታ ኢየሱስ ስለው የተወጋው ጎኑ ትውስ ይላል፣ጌታ ኢየሱስ ስለው የፈሰሰው ደሙ እንደ ወንዝ ጅረት በአይነ ህሊናዬ እልፍ ይላል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በመስቀል እንደ ተንጠለጠ ወድሃለው ሲለኝ ይሰማኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ልክ በሌለው ጭንቀቴ ውስጥ ልክ የሌለው ሰላሙ ይፈሳል፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው ሀዘን ጥላውን ባጠላብኝ ነፍሴ ውስጥ ደስታው እንደ ማለዳ ፀሀይ ይፈነጥቅብኛል ፣ ጌታ ኢየሱስ ስለው በውስጤ ያለው ቅዱሱ መንፈስ ደግሜ እንድጠራው ጉልበት ይሆነኛል ። 

ሰሞኑን ብዙ ተጨነኩ ፣ ብዙ አዘንኩ ፣ብዙ አነባሁ ፣ ብዙ ተልፈሰፈስኩ እና ብዙ ብዙ ልል አስቤ ልፀልይ ተንበረከኩ ጌታ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ብዬ ስጣራ በአንድ ቃል ብዙ ተነፈስኩ ፣ አረፍኩ ፣ እፎይይ አልኩ !!

       ጌታ ኢየሱስ😍

@ownkin
@cgfsd
የተሳለው መልኩ


ከሀምሳ አመታት በላይ አስቆጥሯል አንድ ስመጥር የሀገሪቱ ሹም ወደ ገጠር ከአንድ አማረኛ ከሚችል ፈረንጅ ጋር እግር ጥሎት ይሄዳል ። የስራ ጉዳያቸውን እያጧጧፉ እያለ አንዲት እናት እየሮጠች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስትል ወደ ፈረንጁ ተጠጋች ። ፈረንጁም አማረኛ ይችል ኖሯል ሳቁን ለቀቀው ያ ሹም ግን ደነገጠ አፈረ ተሸማቀቀ ።
     
(የታሪኩ ምንጭ (መልህቅ በዘነበ ወላ))

    ይሔን ታሪክ ማውጠንጠን ስጀምር የተሳለብን ስዕል እንዴት ነው የሚል ጥያቄ ውስጤ ላይ ፈነጠቀ ።

  ክርስቶስ ሲባል በዘልማድ እንደዛች እናት ፈረንጅ ሁሉ ወይስ በልጅነታችን ለገና እና ለፋሲካ በቴሌቭዥን መስኮት የምንከታተለው ክርስቶስ ሆኖ  ፊልም ላይ የሚተውነው መልከመልካም ሰው ድቅን ይልብን ይሆን???  ደግሞም ይሆናል ብዙዎቻችን ይህን ስናይ ስላደግን ስንፀልይ ወይም ጌታን ስናስብ ያ ክርስቶስ ሁኖ የተወነው ተዋናይ በሀሳባችን መምጣቱ የማይቀር መሆኑን አያከራክረንም !
        በመጀመሪያው ገላቲያ ላይ ተስሎ እንደነበረው የክርስቶስ ኢየሱስ መልክ ዛሬም በዚህ ዘመን ላለን ሁላችን ኢየሱስ እንደተሰቀለ መንፈስ ቅዱስ ሊስልብን እና በደማቁ ሊያደምቅብን ግድ ይላል !!!!
    ትክክለኛው የክርስቶስ ማንነት ነፍሳችን ላይ እንዲሳል መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ። 




ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ተረፈ ማዕዴ ደሙን አፍስሶ
ገበታዬን ሞላው ስጋውን ተቆራርሶ


ስለ ህይወት እንጀራ(ኢየሱስ)!!

@ownkin
@cgfsd
የፍቅር ጉልበት ቀመር ቢሰላ #ይቆጠር ቢባል ከምድር ጅማሬ እስከ በኋላ #የፍጥረት ሁሉ ታሪክ ቢደመር #ጀርባህ ላይ ካሉት ሰንበር አንዷ ጋር እንኳን አይደወዳደር (👉)

  ብወድህ ታዲያ ምን ይገርማል (ኢየሱስ)


🎼
@ownkin
@cgfsd
በእቅፍ ያለው ሁሉን ነገረኝ #የፍቅርህን ልክ እያስተማረኝ #መግባት ሁኖልኝ ስገባ አንተ አለህ #በልጅህ በኩል ትታየኛለህ

እንዴት ታምራለህ ፍቅር ነው ገፅህ #አይቼሃለሁ ልጅህ ሲገልፅህ #እንዴት ታምራለህ ውብ ነህ አባቴ #እድለኛ ነኝ አንተን ማየቴ #ይሔ ሁሉ ፍቅር ያንተ ነው ለካ #አየሁህ ባንድያህ #በልጅህ ትረካ #እግዚአብሔር አብ ያንተ ነው ለካ ።

🎼
@ownkin
@cgfsd
ኪዳኑ(ብሉይ ኪዳን) ያረጀው እግዚአብሔር አረጅቶ አይደለም እግዚአብሔርን መሸከም አቅቶት ነው ።ኪዳኑ አዲስ የሆነው እግዚአብሔር ተለውጦ አይደለም አዲሱን ኪዳን  እግዚአብሔር ተሸክሞት ነው።

@ownkin
@cgfsd
ጌታ ኢየሱስ በአለም ካለ ሁሉ ነገር ይልቅ የደምህ ጠብታ ሚዛን ይደፋል ።

@cgfsd
@ownkin
በእጆቹ ቀዳዳ ቢስማር በበሳቸው #የዘመኔን ገና አሻግሬ አያለው # ከተወጋው ጎኑ በፈሰሰው ውሃ አለመለምኩበት የህይወቴን በረሃ አለመለምኩበት ።


🎼
@cgfsd
@ownkin
(በጣም የምወደው የምግብ ፀሎት)


እግዚአብሔር አባት ሆይ ስለሰጠኸን ምግብ እናመስግናለን ። በመካከላችን ፍቅር ፣ሰላም እንዲኖር ባርክልን ። ደግሞ ከሁሉ የሚበልጠውን እውነተኛ የህይወት እንጀራ የሆነውን ኢየሱስን ዘወትር መብላት ፣ ማጣጣም ፣ ማሰብ ፣ መኖር እንዲሆንልን እርዳን ።


@ownkin
@ownkin
(ጌታ ኢየሱስ )


*የዙፋንህን ሚስጥር በበረት ስታድር ገባን 

*የዙፋንህ አላማ ምድር ላይ ስትራመድ ለየነው

*ዙፋንህ እንደማይነቃነቅ ሞት ድል ስትነሳ አየን

*በዙፋንህ ላይ የተመከረውን ምክር በመቃብርህ  ላይ አገኘነው ።

*ከዙፋን እስከ መስቀል የተዘረጋው ረጅሙን ፍቅር አስተዋልን ።


@ownkin
@cgfsd
አቤት ግን ኢየሱስ በሞትህ በስንቶች ህይወት ውስጥ ሞልተህ ተረፍክ !!


@cgfsd
@ownkin
የኢየሱስን ትንሳኤ ከሞቱ አሻግረን ስንመለከት አዲሱ ማንነታችን ፍንተው ብሎ ይታየናል የኢየሱስን ሞት ከትንሳኤ በኩል አሻግረን ስናስብ ከየት እና ከየት ርቀት እንደሳበን ይገባናል ።


@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ መስቀል ላይ ራቁቱን ቢሰቀልም ራሱን አሳልፎ በመስጠት የትህትናን ካባን ለብሷል ።

@ownkin
@cgfsd
በደም የታጀበ ንጉስ  ህማሙ እጅግ የሰፋ
በመስቀል ዘፋን ላይ  የእሾህ አክሊል ደፋ




@ownkin
@cgfsd
እኮ ሌላማ ምን አለኝ  ለአንድዬ እዳ  
እንባ ነው አልባጥሮሴ  ፈሶ የሚቀዳ




@ownkin
@cgfsd
ሰማይ እልል አለ  ልኡሉ ድል ነሳ
  ማህተም ተፈቶ  በበግ አንበሳ


@ownkin
@cgfsd
( ኢየሱስ ይሰበክ ኢየሱስ ይሰበክ)


ጋሽ ንጉሴ ቡልቻ ለአገልግሎት በአንዲት አጥቢያ ለስብክት መድረክ ላይ ተሰይመው ከፑልፒቱ ላይ አንድ ፅሁፍ ያነባሉ እንዲህ የሚል "ጌታው ኢየሱስ እንድታሳየን ነው የምንፈልገው"።

ኢየሱስን በተመለከተ ቆፍጠን ያለ  አቋም ያስፈልገናል ። መድረኮቻችን ላይ መቀለጃ የሆኑ እንቢ ማለት አለብን አዎ ቆፍጠን ነው እንጂ እንደ ሐዋሪያው  ጳውሎስ አናቴማ ! አናቴሜ እንደግመዋለው አናቴሜ ! በክርስቶስ ኢየሱስ ውጭ የሚሰብክ ካለ አናቴማ ።


አሁን ላይ ጥንቅቅ ያለ ደቀመዝሙር አብዝተን ልንመለከት ያልቻልነው የኢየሱስ ማንነት ላይ ስር የሰደደ አገልጋዮች እንኳን ስለሌሉን ነው ። መድረክ የሚያጋፍሩ ሰባኪያን ቢሆኑ የኢየሱስ አምላክነት ፣ ፍፁም ሰውነት (ተሰገዎ)፣ ሞት ፣ትንሳኤ ፣ ዕረገት፣ ዳግም ተመልሶ መምጣቱ በተመለከተ በቅጡ መገንዘብ ያሻቸዋል ። ዘነበ ወላ መልህቅ በተሰኘው ድርሳታቸው ውስጥ አንድ ፈረንጅ ከአንድ ትልቅ ስልጣን ካለው ኢትዮጵያዊ ባለ ስልጣን ጋር ለሰባት ስራ ጉዳይ ገጠር ይሄዳሉ አንዲት ሴትዮ እየሮጠች ፈረጁን ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብላ ትመጣለች ይሔን ጊዜ ፈረንጁ ይስቃል ባለስልጣኑ በተራው ደግሞ ይሸማቀቃል ። ይቺ ድርሰት እንደ ሀገር ክርስቶስ ላይ ያለን የተዛነፈ እይታ መሳያ ነው ።

ፀጋአብ በቀለ ተሃድሶ በተባለው በሌላያኛው የቅፅ መፀሃፋቸው ላይ በንጉሱ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጌል መስክሮ ያለፈ ሚሲዬናዊ ተልዕኮውን ጨርሶ ሲመለስ እንዲህ ተናገረ " ኢትዮጲያ ውስጥ ብዙ ለወንጌል የተሰጠ ልብ አላቸው ነገር ግን ኢየሱስ በቅጡ በመረዳት ዙሪያ አንድ ሰው እንዳላገኘ ይናገራል " ። እንግዲህ እዚህ ጋር በመድረኩ መካከል ድንበር ይሰመር !! ልከኛ የክርስቶስ ትምህርት ያሻናል ።


እኔ በበኩሌ ከተሃድሶ ወንድሞቻችን እንማር ባይ ነኝ ። በተሃድሶ አገልጋዮች ዘንድ ሁሉ ነገራቸው ኢየሱስ ትኩረት የሰጠ ነው ። የክርስቶስ ሊቀካህነት ፣ የመስቀል ስራው ፣ ዘላለማዊነቱ ፣ በወጌላት ላይ የፈፀመው ገድል በእነሱ አገልግሎት አብዝቶ ይወሳል መዝሙሮቻቸውም ለእዚህ ትልቅ እማኝ ናቸው ።

ኢየሱስ ይሰበክ

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd