Arsenal News
2 subscribers
4 links
Arsenal News Update, Premier league, Champions League, FA Cup, Carabao Cup
Download Telegram
Channel created
🚨🇲🇲 በማይናማር ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1700 ደረሰ።

በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 በተለካው ርዕደ መሬት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 700 በላይ ሆኗል።

አደጋውን ተከትሎ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ የደረሰ ሲሆን፥ ረጂ ድርጅቶችም ከጦርነቱ ጋር ተዳምሮ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት ለማይናማር ሰብአዊ እርዳታ ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ ያስፈልገኛል ብሏል።

ድርጅቱ ይህን ያለው በሀገሪቱ የተከሰተው ርዕደ መሬት ካስከተለው መጠነ ሰፊ ጉዳት በኋላ ነው ተብሏል።

ከዛም ባሻገር በሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስት እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል አሁንም ጦርነት መኖሩንም ዘገባዎች አስነብ
🚨🇧🇫 በቡርኪኒፋሶ ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታል ሴቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ ልጅ እንዲወልዱ ተወስኗል።

"እኔ የተወለድኩት ከሴት ልጅ ነው ሴት ልጅ ህይወትን ወደ እዚች ምድር ለማምጣት ብዙ ክፍያ ስትጠየቅ ማየት አልፈልግም ።
ድሃ እናቴ እኔን ለመውለድ በሚከፈል ክፍያ ምክንያት እኔን ልታጣ ነበር። ፈጣሪ ባይፈቅድ ኖሮ እኔም በህይወት የለሁም ነበር:: ዛሬ የዚህች አገር ፕሬዚዳንትም አልሆንም ነበር። ስለዚህ ህይወትን የምትሰጥ እናት ለሆስፒታል መክፈል የለባትም።"
የብርኪናፋሶ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ትራኦሬ
🚨🇲🇲 በማይናማር ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1700 ደረሰ።

በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 በተለካው ርዕደ መሬት ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 700 በላይ ሆኗል።

አደጋውን ተከትሎ በሀገሪቱ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ የደረሰ ሲሆን፥ ረጂ ድርጅቶችም ከጦርነቱ ጋር ተዳምሮ ጉዳቱ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት ለማይናማር ሰብአዊ እርዳታ ከ8 ሚሊየን ዶላር በላይ ያስፈልገኛል ብሏል።

ድርጅቱ ይህን ያለው በሀገሪቱ የተከሰተው ርዕደ መሬት ካስከተለው መጠነ ሰፊ ጉዳት በኋላ ነው ተብሏል።

ከዛም ባሻገር በሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስት እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል አሁንም ጦርነት መኖሩንም ዘገባዎች አስነብ
🚨🇪🇹በየሁለት ሳምንት ልዩነት ተከታታይ የውጪ ምንዛሬ ጨረታ ማካሄድ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ መደበኛ እና ተከታታይ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ ሊጀምር እንደሆነ አስታወቋል። “የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጪ ምንዛሬ ስርዓት ግብ ለማሳካት” የታቀደ ነው የተባለለት ጨረታ፤ ነገ ማክሰኞ መጋቢት 23፤ 2017 ይጀመራል።

በነገው ጨረታ 50 ሚሊዮን ዶላር ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን፤ ፍላጎቱ ያላቸው ባንኮች ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ጥሪ አድርጓል።

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጪ ምንዛሬ ተመን ስርዓት በሐምሌ 2016 ከተደረገ ወዲህ ብሔራዊ ባንክ ሁለት ጊዜ ዶላር ለባንኮች በጨረታ ሸጧል።
ፖሊስ በአራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች ላይ የጠየቀው የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቀደለት
በተጨማሪ አራት የጣቢያው ሰራተኞች ላይ የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ለነገ ተቀጥሯል

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ ጠርጥሬያቸዋለሁ” ባላቸው አራት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። ባለፈው አርብ ፍርድ ቤት ከቀረቡ የጣቢያው ሰራተኞች መካከል፤ የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ቶማስ ደመቀ ከእስር ተለቅቋል ተብሏል።

የአቶ ደመቀን ከእስር መለቀቅ ከፖሊስ የምርመራ ምዝገባ መረዳቱን የገለጸው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው። ችሎቱ የኢቤኤስ ሰራተኞች የተካተቱበት የስምንት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ መመልከት የጀመረው ባለፈው አርብ መጋቢት 19፤ 2017 ነበር።

የፌደራል ፖሊስ ለችሎቱ ባቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ማመልከቻ ላይ በተጠርጣሪዎቹ ላይ እያካሄደ ያለውን ምርመራ “በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት” የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ በዛሬው ዕለት ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ከመስጠቱ አስቀድሞ፤ የፖሊስ ጅምር የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ችሎቱ ዛሬ ሰኞ መጋቢት 22 ከሰዓት በነበረው ውሎው፤ ተጠርጣሪዎቹን በሽብር ወንጀል ለመጠርጠር አመላካች የሆኑ ነገሮች ከፖሊስ ምርመራ መዝገብ ተመልክቼያለሁ ብሏል። የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች፤ ደንበኞቻቸው ቢጠረጠሩ እንኳን “የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣ አዋጅ ስር ባሉ ድንጋጌዎች” እንደሆነ ያቀረቡት መከራከሪያ “የተፈጸመ ጥፋት መኖሩን” የሚያሳይ እንደሆነ ችሎቱ በተጨማሪነት ጠቅሷል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15602/
ኣርሚ 70...
ከኣልቡርሃን ጦር ጎን ተሰልፎ  በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ላይ እንዲሳተፍ ስለተደረገው
ኣርሚ 70 ተብሎ ስለሚጠራው ሀይል (የስም ስያሜው ከየት እንደሚፈልቅ ባላውቅም በታሪክ ግን ሻእቢያ ከ1970 ጀምሮ የነበራት አርሚ 70 የምትለው ተዋጊ ሀይል ነበራት)
የሚያሳፍረው ወጣቱን በዚህ መሰሉ ጦርነት ማግዶ ዶላር የሚያጋብሰውን ቡድን "ለምን"
ብሎ መጠየቅ ሲገባ "ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጦር ጎን ሆና ስትወጋን አልነበር ወይ?" የሚል ማስተባበያ የሚያነሳው ነው። በቀጣይ እንደ ቡድን ብቻ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ጭምር እራስን በመሸጥ መርሰነሪ ለመሆን የተዘጋጀ ትውልድ ለማፍራታችን ይሄ አመላካች ነው።

(ስለ ኣርሚ 70 ለረጅም ግዜ ምንም ላለማለት ብሞክርም እራሴን እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ እና
ከወታደራዊ አለባበሱ ጀምሮ ትጥቁ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴው ለምን ከሻእቢያ ጋር ሊመሳሰል ቻለ?" የኔ ጥያቄ ነው)

- ©Gumaa Saqqataa Gem
ከ50  ሚሊዮን ናይራ በላይ ተሰበሰበለት

በርግጠኝነት የዚህን ልጅ ፎቶ ከዚህ በፊት አይታችሁታል ።
አልበርት ይባላል ። እና በዚህ የሰከንዶች ቪዲዮ ላይ ፡ እናቱ ፕላፕምሌት ስትሰጠው ላለመብላት ብሎ ሲያለቅስ ፡ በዛው ቅፅበት ደግሞ ምግቡን እንዲበላ አያቱ በዜማ ስታባብለው ማልቀሱን አቁሞ ሲስቅ ይታያል ።
.......
የዚህ ጋናዊ  ታዳጊ የአልበርት ቪዲዮና ፎቶ ፡ በፌስቡክ ቲክቶክና ኢንስታግራም ላይ ፡  የተለያየ ሚም እየተሰራበት ታዋቂ ከመሆኑም በተጨማሪ ለብዙ ሰወች የገቢ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል ። በተለይ ቪዲዮው ለመጀመሪያ በተለቀቀበት የቲክቶክ አካውንት ከ370 ሚሊዮን በላይ ሰወች የተመለከቱት ሲሆን ከዛም በኋላ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰወች ሚም ሰርተውበት ፡ በአለም ዙሪያ ያሉ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰወች አይተውታል ።
...
አስገራሚው ነገር ይህ የዚህ ልጅ ቪዲዮ በቲክቶክ የተለቀቀበት መንገድ ራሱ አስገራሚ ነበር ። ይህን ቪዲዮ ለመጀመሪያ ጊዜ ፖስት ያደረገው ሰው ፡ ቪዲዮውን ያገኘው ከሰው ላይ በገዛው ስልክ ውስጥ ነበር ። በኋላ እንደታወቀው ይህን ቪዲዮ የቀረፀው የታዳጊው ልጅ አጎት ሲሆን ፡ ስልኩን በሸጠበት ወቅት ቪዲዮው ባለመደለቱ ፡ ይህን ያገኘው ሰው ይህን ያህል ቫይራል ይሆናል ብሎ ሳያስብ እንደቀልድ ፖስት አደረገው ።
....
በዚህ መልክ ፡ በአጋጣሚ ቫይራል የሆነው ይህ ቪዲዮ ታዋቂ ከሆነ  በኋላም የተለያዩ ኮንተንት ክሪኤተርስ ወደቤቱ እየሄዱ ለቪው ማሳደጊያ ቪዲዮ እየቀረፁ ሲለቁ ነበር ።
በቅርቡ ግን አንድ ታዋቂ የጋና ቲክቶከር ፡ ይህን ልጅ በተመለከተ በሰራው ቪዲዮ የጤና ችግር እንዳጋጠመው እና በድህነት ውስጥ እንደሚኖር ገልፆ ፡  እንዲታገዝ ጥሪ አቀረበ ።
...
ይህን ጥሪም ተከትሎ በሳምንት ጊዜ ውስጥ በጋና እና ናይጄሪያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ከሚኖሩ ቲክቶከሮች ሀምሳ  ሚሊዮን ናይራ  የተሰበሰበለት ሲሆን እስካሁን በቀጠለው የገቢ ማሰባሰቢያ  ይህን ታዋቂ ልጅ ለመደገፍ ብዙዎች ቃል ገብተዋል ።
....
እና ይህንን መረጃ  ያጋራው ዌብ ሳይት ፅሁፉን ሲዘጋ እንዲህ ብሏል ።
When it’s your time, even people who never knew you will come to bless you

የተፃፈው በ©Wasihun tesfaye

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ💎
____

   📌 t.me/Fastsinfo99

              🌴  🌴  🌴
የክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የቆይታ ጊዜ የማራዘም ስልጣን፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው

የፌደራል መንግስት በክልሎች የሚያቋቁመውን ጊዜያዊ አስተዳደር የስራ ዘመን፤ ለሁለት ጊዜ የማራዘም ስልጣን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ በነገው ዕለት ለፓርላማ ሊቀርብ ነው። የአዋጅ ማሻሻያው፤ የአፈ ጉባኤው ውሳኔ በፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተቀባይነት ካላገኘ፤ ጊዜያዊ አስተዳደር በተቋቋመበት ክልል “በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ” “ምርጫ እንዲደረግ” ያስገድዳል።

ይህ የህግ ረቂቅ፤ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ስርአት ለመደንገግ በ1995 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ የሚያሻሽል ነው። የአዋጅ ማሻሻያው በነገው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ የሚቀርበው፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን የስልጣን ዘመን ለማራዘም “የህግ ማሻሻያ” እንደሚያስፈልግ ከተገለጸ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩን የመቆያ ጊዜ “አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ” የማራዘም ስልጣን የተሰጠው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ነበር። በዚህ ድንጋጌ ትግበራ ሂደት ላይ “ባለፉት ዓመታት የተስተዋሉ ሁለት ችግሮች” እንዳሉ የአዋጅ ማሻሻያውን ለማብራራት የቀረበ ሰነድ ያስረዳል።

የመጀመሪያው ችግር “የጊዜያዊ አስተዳደሩን ቆይታ ለማራዘም ውሳኔ የሚሰጠው የፌደሬሽን ምክር ቤት፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ የሚሰበሰብ” ከመሆኑ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ማብራሪያው ይገልጻል። የምክር ቤቱ አባላት “በየክልላቸው ከፍተኛና ተደራራቢ የመንግስት ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ፤ የጊዜያዊ አስተዳደር ቆይታን ማራዘም ሲያስፈልግ በአጭር ጊዜ ስብሰባ በመጥራት ውይይት አድርጎ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስቸግር” እንደሆነ ሰነዱ ያታትል።

በማብራሪያ ሰነዱ የተቀመጠው ሁለተኛ ችግር በነባሩ አዋጅ ለጊዜያዊ አስተዳደር የተቀመጠው የጊዜ ገደብ “ሁለት ዓመት ከግማሽ” መሆኑ ነው። ይህ መነሻ “ከነባራዊው ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ ተገኝቷል” የሚለው ሰነዱ፤ “በዚህ የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይፈቱ እክሎችም ተስተውለዋል” ሲል ያክላል። በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት ያለው “ነባራዊ ሁኔታ” ለዚህ “በአብነት መጥቀስ ይቻላል” ሲልም ያክላል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15597/
🚨በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር በዚህ ከቀጠለ “ነገ የአማራ እናት ከዩኒቨርሲቲ የምታስመርቀው ልጅ አይኖራትም” - #የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

በጸጥታ ችግር ምክንያት የዘንድሮ የትምህርት ዘመን ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም አራዝሞ የነበረው የአማራ ክልል አሁንም ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደምስ እንድሪስ እንዳስታወቁት በክልሉ በጸጥታ ችግር ከሶስት ሺ 600 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል ብለዋል።

“ችግሩ በዚህ ከቀጠለ ነገ የአማራ እናት ከዩኒቨርሲቲ የምታስመርቀው ልጅ አይኖራትም” ያሉት ሃላፊው፤ “እንደ እስካሁኑ አስተምረን በተለያዩ የአለም ክፍሎች የምናሰማራቸው ልጆች አይኖሩንም” ሲሉ ገልጸዋል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7382
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Channel name was changed to «Arsenal News»