በክርስቶስ ( in christ)
712 subscribers
98 photos
33 videos
40 files
38 links
Who is ownership of kingdom
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ አገልግሎት እና ጉዳዬች ላይ ይተኮራል @ownkin
Download Telegram
(በመንፈስ መሞላት )

በመንፈስ መሞላት መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው!!

* ከቃሉ በፀሎት ማሳልፍ
* መንፈሳዊ ርሃብ
* የመንፈስ ቅዱስን አላማ መረዳት

በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ጳውሎስ ልሄድ ከክርስቶስ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ ያለው ኑሮ መሮት ሳይሆን ከቀመስው ዘላለማዊው ፍቅር የተነሳ ክርስቶስ የምርም ናፍቆት ነው።

@ownkin
@cgfsd
የእግዚአብሔር ልጆች አፋቸውን ሲፈቱ ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ ነው ።

@ownkin
@cgfsd
ወደ ኢየሱስ ውደደኝ ተብሎ አይፀለይም! ፍቅርን በመረዳት አብዝቼ ልውደድህ ተብሎ እንጂ ፡፡

@ownkin
@cgfsdj
እግዘብሔርን ያለ ኢየሱስ ሰውም ያለ ኢየሱስ አይተረጎሙም ።

sadi

@ownkin
@cgfsd
የረቡዕ ጥቅምት ፪፫/፪፻፩፭ ፕሮግራም

🔺ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ
(የመጨረሻ ክፍል ፣ክፍል ፪)

ሰባኪ : ፊሊሞን ነጋ
የመልዕክቱ ርዕስ : የምንኖርለት ዓላማ (#መጋረጃውን_ማንሳት)

የመልዕክቱ አንድአንድ ሀሳቦች

፨ለክርስቶስ ያለን ፍቅር የሚመዘነው⚖️ ፣ክርስቶስ ለሰጠን #ተልዕኮ ባለን #ልብ💙 መጠን ነው ።
፨ የክርስቶስ ደቀመዛሙር ማለት ፦ የእግዚአብሔርን #አሰራር ፣ የእግዚአብሔርን #መንግስት_እውነት 👉ወደ ሁሉም🌍 ቦታ የሚያደርስ ማለት ነው ።
፨ክርስቶስ ለሕይወት ያልሰጠን የትኛውም #ዓላማ 👉መጋረጃ 🚫ነው
#stay #blessed 😊💙
t.me/ZOEfellow
#ኢየሱስን መውደድ

* ኢየሱስን መውደድ በምን ይገለጣል?

ቃሉን በመውደድ
አካሉን(ቤተክርስቲያን) በመውደድ
የመንፈስ ቅዱን መቅደስ በመውደድ
የክርስቶስን ተልዕኮ በመውደድ

@ownkin
@cgfsd
የቤተክርስቲያንን ሚስጥርነቷ የክርስቶስ አካል መሆኗ ነው !!

@ownkin
@cgfsd
( 2ቆሮንቶስ )

የወንጌል ጉዞ

በፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
2ጢሞቲዬስ ዳሰሳ
   (ያመኑትን ማወቅ)


2ጢሞቲዬስ መልዕክት በሐዋሪያው ጳውሎስ የተፃፈ መሆኑ እሙን ነው ። ጳውሎስ ከእስር ቤት ከፃፋቸው 5 መልእክቶች መካከል አንዱ ነው ። ይሔ ደብዳቤ በሚፃፍበት ወቅት በሮም በእስር ይገኝ ነበር ። ጳውሎስ ከእስርቤት ጥሩ ጥሩ ተወዳጅ ፅሁፎች አበርክቶልናል ። የ2ተኛ ጢሞቲዬስ ግን ከሁሉም የጳውሎስ መልዕክቶች ለየት የሚያረገው ሐዋሪያው በህይወቱ መጨረሻ የፃፈው ደብዳቤ 2ተኛ ጢሞቲዬስን ነበር ። መልዕክቱ ሲነበብ ጳውሎስ እየተሰናበተ ይመስላል ። በ13 ደብዳቤዎች የምናውቀው የጠርሴሱ ጳውሎስ በ2ተኛ ጢሞቲዬስ ስንብት ላይ ያለ ይመስላል ።
እንደው አገልግሎቱን ተመለከተ በድል እንደጨረሰ እና እዚህ ምድር ምንም እንዳልቀረው በሰማይ ላለው ሽልማት ለመቀበል እየተዘጋጀ እንደሆነ ይናገራል ።
    2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
7፤ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤
8፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።

* ጳውሎስ ደብዳቤውን የፃፈው ክረምት ሳይገባ ቀደም ብሎ እና ክረምት ሳይመጣ የሚፃፍለት ጢሞቲዬስ እንዲመጣ እየጠበቀው ነው ።ምናልባት ክረምቱ ካለቀ በኋላ ለክርስቶስ ተሰውቶ በህይወት ላይኖር እና ወደ ጌታ ሊሄድ እንደሚችል ራዕይ ሳያያይ አልቀረም ።
    2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
21፤ ከክረምት በፊት እንድትመጣ ትጋ። ኤውግሎስና ጱዴስ ሊኖስም ቅላውዲያም ወንድሞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

*በዛው ቁጥር ደብዳቤ የሚፃፍበት እስር ቤት ግራውን እንደሆነ የታሪክ መምህራን ይናገራሉ ።ምናልባት በዛ ከባድ የሮም ቀዝቃዛ አየር ውስጥ ግን ለትውልድ ይፅፋል ። ይሔን የሚያረጋግጥል ለብርዱ መከላከያ በርኖሱን እንዲያመጣለት ጢሞቲዬስን ሲያዘው እናያለን ። በርኖስ ወፈር ያለ የብርድ መከላከያ ነው ። ሌላም ነገር አብሮ አዞታል እሱም በብራና የተፃፉ መፀሀፍት ።እነዚህ መፀሀፍ የብሉይ ኪዳን መፀሀፍት ናቸው በዛን ዘመን አንድ ወጥ መፀሀፍ ቅዱስ አልነበረም እና መፀሀፍቱን እንዲያመጣለት ሲለምነው እናያለን ።ጳውሎስ ምንም እንኳን ክርስቶስ በአስደናቂ ሁኔታ የተገ  ለጠለት ቢሆንም መፀሀፍ ቅዱስ የሆነውን አሁን ይመረምራል ያነባል ይታዘዛል ።ለቃሉ ምን አይነት ልብ አለን !!ስለሚያስፈልገው ነው ይዘኸልኝ ና ያለው ።
   2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
13፤ ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ።

* ደብዳቤ በሚፃፍበት ወቅት ሐዋሪያው ጳውሎስ በወዳጁ በዴማስ ተከድቶ ነበር ። ዴማስ አለምን ወዶ ትቶኛል ይላል ። ምንም በዚህ ከባድ ወቅት በእስር ቤት እያለ ሰው ቢርቀውም አሁን የወንጌል ጉዳይ እንጂ የእሱ ግድ እንደሌለው ይታይበታል በፅሁፉ ። ዴማስን ሲያማርር አናይም እንደውም በቶሎ የሚሰራ ስራ እንዳለ ያመለክታል ።
   2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
9፤ በቶሎ ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤
10፤ ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፥ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤

*ሁሉም እስር ቤት የፃፉት የጳውሎስ መልዕክቶች 5ቱም በቲቲቆስ በተባለ ሰው ተልከዋል ። ከቲቲቶስ ትልቅ ልብ እናያለን ። እግረ መንገዱም ቢሆን ለቤተክርስቲያን መታነፅ ለግለሰብ መበርታት አስተዋፆ አለው ።ወንጌል የሁሉም ስራ ነው ።
   2 ጢሞቴዎስ 4 (2 Timothy)
12፤ ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ላክሁት።

* ከ13 የጳውሎስ ደብዳቤ ውስጥ 9ኙ ለቤተክርስቲያን የተፃፉ ሲሆኑ 4ቱ ደግሞ ለግለሰብ የተፃፉ ናቸው ።የ2ተኛ ጢሞቲዬስ መልክተም ለግለሰብ ከተፃፉት አንዱ ነው ።

* ይሔ ደብዳቤ የመጋቢ መልዕክት ተብሎ ይታወቃል ።አላማው መጋቢ ለሆኑ ሰዎች መጋቢነታቸውን የሚያስታውስ ስለሆነ ።

* ደብዳቤው የተፃፈው ለጢሞቲዬስ ነው ። ጢሞቲዬስ ደግሞ በእድሜ ወጣት የነበረ ገና ወደ ሃያዎቹ የተጠጋ አገልጋይ ነበር ።በኤፌሶን ቤተክርስትያን በመጋቢት እያገለገለም ነበር ። ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ መንፈሳዊ ህይወት ስለተጋ የእምነት ልጄ እያለ ይጠራዋል ።
   2 ጢሞቴዎስ 1 (2 Timothy)
2፤ ለተወደደው ልጄ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።

* ጳውሎስ ጢሞቲዬስን በሚያገኝበት ወቅት በልስጥራ ይገኝ ነበር ። ጢሞቲዬስ በእናቱ አይሁዳዊ ሲሆን በአባቱ ደግሞ ከአህዛብ ወገን ነበር ። ጳውሎስ ሲያገኘው እንዲገረዝ አረገው እንዲገረዝ ያረገበት ምክንያት መገረዝ ለመዳን ግድ ሁኖ ሳይሆን በዛን አካባቢ የነበረ አይሁዳዊያን አልተገረዘም ብለው በረባው ባረባው ለጢሞቲዬስ አገልግሎት እንዳያስቸግሩ ነው ።
     ሐዋ. ሥራ 16 (Acts)
1፤ ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ።
3፤ ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፥ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።

* የጢሞቲዬስ እናት እና አያት በወንጌል በረቱ የተጠነከሩ የተመሰከረላቸው ነበሩ ይሔም ጢሞቲዬስ ላይ አስተዋፆ አርጓል ።  2 ጢሞቴዎስ 1 (2 Timothy)
5፤ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።

* ጢሞቲዬስ እንባ ያነባ እንደነበር እናነባለን ። ያነባ የነበረው 1, ጌታን ይወድ ስለነበረ ለጌታ ያለው ፍቅር ወይም
2, ጳውሎስን ይወደደው ስለነበር እሱን ሲያየው ደስ ብሎት ሊሆን ይችላል ይላሉ ብቻ ምንም ይሁን ጳውሎስ የጢሞቲዬስ እንባ ማየት ይናፍቃል ።
   2 ጢሞቴዎስ 1 (2 Timothy)
4፤ እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።

እና የጢሞቲዬስ ታናሽነት በላይ እንዲበረታ እራሱን በወታደር ፣በገበሬ እንዲመለከት ጳውሎስ ይመክራል ። በመከራም እንዲፀና አብሮ የጳውሎስን መከራ እንዲካፈል ።ያሳስባዋል ። አደራ አለ የወንጌል የቤተክርስቲያን እሱን አደራ ይላል ።
አንተ ግን አንተ ግን ይለዋል ክርስትና እራሱን በማነፃፀር ሳይሆን ራሱን በመገምገም እንዲኖር ያስተምረዋል ።

  ዳራው ለዛሬ ይሔ ነው!!

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
2⃣ቆሮንቶስ

የተፅናናንበት መፅናናት

2ቆሮ 1:3_7

ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd
ከመከራው በፊት መጽናናቱ አግኝቶናል

👉 የቀመስነዉ ከመከራዉ ከችግሩ በፊት መጽናናትን ነዉ በአለም ላይ መጽናናት ከጉዳት በዋላ የሚመጣ ነገር ነዉ እግዚአብሔር ግን ቀድሞ የሰጠን መጽናናትን ነዉ 
                 👉በልጁ አጽናናን
                  👉በመንፈስ ቅዱስ አጽናናን
                   👉በፍቅሩ አጽናናን
👉የተጽናናንበት መጽናናት መከራዉን ሳይሆን የቀረልንን የክብር ተስፋ ያስመለክተናል 👉“ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው..... ክብር ጋር ቢመዛዘን..... የአሁኑ ዘመን ሥቃይ.... ምንም እንዳይደለ አስባለሁ።”😍
  ሮሜ 8፥18
👉 መጽናናታችን መከራዉን አቅልሎብናል.... ከመጽናናታችን የላቀ መከራ አይታየንም 😎..... በወንጌል ለዘላለም አጽናንቶናል.... በመንፈስ ቅዱስ እስከ ፍጻሜ አጽናንቶናል😍
“በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤”
  — ኤፌሶን 1፥1



  በኤፌሶን የሚገኘ ቅዱሳን
በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ

አስገራሚ እውነት ነው ። ሁለት አድራሻ በዚህ ምድር ናቸው ደግሞ ሰማይ አሉ ። በኤፌሶን ናቸው ደግሞም በክርስቶስ ናቸው ።

በኤፌሶን ውስጥ ይኖራሉ በክርስቶስ ውስጥም ይኖራሉ ። በኤፌሶን እንደሚኖሩ ምድር መዝግባቸዋለች በክርስቶስ እንዳሉ ሰማይ መዝግቧቸዋል ።


   በክርስቶስ( inchrist ). in.ማለት ውስጥ ማለት ነው ።  in christ ክርስቶስ ውስጥ እንደማለት ነው ።

ምሳሌ እኛ በአብ ቀኝ አልተቀመጥንም ።ክርስቶስ በአብ ቀኝ ተቀምጧል እናም እኛ በክርስቶስ ወይም በክርስቶስ ውስጥ ስለሆን ተቀምጠናል ።እኛ ሳይሆን እሱ ስለተቀመጠ
በአዲስ ኪዳን መነቃቃት ሳይሆን መንቃት ነው ያለው ።

@ownkin
@cgfsd
በረከታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘነው ማንነት ነው ።

@ownkin
@cgfsd
ኢየሱስ በእግዚአብሔር ዘንድ አንድያ ስለሆነ ውድ ልጁ ነው ። ልጁ በአባቱ ዘንድ ስለተከበረ እና ስለተወደደ የአባቱ ምርጥ ነው ።የሚደሰትበት እና የሚረካበት ውድ ልጁ ነው !!

@ownkin
@cgfsd