🎤ቦርፎሪኮን🎸
2.04K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
654 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
#ክፍል_አንድ
መሻላችንን ሳይሆን ከሁሉ የሚበልጠውንና ለዓለም ሁሉ ኃጢአት የሞተውን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ እንስበክ!።

ክርስቶስን ዘንግቶ የራሱን መሻልና ያለበትን የቤተክርስቲያን ስም የበላይነት የሚሰብክ ሰው ሆነ መላዕክት ፣ ያለው ሆነ የሚመጣ ፣ ኃይላት ከከሃዲ በምንም አይሻልም።

📝አንዳንዶች ሌላውን ሃይማኖት ሁሉ እንደ ሀገር አጥፊና ሰላይ አድርገው የመፈረጅ አበዜ ዛሬም ይታይባቸዋል።

🎯ኢትዮጵያዊነት ማለት የእነርሱ አንድ ሃይማኖት አድርገው የሚቆጥሩ ብቻ ሳይሆኑ ሃይማኖትንና አገርን እንደ ድሮው አንድ ላይ ጨፍልቀው የሚመለከቱ፣ መረጃ አልባ ፣ ውሃ የማይቋጥር ፣ ባዶና ያረጀ ሀሳብ ለማስረዳት የሚጥሩ "#ምሁራን" #አስተማሪዎችና #ፕሮፌሰሮች ዛሬም ቁጥራቸው በምድረ ኢትዮጵያ ቀላል የሚባል አይደለም።

📝መንግስትና ቤተ ክርስቲያን በአገራችን #ከ16_ምዕተ_ዓመት በላይ በጥምረት ይገዙ የነበረበት ዘመን ገና 70 ዓመት እንኳን ያልሞላው በመሆኑ በተለይ በዚያ ዘመን የነበሩና የሥራዓቱ ተጠቃሚዎች ያን ዘመን ቢያደንቁ አይፈረድባቸውም። ይሁንና #መልካሙን_ስናደንቅ_ክፉውን_መኮነን መሆኑ መዘንጋት የለብንም።

ሌላው ደግሞ ብዙዎች ለራሳቸው የሃይማኖት ስም #ሰጥተው ወይም በማድላት በኢትዮጵያ የነበረው አንድ ሃይማኖት ብቻ ነበር በሚል ክርክር ያነሳሉ! ለመሆኑ ከ3000 አመት በፊት በኢትዮጵያ ምን አይነት ሃይማኖት ነበር??? አሁን ያ አንዱ ሃይማኖት ብቻ መኖር አለበት ወዘተ....ከሚል የተሳሳተ ድምዳሜ በመንሳት ፍርድ የሚገመድሉና ዛሬም ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን በቁጥር መነጽር ብቻ የሚያዩ ናቸው።

🎯ይህ ከግላዊ ጥላቻ የተነሳ፣ የእግዚአብሔር ቃል ስል ቤተ ክርስቲያን የሚናገረውን ትክክለኛ አስተምህሮን በትክክል ካለመረዳት፣ ግላዊና ቁንጽል አገራዊ መረዳትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ለማድረግ ከመጣር፣ በዛሬይቷ ኢትዮጵያ ሁሉን ሃይማኖት በእኩልነት የሚያቅፍ አዲስ ህግ መታወጁን ለመቀበል ካለመፈለግና ለራስ የተጋነነ ሚዛን እና በየሶሻለረ ሚድያዎች ተከታዮችን ለማፍራት ብሎም ዩቶበር ስለሚከፍል በእይታ ብዛት እንካም ሊፍጥር ከማለት የመጣ ሊሆን ይችላል።

▶እናስተውል!! ወገኔ እግዚአብ ሔር ያንተን #ፕሮቴስታንት መሆን ፣ ያንቺን #ኦርቶዶክስ መሆንሽን፣ ወይም #ካቶሊክ ብሎም #እስላም ብለህ ከሰየምከው ተቋም ጋር ከህይወትህ ጋር ነው ጉዳዩ! እናም ቆም ብለህ /ሽ አስብ /ህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ሲመጣ ሃይማኖትን ሊያድል ሳይሆን ህይወት ልሆንልህ/ሽ መቷል።

ስለዚህ ዛሬ እንወስን ንሰሐ እንግባ!! ከዚህ ቀደም የንሰሐን ጥሪን ሰምታችሁ ህይወታችሁን ለጌታ ያልሰጣችው አብረን ለመፀለይ በዚህ ቁጥር ደውሉልኝ።
+251911013333

በጌታ ፍቅር ላልዳኑ እና ለጓደኞቻችሁ ሼር ያድርጉ።

Join share it👇👇👇👇
@borforiconn