( የዩሀንስ ወንጌል ጥናት)
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው !!
የዩሀንስ ወንጌል ከአራቱ የወንጌል መፀሀፍት አንዱ ነው ። አራቱ ወንጌላት :-
ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ ፣ዩሀንስ ናቸው ። እነዚህ አራቱ ወንጌላት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት ፣ ያስተማራቸውን ፣የተናገራቸውን የሚናገሩ ናቸው ። ሶስቱ ወንጌላት (ማቴዎስ፣ማርቆስ፣ ሉቃስ) በብዛት የአፃፃፋቸው ፣ የአተራረካቸው፣ አጀማመራቸው ይመሳሰላል ። ሶስቱም ወንጌላት ስለ ኢየሱስ መናገር የጀመሩት ከኢየሱስ ወልደት በመጀመር ነው ይሔ ማለት ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነው እና እነዚህ ወንጌላት ከፍፁም ሰውነት በመነሳት ይፀፋሉ ። የዩሀንስ ወንጌል ደግሞ ከሶስቱ ወንጌል አተራረኩ ለየት ይላል ።የሚያተኩረው እንደ ሶስቱ ወንጌላት ከፍፁም ሰውነቱ በመነሳት ሳይሆን ፍፁም አምላክነት ላይ በመነሳት ይተርካልናል ።
የዩሀንስ ወንጌል የተፃፈው ከሶስቱም ወንጌል መጨረሻ ላይ ነው ። ጊዜው አዲስ ትውልድ እየመጣ ስለሆነ የጌታችን ኢየሱስ ማንነት እንዲያውቁ በማሰብ ነበር የተፃፈው ።
#ዩሀንስ ወንጌል የተፃፈበት ዋነኛው ዓላማ ሰዎች የኢየሱስ ስም በማመን የዘላለም ህይወት እንዲያገኙ ነው ። ዩሀንስ የዘላለም ህይወት የሚገኘውን መንገድ ነው የፃፈው ...የዘላለም ህይወት የሚገኘው ደግሞ ኢየሱስ በማመን ነው። ኢየሱስን ማመን ማለት ደግሞ ስለ እኛ እንደሞተ እናም የሀጢያት ዋጋ እንደከፈለልን ደግሞ ጌታችን እንደሆነ ማመን ነው ።
ዮሐንስ 20 (John)
31፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።
#የዘላለም ህይወት ሰው እንዲያገኝ ይሔ የእግዚአብሔር ሀሳብ ነው
።እግዚአብሔር እኛ የዘላለም ህይወት እንድናገኝ ስለሚፈልግ ልጁን ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንዲሞት እና እኛን ለማዳን አንድ ልጁን ሰጥቷል ። ሰው የዘላለም ህይወት እንዲያገኝ ነው ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው ለዚህ ዓላማ ነው ።
ዮሐንስ 3 (John)
16፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
#የዘላለም ህይወት ተቃራኒው የዘላለም ሞት ነው ። የዘላለም ሞት ለዘላለም መሞት ማለት ከእግዚአብሔር መለየት ነው ። አዳም ሀጢያት በመስራቱ ከእግዚአብሔር ተለየ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ ስለዚህ የዘላለም ሞት ሞተ !! ስለዚህ የዘላለም ህይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ ነው ። የዘላለም ሞት ከእግዚአብሔር መለየት ከሆነ የዘላለም ህይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ነው ።
#የዘላለም ህይወት እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። ሰው ስለ ብዙ ነገር ማወቅ ይፈልጋል ስለ ሰው ፣ ስለ ሀገር፣ ማንኛው እውቀት ማወቅ ይፈልጋል ። እግዚአብሔርን ማወቅ እንደ ማንኛው እውቀት አይደለም ! እግዚአብሔር ማወቅ ከእውቀት ያለፋል !!!ከእውቀት ሁሉ ትልቁ እውቀት እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። እግዚአብሔር ማወቅ የአይምሮ ክምችት ወይም የአይምሮ ሀብት አይደለም !!!!እግዚአብሔር ማወቅ የዘላለም ህይወት ነው ። እግዚአብሔር እንዲታወቅ ይፈልጋል !!!ትልቅ አምላክ ነው ቢሆንም ራሱን አይደብቅም ፣ ራሱን አይሸሽግብንም እንድናውቀው ያረጋል ። እናም የዘላለም ህይወት ዋና ዓላማው እግዚአብሔር ማወቅ ነው ። እኛን ከሞት እንድንድን ከሲኦል እንድንተርፍ የፈለገው ተርፈን ቁጭ እንድንል ብቻ አይደለም ...እግዚአብሔር እንድናውቅ ነው ።
ዮሐንስ 17 (John)
3፤ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
** እግዚአብሔር እንዴት ሊታወቅ ይችላል ??? ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እናውቀዋለን በማለት ጥያቄ ያነሳሉ ። እግዚአብሔር የሚታወቀው በኢየሱስ ብቻ እና ብቻ ነው ።ኢየሱስ በምድር በነበረ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ነው ። ስለ እግዚአብሔር ማንም በሙላት ሊናገር የሚችል እግዚአብሔር በደንብ በሙላት ከኢየሱስ በቀር ማንም አያቀውም ። ወደ እግዚአብሔር ከኢየሱስ በቀር ማንም ሊሄድ አይችልም ። ለምን ኢየሱስ ብቻ ካልን ኢየሱስ ስላሴ ነው ። ኢየሱስ አምላክ ነው ።
ዮሐንስ 1 (John)
18፤ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።
ዮሐንስ 14 (John)
6፤ ኢየሱስም፡— እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
@ownkin
@cgfsd