Hope line _የተስፋ መንገድ
36 subscribers
22 photos
7 links
ይህ ቻናል ,የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ፁሁፎችን እንድሁም ታሪኮችን የምናገኝበት ነው;
ከመጥፎ ሰዎች ጋር ጣፋጭ ነገር ከምትበላ ከደጋግ ሰዎች ጋር ድንጋይ ብትሸከም ላንተ የተሻለ ነው ።
Download Telegram
😘ያበደው ፍቅሬ😘


ክፍል 1⃣

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም... ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።

ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ....

ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻልኩም በሀሳብ ወደ ተገናኘንበት ጊዜ ጋለብኩ....

ከምናምን አመት በፊት በክህደት የተሰበረ ልቤ ላይ ትኩስ ሀዘን ተደምሮበት ግራ ቀኜን ሳላይ እግሬ ወደመራኝ ስጓዝ ሲጥጥ ብሎ እግሬ ስር የቆመ መኪና ከሀሳቤ አነቃኝ... አልደነገጥኩም እንደውም ተናደድኩ ለምን ፍሬኑን ያዘው? ለምን አልገጨኝም? ብሽቅ... የማይገኝ እድል አስመለጠኝ.... ይህን ሁሉ የማስበው ከመኪናው ወርዶ በአካባቢው ከነበሩ ሰዎች ጋር የስድብ ናዳ ሲያወርድብኝ ነው። "ያምሻል.... እያዬሽ አትሄጂም..... መሀል አስፓልት ላይ ምን ትሰሪያለሽ...... እብድ ነሽ..... ጦስ ውስጥ ከታው ነበር........." አይገርምም አንድ እንኳን ችግሬን ለማወቅ የፈለገ ምን ሆና መሀል አስፓልት ላይ ተገኘች ያለ ሰው የለም.... አስመሳይ ብቻ።

እጄን ይዘው ወደዳር ወስደውኝ የጀመሩትን ስድብ ያዘንቡብኝ ጀመር... ለትንሽ ሰከንድ አየሁዋቸው... ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ 'ዞር በሉልኝ አስመሳዮች' ያልኳቸው አላስደነገጠኝም ምክንያቱም ይሉኝታም ሆነ ሀፍረት ከኔ በእጥፍ እርቀዋል... ይሉኝታ የተሰጠው ለሰው ነው እኔ ደግሞ ከሰውነት ደረጃ በትንሹ ወርጃለው..... ምናልባትም እንደማስበው አልወረድኩ ይሆናል ግን በቃ ለኔ የሚሰማኝ ያ ነው......
በበረሀ ላይ ያለ እህል ውሀ የተጣልኩ..... ሙቀት ሀሩሩ ያነደደኝ..... ከአካላቴ አብዛኛውን በከሀዲዎች የተነጠኩ.... ለመኖር ተስፋ ለመሞት አቅምና ወኔ የሌላት ፍጡር እንደሆንኩ ይሰማኛል። አዎ ለመሞትም እኮ አቅም እና ወኔ ያስፈልጋል.... ወኔ ቢኖረኝማ ይህን ጊዜ ሙት አመቴ አልፎ ነበር።
ስልችት፣ ድክም፣ ልፍስፍስ እላለሁ...
ማሰብ ያደክመኛል...
መብላት መጠጣት ይሰለቸኛል...
ስሜን ጠርተውኝ እንኳን 'አቤት' ማለት ትልቅ ተራራን የመግፋት ያክል ይሆንብኛል።

የልብ ስብራት ብቻ ሳይሆን ከአካል ክፍሎቼ እያንዳንዳቸው ስብርብር እንክትክት እንዳሉ ይሰማኛል። በቃ ዝምምምም ብሎ መኖር ከነኝህ ጊዜያቶች በአንዱ ነው እንግዲህ ከዚህ ሰው ጋር የተገናኘሁት....


በቆሙበት ትቻቸው እየሄድኩ ነው ከኋላዬ የራቀ ድምፃቸው ይሰማኛል..." ያማታል መ ሰ ለ ኝ..." እኔ ግን እየሄድኩ ነው... ከቤት ስወጣ ማንም ያየኝ የለም ለነገሩ ማን ሊያየኝ ይችላል... እንደሚሰበር እንቁላል የሚንከባከቡኝን ሁሉ አጥቻለው..... እየሄድኩ ነው....መነሻዬን አስታውሳለሁ መድረሻዬን ግን እንጃ.....

✎ክፍል 2⃣ ከ 50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲ🀄️ጥል Vote♥️ እና Share አድርጉ።

ይቀጥላል....

ሀሳባችሁን ኮሜንት አድርጉ
👇 👇 👇 👇
የቴሰስ መርከብ ተቃርኖ

ቴሰስ (አቴንስን የመሰረተ ንጉስ ነው) ለኀሠሣ ይሁን ለሌላ ነገር አይታወቅም ብቻ አዲስ ያሳነፃትን መርከብ ሸራዋን ወጥሮ፣ መልህቋን አንስቶ ከባህር ላይ ጉዞ ጀመረ። ከረጅም ቆይታ በኋላ ሲመለስ በጉዞ ላይ ያረጀውና የበሰበሰው የመርከቧ ጣውላዎች አልቀው በአዲስ ስለተተኩ ልክ ስትሄድ እንደነበረችው ጥሬ (አዲስ) ትመስል ነበር። ምክንያቱም ቀዘፋው ረጅም ነበርና የመርከቧ አካሎች በየጊዜው ይበላሹ፣ ይበሰብሱ ስለነበር ቴሰስ የመርከቧን አካሎች በአዲስ ለመቀየር ተገዷል።

ይሄ ታሪክ ወሳኝ ጥያቄን አነሳ፤ ቴሰስ የሄደባት እና የተመለሰባት መርከብ ተመሳሳይ ናት? የሚል። በፍፁም አይደለችም ይሆናል መልሱ። ምክንያቱም በጉዞ ላይ የበሰበሱት እና የተበላሹት አካላቶቿ በአዲስ ስለተቀየሩላት ልክ ስትሄድ የነበረችው መርከብ ከተመለስችው ጋር ፍፁም ተመሳሳይ አይደለችም። እሺ ፍፁም ተመሳሳይ ካልሆነች ፍፁም ተቀይራለች ማለት ይቻላል? ተብሎ ቢጠየቅስ። አሁንም ምላሹ ማለት አይቻልም ይሆናል። ምክንያቱም ስትሄድ የነበረው የተወሰነ ክፍሏ ከቦታው ሳይቀየር ስትመለስም ነበረ። እና ካዲያ አንድ ነገር ፍፁም (ሙሉ በሙሉ፣ perfect) ተቀየር ሊባል የሚችለው ምን ያህል ፐርሰንቱ ሲለወጥ ነው? መቶ% ሲቀየረ ነው ከተባለ ደግሞ ይሄ ቅይርታ ሳይሆን በአዲስ (በፊት ያልነበረ) ተፈጠረ ወይም ታነፀ ነው የሚሆነው። እናም ጭብጡን ይበልጥ ለማሰላሰል (contemplate) እና ለመረዳት ወደ ቃላቶቹ ፍቺ ወርዶ መጠየቅ ይሻላል መሰለኝ? ቅይርታ (change) ምን ማለት ነው? እንዴትስ ይገለፃል? ተመሳሳይነትስ?

በ17ኛው ክ/ዘመን የኖረው ፈላስፋ ቶማስ ሆብስ ደግሞ እዚህ ተቃርኖ (paradox) ላይ ሌላ እንቆቅልሽ ጨምሮበት ነገሩን ይበልጥ አወሳሰበው። ቴሰስ በጉዞ ላይ ሳለ አርጅተው እና በስብሰው የጣላቸውን የመርከቧን ስብርባሪ ጎበዝ አናፂ አግኝቷቸው የራሱን መርከብ ሰራበት። ከዚያም ሁለቱም መርከቦች በእኩል ሰዓት ወደብ ቢደርሱ ቀዳሚዋ የቴሰስ መርከብ የትኛዋ ናት? ቴሰስ ጠጋግኖ እንደ አዲስ የሰራት ወይስ አናፂው ከቴሰስ የመርከብ ልቅምቃሚ ያነፃት? ቴሰስ ባዲስ መልክ የሰራት መርከብ የቀድሞዋ ልትሆን አትችልም ምክንያቱም ብዙ የበሰበሱ እና ያረጁ ክፍሎቿ ተቀይረውላት የቀደመ ማንነቷ ተቀይጧል። በሌላ በኩል ደግሞ በስብሰው እና አርጅተው ከወዳደቁት ጣውላዎቿ የተገነባችው የአናፂው መርከብ ደግሞ ቁርጥ የቀድሞዋን አይደለችም፤ ምክንያቱም ቴሰስ የበሰበሱትን እንጂ ጠንካራ ክፍሎቿን አልቀየራቸውም። ስለዚህ አናፂው ባገኛቸው የተወሰኑት ጣውላዎቿ ስላነፃት ቴሰስ ያልቀየራቸው ጣውላዎች ይቀራሉ። እናም አንድን መርከብ፣ መርከብ የሚያሰኘው ምኑ ነው? የታነፀበት የአካል ክፍል ወይስ ውቅር (structure) ወይስ መጠን ወይስ የመርከቡ የኋላ ታሪክ (History)? ምን ይመስላችኋል…?

ከላይ ባለው ተቃርኖ ተመስርተን ወደ ዋናው ማጠንጠኛችን እንምጣ። የሰው ልጅ የጊዜ እስረኛ ነው። ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ያረጃል፣ ይሞታል። ካልሞትን በስተቀር ጊዜ በነጎደ ቁጥር እያደግን፣ የሰውነታችን ክፍሎች በብዙ እየተቀየሩ ይሄዳሉ። በውስጥም፣ በውጪም (በአካል፣ በአዕምሮ፣ በመንፈስ) የፈለገ ቅይርታ ብናሳይም ራሳችንን ያው የድሮው እኛነታችን እንደሆነ አድርገን እያሰብን እንቀጥላለን። እንዲህ እንድናስብ ወይም እንዲሰማን የሚያደርገን ግን ምንድነው? ምናልባት ከዛሬ 15 ዓመት በፊት አካላቹ ውስጥ ከነበሩና እናንተን ከገነቡ ሕዋሳት መኻል አሁን ላይ ከናንተ ጋር ያለ አንድም የለም። ከ15 ዓመት በፊት እንደ ነበረው አሁን ላይ ተመሳሳይ እሳቤ (አዕምሮ) አይኖራችሁም። ስለዚህ ማንነታችሁ የትኛው ነው? ያለፈው እኛነት (ልጅነት) ወይስ የአሁን እኛነት (ወጣትነት፣ ጎልማሳነት) ወይስ የወደፊት እኛነት (ሽምግልና)? በአጠቃላይ የሰውን ልጅ ሰው የሚያስብለው፣ የሚያሰኘው ምኑ ነው? …እስቲ እየተወያየን፣ ሐሳብ እየሰጠን!



"የፍልስፍና ሀሁ" ከፖል ክሌንማን ትርጉም ራሴላስ ጋሻነ
Forwarded from ቀልድ ብቻ (༼᳠ᎠᎡᎬᎪᎷᣵ༽᳠ᏞϴᏙᎬ߷😗😙)

የዩንቨርስቲ ላይብረሪ
ውስጥ፣ልጁ ወደ ልጅቷ ጠጋ
ይልና
"እሙ እዚህ ጋር ብቀመጥ ቅር
ይልሻል?" ይላታል፣
ልጅቷም ከመቀመጫዋ ብድግ
በማለት ድምጿን
ከፍ አድርጋ:
"እኔ እንደ ማንም ተራ ሴት
መሰልኩህ አብረሺኝ እደሪ
የምትለኝ?!"
ትልና እሪ ትላለች፣ይሄኔ
ላይብረሪ ውስጥ የነበሩት
ተማሪዋች
በግርምት ልጁ ላይ
ያፈጡበታል! ልጁም በሀፍረት
እና በመሸማቀቅ ቀስ ብሎ
ይቀመጣል፣
ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ልጅቷ ወደ
ልጁ ጆሮ ጠጋ ብላ "አየህ የስነ-
ልቦና
ተማሪ ስለሆንኩኝ ወንድ ልጅን
ማሸማቀቅ
አውቅበታለሁ!"ትለዋለች
ልጁም ወዲያው
ከመቀመጫው ጮክ ብሎ "ለብላ
አንድ
አዳር አምስት ሺ ብር!?
አልበዛም!? ፌር አይደለም
!ይልና ቁጭ ይላል፣በዚህ ጊዜ
ላይብረሪ ውስጥ የነበረው
ተማሪ
እሷ ላይ ያፈጣል ልጅቷም
በሀፍረት ኩም
አንገቷን ታቀረቅራለች ይሄኔ
ልጁ ወደ ጆሮዋ ጠጋ
ይልና
"አየሽ....የህግ ተማሪ ስለሆንኩኝ
ሴትን ልጅ
ወንጀለኛ ማድረግ አውቅበታለሁ
ብሏት ጥሏት ውልቅ!😜😜😜
አሳዛኝ ታሪክ 
ነገሩ እንዲህ ነው

የሆነ ልጅ ነበር አንድ ቀን አባቱ ጠራውና ወረቀት ፅፎ ሰጠው ልጄ ሆይ ይህን ወረቀት በፍፁም አንተ እንዳታነበው ስታገባ በስርግህ ቀን ለሚስትህ ሰጣት ይሄ የኔ የኑዛዜ ቃል ነው ይለዋል ይሄንን ባለው ከቀናት በሆላ ይሞታሉ ። ልጅም  የአባቱን የሙት ሃዘን ከጨረሰ በኋላ  ለማግባት ይወስንና ለፍቅረኛው ይነግራታል እሷም በሀሳቡ ተስማምታ ሰርግ ተደርጎ ተጋቡ ።

ማታ እሷ ጋር ከመግባቱ በፊት አባቱ የስጠውን የኑዛዜ ወረቀት ለሚስቱ ሰጣት ምንድነው ስትለው አንብቢው አላት አንብባ ከጨረስች በኃላ እያለቀስች በጥፊ መታቸውና ፍታኝ ብላው ተፍቱ ልጁ ግራ ገባው ምን እንደሚል ለማወቅ ሊያነበው ፈለገና አባቱ እንዳያነበው አደራ ስላሉት መልሶ ተወው አሁንም ከአመት በኃላ ሌላ ሴት አገባና በስርጕ ምሽት ወረቀቱን ሰጣት እሷም በጣም ተናዳ በጥፊ መታችውና ፍታኝ ብላው ተፍቱ ።

ልጅም ተስፋ ቆርጦ ሀገሩን ለቆ ለመሄድ ያስባል አይሮፕላን ውስጥ እንደገባ አጠገቡ ለተቀመጠችው ወጣት ወረቀቱን ይስጣትና አንብቢልኝ ይላታል እሷም ለብቻዋ ዝም ብላ ካነበበችው በኃላ በጥፊ መታችውና ይሄንን ከማነብልህ ሳትስማው እራስህን ከአይሮፕላኑ ላይ ጥለህ ብትሞት ይሻልሀል ስትለው ደብዳቤውን ወሰደባትና አጣጥፎ ይዞት እራሱን ከፕሌኑ ላይ ወረወረ ልጁ በአየር ላይ እየተንሳፈፈ አንድ ነገር አሰበ ።

አሁን ልሞት ነው ከመሞቴ በፊት ግን አባቴ የስጠኝ ደብዳቤ ምን እንደሚል ማወቅ አለብኝ አለና ከኪሱ አውጥቶ ሊያነበው ሲከፍተው ሀይለኛ ንፋስ መጣና ወረቀቱን ይዞበት ሄደ ልጁ ያባቱን አደራ ባለመጠበቁና ምን እንደተጻፈ ባለማወቁ እየተፅፅተ ሞተ እኔ ግን ከእርሱ በላይ እንዴት እንደ ጓጓሁ አጠይቁኝ ሆዴን አስጩሆት ቀረ ለማንኛውም ደብዳቤውን ንፋስ የት ወስዶ እንደ ሚጥለው ስለማይታወቅ ያግኛቹ ጓደኞች አደራችሁ አባትየው ምን ብለው ፅፈው እንደነበር መጨረሻውን አሳውቁኝ😂😂
Forwarded from  የፍቅር ግጥም🌹 (Addisu)
የታጨደው ስንዴ !

ለመሪዎች ወንበር የታጨደው ስንዴ፣
እኩል ነው መርምሩት ከሞተው ዘመዴ።
ቶሎ እንደታጨደው እንደስንዴው ሁሉ፣
ለመሪዎች ወንበር አልቋል ሰው በሙሉ።
በዚህች በኔ ዘመን በዚች በኔ ዓለም፣
ለመሪዎች ወንበር ያልታጨደ የለም፡፡


@Addisu32
@selafeker
አፄ ምኒልክ ለብዙ ጊዜ ሲብሰለሰሉበትና ሲጨነቁበት የነበረ አንድ ጉዳይ ነበር። ዙፋን ፣ አልጋ፣ ቀጣዩ ንጉሥ አልያም ቀጣዩ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ልንለው እንችላለን። ንጉሱ ታመው በአልጋ ላይ ከዋሉ በኃላ ብዙ ጊዜ ይጨነቁ እንደነበርና በልጅ እያሱ ላይ የሹመት[የንግስና ] ሥርአተ መንግስቱን አሳልፎ ለመስጠት ልጅ እያሱም ገና ልጅ መሆናቸውና የቤተመንግስት ጠባይና ሥርዓትን በደንብ ያልተረዱ መሆኑ ብዙ እምነት ለመጣል ተቸግረው ይብሰለሰሉ ነበር። የሆነው ሆኖ ምርጫ ያጡት ንጉሱ ይሁንታቸውን በኑዛዜ አስተላለፉ። ፀሀፉ ትዕዛዝ ገበረ ሥላሴም በታሪክ ነገስት ዘዳግማዊ መጽሐፍ ውስጥ እንደሚከተለው አስፍረውታል። ~አዲስ አበባ ጃን ሜዳ ጉባኤ ተደርጎ ስለ ልጃቸው ኢያሱ አልጋ ወራሽነትና አገዛዝ ያዘዙት ቃል ተነበበ። ቃሉም ይህ ነው። "ያገሬ የኢትዮጵያ ሰዎች ልጆቼ ወዳጆቼ እግዚአብሔር የገለጠልኝን ምክር ልምከራቹ ምክሬም በልባቹ እንደሚፀና ተስፋ አደርጋለሁ። ዓፄ ቴዎድሮስ በሞቱ ጊዜ ከርሳቸው ጋር የነበረውን ሰው ሁሉ ያንዱን አገር አንዱ እደርባለሁ አንዱን ገድዬ እኔ ጌታ እሆናለሁ እያለ ሁሉም ሳይረባ ተላልቆ ቀረ። ከዚያም በኋላ የዓፄ ዮሐንስም ሰው የሆነውን የምታውቁት ነው።ባገር በሽታ ሳይገባበት ሌላ ጦርነት ሳያነሳበት በምቀኝነት እርስ በርሱ እንደተላለቀ አይታችሁበታል። አሁንም ልጆቼ ወዳጆቼ አንዱ ባንዱ ምቀኝነት ይቅር ።ያአንዱን አገር አንዱ እደርባለሁ እንዳትባባሉ ።እኔ እስካሁን በፍቅር እንዳኖርኋችሁ እናንተም በፍቅር ተስማምታቹ በፍቅር እንድትኖሩ እለምናችኋለሁ።እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርስ ተዋግታቹ ካላለቃችሁ በቀር አገራችንን ለሌላ ለባዕዳን አሳልፋቹ አትሰጡም።ክፉ ነገርም አገራችንን አያገኛትም ።ንፋስ አይግባባችሁ አገራችንን በያላችሁበት በርትታችሁ ጠብቁ።ወንድሜ ወንድሜ ተባባሉ። ይህን ምክር መፃፌ እኔማ በእግዚአብሔር ፈቃድ ይህንን ያህል ዘመን ገዛሁ።ነገር ግን ሰው ነኝና ለዘላለም አልኖርም።እኔም እንደምመኘው ልጄን ኢያሱን እግዚአብሔር ካቆየላቹ አብራችሁ አገራችንን ጠብቋት።ከዚህ ከፃፍኩት እኔም ሳለሁ ሆነ ካለፍሁ በኋላ ከፈቃዴ የወጣ ሰው ረግሜአለሁ። በሰማይም በምድርም የተረገመ ይሁን" የሚል ነበር፡፡

ሹማምንቱና መሳፍንቱ የንጉሱን ቃል ለመተግበር ቢሞክሩም በልጅ እያሱ በኩል የነበረው የበሳል ዓስተዳደር ችግር ሀገሪቷን ወደ ሌላ ምዕራፍ አሸጋገራት አልያም የአርባ ዓመታትን ሌላ ቅርጽ ሰጥቶ አስጓዛት።

መልካም ንባብ

የቻናላችን ተከታይ ስለሆኑ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ለንባብ መጎልመስ ሁሌም እንተጋለን።
📚📚📚📚📖📖
የንጉስ ልጂ ፍቅር

አንድ የኔ ቢጤ ጫማ ጠራጊ ነበር አንድት የንጉሥ ልጂ በፍቅር ንውዝ አድረጋ ይሳካ የማይመስል የድሀና የሀብታም ፈቅረ ይጀምራሉ ልጂቱ የንጉስ ልጂ ስለሆነች የምትኖርው ቤተ-መንግሥት ነው ልጁ ደግሞ በላስቲክ በተወጠረች የጎዳና ቤት ፡ልጁ ምንም እንኳን ድሀ ቢሆንም የሚወዳትን ልጁ አግኝቶ ሻይ ቡና ማለት ፈለገ ነገረ ግን ልጂቱ ከቤተ-መንግሰት መውጣት አይፈቀድላቸውም ነበረ ስለሆነም ልጁ ቤተ-መንግሥት የሚገባበትን መንገድ ማፈላለግ ጀመረች ከቤተ -መንግሥት ጥበቃ ከሆኑት መካከል አንዱ ልጁን ቤተ-መንግስት እንድያስገባው ተስማሙ ለዘህም ብዙ ገንዘብ ልትከፈለው ይስማማሉ በስምምነታቸው መሰረት ልጁ ቤተ-መነግስት የገባና ፍቅር መስራት ይጀመራል ልጁ ድሀ ከመሆኑም የተነሳ ለፍቅረኛው ስጦታ ብሎ የወሰደው የባቄላ ቆሎ ነበር ልጂቱም በደስታ ተቀብላ ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ ሳለ የባቄላው ቆሎ ጉሮሮው ውስጥ ይገባና የልጁ ሕይወት ያልፍል በድብቅ የገባ ልጂ እንደት አስከሬን ሁኖ ይውጣ እንደተለመደው የጥበቃ ሰራተኛ እጥፍ ገንዘብ ተከፍሎት አወጣው በሀዘን ውስጥ የምትገኘው ልጂ ያልጠበችው ነገረ ተፈጠረ የነጉስ ልጂ ለባለፀጋ ወይም ለንጉሥ ልጂ ነው የሚያገባው እና ለ ሌላ የንጉስ ልጁ ሊያጋቧት እንደሆነ ተነገራት ይሁን እንጂ የንጉሥ ልጂ ሚስት ለመሆን ክብር ንፅህና ወይም ድንግል መሆን የግድ ነው እሱም የለም ምን ይደረግ ይህ የቤተሰብ ክብር ነው ሁሉም ነገረ አልቆ ሰረጉ ደረሰ መፍትሔ ፈለጋ ላይ ነች አሁንም ብዙ ብር ተከፍሎት የጥበቃ ሰራተኛው ድንግል የሆነች ልጂ ተፈልጋ የሰረጉ ቀን ሙሽራ ሁና እንድታሳልፍና ብዙ ብረ እንድከፈላት አድረግ ተባለ ሁሉም ነገረ በታቀደው እየሄደ ነው ሰረጉ ደረስ ልጅቱ ሁሉንም ነገረ ተወጣችው እንኳንስ ገንዘብ ተከፍሎኝ እንድሁም አለሜን አየሁት አለች በስምምነቱ መሰረት በሰረጉ ማግስት ውላቸው ያልቃል እና የንጉስ ልጂ ወደ ትዳረ የድሀዋ ልጂ ቢሯን ይዛ ወደ አስቀያሚው ሕይወት መመለስ ነበር ግን እንደት ቤተ -መንግስት የመግባት እድል ተገኝቶ ይወጣል አይ እኔ ባጋጣሚ የገኘሁት ሕይወት ነው የናንተ ብር ይቅረብኝ እኔ ሕይወቴን በብር አልሸጥም በማለት ትዳሩን አፀናችው ይሕንን የሰማችው የንጉስ ልጂ እራሷን አጠፋች፡፡ ለፍቅርም ይሁን ለችግሮቻችን ገንዘብ ፍትሄ ሊሆን አይችልም ፡፡
በሀራ በኩል ወርቄ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ ሲሆን በቃሉ እና ወረባቦ ድንበር አቅራቢ(ጄባ) የሚገኙ ነዋሪዎችም የከባድ መሳሪያ ድምፅ በቅርበት እየተሰማን ነው ብለውኛል።
©አዩ ዘሀበሻ
==============
ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ፣ የቻናሌ ቤተሰብ በመሆን ተከታተሉ❗️👇👇
http://t.me/ayuzehabesha http://t.me/ayuzehabesha
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በድጋሚ ከቤቱ የፌደራል ፖሊስ መለዮ በለበሱ ፖሊሶች መወሰዱን ወንድሙ ተናገረ!

© ሮሃ ሚዲያ

የዩቲዩብ ቻናላችንን ጎብኙልን ሰብስክራይብ አድርጉን 👇👇

https://youtube.com/channel/UCxxg53ZZwSbKMzeqTvj__Vg

@Addis_News
@Addis_News
በክልሉ የማህረሰብ አቀፍ የበሽታዎች ቅኝትና አሰሳ ስራዎችን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ተገለጸ።

በማህበረሰብ ደረጃ የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝት እና አሰሳ ስራዎችን ለማጠናከር ያለመ ውይይት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ ስራ አመራር ተቋም ተካሂደዋል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአገራችንም ሆነ በክልላችን በበሽታዎች አሰሳና ቅኝት ስርዓት (surveillance system) ሪፖርት የሚደረጉ የተለዩ 22 በሽታዎችና የማህበረሰብ ጤና ኩነቶች አሉ።ከነዚህም ውስጥ 12ቱ ወዲያውኑ እንደተለዩ ሪፖርት የሚደረጉ ሲሆን 10 ደግሞ በሳምንታዊ ሪፖርት የሚደረጉ ናቸው።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር እንዳሉት ውይይቱ በተለይ በጤና ተቋማት ደረጃ ሊለዩ የማይችሉ በማህበረሰብ ውስጥ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ቶሎ በመለየት ለጤና መዋቅር በጊዜ ሪፖርት ለማድረግ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል።

ማህበረሰቡን በማሳተፍ የበሽታዎች ቅኝትና አሰሳ ስራዓቱን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት አቶ አብዱልሙኒየም ለተፈጻሚነቱም የብዝሀ ሴክተር ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት።በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችም ግንዛቤ የመፍጠር ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሀላፊው ጠቁመዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ በቀለ አንበሳ በበኩላቸው በዘርፉ የሚጠበቀው ውጤት ለማምጣት ተቀናጅተው መስራት እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

በውይይቱ ላይ ከዞንና ከወረዳ የመጡ የጤና፣የግብርናና የስራ ሀላፊዎችና ለሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይ በማህበረሰብ ደረጃ የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና አሰሳ ስራውን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንድደሚወጡም በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
👉በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ወታደራዊ ምልመላ ይደረግ ነበረ ሲል ተመድ ገለጸ
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃው ነበረኝ አለ።የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም እንዳለው ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ “ተአማኒ ሪፖርቶች” ደርሶት እንደነበር ገልጿል።

በጥቅምት ወር ማብቂያ 2013 ዓ.ም. ላይ ትግራይ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ድንበር ተሻግረው ወደ ምሥራቅ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል። እነዚህን የትግራይ ተወላጆች ማን እንደሚመለምላቸው እየታወቀ ተመድ ኝ መልማዮቹን ለመደበት በመግለጫ ሲንደፋደፍ ታይቷል።

የስደተኞቹ ከፍተኛ ኮሚሽን ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘበ ጉዳዩን በተመለከተ ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት እና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቱን መግለጹን አመልክቷል።ይህንንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ እንደነበር የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ተቋም በሰጠው ምላሽ ገልጿል።ደርጅቱ “ወታደራዊ ምልመላውን ለማካሄድ ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች እንደነበሩ” ከስደተኞች መረዳቱን ገልጿል።

ድርጅቱ ይህን ይበል እንጂ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በተደጋጋሚ በሱዳን በስደተኝነት የተመዘገቡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ከትግራይ ኃይሎች ጋር በመወገን ሲዋጉ ነበር በማለት ሲከስ ቆይቷል።ሁለት ዓመት ሊደፍን የተቃረበውን የሰሜን ኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነት መቀስቀስን ትከተሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በአብዛኛው ከምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ወደ ሱዳን መሸሻቸው ይታወሳል።
BBC
#ትምራን

ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ነገ ሀሙስ " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ይካሂዳሉ።

በዚህም ወቅት ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞቶ የሚተላለፍበት እንዲሁም ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ የሚጠየቅበት መርሀግብር ይኖረናል ተብሏል።

የእግር ጉዞው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ በካዛንቺ ሴቶች አደባባይ ጀምሮ መስቀል አደባባይ ላይ እንደሚያበቃ ተገልጿል።

አዘጋጆቹ በዚህ የእግር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ መሳተፍ እንደሚችሉ ገልፀው ግብዣ አድርገዋል።

@tikvahethiopia
የእርዳታ ምግቦች ጉዳይ ?

" ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቀረበውን እርዳታ ለጦርነት እያዋለው ነው " - ኢትዮጵያ

" ከሰብዓዊ እርዳታ ስርቆት ጋር በተያያዘ ማንኛውም ክሶች እመረምራለሁ " - USAID

ዳግም ያገረሸው የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በቀጠለበት በአሁን ወቅት በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት " ህወሓት " ለትግራይ ህዝብ የገባውን ሰብዓዊ እርዳታ ለጦርነት እያዋለው መሆኑን በተደጋጋሚ አንፅንኦት ሰጥቶ እየገለፀ ነው።

ግጭቱ የተጀመረ ሰሞን ምንም እንኳን ህወሓት ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስጃለሁ የሚል ማስተባበያ ቢሰጥም 500 ሺህ ሊተር ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዘረፉን የዓለም አቀፍ ተቋማት መግለፃቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መሰል ድርጊት እንደሚያወግዝና ነዳጁ እንዲመለስ ጠይቆ ነበር።

በአሁን ወቅት ደግሞ ውጊያ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ህወሓት ለህዝብ የቀረቡ ምግቦችን ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ይገልፃል። ለአብነት ኮርን ሶያ ብሌንድ (USAID ምልክት ያለበት) የተሰኘውን አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል አልሚ ምግብ በውጊያ ስፍራ መገኘቱን አሳውቋል።

በተጨማሪ መከላከያው በሚሰብራቸው ምሽጎችን ለእርዳታ የተላኩ የስንዴ ክምችቶች (USAID - የአሜሪካ ምልክት ያለባቸው) መገኘታቸውን ተገልጿል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን #በቀጥታ ምላሽ የሰጠ ዓለም አቀፍ ተቋም ባይኖርም ትላንት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከእርዳታ ምግብ ጋር በተያያዘ በትዊተር ገፁ አንድ ፅሁፍ አውጥቷል።

በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲቪሎች ህይወታቸው ጥገኛ የሆነበትን ምግብ ከአፋቸው ተነጥቆ በታጠቁ አካላት ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም በታጠቁ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ መውሰድና ጥቅም ላይ የማዋል ድርጊትን አወግዛለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
🌼🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻መልካም አድስ ዓመት 2015 ዓ.ም በዓሉ የሰላም የጤና ና የብልፅግና በዓል ይሁንልን፡
Forwarded from እንማር (Kiya1988)
#1 ኢጎ ነው ጠላቴ።

በአንድ ወቅት በሥዕል ችሎታው ወደር የሌለው የፈጠራ ሰው ይኖር ነበር።ከሥራው ፍፁማዊነት የተነሣ ከድንጋይ የአንድ ሰው ምስል ከቀረፀ፣ ሰው ይሁን ድንጋይ መለየት በጣም ያስቸግራል። ሥራዎቹ ሕይወትን የተሞሉ ሕያውነትን የተላበሱ ስለነበሩ እውነት መስለው ይታያሉ።
ታዲያ አንድ መሰግል(ጠንቋይ) ጊዜ ሞቱ የቀረበ መሆኑን ይነግረዋል እንደ ማንኛውም ሰው ይህ የፈጠራ ሰውም ሞቱን ይፈራ ስለነበረ ከመጣበት ሞት ማምለጥ ፈለገ። አስቦበትና አብሰልስሎበት ሲያበቃ አንድ መፍትሄ አገኘ። የራሱን ምስል ከድንጋይ እየቀረፀ አስራ አንዱን ካዘጋጀ በኋላ የተቆረጠለት ዕለት መልዓከ ሞት በሩን አንኳክቶ ሲገባ፣ ትንፋሹን ውጦ ከድንጋይ አምሳያዎቹ መሃል ገብቶ ተመሳስሎ ቆመ። መልአከ ሞቱ ግራ ገባው፣ ዐይኑን ማመን ተሣነው። እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም! ፈጣሪ ሁለት ፍፁም ተመሳሳይ ሰዎችን ፈጥሮ አያውቅም። የሚፈጥረው እየለያየ ነው። ፈጣሪ እንደ ጠርሙስ መፈብረኪያ ማሽን አይደለም። የአንድን ፍጡር አምሳያ ደግሞ አይፈጥርም። ታዲያ ምን አዲስ ነገር መጣ? አስራ ሁለት ተመሳሳይ ሰዎች? እሺ ማንን ይውሰድ? ከአንድ በላይ ይዞ መሄድ አይችልም... መልአከ ሞት መውሰድ አቃተው። ግራ ተጋብቶ፣ተጨንቆ በስጋት ተውጦ ተመልሶ ሄደ። ፈጣሪ አምላክ ዘንድ ሲደርስም " ምንድነው ያደረግኸው? እኔ ማምጣት የምችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፣ ሄጄ ያገኘሁት ግን አስራ ሁለት አንድ አይነት ነው። እንዴት ነው መምረጥ ያለብኝ? ሲል ይጠይቃል። ፈጣሪ አምላክም ሳቀና መልአከ ሞትን ከጠራው በኋላ፣ ከሃሳውያን መካከል እውነተኛውን የማግኛውን ቁልፍ ቀመር በጆሮ ሹክ አለው። ይህን የሚስጢር ቃል ከሰጠው በኋላም፣ "አሁን ብቻ ያ የፈጠራ ሰው ራሱን በመሠሎቹ ድንጋዮች መሀል በደበቀበት ቤት ውስጥ ትገባና ይህንን የነገርኩህን የሚስጢር ቃል መናገር ብቻ ነው።" ይለዋል።
መልአከ-ሞትም "እንዴት ነው የሚሰራው? " ሲል ይጠይቀዋል። ፈጣሪም፣ " ስለ እርሱ አትጨነቅ አንተ ብቻ ሂድና የነገርኩህን አድርግ።" ብሎ ያሰናብተዋል።
መልአከ-ሞትም የተነገረው ውጤት ይኖረዋል ብሎ ባያምንም የፈጣሪን ቃል አክብሮ ይሄዳል። የፈጠራ ሰውዬው መኖሪያ ቤት ከገባ በኋላ ዙሪያውን ተመልክቶ ሲያበቃ እንዲህ አለ፣" ጌታዬ ሁሉ ነገር እንከን የለሽ ነው ። ግን አንድ ቅር የሚያሰኝ ነገር አለ። ጥሩ ሰርተሃል ግን አንድ ስህተት አለው።" ይላል፣ በደፈናው ለአስራ ሁለቱም እየተናገረ።
ይህን ጊዜ አርቲስቱ መደበቁን ከነአካቴው ዘንግቶት።
" ስህተት፣ የታለ ስህተት፣ የቱ ጋ?" እያለ ዘሎ ወጣ።
መልአከ-ሞት ከት ብሎ ሳቀ! "ተይዘሃል ብቸኛው ስህተትህ ይሄው ነው። ራስህን መርሳት አትችልም። በል ና ተከተለኝ።" አለው እላችኋለሁ።
... እውነተኛ የሕይወት አርቲስት ፍፁም የተሰወረ እና ከእኔነት የወጣ ነው።
ኢጎ ካልተወገደ በቀር 'ከእኔ-በቀራችን' ማን ሊያድነን ይችላል???
Forwarded from zewed media
1 ሩሐማ፦ምሕረት ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ፦ማስረሻ ማለት ነው።
72 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው።
73 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
74 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው።
75 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
76 ጽዮን፦አምባ ማለት ነው።
77 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
78 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
79 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
80 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።
81 ኄራኒ፦ሰላም እና ፍቅር ማለት ነው።
91 ሐና፦ጸጋ ወይም ስጦታ ማለት ነው።
92 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ ማለት ነው።
93 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል ማለት ነው።
94 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ ማለት ነው።
95 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና ማለት ነው።
96 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት ማለት ነው።
97 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ ማለት ነው።
98 እስጢፋኖስ፦አክሊል ማለት ነው።
99 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ ማለት ነው።
100 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ ማለት ነው።
101 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ ማለት ነው።
102 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል ማለት ነው።
103 ዮርዳኖስ፦ወራጅ ውሃ ማለት ነው።
104 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
105 ገነት፦የአትክልት ስፍራ ማለት ነው።
106 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር ማለት ነው።
107 ዲና፦ፈረደ ማለት ነው።
108 ማኑሄ፦እረፍት ማለት ነው።
109 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
110 ራማ፦ከፍታ ማለት ነው።
111ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
112 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ ማለት ነው።
113 ሕርያቆስ፦ኅሩይ ምርጥ ማለት ነው።
114 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ ማለት ነው።
115 ቶማስ፦ፀሐይ ማለት ነው።
116 ታዴዎስ፦እሸቱ ማለት ነው።(ግብራዊ ትርጓሜ)
117 ማትያስ፦ፀሐይ ወይም ምትክ ማለት ነው።
118 ቀሌምንጦስ፦ግንብ ማለት ነው።
119 አቤል፦በግ ወይም ደመና ማለት ነው።
120 ኖኅ፦ደስታ ማለት ነው።
121 ሴም፦ተሾመ ማለት ነው።
122 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም ይሳቅ ማለት ነው።
123 ሙሴ፦የውሃ ልጅ ማለት ነው
124 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ ማለት ነው።
125 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
126 እሴይ፦ዋጋየ ማለት ነው።
127 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ ማለት ነው።
128 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ ማለት ነው፣
129 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ ማለት ነው።
130 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ ማለት ነው።
131 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው ማለት ነው፣
132 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
133 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ ማለት ነው።
134 ራኄል፦በግዕት ማለት ነው።
135 ዕዝራ፦ረዳቴ ማለት ነው።
136 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች ማለት ነው።
137 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ ማለት ነው።
138 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ ማለት ነው።
139 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ ማለት ነው።
140 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት ማለት ነው።
141 ሶምሶን፦ፀሐይ ማለት ነው።
142 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
143 ማርታ፦እመቤት ማለት ነው።
144 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር ማለት ነው።
145 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው ማለት ነው።
146 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች ማለት ነው።
147 ታዴዎስ፦ተወዳጅ ወይም ፍቁር ማለት ነው።(ቃላዊ ትርጓሜው)
148 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር ማለት ነው።
149 ሄኖስ፦ሰው ማለት ነው።
150 ሰሎሜ፦ሰላም ማለት ነው።
151ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው