Central Ethiopia Regional State EDUCATION BUREAU
4.45K subscribers
771 photos
5 videos
12 links
Regional Education Bureau
Download Telegram
የትምህርት ቤት አመራሮች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው - አቶ አንተነህ ፈቃዱ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓሰ ላለፉት 3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ በማጠቃለያው መርሃግብር ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክ ለመምህራንና ትምህርት ቤት አመራሮች ትልቁ ስኬት ኢትዮጵያን መገንባት የሚችል ትውልድ መፍጠር ነው ብለዋል።

የትምህርት ቤት አመራሮች ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት መሪዎች ናቸው ያሉት አቶ አንተነህ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥና የተማሪዎች ውጤትን በማሻሻል የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በክልሉ የትምህርት ቤት አመራር ሪፎርም ተግባራዊ ሲደረግ ነባር የትምህርት ቤት አመራሮችን ለማፈናቀል ነው በሚል ሪፎርሙን ለማሰናከል ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።

በአንጻሩ ሪፎርሙ ትምህርት ቤቶች በሰለጠኑ እና የተሻለ የሙያ ብቃ ባላቸው የትምህርት ቤት አመራሮች መመራት እንዲችሉ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ያስረዱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፎርሙ ተወዳድረው ምደባ ካገኙት መካከል 68 በመቶው ነባር የትምህርት ቤት አመራሮች 31 በመቶው መመህራን እና አንድ በመቶው የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አስረድተዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃግብር የተገኙት የኢፌዴሪ ፈተናና ምዘናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ትልቁ ክፍያ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ማፍራት መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ የትምህርት ቤት አመራር ለመሆን ዕድል ያገኛችሁ ሩቅ ዓልማችሁ የተሰጣችሁን ታሪካዊ ኃላፊነት ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ መጠቀም ይኖርባችኋል ብለዋል።

በይዲድያ ተስፋሁን
👍30❤9
በትምህርት ቤቶች የስርዓተ ጾታ ክበባትንን በማጠናከር በሴቶች ላይ የሚፈጠሙ ጾታዊ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

ቢሮው ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር በክልሉ በጠምባሮ ልዩ ወረዳ በጉራጌ፣ በሀዲያና ከምባታ ዞኖች ከሚገኙ 62 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ የስርዓተ ጾታ ክበባት አስተባባሪዎች፣ ርዕሰ መምህራንና የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው በትምህርት ቤቶች የስርዓተ ጾታ ክበባትንን በማጠናከር በሴቶች ላይ የሚፈጠሙ ጾታዊ ጥቃቶችንና ጎጂልማዳዊ ድርጊቶችን በተለይም ያለ ዕድሜ ጋብቻን መከላከል ላይ ያተኮረ መሆኑን የቢሮው የስርዓተ ጾታ ስራ ክፍል አስተባባሪ ወ/ሮ ዘሪቱ ብርሃኑ ተናግረዋል።

ስልጠናውን የወሰዱ የስርዓተ ጾታ ክበባት አስተባባሪዎች በትምህርት ቤቶች ለክበቡ አባላትና ለትምህርት ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጫበጫ ስልጠና እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የዩኒሴፍ አስተባባሪ አቶ አበበ በክልሉ በጉዳዩ ዙሪያ ከሴቶችና ህጻናት ቢሮ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ቢሮው ልዩ ትኩረት ያሻቸዋል በሚል ለይቶ በሚያቀርባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰባዊ ግንዛቤ በማሳደግ ጾታዊ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከልና ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህም የሴቶች የመማር ተነሳሽነት በመጨመር ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩና በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ያግዛል ብለዋል፡፡

ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን ያለ ስጋት ትምህርት ቤት እንዲልኩና በትምህርት ቤቶች የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ እንዲጨምር እንደሚያስችል አቶ አበበ አክለውም ገልጸዋል፡፡

ለዚህም በክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ከጠንባሮ ልዩ ወረዳ 48 ትምህርት ቤቶች፣ ከሀዲያ ዞን ምስራቅ ባደዋቾ፣ ወረዳ ከጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳና ከከምባታ ዞን ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ለተውጣጡ 14 ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ በክልሉ ለሚገኙ 62 ትምህርት ቤቶች የስርዓተ ጾታ ክበባት አስተባባሪዎች፣ ርዕሰ መምህራንና የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በይዲድያ ተስፋሁን
❤10👍2
በክልሉ ባለፈው የ2016 የትምርት ዘመን ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ መሻሻል ታይቷል- ትምህርት ቢሮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በ2017 የትምህርት ዘመን ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገለጸ።

ቢሮው የማጠናከሪያ ትምህርቱን በክልሉ በሁሉም ዞንና ልዩ ወረዳዎች ወጥነት ባለው መልኩ መስጠት እንዲቻል በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በቡታጅራ ከተማ ምክክር አድርጓል።

በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትልና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ማልደዮ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት እንደ ሃገር የትምህርት ውጤት ስብራት አጋጥመናል።

በተለይም ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ፈተና እና በአገር አቀፍና ክልላዊ ፈተናዎች የሚያስዘግቡት ውጤት ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ጠቁመዋል።

ይህን ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችል በክልሉ በመምህራን በተማሪዎች ላይ ያተኮሩ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

ለአብነት ለመምህራን በፈተና አዘገጃጀትና ላይ ስልጠና መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊው በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ለ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከርያ ትምህርት እንደተሰጠም አንስተዋል።

በዚህም 4 ሺህ የሚሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሆሳዕና ትምህርት ኮሌጅ ከ22 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ በክልሉ በሚገኙ ሦስት ዩንቨርስቲዎች አማካኝነት የማጠናከሪያ ትምህርት እንደተሰጣቸው አመላክተዋል።

በዚህም በተሠራው ስራ በክልሉ ካለፍት ዓመታት በተሻለ በተማሪዎች ውጤት ላይ አበረታች ለውጥ ታይቷል ያሉት አቶ ማቲዎስ ለአብነትም በ2015 በ8ኛ ክፍል 18 ነጥብ 5 በመቶ የነበረውን የማለፍ ምጣኔ በ2016 የትምህርት ዘመን 44 በመቶ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ 12ኛ ክፍል በ2015 የነበረውን 2 ነጥብ 7 በመቶ የማለፍ ምጣኔ ወደ 3 ነጥብ 4 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቁመዋል።

ለዚህም ውጤት መመዝገብ ዩኒቨርሲቲዎችንና የሆሳዕና ትምህርት ኮሌጅ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበራቸው አቶ ማቴዎስ ገልጸዋል።

በዘንድሮ የ2017 የትምህርት ዘመን ይህንኑ በማጠናከር በተማሪዎች ውጤት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመዘግብ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከታህሳስ 5 ጀምሮ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የማጠናከር ትምህርት ለመስጠት በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል።

በዚህም ከ26 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ29 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት መታቀዱን ኃላፊው ተናግረዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና የትምህርት ሱፐርቪዥን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ በኩላቸው በዘንድሮው የማጠናከሪያ ትምህርት ካለፈው ዓመት በተለየ መልኩ የ7ኛ እና 11 ክፍል ተማሪዎችን ጨምሮ ለመስጠት መታቀዱን ገልጸዋል።

በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለተፈጥሮ ሳይንስና እና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በምክክር መድረኩ ከወራቤ፣ ዋቸሞና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ከሆሳዕና ትምህርት ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በይዲድያ ተስፋሁን
👍90❤53👏9
የትምህርት ኮሌጆች ዲን፣ ምክትል ዲኖች ዉድድር ምልመላና መረጣ ማሰፈጻሚያ ረቂቅ መመሪያ በህዝብ አሰተያየት እንዲሰጥበት ቀረበ

ትምህርት ኮሌጆች ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ብቁና ተነሳሽነት ያላቸውን ዲኖችና ምክትል ዲኖች ግልጽ የሆኑ የውድድር መስፈርቶችን በመጠቀም መምረጥና ማሰማራት በተቋማቱ አጠቃላይ አፈፃፀም ላይ የላቀና ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ይህን ለማሳካት የትምህርት ኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች ምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ማስፈፀሚያ መመሪያ ማዉጣት አስፈልጓል፤

በዚህ መነሻ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በርዕሰ መስተዳድር ምክር ቤት የትምህርት ኮሌጆችን ለማስተዳደር በወጣ ደንብ ቁጥር 38/2017 በአንቀጽ 31 ንዑስ አንቀጽ ሰ) ላይ በተሰጠ ስልጣን መሠረት የትምህርት ኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች ውድድር፣ ምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ማስተግበሪያ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
 
ቢሮው በረቂቅ መመሪያው ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ለመሰብስብ የሚያስችል ዉይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ህዝቡ በረቂቅ መመሪያው ላይ አሰተያያት እንዲሰጥ በማስፈለጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ ረቂቅ መመሪያውን በማየት ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በዌብሳይታች አስተያየት መስጫ ላይ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችን እንድሰጡ እንጠይቃለን።
❤40👍30