ብራና ሚዲያ BRANA MEDIA
354 subscribers
1.3K photos
11 videos
146 files
169 links
Download Telegram
+መጻሕፍትንና አበውን ያናገረ መጽሐፍ+
#ጽንዐ_ተዋሕዶ

#መግቢያ

መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ በኤማሁስ ሲያቀኑ የነበሩትን መንገደኞች መጻሕፍትን ተርጉሞ አእምሮ መንፈሳዊና እንደቸራቸው ሁሉ የራቀውን አቅርበው የረቀቀውን አጉልተው የሚያሳዩ በዘመን ሁሉ የተነሱ ሊቃውንትም መጸሐፍትን እየተረጎሙ የሳተውን እያረሙ የሰው ልጆች ጥራዝ ነጠቅ ፈቺ ሆነው እንዳይቀሩ ሲደርሱ ሲደጉሱ ኖረዋል።

ሃይማኖት እያቀኑ ብዙዎችን ስሁት ከሆነ ትምሕርት ነጥቀዋል በቃል የመጣውን በቃል በመጸሐፍ የመጣን በመጸሐፍ እያደረጉ ድል ነስተዋል። ዘመን የሚወልዳቸው ጸሐፍያን ደግሞ የሊቃውንቱን ትምህርት ማመሳከርያ እያደረጉ የቤተክርስቲያንን መሠረተ እምነት በጎልሕና በተረዳ አስቃኝተውናል። ከእነዚህም ውስጥ መምህር በዓማን ነጸር አንዱ ነው ብዬ አምናለው። የመስኮት ሰው ስላልሆን በመልክ ብዙዎቻችን ባናቀውም ቅሉ ባበጀው ክታበ ገጽ(fb) ላይ ጠንከር ያሉ ምን አልባትም ወተት ለለመድን ሰዎች እንደ አጥነት የጠነከሩ ጽሑፎችን ሲያጋረን እናቀዋለን። በጽሑፎቹ በጥበብ ሲገስጽ እና በብስለት ሲያስተምርም ተመልክተነዋል።

ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከአንጻሩ የሚያነጻጽር ጥንተ አብሶን ከነጓዙ የሚተነትን ቁንጸላዎችን የሚወድር ወለታ ጽድቅ በተሰኘው መጽሐፉ የተዋወቀን በአማን ነጸረ ተቀብዓ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋት ጉባኤያት ታሪክና ዶግማ ከምክንያተ ጽሕፈት ከዘርዝር የነገረ ክርስቶስ ሐተታ ጋር የቀረበ ጽንዐ ተዋህዶ የተሰኘ መጽሐፍ በ2012 በገበያ ላይ አውሏል። ይሕን መጽሐፍ ባናነበው እንኳን ለብዙ ጥያቄዎች ምላሽ አንድም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል መጽሐፍ በመሆኑ ለትውልድ ቢሻገሩ ብዬ መምኛቸውው መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ሆኗል።

#የምዕራፎቹ_ጭብጥ ሐሳቦች

1👉በመጀመርያው ምዕራፍ በዘመነ ሊቃውንት የተዘጋጁ ተቀብዐ ተኮር ምንባባትን ከምክንያት ጽሕፈት ጋር ያትታል። በዚህ ክፍሉ የሄሬኔዎስን÷ የባስልዮስ ዘቂሳርያን÷የጎርጎርዮስ ዘኑሲስን÷ የአርጌንስን÷የአውሳብዮስ ዘቂሳርያን÷የአርዮስን የጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙን÷የአትናቴዎስን የዩሐንስ አፈወርቅን÷የንስጥሮስን÷የቅዱስ ቄርሎስን የቴዎዶስዩስ ዘእስክንድርያን÷የሳዊሮስ ዘአንጾኪያን÷ ተቀብዐ ተኮር ጽሑፎችን ያብራራል አንድም "ተቀብዐ" የሚለውን ቃል በምን መልኩ ለማን እና ለምን እንደተጠቀሙበት በጥልቀት ያስረዳል። ተቀብዐን በሁለቱ ጉባኤ ቤቶች ውስጥም ያለውን ፍቺ ይገልጣል። በምንፍቅና የተወገዙትን እንዲሁም የቅዱሳን ሊቃውንት የአበው መጻሕፍት እንዲናገሩ እድል ሰጥቷል።

2👉በዘመነ ሊቃውንት ያሉትን ተቀብዕ ተኮር መጽሐፋዊ ሐረጋትና ካስቃኝ በኋላ "ተቀብዐ" በመካከለኛው ዘመን በኢትዮጵያ በተደረሱና የተተረጎሙ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከተጨባጭ ታሪኮች ጋር ያስቃኘናል። ሁለቱ ቤተ መነኮሳት ማለትም በቤተ ተክለሃይማኖት እና በቤተ ኤዎስጣቴዎስ የተደረገው የቅድምና ክርክርን ይተርካል። ተቀብዕ ከልሳነ ዐረብ ከተተረጎሙ ድርሰቶች ውስጥ በሃይማኖተ አበው ዘቄርሎስ÷ በሃይማኖተ አበው ዘሳዊሮስ ዘአንጾኪያ÷በሳዊሮስ ዘእስሙናይን ድርሳን÷ግብረ ሕማማት ዘሐሙስ ውስጥ ያሉትንም ሐረጋት ይመረምራል። "ተቀብዕ" ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ በተሰኘው በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሥራዎች ላይም እንዴት እንደተገለጠ ያስነብባል የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ሚላድንም ይዳስሳል።

3👉በመቀጠል ድኅረ ምጽአተ ካቶሊክ የተደረጉ ጎባኤያትን ከሥር መሠረታቸው ይተርካል። ሱታፌ መንፈስ ቅዱስ በነገረ ሥጋዌ የተነሣበት ከካቶሊካውያን ጋር የተደረገውን የመጀመርያውን ጉባኤ÷በዐፄ ዘድንግል ዘመን የተደረገውን ጉባኤ÷ በዓፄ ሱሲንዮስ የተደረጉ ተጨማሪ ጉባኤያትን እና የነገረ ክርስቶስ አለመግባባት የወለዳቸው አመፃዎችና ምዕላዶች ከፎገራ ጉባኤ ማግሥት እስከ ፋሲለደስ ንግሥና ድረስ ያለውንም ይተርካል። በዚሁ ሳያበቃ የነገረ ክርስቶስ ምዕላዳት መጀመርና ውስጣዊ የነገረ ክርስቶስ ክፍፍሎችንም እያስቃኘ ይሔዳል። የአልፎዝ ሜንዴዝ ወደ ሐገር መምጣት÷ተቀብዐ ተኮር ትምሕርቱና የተሰጠው ምላሽ÷ከሀገር በምን መልኩ እንደለቀቀና÷በእርሱ ምክንያት ስለተደረገው ጉባኤ÷እንዲሁም የሜንዴዝ እሾሆች የተባሉትን ይገልጻል። "የቅብዓት አስተምህሮ የት መጣ" በሚለው ንዑስ ርዕስ ምዕራፍ ሦስትን ይዘጋል።

4👉በቀጣዩ ምዕራፍ ማለትም በምዕራፍ አራት ከ1624-1762 የነበረውን ዘመን ያስቃኛል በዘመነ ጎንደር በነገረ ክርስቶስ ጉዳይ የተደረጉ ክርክሮችን ይዟል። በዘመነ ፋሲል÷በዘመነ አእላፍ ሰገድ÷በዘመነ አድያም ሰገድ ኢያሱ÷ በዘመነ ንጉሥ ተክለሃይማኖት÷በዘመነ ዐፄ ቴዎፍሎስ÷በዘመነ ዐፄ ዳዊት ሣልሳይ ÷በዘመነ ዐፄ በካፋና ብርሃን ሰገድ ኢያሱ÷በዘመነ ኢዩአስ በነገረ ክርስቶስ የተደረጉ ጉባኤያትና ያለ ጉባኤ የተደረጉ አዋጆችን ይዞ እናገኘዋለን።

5👉ከዘመነ ጎንደር ወደ ዘመነ መሳፍንት ያቀናና የጸጋን አመጣጥ በአቡነ ዮሳብ ዘመነ ጵጵስና÷ጸጋ ከተዋህዶ ጋር÷የጸጋና የቅብዐት ዳግም ግንባር መፍጠር በዘመነ አቡነ ቄርሎስ÷ በስተመጨረሻም ከፕሮቴስታንታውያን ጋር የተካሄዱ የነገረ ክርስቶስ ንግግሮችን ይገልጻል።

6👉ጉባኤያት ድኀረ ዘመነ መሳፍንት እና መጽአተ አቡነ ሰላማ ሣልሳይ በምዕራፍ ስድስት ሠፍሯል። የአቡነ ሰላማ ምርጫበተመለከተ ወደ ሀገረ ኢትዮጵያ ሲመጡ ነበረውን ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ነባራዊ ሁኔታ÷የአቡነ ሰላማና የዐፄ ቴዎድሮስ ጉዞ ከአምባ ጫራ እስከ መቅደላ ዘልቆ ካሳየ በኋላ ዐፄ ዮሐንስ መፍቀሬ ተዋህዶ አቋማቸውን እንዲሆም የቦሩ ጉባኤ እንዲሁም በተለምዶ ዘጠኝ መለኮት ስለሚባለው አስተምህሮ ይይዛል።

7👉ሰፊ ርዕሶችና በዛ ያሉ ንዑስ ርዕሶች የተካተቱበት ምዕራፍ ሰባት ሦስቶ የኢትዮጳውያን የነገረ ክርስቶስ ዘውጎች ካነሷቸው አርእስት ጋር ያብራራል። ተዋህዶ÷በተዋህዶ ከበር÷ሁለቱ የጸጋ አስተምህሮዎች÷ብሂለ ቅብዓት የተሰኙ ዐበይት ርዕሶች አሉት።

8 👉የመጸሐፉ የመጨረሻው ምዕራፍ ስምንት ከነገረ ክርስቶስ ጋር የተገናኙ ቅኔያትን ያስነብባል።

#ማጠቃለያ_{_የመጽሐፉ_አስፈላጊነት_}

👉መማርያ እና ማመሳከርያ

ይህ መጽሐፍ ጥናታዊ ስልትን የተጠቀመና ከሀገር ውጪ እንዲሁም ሀገር በቀል ድርሰቶች ተመርምረው የቀረቡበት ተቀብዐ ተኮር እና ነገረ ክርስቶስ የተዳሰሰበት በመሆኑ በቲዎሎጂ ላሉ መማርያ አልያም ማመሳከርያ ሊሆን የሚችል ክታብ ነው። በሀገራችን እንደነ አድማሱ ጀንበሬ አይነት ሊቃውንት የጻፏቸውን የመልስና የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የሸከፉ መጻሕፍትን ለትውልድ ከማስተላለፍ ባሻገር በመንፈሳዊ የትምሕርት ተቋማት ውስጥ እንደ ማመሳከርያ ሊቀርቡ ሲገባቸው ከግለሰቦች ውጪ ብዙ ምዕመናን እጅ ውስጥ መገኘት ተስኗቸዋል። እንዲህ ያሉ ችግር ፈቺ እና አንኳር ርዕሰ ጉዳዩች የያዙ መጽሐፎች ተመርጠው ለመማርያና ለማመሳከርያ ሊሆኑ ይገባል የሚል ቅናታዊ ሐሳብ አለኝ። ቢቻል ቢቻል የጥናትና የምርምር ማዕከል ተገንብቶ ዶግማቲክ ርዕሰ ጉዳዩች የሚዳሰሱበት መጽሐፋዊ ሐረጋትም ትንታኔ የሚሰጥባቸው ቢሆን እጅግ የተሻለ ይመስለኛል። በጥቅሉ ጽንዐ ተዋህዶ ከገበያ ሽያጭ ባለፈ ማጣቀሻ እና ማመሳከርያ ሆኖ ከቤተመዛግብት ሊቀመጥ የሚገባ ይመስለኛል።

👉የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የገለጠ

የቤተከርስቲያኒቱን አስተምህሮ ያበራል።
አንድ አንድ መጽሐፉች ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎችን ከመስጠት ባሻገር የተለየ ድርሳናትነ እና ሐረጋትን እና ሐረጋትን አያትቱም። የሳተውን የሚመልሱ የመጸሐፍትን ምሥጢር እየመረመሩ እውነትን የሚገልጡ ጸሐፍት ባይኖሩ ኖሮ ለብዙ ዘመናት በተለይ በሐገራችን ሲያነታ
#ቡሄ_ሔ
የደብረ ታቦር በዓል ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ ቢሆንም በምዕመናን ዘንድ ቡሄ/ሔ በመባል ይታወቅል ለመሆኑ የደብረ ታቦር በዓል ለምን ቡሄ/ሔ እያልን እንጠራዋለን? ስለምንስ ችቦ እናበራለን? የሚጮኸው የጅራፍ ድምጽ ምንድነው ምሥጢሩ የሚለውን በአጭሩ እንመከታለን፡፡
=================_//_==============
ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስለ ደብረ ታቦር በዓል አከባበር በኢትዮጵያ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ “ቡሄ/ሔ ዘውእቱ በዓለ ኖሎት ደቀ መዛሙርት “ ይህውም ደብረ ታቦር ወይም የቡሄ/ሔ በዓል የደቀ መዛሙርትና የእረኞች በዓል ነው እንደ ማለት ፡፡ ምክንያቱም በጥንቷ ኢትዩጵያ የደብረ ታቦርን በዓል እረኞች የቆሎ ተማሪዎች በስፋት ስለሚያከብሩት ነው፡፡
===============_//_=================
#ቡሄ፡- ማለት “የበራ የደመቀ የጐላ ብርሃን“ የብርሃን በዓል እንደ ማለት ነው ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን በገለጠ ጊዜ ፊቱ እንደ ፀሐይ በማብራቱ፥ ልብሱም አጣቢ በምድር ላይ ሊያነጣው እስከማይችል ድረስ በጣም ነጭ አንጸባራቂ በመሆኑ ነው ማቴ 17፥2 ማር9፥3 ሉቃ9፥29
=============_//_===================
#ቡሔ፡- ማለት ደግሞ “ደስታ ፍሥሐ“ማለት ይሆናል፡፡ ይህውም በትንቢት እንደተፃፈው ታቦር ወአርምንዔም በስመ ዘአከ ይትፈሥሑ መዝ88፥12 በዚህ ትንቢታዊ ቃል መሠረት በወቅቱ የጌታ ብርሃን በዙሪያቸው አብርቷል ከታቦርም እስከ አርምንዔም ተራራ ድረስ ታይቷል፡፡ ይህም መለኮታዊ ብርሃን በወረደበት ጊዜ ከብቶቻቸውን ይጠብቁ የነበሩ በታቦርና በአርሞንየም አካባቢ ያሉ መዓልቱ የሌሊቱን ቦታ ስለ ወሰደው በሁኔታው ሐሴትን አድርገዋል፡፡ሙልሙል/ኀብስቱ፡- በታቦር ተራራ ዙሪያ ለነበሩት እረኛች ወላጆቻቸው ምግባቸውን ይዘው መሄዳቸውን ያጠይቃል፡፡ አንድም የኀብስቱ ምሳሌነት ለክርስቶስ ነው “አነ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት” ዮሐ 6፥32-59
=================_//=================
#ጅራፍ፡- በደብረ ታቦር ዋዜማ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆነን ጅራፍ የምናጮኸው መሠታዊ ሃይማኖታዊ ምሥጢር ምሳሌነት አለው።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
እግዚአብሔር አብ በመልክ የሚመስለኝ በባህሪ የሚተካከለኝን ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጄ ነው፡፡ እርሱን ስሙት ተቀበሉት ብሎ ድምጹን በደመና በደብረ ታቦር ተራራ ላይ የመሰከረበትን እያሰብን ነው፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የጅራፍ ጩኸት ከጫፍ ጫፍ ይሰማል በመዝሙረ ዳዊት “……….. ድምጻቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም አስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡” መዝ18፥4 በማለት የሐዋርያት ስብከት በዓለም ዳርቻ መድረሱን ያመለክታል፡፡ መኃ 2፥12
ሌላው የጅራፍ ጩኸት ማስደንገጡ ደግሞ ሦስቱ አዕማድ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ድምጸ መለከትን ሰምተው ደንግጠው መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በተጨማሪም የልጆቹ ወላጆች በታቦር ተራራ ዙሪያ የነበሩትን ልጆቻቸው ለመፈለግ ችቦ እያበሩ ሲሄዱ ልጆቹም ጅራፍ በማጮኽ ያሉበትን ሥፍራ መጠቆማቸውን ያስረዳል፡፡
ችቦ፡- ተሰብስበን ችቦ የማብራታችን ምሳሌ ደግሞ ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለፀበት ምሳሌ በመሆኑ ነው፡፡ የሐ 8፥1፣ መዝ 26፥1 “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሐኒቴ ነው……..”
================_//=================
#ማጠቃለያ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደብረ ታቦርን በዓል በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን ታከብረዋለች፤ ይኸውም በዕለቱ በዓሉን የሚያዘክር በቤተክርስቲያን ምንባባት ይነበባል፡፡ ቅዳሴ ይቀደሳል፣ ምስባክ ይሰበካል፣ ቃለ እግዚአብሔር ይሰጣል፣ ወረብ ይወረባል………… ወዘተ በዚህም ዕለት የቤ/ክ አባቶችና ምእመናን በዓሉን በደማቅ ሥነ ሥርዓት ያከብሩታል፤ ምክንያቱም ከላይ በስፋት እንደ ተመለከትነው ደብረ ታቦር እሥራኤላውያን የድል ካባ የደረቡበት መሳ 4፥1—3 የትርጓሜ ትምህርት የተሰጠበት ማቴ 15፥15፣ ኑፋቄ (ጥርጥር) የተወገደበት ማቴ 16፥13—20፣ ምሥጢረ ሥላሴን የተረዳንበት፣ የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተሰበከበት፣ የሐዋርያት ባለሟልነት የተገለጠበት፣ የተግባር ትምህርት የተሰጠበት፣ አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣ የቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት ክብር የተገለጠበት፣ የተቀደሰን ቦታ አክብሮት፣የተማርንበት የታየበት፣ ብሔረ ሕያዋን መኖሩ የተመሠከረበት፣ የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተረጋገጠበት ነው፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
“በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል…………” ኢሳ ፪፥፪
••MIKIYAS DANAIL••
https://t.me/mikiyasBRANAbook
https://www.facebook.com/mikiyas.danail
=============//================
መልካም የደብረ ታቦር በዓል
••••••••••••••
©መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል
ነሐሴ12/2014