የደጋገምናቸው ስሜቶች ጥቅል ስብእናን ይሰራሉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የምንብሰለሰልባቸው ቃላትና ሀሳቦች በድግግማቸው ልክ ባህሪዎቻችን ላይ ሂድታዊ ለውጥ ይፈጥራሉ። የደጋገምናቸውን ስሜቶች እንሆናለን። ባህሪያችን ቅርጸ መልኩ ከየቅጽበቶቻችን መብሰልሰል የተንጸባረቀ ነው። ምንግዜም ወደ በጎነት ብቻ ተዘንባይ ውጤት ያለውን በመፈለግ ላይ መገንባት ይልቃል ።

👍22❤20🥰4
ለራሱ የታመነ ለሀገሩ ይታመናል፡፡
ራሱን ያላከበረ ሀገሩን አከብራለሁ ቢልም እየዋሸ ነው፡፡ ስለሀገር ለውጥ አስባለሁ ከማለት በፊት ራስን መታመን ይቀድማል፡፡ ሁላችንም… በየቀኑ ተማሪዎች ነን፡፡ የምናውቀውንና የሆንነውን መጠን ብቻ ነን፡፡ ራስን አክባሪ ስብዕና መገንባት ማለት በራስ ልክ መወሰን ማለት ነው፡፡
ከምናውቀው አልፈን መገመትን ማቆም እንደማለት ነው፡፡ የምናውቀው ድረስ እርግጡን እንታመነው፤ ራሳችንን እንስራው፤ እንድረሰው፡፡ የተለየውን የራስ እውነታ ለራስ ማንበብ የጥበብ አካል ነው፡፡
እንዲያ ያደረገ ሰው ነው ወደ ሀገሩ የማቅናት ጉዞ እርምጃውን ‹ሀ› ብሏል የምንለው፡፡

👍28❤14
መሆንን መድረስ፤
የምንደርሰው ምን ይዘን ነው እንጠይቃለን፤ በመጀመሪያ፡፡ በታወቀ የጊዜ እድሜያችን የምንፈጥረው የእድሜያችን መጠን የሆነ የመረዳት መብቃት ይገደናል፡፡ ራስን መስራትና መሆንን ማጽናት የሰውኛ ሰው መሆን መልኩ ነው፡፡ እሱን የበቃነውን ራስነት ወደ መንገዱ መሀል ማድረስ በህይወት የራስ ፋይዳ ያለው ሰው ያደርጋል፡፡ የመኖር ምክኒያታዊነት መጎናጸፍም ይሆናል፡፡

❤26👍9😁1
እውነትን መጠበቅ ልክን ጸንቶ መዝለቅ ነው፡፡ እውነት የለለው ሰው ለጥበብ እንግዳ ነው፡፡ ስለጥበበኛነት መመስከር አይቻለውም፡፡ ጥበብ የሰውን ፊደል አልባ ቋንቋ የሚያወራልን የተሻገረ መድረስ ነው፡፡ ለጥበብ የታመነ ሰው በደግነቱ ይዘምታል፡፡ በማያባራ ጉዞው ብርሀንን እንጂ ጽልመት አያይም፡፡ ስውር ጠላፊነት የለውም፤ ቀጥታ መግለጥ እንጂ…
ለልብ ዓለም ታማኝ ነው፡፡ በስሌትና ስልታዊነት አያልፍም፡፡ ወደ ሰው ልቦና ጥልቅ ይደርሳል፡፡ ትርጉም ያለውን የፋይዳ ሰብነት ሚና ይጫወታል፡፡

❤31👍5🔥2
የጥበብ ሰዎች መንገድ ከመንፈሳዊነት ጋር የተሳሰረ ነው። ብዙ ጊዜ መንፈሳዊነት ከሃይማኖታዊ ምንጭ ብቻ ሲያያዝ፣ የጥንቱን ወርቀ አልማዝ እያጣ መጥቷል።
የጥበብ ሰዎች የዚያን የጠፋውን የመንፈሳዊነት ብርሃን በራሳቸው መንገድ ያበራሉ። ጥበበኞች በመንፈሳዊነት ውስጥ የጠፋውንና የተደበቀውን ውብ የህይወት ምሳሌ ለመግለጥ የቀረቡ መልክተኞች ናቸው። መንፈሳዊነትን በልክ የሚያበሩ ምሳሌም ናቸው

❤23👍3🔥2
ጥበብ አንድም ለወርቁ ለሀብቱ የግራ ጎን አላት፤ አንድም ዘላለማዊ ስለሆነ ፍሬ የቀኝ ዓለም አላት፡፡ ጥበብን በልኳ ከገለባዋ ሳይሆን ከውቅያኖሷ የሚደርሱ አገልጋዮች እንዲኖሯትም አልሰራንም፡፡ አለመስራታችንም ይኼው ግዙፍ ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡
የዓለም ሰዉ ሆኖ በዓለም ሰዎች ዘንድ ስለመክበር የተመኘ የጥበብ ግራ ሊቅ… አለ፡፡ ስጋውን የሚያስከበር፤ ለስጋው ክብር የሚታትር፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ህያው የልብ ሰውነትን የሚደማ የጥበብ ቀኝ ክፋይም አለ…
….
መራራ እውነቶች ውስጥ ነን፡፡ ስናምን ከምግባሩ አልተሞላንም፡፡ ምግባር ስንራብ ቆየንና …. አነስን፡፡ ስንማርም…. ደረቁን ሆድና ስጋ የማብላትና የማጌጥ ብልጭታ ቀረጸንና ደረቅን፡፡
አስታራቂ ስለሆነው የልባዊ ጥበብ መንጋት ግን ይቻላል። አሁንም ያነስነውን ሰው መሆን ማደግ ላይ መጽናትን መበርታት ነው። ሰው ትልቅ እንጂ ትንሽ አይደለም።

❤19👍6
እናትን ማጣት የስጋ ዝምድናን ማጣት ሲሆን ሀገር ማጣት ግን አመለካከትን ማጣት እንደማለት ነው፤ ሀገር የአሳቢነት ልዕልና የሚወልደው ክብር ነው፡፡
ሀገር በማሰብ ስናድግ የምንፈጥረው የእናት መሆን ህያው አለኝታነት ነው፡፡ ወላጅ እናትን ግን አንፈጥራትም፤ እንድንፈጠርባት ሰበብ ናትና ተፈጥሯዊ ሽልማቷ ነው፡፡ አንክደውም፤ እንኖረዋለን…፡፡
በሀሳብ መብቃት በልብ የምንፈጥረው እናትነት ግን አለ፡፡ ሀገር የምንለው የተባ ምናብ ያጎለበተ ሰው የሚወልደው እናትነት ማለት ነው፡፡ ተፈጥሮ የሰጠችው እናትነት አብራካዊ ነው፤ ማሰብ የሚወልደው እናትነት ደግሞ ሀገር ይሆናል፡፡
የተፈጠረ ሀገር ብቻ አይደለም የምንፈጥረው የእናት ወዲያኛ ትርጓሜ፡፡ ልባዊ ትጋትና የአእምሮ መዳበር የሚወልዱት የሩቅ ባለምናብነት ስፍር ነው፡፡

👍18❤10
ሁለት አመጻ አለ፤ ራስን በመሆን ጉዞህ በጥባጭ የራስህ ጎን አለ፡፡ በሱ ላይ ካላመጽክ አንተህን የመድረስ ጀብዱ አትሰራም፡፡ በራስህ ላይ ተሰየም፡፡ አንተህን ማጽደቅ አንተህን በምናብህ ውስጥ ካየኸው በኋላ የምትጀምረው ጉዞህ ነው፡፡
ሁለተኛው አመጻ፡ የቀበጠና ያነሰውን ያንተን መልክ በማክሰም ላይ የምታደርገው ነው፡፡ ሁለቱም አጀማመራቸው ከተቃራኒ አቅጣጫ በመሆኑ ነው ሁለት ያልናቸው፡፡ ከታችኛው ጀምረህ ወደ ላይኛው አንተህ በመውጣት ካልሆነም፤ ከደረስክበት ከፍታህ ወደ ታች ባለመውረድ ትጋትህ ላይ የምትሆናቸው ሁለት መልኮችህን ለማለት ነው፡፡
ከመውረድ መሟሟት መጠበቅን ያጸና በማደግ መተለቅ ላይ የተማከለ ሰውህን በመስራት ትለመልማለህ፡፡
የምታድገው ከማይታየው የልብ ደጅህ እንጂ ከሚሰፈረው ስጋህ አይደለም፡፡ ከምትበላና ከምትለብሰው አይነት ሳይሆን ከምታስበውና ከምትዘነበለው ባህሪህ የተሳሰረ ነው፡፡
እውነታው ቀላል ነው፡፡ የሀሳብና የስብዕና እድገትህ በአይን አይታይም፤ በሜትር ወይም በኪሎም አትሰፍረውም፡፡ ከማይጨበጠው የውስጥህ ገሃዶች ስለሆኑ መለኪያቸው በሰዎች ዘንድ የምታሳርፈው ሚናና ፋይዳ ክብደት ነው፡፡
በራስህ ላይ ሳይቀር ሚዛንህ የቀለለ ሳለ እንደምን ወደ ሰው መሆንህ ጉርብትና እንዳለህ ታስባለህ? አንተህ ያለው ክብደትና ሚዛን በሌሎች ላይ ካለህ የብርሃን መልክህ ይሰፈራል፡፡ ብርሃን ያሳያል እንጂ አይጨበጥም፡፡ ራሱም አያይም፡፡ መመልከቻ ግን ስለሆነ ያለሱ አናይም፡፡
ለሰዎች መመልከቻ በሆንከው ውጋገን ነጸብራቅህ መጠን አንተን ታያለህ፡፡ እሱ ነው የተፈጥሮህ አቅም፡፡ ሰዎች ባንተ በኩል ማየት የሚችሉትን በጎ መንገድ በጥቂትም ሳትሆን እንደሰው ራስህን አትመልከት፡፡ የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ከተወለደ በኋላ ሰው የሚሆንበትን መንገድ የሚያበጅ አሳቢና አሰላሳይ ብሎም ከዛ ሲያድግ የሞራል ክስተት የሆነ ተፈጥሮ ነው፡፡

👍15❤9👏3
"ሸንበቆም ከተሰበረ በኋላ ነው ዋሽንትን የሚያዜመው"
ሩሚ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መሰበርን አትፍራ። ተጋፈጥ እንጂ ፈጽሞ አትሽሸው። ኑረው። እመነው። ይበልጥ የምታስታውሰው የታመምክባቸውን ገጠሞኞች አይደል?! በደስታ ጮቤ ያሳለፍካቸውን ዘለህባቸው አልፈኻል።
ሸንበቆ ሳይሰበርና ሳይነደል መዚቃ አይፈጥርም፣ አያንጎራጉርም። ጀግንነት ከብዙ መታመንና ለሞራል ሰውነት በጽናት ከመቆየት ይታያል።
በዓለም ጥቂት ጀግኖች ብቻ እናገኛለን። ብዙ አሸናፊዎች አናይም። የሚበዛው የአለም ሰው መጋፈጥ አይፈልግም። መታገል አይመርጥም። ለመፋለም ዝግጁዎች ጥቂት ናቸው። ከሌሎች ድላቸው ቢዘገይም የማይናወጥ *ሌጋሲ* ይከስታሉ።
።።።።።።።።።።
ለትውልድም አብሪ ፈርጦች ናቸው። ቢያዝኑም አይወድቁም። ባይደሰቱም ሰላማቸውን አያጡም። በመነሳትና ሰላም ውስጥ ብርቱ ጽናት አለ። ሰው የማይነቃነቅ ጀግና ሆኖ ከላይ ከተራራው በላይ ከጸሀይ አይነት ከፍታ የሚንጸባረቅ ብርሃን እንዲሆን ትጋቱ ፍርሀትን ድል ከማድረጉ ነው። ፊት ለፊቱን በብቃት ለመፋለም ካለው ቁርጠኛ ተግባሩ ነውም።
።።።።።።።።።።።።።

❤23👍9🔥2
... "ነፍስ በፍቅር ትሸነፋለች፤ ስለዚህ ወደ ፍቅር ቦኖ ፊቷን ታዞራለች። ፍቅር ለሰው ልጅ ከዳበረ ሰውነት በተሻለ መሠረቱ የሚጸና ከሌላ አቻ ሰብዕ ወይም የተፈጥሮ አካል ጋር በመረዳዳት የሚኖሩበት መንገድ-ስልት ነው።
በፍቅር ሥልጣን መገዛት ወይም ለፍቅር ማደር ማለት ነፍስን በወሰን ተገድባ ሕይወቷን እንድታጣጥም ማድረግ ማለት ነው። ነፍስ የውጪውን ዓለም በራሷ ዓይን ማየት ስለማትችል ከዓለም ያለ ሁሉ ቀላል ይመስላታል።
እርሷ መሻቷ የሚደርሳት በስሜት ሕዋሳቶቻችን በሚጓጓዙ የውጪው ዓለም ሸቀጦች አማካይነት ነው። ሆኖም ሰውን ከሚችለው በላይ ከተፈጥሮ ጋር እንዲታገልና እንዲላተም ታደርገዋለች። የዓለማችንን ሰው ሁሉ ቅጥ ባጣ ዕረፍት የለሽ መባዘን የተሞላ እንዲሆን ያደረገችው ነፍስ በቀላሉ የማትረካ ስለሆነች ነው።"...
[መሆንን መድረስ]

👍13❤6
ጥልቅ ህመም የብርቱ መነሳት ዋዜማ ነው፤
ሁለት ፈተናዎች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ ነው፡፡ ውጫዊ ማለት ከእኛ ውጪ የሆነ እንከን ሲሆን ገንዘብ ማጣት፤ ጤና ማጣት፣ ወዳጅን ማጣት ወዘተ… እንደማለት ነው፡፡
ውስጣዊ ፈተና ግን ጠሊቁ ሰውነትን የሚገነባው… ከተርታነት የሚያልቀው ሁነኛ የህይወት ጉዞ መሻገር ወይም መሰናከል ምንጭ የሆነው ረቂቅ፣ ውስብስብ የማይታይ የመንፈስ ውጊያ መሳይ የሆነ ደዳር የውስጥ ጦርነት አዉድማ ነው፡፡
ይህን ፍልሚያ ጥሞና ወስደን ልንረዳው የተገባ ነው፡፡ ምክኒያቱም በትክክል ራስን የማወቅ አቅራቢያችን ስንደርስ የሚከሰት በመሆኑ ነገሩ ከትልቁ የራስነት ጸሃይ የሚያጠልም ዲያቢሎሳዊ ዛር ስላለው ነው፡፡
ዲያቢሎሳዊ ባህሪ ያለው ትግል ነው፡፡ በምንፈልገው ጉዞ ደስተኛ ሆነን እየተጓዝን ከምንፈልገው መድረስ ስንቃረብ ድንገት ይዘንባል፡፡ እኩይነት ያለው፣ ያልጠበቅነው እንግዳ የማይታይ ሰራዊት ሆኖ ይፋለመናል፡፡
የኖርነውንና የወሰነውን ሁሉ የድል ብርሃን አስክዶ… ሁሉም የመጣነው…. በዛም ያሳከነው ድል ሁሉ ስህተት ነው ብለን እንድናምን የሚወሰውስ የውስጥ ነፍሲያ በሽታም ይሆናል፡፡
እንዲህ አይነቱን ፈተና ለማለፍ ጥቂት ቆም ብሎ ምንድን ነው የገጠመኝ? ብሎ መጠየቅና በመረጋጋት ጥሞና እውነቱን ማወቅ ይፈልጋል፡፡
ሰው አንድም በስጋው ይፈተናል፡፡ ስጋዊ ፈተና የቁስ፣ የዝና፣ ወይም የእውቀት አይነቶች አሉት፡፡
በሀብት ስንፈተን፣ ወይም የነበረንን ክብር ስናጣው የሚያመን ስሜት አለ፤ እውቀትም በራሱ ብቻውን የዓለም ፈተና ነው፡፡ ስጋዊ ፈተና መሆኑን ማጤን ግድ ነው፡፡ እነዚህ የተለመዱ ፈተናዎች ባብዛኛው ሰዎች የሚጎነተሉባቸው ተጠልፈው የሚወድቁባቸው ከዛም ለመነሳት የሚዳክሩባቸው የትግል ጦሮች ናቸው፡፡
…
ከዚህ በላቀ መድረስ ወይም ራስን የመሆን ትንንቆሽ የሚያልፉ ጥቂት ሰዎች የሚፈተኑባቸው ፈተናዎች እጅግ ጥልቅ ይሆናሉ፡፡ የሞራል፣ ወይም የመንፈሳዊ ባህሪ ካላቸው ሰራዊቶች ጋር የሚደረግን እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ይመለከታል፡፡
የውስጣዊ ማንነትን የሚፈትኑ… አቋምና የህይወት ዘመን ማንነትን የሚገዳደሩ ፈታኝ ኃይሎች ናቸው፡፡
ምክኒያት አያብራራቸውም፤ ሳይንስ አያውቃቸውም፤ መረጃ አይተነትናቸውም፡፡ ኢ-ምክኒያታዊ፣ ኢ-ተለምዷዊ ናቸው፡፡ የሚያውቃቸው ከጦሩ ማዕበል መሀል ገብቶ የሚፋለመው ጀግናው ታጋይ ብቻ ነው፡፡
ይህኛውን ፈተና ለማለፍ፤ ከስጋዊ ጎናችን መነጠል ግድ ይላል፡፡ በስጋዊ ስሌት አናሸንፈውም፡፡ ሰው ከሀብት፣ ከክብርና ከእውቀቱ ባሻገር የሆኑ… የሞራል፣ የስብዕና ወይም ሜታ-ፊዚካዊ መታወቂያዎች እንዳሉት መረዳት ሲችል ይሕኛው ፍልሚያ ምን እንደሆነ ያውቃል፡፡
…
ጊዜን መጠበቅ … ጥቂት የአፍታ ጥሞናዎች መውሰድ፤ ባለማሰብ እንዲሁ የጊዜ ዥረት ጥቂት እስኪያልፍ በመጠበቅ መረጋጋት ውስጥ እንደጸሃይ ደማቅ ቀን እንደሚወጣ ማመን የመጀመሪያው የድል መነሻ ነው፡፡
ከዛ ሂደት በሂደት በጠሊቁ የህይወትን ምንነት፣. ሰው የመሆንን ፋይዳ፣ በምድር ዓላማ የተሞላ የሚያሳካው ‹ፐርፐዝ› ያለው ሰው መሆንን በመጸበል ሁለተኛው አከርካሪ ሰባሪ ፍልሚያ ድል ይነሳል፡፡
….
ጥልቅ የሚሰባብረን የውስጥ ፈታኝ በሽታ እንከን ሁሉ በምንወስደው የአፍታ ጊዜያት ጥሞና ይዳከማል፤ በምትኩ በውስጣችን የማናውቀው ኃይል ይበዛናል፡፡ እዛ ከደረስን አንወድቅም፤ አንሸነፍም እኛው ራሳችን የድልና ብርሃን ዳኞች እንሆናለን፡፡
/////

❤21🥰3
ራሱን ለመስራት ከራሱ ጋ የሚዘልቅን ያከለ አስተዋይ የራሱ ጠባቂ ነው። በራሱ ላይ አብዮት የጀመረ ሰው ብቻውን ይበዛል። ዘመኑን ይፈጥራል። ይሻገራልም። ራስን በራስ አይኖች የማየት የዝምታ ሙግት የማደግ ጉዞ ነው፣ ወደ ራስ እንዙር። ከራስ ጋ እንዝመት፣
❤45👍10👏4🔥1
ነብይና ፈላስፋ
ታሪክ ጠቃሚያችን የሆነ የህይወት መስታወት ነው። የሀገርነት መሰረት ነው። የባህል ፈትል መቀጠያ ነው። የዛሬው እሴት ዛፍ ስር ነው። ወደ ነገ መዳበር ለመሄድ ኃይል ነው።
የሰውን ተፈጥሮ ለመረዳት የመጀመሪያው መግቢያ ነው። በታሪክ ውስጥ ራስን ማየት አለ። ዛሬን አንጽሮ ለመታዘብ ስፍር ነው። ስለሰው ልጅ የእድገት ጉዞ የእውቀት ምንዳሬ ሂደት ወይም ስለምንሄደው መንገድ ዋቢም ነው።
ሰው ከኑሮ ልምምዶቹና የምክኒያታዊነት ተሰናሳይ ብቃቶቹ ከሚያጎለብተው መረዳቱ ቀድሞ በታሪክ ውስጥ ቀላል የግንዛቤ መርጃዎች ያገኛል። እንደህጻናት ተረትም እንደቀላል ገጸ-ባህሪያዊ ተረክም ሆኖ መስማት ደስ እያለን የአንጎል መነቃቃት እናገኝበታለን።
እየዳበርነውም ታሪክ ህይወት መሆኑ እስኪገባን ያለው ርቀት ድረስ ብዙ የሚሰጠን ስፋት አለ።
በታሪክ ውስጥ የትናንት ህያው ሰው አለ። ገድል አለ። ኑሮ አለ። ትግል አለ። ሀገር ምስረታ አለ። ፍቅር አለ። እምነት አለ። ክህደት አለ። ደግነት አለ። ክፋት አለ። ጥበብ አለ። እውቀት አለ። ሁሉም ለዛሬው ሰው የሀሳብና ስሜት መናገሻዎች ናቸው።
የእውቀትና የትዝታው የሩቅ አለም ቃናዎች መገኛ ነው። ሰው ወደ ትናንት እንዲያይ አንድም ስሜቱ ትዝታን ይለዋል፤ አንድም ምናቡ በሀሳብና ትውስታው ዥረት ያፈሰዋል።
መለስ ብሎ ማየትን በብዙ ካሰብነው፤ እውቀትን ከትዝታችን አቆራኝተን ጥቂት እንቆያለን። በቀጥለን የምንሰፍረው ከትዝታዎቻችን መንደሮች እና ከኖርነው የህይወት ልምድ አለን የምንለውን እውቀት በማጣጣም ይሆናል።
ሰው በመንገዱ ነው የሚኖረው። በምናቡ ፊትና ኋላ ይመላለሳል። ወደላፈውም ወደሚመጣውም ይመሰጣል፥ ይብላላል፤ ከራሱ ጋ፤ በዚህም ወደ ከኋላው ትዝታና ከሚመጣው ህልሙ ራሱን ይመለከታል። ዛሬን እየኖረ ያስባቸዋል።
ገጽ 20📚

❤28🔥2👏1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ነብይና ፈላስፋ
ትናንት ምንድን ነው?
ባጭሩ የተከማቸው እኛነታችን ማለት ነው። ትናንት ከርዕሳችን አዉድ አኳያ ስለምናየው ትርጉማችንም በዛው የተቃኘ ሆኗል። የተከማቸው እኛነት እስከትናንት የኖርነው ማለት ነው። ዛሬ የምናጸባርቀው አመለካከት ወይም የሚሰማን ስሜት እስከትናንት በኖርነው እድሜያችን የተሰራ ነው።
እገሌ ማን ነው ስንባል የምንለው አለን። አጠገባችን ያለ ጓደኛችን ባህሪው እንዲህ ነው አመለካከቱም እንዲያ ብለን ስንመዝነው ሚዛናችን እስከትናንት የኖረው እሱነቱን ስለሚያንጸባርቅልን ነው። የእያንዳንዳችን ማንነት የመጣነው ጊዜ ግልባጭ ነው።
ትናንት ውስጥ የህይወት ልምዳችን አለ። ያዳበርነው እውቀት አለ፥ የደረስንበት አመለካከት አለ፥ የምናስታውሳቸው በርካታ ትዝታዎችም አሉ። ሁሉም በአንድነት የዛሬው እኛነት ብይን ሆነዋል። የትናንት ጉልበት የዛሬ ክውናችን ላይ ያስወስናል፥ ስሜታችን ላይ ጉልበት አለው። ትናንት ዛሬን እንዲህ ይወስናል ቀጣዩም መንገዳችን ላይ።
ትዝታ ያለፈው ስሜታችን ነው። ተሞክሮ (የህይወት ልምዳችን) የኖርነው የትምህርትና የግንዛቤ መስፈሪያችን ነው። በትዝታችን ስሜታችንን እንጠሙናለን። በዛው ስፍር ሁሉ ለእውቀት ክምችት የመጣነውም አለ። የተማርነውን እውቀት በስሜት አናየውም። የምናብራራው ስለሆነ። ከስሜት ውጪ የሆነው እኛዊነት ማለት ነው። እውቀት ስሜት የለለው ደረቅ ገሃድ ነውና ለስሜት ባይተዋር ነው።
ግለሰብነታችን የግል አመለካከትና እይታችን የሚሰራበት ያለፈው መንገዳችን ማለት ነው። እንደግል በአስተሳሰባችን ላይ ያከልነው መረዳት ልምድ ወይም ተሞክሯችን ይሆናል። በትዝታችን ውስጥ ስሜታችን ይነካል። ተሞክሯችን ባሳወቀን ደግሞ አመለካከታችን ላይ እክያ እናገኛለን።
በእውቀት ደጅ ስሜት አይኖርም።
tiktok.com/@burhanadisofficial

❤17👍4🔥1🥰1
ነብይና ፈላስፋ
እንዴት ነው ወደ ትናትን ማሰብ ያለብን? የመጣነው ጊዜ ዛሬን ስናስብ የሚመላለስብን በምን መልኩ ነው? እንዴት ነው ልንረዳው የተገባው? ትናንት ለዛሬ ምናችን ነው? ወደፊት ወደ ሚመጣው ትኩረታችን እንዳይጸና እየተመላለሰ የሚቀንሰው አለ? ወይስ ወደፊት ስለምናስበው የጸና መሰረት እንድንይዝ የሚረዳው በጎ ኃይል አለው?
በጥሞና ማሰቡ ግድ ነው፥ ሰው የትናንቱ ማግስት ነው። ዛሬን ነን፥ አሁን የሆነው ሁሉ ከትናንት የተገለበጠ ነው። ያለፍንበት ጊዜ ማለት እኛን የሰራ ነው። ማናችንም ስለራሳችን ስናስብ በቀጥታ የኖርነው ህይወት ትርክቶች መሆናችንን እንገልጣለን።
ዛሬ የሆነው በሰዎች ዘንድ ተገልጦ የሚመዘነው ማንነታችን ትናንት የዘለቅነው የየእለት ተሞክሮዎችና ማህበራዊነት ተጋምዶ የተጻፈው ጠባያችን ነው። ግንዛቤያችንም እንዲሁ የተኖረው ትናንታችን ስንድት መሆኑን እንረዳለን።
Join us👇👇👇👇
https://tiktok.com/@burhanadisofficial

❤14
ነብይና ፈላስፋ
👇👇👇
በትዝታችን ስሜት አለን፤
በልምዳችንም እውቀት አለን፤
ስሜት ኢ-ምክኒያታዊው ጎናችን ነው። የስሜታችን እኛ፥ በስሜት የምንኖረው የህይወት ጉዞ፤ ከሰዎች ጋ ስንሆን የሚሰማን መደሰት መከፋት፤ ማፍቀር መፈቀር ጥላቻ ክብር ወዘተ የምንለው አይነት ስሜት አለን። ደስታን በምክኒያት አንመዝነውም። ጥላቻንም ሁሌ ሳናውቀው ሊጣባን ይችላል። ሌላም ሌላም ስናፈቅር በምክኒያት አይሆንም። ስንናፍቅም ምክኒያት የለንም። ግን የኖርናቸውም የምንኖራቸውም የእኛው አካሎች ናቸው፥
የምንወደውን ሰው በማጣት ከባድ የሀዘን ትዝታ ይኖረን ይሆናል። እጅግ ተደስተን ያለፍንበትም ገጠመኝ ይኖረናል። የምናስታውሳቸው ሲሆኑ በትውስታችንም ጊዜ የሚሰማን የደስታ ወይም የማዘን ስሜት አሁናችንን ይዳኛል። የምንሆነው ላይ አሻራ ያሳርፋል።
ያሳለፍነው ትናንት ውጤቶች ነን። የምናስታውሰው ስሜትን የሚሰቀዝ ክስተት አለን፤ ያዳበርነው የእውቀት ልምድ የሆነን መረዳትም አለን። በእውቀታችን ዛሬን ለመኖር ስንጠቀም፤ በትዝታችን ደግሞ በጎውንም ክፉውንም አስበን በስሜት እንነካለን።
ወደ ትናንት የመመለስ ኃይል በዚህም መስክ አይለቀንም። ሁሌም አብሮን አለ፤ አሁንም አለ፤ መለስ ብለን ለማስታወስ ስንሞክር የምንችለው ብዙ ማስታወስ ይኖረናል።
ስንፈልግ የምናስታውሰው ምንም ነው፤ እንዲሁ ሳንፈልግ ትዝ እያለ የሚረብሸን ብዙ ትናንት ግን ዛሬን ይጎዳብናል። በሁላችንም ዘንድ መጠኑ ቢለያይም የትናንት ጉልበት ተጽዕኖ አለብን። የምንመዝንበት ኃይል ያስፈልገናል።
ትዝታዎቻችን የጉድኝት ስሜቶቻችን ናቸው። የኖርንበት ቤተሰብ አብሮነት የሚወልዳቸው ትውስታዎች። የበዓላት፥ የጨዋታ፥ የጸሎት፤ ወዘተ አይነት ጠባያት። የመንደራችን ሰዎች የተለያየ ገጠመኝ፥ የእኛ ግንኙነትና የተለየ ስሜት የፈጠሩብን ትውስታዎች ወዘተ ከፍ ስንል ደግሞ የወደድናቸው የፍቅር አጣማጆችና የኛ ሁኔታ፥ በትምህርት ቤት የማንረሳው መምህርና ድርጊት ወዘተ ብዙ ብዙ ነገሮችን በማስታወስ ውስጥ ስሜታችን ይነካል።
እንደኃይማኖተኛም ከእምነታችን ግብር የተቆራኙ ድርጊቶች፥ ኃይማኖታዊ ጉዞዎች፤የስብከት ስርዓቶችና ትዝታዎች ወዘተ አስታውሰን የሚሰማን ስሜት አለ አሁን ላይ።
የኖርነው ሁሉ በመጠን ይለያያል፤ አሁን ላይ ሆነን ልናስታውሰው የምንችለው በየደረጃው ለስሜታችን የቀረበ ከነበረና ከብርታቱ ይሆናል። ከፈጠረው የተለየ ትውስታ፥ ነገር ግን ማናችንም በኖራቸው ህይወቶች የምናስታውሳቸው ትዝታዎች አሉን።

❤17👍7