Forwarded from ጦር ሜዳ
Audio
ድንግልናሽን ፡ ግን ፡ አጥብቀሽ ፡ ጠብቂ
*******************************
አንቺን ፡ ፈልገውሽ ፡ በዙሪያሽ ፡ ሚያደቡ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ ለመዋጥ ፡ የጓጉ
#ድንግልናሽን_ግን_አጥብቀሽ_ጠብቂ
ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ ቁሚ ፡ ተጠንቀቂ
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ እውነተኛው፡ መሲህ
ሊመጣ ፡ ነውና ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ (፪x)
*******************************
አንቺን ፡ ፈልገውሽ ፡ በዙሪያሽ ፡ ሚያደቡ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ናቸው ፡ ለመዋጥ ፡ የጓጉ
#ድንግልናሽን_ግን_አጥብቀሽ_ጠብቂ
ሙሽራሽ ፡ ይመጣል ፡ ቁሚ ፡ ተጠንቀቂ
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ እውነተኛው፡ መሲህ
ሊመጣ ፡ ነውና ፡ ልብስሽን ፡ እጠቢ (፪x)
🙏2
Audio
➡➡ይሆንልኛል⬅⬅ አስቴር አበበ
*********
ይሆንልኛል ይሳካልኛል
ሥጋት ሰፈሬን ከራቀ ሰንበትበት ብሏል (4x)
አልረሳውም ማንነቴን
በደም ዋጋ መገዛቴን
ንጉሥ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ
ልጄ ምርጤ ርስቴ እንዳለኝ (2x)
በምሰማው ሌላ ውሸት
አልጥለውም ይህን ዕውነት
ንጉሥ ልጁን የላከልኝ
የተወደድኩ ምርጥ ዘር ነኝ (2x)
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ሁኔታ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ተደርጐልኛል ተሳክቶልኛል ይህን አውቃለሁ
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ጠላቴ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ይሆንልኛል ይሳካልኛል ይህን አውቃለሁ
ቁም ነገር አድርጐት የእኔን ጉዳይ
ክብሩን ሁሉ ትቶ ወርዷል ከላይ
አቅሜን አውቃለሁ በእርሱ ያለኝን
የሆንኩትን ሆኖ ያረገኝን (2x)
ደዌ በእኔ ላይ ላይሰለጥን እርግማን በቤቴ እንዳይገኝ
ዝቅታ ላይሆንብኝ በላዬ መሸነፍ መረታት ላያገኘኝ
ከፍ ላለ ሕይወት በክርስቶስ ታጭቻለሁ ይህ ነው ዕጣ ፈንታዬ
የሆንኩትን ሁሉ ሆኖልኛል በድል ተፈጽሟል ጐዳናዬ
ያለቀ ነው ያኔ ድሮ
የእኔ ጉዳይ የእኔ ኑሮ
በቀራኒዮ ተራራ ላይ
ተፈጽሟል ብሎኛል የእኔ ጉዳይ (2x)
*********
ይሆንልኛል ይሳካልኛል
ሥጋት ሰፈሬን ከራቀ ሰንበትበት ብሏል (4x)
አልረሳውም ማንነቴን
በደም ዋጋ መገዛቴን
ንጉሥ ከላይ ሆኖ እንዳየኝ
ልጄ ምርጤ ርስቴ እንዳለኝ (2x)
በምሰማው ሌላ ውሸት
አልጥለውም ይህን ዕውነት
ንጉሥ ልጁን የላከልኝ
የተወደድኩ ምርጥ ዘር ነኝ (2x)
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ሁኔታ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ተደርጐልኛል ተሳክቶልኛል ይህን አውቃለሁ
አይሆንም አይሰምርም ያለው ኧረ ማን ነው?
ጠላቴ ነው? ነቅቻለሁ!
ቃሉን በንጉሥ ቃል ሽራለሁ
ይሆንልኛል ይሳካልኛል ይህን አውቃለሁ
ቁም ነገር አድርጐት የእኔን ጉዳይ
ክብሩን ሁሉ ትቶ ወርዷል ከላይ
አቅሜን አውቃለሁ በእርሱ ያለኝን
የሆንኩትን ሆኖ ያረገኝን (2x)
ደዌ በእኔ ላይ ላይሰለጥን እርግማን በቤቴ እንዳይገኝ
ዝቅታ ላይሆንብኝ በላዬ መሸነፍ መረታት ላያገኘኝ
ከፍ ላለ ሕይወት በክርስቶስ ታጭቻለሁ ይህ ነው ዕጣ ፈንታዬ
የሆንኩትን ሁሉ ሆኖልኛል በድል ተፈጽሟል ጐዳናዬ
ያለቀ ነው ያኔ ድሮ
የእኔ ጉዳይ የእኔ ኑሮ
በቀራኒዮ ተራራ ላይ
ተፈጽሟል ብሎኛል የእኔ ጉዳይ (2x)
❤4
Pastor Tamrat Haile Egziabeher Terarayen Anagerew
Gedion Dessie
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው-ታምራት ሃይሌ
**********
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
ከእንግዲህስ ምን ሊበጀኝ እዬዬ ማለት ሰለቸኝ
አይደርሰኝም ወይ ወረፋ አይገድህም ወይ ስጠፋ
አምላካዊ መልስ ከሰማይ ዘሎ በኮረብታዎች ላይ
ዙሪያ ገባውን አበራው ተገፈተረ ተራራው
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
Yedura ሜዳ ሃውልቱ ሰባት እጅ ነዶ እሳቱ
ሊያጠፋኝ የተመኘው ጌታ በቁጣው ጐበኘው
ጠላት ለራሱ ቆፈረ ሊያስረኝ የወጣው ታሰረ
ሊበላኝ ያሻው ተበላ እኔ ግን አለሁ በተድላ
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
የብዙ ዘመን ጠላቴ ቆሞ የነበረ በፊቴ
ብርሃን እንዳላይ ከልሎ አየሁ በጌታዬ ተጥሎ
ጌታ በሰራው ከበረ መዝሙር በአፌ ጨመረ
ሰማይ ያጨብጭብ በደስታ ምድር ታክብረው በእልልታ
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
**********
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
ከእንግዲህስ ምን ሊበጀኝ እዬዬ ማለት ሰለቸኝ
አይደርሰኝም ወይ ወረፋ አይገድህም ወይ ስጠፋ
አምላካዊ መልስ ከሰማይ ዘሎ በኮረብታዎች ላይ
ዙሪያ ገባውን አበራው ተገፈተረ ተራራው
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
Yedura ሜዳ ሃውልቱ ሰባት እጅ ነዶ እሳቱ
ሊያጠፋኝ የተመኘው ጌታ በቁጣው ጐበኘው
ጠላት ለራሱ ቆፈረ ሊያስረኝ የወጣው ታሰረ
ሊበላኝ ያሻው ተበላ እኔ ግን አለሁ በተድላ
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በልጄ ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
የብዙ ዘመን ጠላቴ ቆሞ የነበረ በፊቴ
ብርሃን እንዳላይ ከልሎ አየሁ በጌታዬ ተጥሎ
ጌታ በሰራው ከበረ መዝሙር በአፌ ጨመረ
ሰማይ ያጨብጭብ በደስታ ምድር ታክብረው በእልልታ
እግዚአብሔር ተራራዬን አናገረው
እንዲህ አለው (፫x)
"አንተ ተራራ!
ኧረ ለመሆኑ ምንድነህ?
በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ"
አለው (፫x) ናደው ደለደለው
❤1
⚠️ ጠንከር ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ለአማኞች
📖 “አማኝ ነኝ”፣ “ክርስቲያን ነኝ”፣ “ወንድም ነኝ” እያለ...
“...ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር እንዳትተባበሩ፤ ከእንደዚህ ዓይነቱ ሰው ጋር ምግብ እንኳ አትብሉ።”
📖 1 ቆሮንቶስ 5፥11
━━━━━━━━━━━━━━
🔥 እንወያይ!
በዚህ ጥቅስ ውስጥ ትኩረት የሚስቡ ቃለት፦
❗ “እንዳትተባበሩ”
❗ “ምግብ እንኳ አትብሉ”
🤔 ጳውሎስ ምን እያለን ነው?
ምን ማለቱ ነው?
━━━━━━━━━━━━━━
🧐 “ማይስገበገብ ይጠፋል” ብለን ነው?
እንዲሁም፣
“ቢጠፋ ቢጠፋ ተሳዳቢ ይጠፋል?”
🤔 ታዲያ ጳውሎስ ከእንደዚህ ዓይነት ክርስቲያን ጋር “አትተባበሩ” “ምግብ እንኳ አትብሉ” ሲል በእውነት ምን እያለ ነው?
━━━━━━━━━━━━━━
🧐 እሺ… “መሴሰን” ማለትስ ምን ማለት ነው?
“የሚሴስንማ አይጠፋም!?” ልል ነበር 😄
ነገር ግን “መሴሰን” የሚለው በደንብ አልገባኝም።
🤔 ታዲያ፣ “በጌታ ነኝ” ከሚሉ ሰዎች ጋር እንዴት ነው አብረን የምንሆነው?
❓ እንዴት ነው አብረን የምንበላው?
❓ እንዴት ነው አብረን የምንመላለሰው?
❓ ጳውሎስ ደግሞ “እንዳትተባበሩ… ምግብ እንኳ አትብሉ” ለምን ይለናል?
━━━━━━━━━━━━━━
🔥 እስቲ እንወያይ!
ለምንድነው እኛ ክርስቲያኖች ጠንከር ባሉ በሥነ-ምግባር ላይ ትኩረት ባደረጉ በእግዚአብሔር ቃል የማንወያየው?
💬 እስቲ ከጥቅሱ በመነሳት ሀሳባችሁን ስጡ።

❓ ኢየሱስ ምን አለ?
📌 ስለ እምነት ብቻ
📌 ስለ “ጌታ ሆይ” ስለማለት
📌 ስለ የአብን ፈቃድ ስለማድረግ
📌 ስለ መታዘዝ
📖 ሉቃስ 6፥46
«“እኔ የምለውን አታደርጉም፤ ታዲያ ለምን፣ ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ?”»
😳 ኢየሱስ ራሱ ይህን ጥያቄ ጠየቀ።
👉 “ጌታ ሆይ” ማለት ብቻ በቂ ነው?
👉 ወይስ እርሱ የሚለውን ማድረግ ያስፈልጋል?
---
🔥 ኢየሱስ ሌላ ቦታ ደግሞ ምን አለ?
📖 ማቴዎስ 7፥21
«“በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ ሳይፈጽም ‘ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤’ የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማይ አይገባም።”»
❗ ኢየሱስ እዚህ ላይ ምን እያለ ነው?
❌ “ጌታ ሆይ” የሚለኝ ሁሉ...
✅ “የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ”
---
❤️ ኢየሱስ ስለ መውደድስ ምን አለ?
📖 ዮሐንስ 14፥15
«“ብትወዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።”»
እዚህም ኢየሱስ እኔን መውደዳችሁ የምታወቀው በመታዘዛችሁ ነው ይለናል።
---
🔥 እንግዲህ ዋናው ውይይት፦
❓ በኢየሱስ ማመን ብቻ ወይስ የአብን ፈቃድ ማድረግ/መታዘዝ?
ኢየሱስ ራሱ ምን አለ?
«“ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ትሉኛላችሁ፥
እኔ የምለውን ግን አታደርጉም።»
«“የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ” እንጂ።»
«“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።”»
---
🤔 እንወያይ
❓ “የአብ ፈቃድ” ምንድነው?
❓ ኢየሱስ ስለ አብ ፈቃድ ምን አለ?
📖 ማቴዎስ 21፥28–31 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦
«“ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው።»
«“ልጁም፣ ‘አልሄድም’ አለው፤ ኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ።»
«“ወደ ሁለተኛው ልጁ ሄዶ እንደዚያው አለው፤ ልጁም ‘እሺ ጌታዬ እሄዳለሁ’ አለው፤ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ።»
«“ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?”»
📖
---
3️⃣ አንድ ሰው
“ጌታ ሆይ”
“አደርጋለሁ”
“አምናለሁ”
“ክርስቲያን ነኝ”
“በጌታ ነኝ”
“አማኝ ነኝ”
እያለ በተግባር ግን ካላደረገው ምን እንላለን?🤔
---
🔥 ከሰዎች ሀሳብ ትንሽ ወጣ ብለን፣ ቲዎሎጂ ክርክርንም ትተን፣ ከራሳችን ፍላጎትም ርቀን —
ኢየሱስ ምን አለ? እንበል
💬 እንወያይ።

❤5
Track 11
artist
ሰላም
Dr. ደረጄ ከበደ
---
በየአመቱ ሲፋረሙ የብራናው የቀለሙ
እንዲያው ሊፋት መካሪ አጡ
ሰላም ውድዋን ከየት ያምጡ
ይህን ቋጥረው ያን ሲፈቱ
ጀንበር ገባች መላ አልመቱ
ምስጥሩማ ቅርብ ነበር
ለእግዚአብሔር ሰው ቢሰበር
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
የሰላሙን ልዑል ናቁት
አልፈው ሄዱ ገላመጡት
አቅማቸውን ያለወቁ
በምድር ገነው የመጠቁ
በስቅል ወርቅ በእልፍ ሽልንግ
በጠፍ መሬት ያም ቢያስፈልግ
ከገበያ ሊሸምቷት
በምጥ ውለው ወይ ሊወልጧት
ሰላም ስሟን ወተወቷት!
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ሰላም ለዓለም!
ሀገሯ ሰማይ ነው
ዘሯ በምድር የለም
ምንጯ በዚህ የለም
በሩቅም በቅርቡም
ክቡራን ክቡራት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ክቡር ፕሬዚዳንት
ዘውድም የጫናችሁ
ንግስተ ነገስታት
እሩጫችሁ ይብቃ!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በትጋት
ግራ የተጋቡ ተላላቅ መንግሥታት
ደመሩ ቀነሱ
አወጡ አወረዱ
የሰላም መኖሪያ
ጠፍቷቸው መንገዱ።
Dr. ደረጄ ከበደ
---
በየአመቱ ሲፋረሙ የብራናው የቀለሙ
እንዲያው ሊፋት መካሪ አጡ
ሰላም ውድዋን ከየት ያምጡ
ይህን ቋጥረው ያን ሲፈቱ
ጀንበር ገባች መላ አልመቱ
ምስጥሩማ ቅርብ ነበር
ለእግዚአብሔር ሰው ቢሰበር
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
የሰላሙን ልዑል ናቁት
አልፈው ሄዱ ገላመጡት
አቅማቸውን ያለወቁ
በምድር ገነው የመጠቁ
በስቅል ወርቅ በእልፍ ሽልንግ
በጠፍ መሬት ያም ቢያስፈልግ
ከገበያ ሊሸምቷት
በምጥ ውለው ወይ ሊወልጧት
ሰላም ስሟን ወተወቷት!
ሰላም! ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ወዴት አለሽ?
እሩቅ ሀገር፣ እሩቅ ሀገር
ተሸሽገሽ!
ያለሽበት ያንቺ ማረፍያ ከጠፈር በስቲያ
ሰው ተፍጨርጭሮ ሊያገኛት እንቅልፉን አጥቶ
ዛሬም እንደ ትላንት ባዶ እጁን ቀረ መና ለፍቶ
የሰማዩን አምላክ አቤት ማለት ጠልቶ
መና ቀረ ለፍቶ፣
መና ቀረ ለፍቶ!
ሰላም! ሰላም! ሰላም!
ሰላም ለዓለም!
ሀገሯ ሰማይ ነው
ዘሯ በምድር የለም
ምንጯ በዚህ የለም
በሩቅም በቅርቡም
ክቡራን ክቡራት
ጠቅላይ ሚኒስትሩ
ክቡር ፕሬዚዳንት
ዘውድም የጫናችሁ
ንግስተ ነገስታት
እሩጫችሁ ይብቃ!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ሰላም ከእግዚአብሔር ናት!
ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በትጋት
ግራ የተጋቡ ተላላቅ መንግሥታት
ደመሩ ቀነሱ
አወጡ አወረዱ
የሰላም መኖሪያ
ጠፍቷቸው መንገዱ።
❤6🔥4
Track 09
artist
ሮጦ ሮጦ-ደረጄ ከበደ (ዶ/ር)
━━━━
ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተስ በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን
ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን
ላንተ የሚበጅ
ሳትሆን በአንቀልባ አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ
ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
እድሜ ጤዛ ነው ረጋፊ አበባ
ባለም ስትኖር
የጭንቅ የስቃይ ዘመነ ለቅሶ
ዋይታና ሽብር
የእፎይታህ ናፍቆት የሰላም ፍቅር
ካለ በልብህ
ጌታን ተቀበል እርሱ ታማኝ ነው ሁሉን ሊሰጥህ
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
ሮጠህ ሮጠህ
ዛሬም ሮጠህ ሮጠህ
ትላንትም ሮጠህ
ነጌም ትሮጣለህ
ነገር ግን የትስ ትደርሳለህ
ሁሉም አልረባህ
ሁሉን ሞክረህ
ቧጠህ ቆፍረህ
ትንፋሽ አልቀረህ
ዛሬ ግን ተው ይብቃህ
አጋዥ ጌታ እያለህ
ሮጠህ ሮጠህ
ዛሬም ሮጠህ ሮጠህ
ነጌም ሮጠህ
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
የትስ ትደርሳለህ
ኦኦ የትስ ትደርሳለህ ሮጠህ ሮጠህ
ሮጦ ሮጦ ሳይደርስ የልቡ
ለሞተ አዝናለሁ ሳይሞላ አሳቡ
አንተስ በሕይወት ሰምተሃል ቃሉን
ፍርድ ባንተ ነው ብትንቅ ማዳኑን
ሌላ ምን አለ የሚያስጨንቅህ ላንተ ያቃተህ ሱስ ነው መዋተት ባሪያው አድርጎ አንተን የገዛህ
ዝሙት ነው ስካር ያስፈራህ ጓዴ ካንተ አይሎ
ጌታን አማክረው እርሱ ችሎታል ሕይወቱን ከፍሎ
ወንድሜ ስማ ቁምነገር ምክሬን ላንተ የሚበጅ
ሳትሆን በአንቀልባ አቅም ሳያንስህ እንደ ሕጻን ልጅ
ሞት አጥልቶብህ መቃብር ውጦህ ትንፋሽህ ሳይቆም
ጌታን ተቀበል ዋስትና አድርገው ሳትጠፋ ከአለም
ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ ሮጠህ
....

❤3🙏1
በምድር #እንደመፃተኛ እና #እንግዳ የምኖር ነኝ፤ ከአለም ጋር የማልስማማ ነኝ።
የአለምን ያደፈ የቆሸሸ ግብዣ በደም በተጨማለቀ እጅ ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች ያለ የእግዚአብሔር ጠበኛ የሚያቀርበውን ነፍሴ እጅጉን ትፀየፋለች።
በአለም የሚያምር ነገር የለም።
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ናና፤
አመፀኞችን ተበቀል፣
እምቢተኞችን ዋጋቸውን ክፈላቸው
ናና ከዚች አለም አመፃ አሳርፈን።
ክርስቲያን እንዴት ከአለም ጋር ይተባበራል።
እንዴትስ በአመፀኞች ድል አብሮ ይደግሳል።
ክርስቲያን ድንበሩን ጠብቆ ይኖራል።
ክርስቲያን በአለም ውሸት አይታለልም።
የጠራውን ታምኖ ይኖራል እንጂ ተበልቶ ለሚጠፋ እንጀራ ብዙ ዋጋ በመክፈል የተጠራበትን ትልቁን ሽልማት አይጥልም።
ወገኖች ንቁ ተግታችሁ ጌታችሁን ጠብቁ እሱ እንደተናገረው ይመጣል።
መምጫው ቀርቧል
አሁን ጊዜው ነቅተን ታጥቀን የምንቆምበት እንጂ ከአላፊው አለም ጋር የምንሟሟቅበት ጊዜ አይደለም።
#ኧረ_እንንቃ!
ለኔ ግን ኢየሱስ ይምጣልኝ ተስፋዬ ምፅዓቱ ነው። እንጂ በዚህች አለም እኔስ #እንግዳና_መፃተኛ ነኝ!!

❤3
🌿✨ ከግል ምልከታ ይልቅ ለእውነት ዋጋ ስጡ! ✨🌿
📌 ይህ መርህ ሁሉንም የሕይወታችን አቅጣጫ ይመለከታል።
🏫 በትምህርት ቤት፣
👨👩👧👦 በቤተሰብ መካከል፣
🤝 በጓደኝነት ውስጥ፣
💼 በሥራ ቦታ፣
👑 በአመራር ውስጥ፣
📖 በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣
🌍 በባህልና በማኅበረሰብ አመለካከቶች፣
🔄 በዕለት ተዕለት ኑሮና በማንኛውም ውይይት።
የትም ብትሆኑ፣ ከማንም ጋር ብትሆኑ፣ ምንም እያደረጋችሁ ብትሆኑ፦
✅ ከግል ምልከታ ይልቅ ለእውነት ዋጋ ስጡ።
✅ ከግል አመለካከትና አስተያየት ይልቅ እውነትን አስቀድሙ።
✅ ከሰዎች ሀሳብ ይልቅ እውነታውን ምረጡ።
✅ ከግል ጥቅም ይልቅ ለእውነት ቁሙ።
📖 የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት
🌿 «ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ።»
📌 1 ተሰሎንቄ 5:21
🌿 «ይልቁንም እውነትን በፍቅር እየተናገርን፣ ራስ ወደ ሆነው ወደ እርሱ በነገር ሁሉ እናድጋለን፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።»
📌 ኤፌሶን 4:15
✨ እውነትን ፈልጉ። እውነትን ምረጡ። እውነትንም በፍቅር ተናገሩ! 🌿

❤2🙏1
አውጃለሁ_Awjalehu_ቃልኪዳን_ጥላሁን_Lily_#2026_Mezmur_Tube.mp3
15.5 MB
አውጃለሁ- ቃልኪዳን ጥላሁን
******************
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ (2x)
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
******************
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ (2x)
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
አውጃለሁ ዛሬ ታላቅነቱን
አውጃለሁ ዛሬ አምላክነቱን (4x)
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነህ ፣ ትልቅ ነህ
ትልቅ ነዉ ትልቅ ከሚመስለው በላይ
ኃያል ነዉ ኃያል ከሚመስለው በላይ
ብርቱ ነው ብርቱ ከሚመስለው በላይ
ጌታ ነው ጌታ ከሚመስለው በላይ (2x)
ከእግዚአብሔር የሚበልጥ አንድ ነገር አላውቅም
ይህ እንደዚህ ነው አንደዚያ ነው አልልም
ግን እርግጠኛ ነኝ አንድ ነገር አውቃለሁ
የማምልከው አምላክ ከዚህ ሁሉ በላይ ነው (2x)
በላይ በላይ ፣ በላይ በላይ (4x)
❤3
Mulu_Wongel_A_Choir_ሙሉ_ወንጌል_ሀ_መዘምራን_Amlak_Eregnaye_Neew.mp4
19.5 MB
ሙሉ ወንጌል ሀ መዘምራን-አምላክ እረኛዬ ነው
*****
ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ
ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ
ብቻ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ
ጽልመት ሲመጣ የመከራ ጉም
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩም ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
*****
ክንድህ ይበርታ በጠላትህ በር
ሥራቸው ይፍረስ ይድቀቅ ይሰበር ሃሌሉያ
ስምህ ይለምልም ዙፋንህ ይጽና
ለባሪያህ በጐ ውለሃልና ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ውዳሴን ከአፌ አንተን ከልቤ
ከቶም አይጠፋ ብኖር ተርቤ ሃሌሉያ
የቅርብ ወዳጄ የጦር አዝማቼ
ብቻ አትለየኝ ብቆይ ታክቼ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ብቆም ብቀመጥ ብሄድ ብተኛ
አምላኬ አንተ ነህ የእኔ ጓደኛ ሃሌሉያ
ጽልመት ሲመጣ የመከራ ጉም
አንተን ጠርቼ እኔ አላፈርኩም ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ሕመም ሞትህን ሥጋዬ ለብሶ
ይዋረድ ይለፍ ጽዋህን ቀምሶ ሃሌሉያ
የጻድቁን ሞት ነፍሴ ተጠምታ
ትጥገብ አትፈር ስምህን ጠርታ ሃሌሉያ
አዝ፦ አምላክ እረኛዬ ነው
አምላኬ እረኛዬ ነው (፪x)
ሮሜ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤
²⁹ ዓመፃ ሁሉ፥ ግፍ፥ መመኘት፥ ክፋት ሞላባቸው፤ ቅናትን፥ ነፍስ መግደልን፥ ክርክርን፥ ተንኰልን፥ ክፉ ጠባይን ተሞሉ፤ የሚያሾከሹኩ፥
³⁰ ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚያንገላቱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
³¹ የማያስተውሉ፥ ውል የሚያፈርሱ፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ምሕረት ያጡ ናቸው፤
³² እንደነዚህ ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።
Romans 1 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ Being filled with all unrighteousness, fornication, wickedness, covetousness, maliciousness; full of envy, murder, debate, deceit, malignity; whisperers,
³⁰ Backbiters, haters of God, despiteful, proud, boasters, inventors of evil things, disobedient to parents,
³¹ Without understanding, covenantbreakers, without natural affection, implacable, unmerciful:
³² Who knowing the judgment of God, that they which commit such things are worthy of death, not only do the same, but have pleasure in them that do them.
፦በዚህ ክፍል ላይ የተጠቀሱትን የሐጢያት አይነቶች በዝርዝር እንመልከት፤ ሌሎችን ለመገምገም እና ለመፍረድ ሳይሆን እራሳችንን እንመርምር፤
1#አመፃ(Unrighteousness,Injustice, wrongdoing) አመፃ ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክለኛ ከተባለው ነገር ተቃራኒን መስራት ነው።
ለምሳሌ፦ፍትህን ማጓደል፣ የሰራተኛን ደሞዝ ማወናበድ፣ ማጭበርበር፣ ችግረኛውን ድምፅ የሌለውን መጨቆን፣ አድሎ ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል ።
2,#ዝሙት፣መመኘት(fornication,sexual immortality,adultery)፦
#ዝሙት የሚለው ቃል የትኛውንም አይነት ወሲባዊ ርኩሰትን ያካትታል።
ለምሳሌ፦ #መዳራት፣ ከጋብቻ በፊትና ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ግንኙት፣ ግለ ወሲብ፣ የወሲብ ምስሎችን ሆን ብሎ ለወሲብ አላማ መመልከት፣ሴተኛ አዳሪነት፣ተመሳሳይ ፆታ ወሲብ እና የመሳሰሉትን የሚያካትት ነው።
3, #ክፋት(wickedness)፦ ክፉ ጠባይ፣ ከመጥፎው ጋር የመወዳጀት ዝንባሌ፣የክፋት ስራ።
ለምሳሌ፦አንድ ሰው ሆን ብሎ ሌላውን ሰው ለራሱ ጥቅም ሲል መጉዳት፣ ህፃናትን መጉዳት ማሰቃየት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
4, #ስግብግብነት፣መጎምጀት ፣የማይረካ፡በቃኝ የማይል ምኞትና አምሮት(Covetousness,greed,insatiable desire to have more) በቆላስይስ 3:5 ላይ ስግብግነት አምልኮተ ጣዖት ተብሎ ተጠቅሷል?? ምን ለማለት ፈልጎ ነው ለሚለው እናንተ የራሳችሁን ጥናት አድርጉ.....
ለምሳሌ፦ አንድ ነጋዴ የሚበቃው ነገር እያለው የበለጠ ትርፍ ለማግኘት ሲል ያለአግባብ ዋጋ ሲጨምር ወይም ሲያጭበረብር፣ሚዛን ሲሰርቅ፣ 😁የዘመኑ ሴቶችና አንዳንድ ወንዶች በተፈጥሮ ባላቸው ውበት ባለመርካት ያለማቋረጥ እራሳቸውን መልካቸውን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችም ብዙ አሉ።
እናንተ ከዚ ማብራሪያ አንፃር የተረዳችሁትን በcomment ማጋራት ትችላላችሁ።
5, #ምቀኝነት ፣ምግባረ ብልሹነት፣ ሆደመጋዝነት(Maliciousness,morally bad disposition)
ለምሳሌ ፦አጠገባችን ያሉ ሰዎች ሲጎዱ ውስጣችን ሲደሰት፣ የምንረዳ እያስመሰልን በጉዳታቸው ላይ ጉዳት ለመጨመር መፈለግ፣በንግግር መውጋት፣ ህመማቸውን የሚያባብስ ነገር ሆን ብሎ ማንሳት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
6, #ቅናት(Envy)፦ በሌሎች መልካም እድል መጠቀም ወይም ቅር መሰኘት ማዘን፣እንዳይሳካላቸው መመኘት ወይም መፈለግ፦
ለምሳሌ፦ ጓደኛችን ነፃ የትምህርት እድል ቢያገኝ ለሱ ደስ ሊለን ሲገባ እንዳይሳካለት እንዲወድቅ መመኘት ምክንያቱም የሱ ስኬት እኛን ዝቅ እንደሚያደርግን ስለምናስብ።
7, #ነፍሰ ገዳይነት(murder)፦
ለምሳሌ፦ ሆን ብሎ የሰውን ነፍስ ማጥፋት ይኸውም ለራስ ጥቅም ሲባል የሚደረግ ነው(ፅንስን ወዶና ፈቅዶ ማስወርድ እዚህ ስር ይካተታል።
8, #ክርክር፣ጥል(debate/strife,quarrelling, contention, rivalry)፦
ለምሳሌ፦ ሁለት ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ እውነትን ከመፈለግ ይልቅ እርስ በርሳቸው ለመሸናነፍና የሰውን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ሲከራከሩ ፣ ይሄ ብቻ አይደለም በሁሉም ግንኙነቶች መሃል ሰላምን የማያመጣ ችግርን የማይፈታ ወደ ስምምነት የማያደርስ በአልሸነፍ ባይነት መንፈስ #እውነትን ከመፈለግ ይልቅ የራስን ማንነት ላለማስነካት የሚደረግ ጥረት ሁሉ እዚህ ስር ይካተታል።
9, #ተንኮል፣ማታለል(Deceit):- ለራስ ጥቅም ሲባል ሌሎችን የሚጎዳ ዘዴ መጠቀም።
ለምሳሌ፦ ለድሆች ድጋፍ እናድርግ ወይም የቤተክርስቲያንን ስራ እንስራ በማለት ገንዘብ ሰብስቦ ለራስ መጠቀም፤ ገንዘብ አንድ ላይ እናስቀምጥ በማለት ወይም እኔ ጋር ይሁን በማለት ኋላ መካድ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
10,ክፉ ጠባይ(Malignity):-
ለምሳሌ፦የሌሎችን ደካማ ጎን መፈለግ፣ የሌሎችን ድርጊት በቀና መረዳት አለመቻል እና ስለሌሎች መጥፎውን ማሰብ የሚወድቁበትን መንገድ ማውጠንጠን በሌሎች መከራ መደሰት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
11, #ሐሜተኞች፣ የሚያንሾካሽኩ(Whisperer)፦ በቡድን ወይም ህብረት መካከል አፍራሽ መረጃን የሚያሰራጩ የህብረት ጠንቆች።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በህብረት መካከል ስለ አንድ ወንድም ወይም እህት ያልተረጋገጠ ክስን በድብቅ ማሰራጨትና ህበረቱ በዚያ ሰው ላይ እንዲነሳበት ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
12, #ስም
አጥፊዎች(backbiters) ፦ ሆን ብሎ የአንድን ሰው ስም ወይም ክብር ወይም ተቀባይነት ለማጉደፍ የሚደረግ ነው።
ለምሳሌ፦ ስለ አንድ ወንድም/አገልጋይ ታማኝ አለመሆን ሆን ብሎ ማውራት ይህም ሰውየው ታማኝ ስላልሆነ ሳይሆን ሰዎች እሱን እምነት እንዳይጥሉበት፤ በሌሎች ዘንድ ያለውን ምስል ማጥፋት እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
13, #አምላክን የሚጠሉ(haters of God)፦ የእግዚአብሔርን ፅድቅ ማንነት አምላክነት ከሐጢያቲዊ ድርጊታቸው ጋር ስለማይሄድ መጥላትን ያመለክታል።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው እግዚአብሔር ውሸት ሐጢያት ነው እንዳለ እያወቀ ነገር ግን ውሸት ጥቅምን ስለሚያስገኝለት ሲል የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ወደጎን ትቶ ወይም ችላ ብሎ ውሸትን መናገር እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
14, #ተሳዳቢዎች፣ የሚያንገላቱ(Despiteful)፦ሌሎችን በንቀትና በወረደ አመለካከት መመልከት፣ በንግግር መሃል ክብራቸውን ማዋረድ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ጓደኛውን ስለሌለው ነገር በማንሳት በሰዎች ፊት እንዲሸማቀቅ ማድረግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።

❤2
15, #ትዕቢተኞች(proud) የራስን ማንነት ራስን የራስን ነገር ከሌሎች እንደሚበልጥ እና የሌላው ሁሉ ከሱ በታች እንደሆነ የማሰብ ዝንባሌ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በትምህርት ብዙ ስለሄደ ብቻ በተሳሳተበት ጉዳይ ከሌሎች እርምትን መቀበል አለመፈለግ ምክንያቱም 'እኔ አልሳሳትም' ብሎ ስለሚያስብ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
16, #ትምክህተኞች(Boasters)፦ስላላቸው ነገር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማውራት ዝንባሌን ያሳያል። ስለራሳቸውም የተጋነነ እሳቤ መያዝ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ስላገኛቸው ድሎች መንፈሳዊ ስጦታዎች አጋኖ ተፅዕኖ እንዲፈጥር በመፈለግ ማውራት። (#ጉራ ማለት ነው) እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
17, #ክፋትን የሚሰሩበትን መንገድ ማውጠንጠን(Inventors of evil things) ይሄ በዚ ዘመን ፈጠራ ወይም አዲስ ነገር የመስራት ችሎታ እንደሚባል፤ ክፋትን ሌሎችን የመጉዳት አዲስ መንገድ መፈለግን ያሳያል። እንዴት ልጉዳው፣እንዴት ላጥፋው፣እንዴት ቤቱን ልበጥብጥ፣እንዴት ስሙን ላጥፋ፣እንዴት ልጣለው እያሉ ጊዜ ሰጥቶ ማሰብ፣ መንገድ መፈለግ ነው።
ለምሳሌ፦አንድ ሰው ሌሎችን ጎድቶ ወይም ሰሮቆ እንዴት ገንዘብ እንደሚያገኝ ማሰብ፤ በsocial media ሌሎችን ለማንቋሸሽ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ለማደረግ በአደባባይ እነሱን የሚያዋርዱበትን መንገድ መፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
18, #ለወላጅ የማይታዘዙ(Disobedient to family)፦ ልጆች ለወላጆቻቸው ሊታዘዙ እንደሚገባ ይህም በረከትን እንደሚያስገኝላቸው መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። ወላጆች የተማሩም ሆኑ ያልተማሩ ሃብታም ሆኑ ድሃ ልንታዘዛቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያለምንም ቅድመሁኔታ አዟል።ወላጆችህን የመረጠለህ እግዚአብሔር እንጂ አንተ ወይም ወላጆችህ አይደሉም ስለዚህ ያለምንም ጥያቄ ለወላጅ መታዘዝ ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ነው
ወላጅን አለመታዘዝ ደግሞ ለእግዚአብሔር ቃል አለመታዘዝን ያሳያል።
19, #የማያስተውሉ፣የማያመዛዝኑ፣የድርጊታቸውን መዘዝ ቆም ብለው የማያስተውሉ።(የማያስተውል ልቦናቸው ጨለመ የሚለው ትርጉም ከዚህ ጋር ይመሳሰላል።)፣መለየት የሌላቸው(Without Understanding)፦በደመ ነፍስ መመራትን ያሳያል ይህም ልናደረግ ስላለው ነገር መጥፎና መልካም ጎን አለማየትን ይገልፃል።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው የድርጊቱን መጥፎ መዘዝ እያወቀ ከማድረግ መመለስ አለመፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
20, #ውል የሚያፈርሱ(covenant breakers)፦ ታማኝነትን ማጉደል፣ ቃልን ማጠፍ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በሆነ ጉዳይ ቃል ገብቶ ወይም ውል አድርጎ ግን ውሉን ለማፍረስ አስቦ ኋላም ሲያፈርስ
እና የመሳሰሉትን ያካትታል። ከአንደበታችን ለሚወጣ ቃል መጠንቀቅ እና ከተናገርን ግን ቃላችንን ልንፈፅም ይገባናል።
21, #ርህራሄ_የሌላቸው(Without natural affection)፦ በተፈጥሮ ለሰዎች ወይም ለቅርብ ሰዎች፣ለቤተሰብ፣ለልጆች፣ለወላጅ፣ለትዳር አጋር ሊኖር የሚገባን ፍቅርና ርህራሄ ማጣት።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ለራሱ ለመጠቅም ሲል የገዛ ወንድሙን ሲገፋ፣ ሲጠላ፤እናት ባለውና በሌለው ልጆቿ መሃል አድሎ ስታደርግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
22, #እርቅን የማይወዱ(Implacable)፦ ሰላምን መፍጠር የማይወዱ ወይም የማይታረቁ ይቅርታ የማያደርጉ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ከተጋጨው ሰው ጋር ሰው ለማስታረቅ ሲሞክር ወይም የተጣለው ሰው ራሱ ሄዶ ይቅርታ ሲጠይቅ አለመቀበልና ሆን ብሎ በጥል መቆየት ቂመኛ መሆን እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
23, #ምህረት የሌላቸው፣ጨካኞች(Unmerciful)፦
ርህራሄ ማጣት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አለማድረግ።
ለምሳሌ፦ አንድ ሰው የተጎዳን ሰው መርዳት እየቻለ ከጭካኔ የተነሳ ለመርዳት አለመፈለግ እና የመሳሰሉትን ያካትታል።
NB እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ድርጊቶች እንደሁኔታው እግዚአብሔር በሚሰጠን ጥበብና ማስተዋል የምንይዛቸው እንጂ ወጥ የሆነ ተፈፃሚነት አላቸው ማለት አንችልም ለምሳሌ አንድ ሰው መንገድ ላይ ታሞ የወደቀ መስሎ ሊረዳው የሚመጣውን ሰው ለመዝረፍ የሚሰራ አለ ይህን ሰው ትቶ መሄድ ጭካኔ አይባልም። ነገር ግን በእውነት ሰውየው የተጎዳ ሆኖ፣ እኛ መርዳት እየቻልን፣መንፈስ ቅዱስ እያሳሰበን ችላ ብሎ መሄዱ ነው በደል!!
🙏ራሳችንን እንገምግም!!

❤4🙏2