🎤ቦርፎሪኮን🎸
2.01K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
662 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
>>>>>>>> #ስላሴ <<<<<<<<
" ስላሴ " የሚለው ቃል በቀጥታ ወይም በብሉይም በአዲስም ኪዳን የማናገኘው ቢሆንም ፤ አንድ አምላክ እግዚአብሔር በሶስት አካላት መኖሩን እና በሶስትነት አንድነት የሚገልፅ ቃል ነው።
መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር አንድ አምላክ መሆኑን ፤ በዚህ አንድ አምላክ ሶስት አካላት ( ስላሴ ) እንዳሉ ፤ ሶስት አማልክት ሳይሆኑ አንድ አምላክ ብቻ እንደሆነ ፤ እርስ በእርሳቸው በዘለአለምነት ፤ በባህሪ ፤ በስልጣን የማይበላለጡ እና እኩል መሆናቸውን ያረጋግጣል።

በዝርዝር እንመልከተው ፦
1. እግዚአብሔር በ3 አካላት ተገልጧል።
---- በብሉይ ኪዳን ------
ሀ. በብዙ ቁጥር መገለፁ

> ዘፍ 1÷26 "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሎያችን #እንፍጠር "
> ዘፍ 3÷22 "አዳምም መልካሙንና ክፉውን ለማወቅ #ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ "
> ዘፍ 11÷6-7 "ኑ እንውረድ ... ቃንቋቸውን በዚያ #አንደባልቀው "
>ኢሳ 6÷8 "የጌታ ድምፅ ማንን እልካለው ? ማንስ #ይሄድልናል ? ሲል ሰማሁ "

እግዚአብሔር በብዙ ቁጥር ወይም አካላት ለመገለፁ እነዚህ ጥቅሶች ከላይ ያየናቸው በቂ ማስረጃ ናቸው።

ለ . ከአንድ በላይ አካላት በአንድ መገለፃቸው ፦
አንዱ አካል ከሌላው አካል ጋር በራሱ ማንነት እንዳለው ሆኖ ሲነጋገርና ራሱን ሲገልጥ በአንድ ጥቅስ ውስጥ በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልጧል።
መዝ 110÷1 "እግዚአብሔር ጌታዬን ....በቀኜ ተቀመጥ አለው። " ይህ አብ ስለ ወልድ የተናገረው ነው ፣ ይህንንም ጌታ እየሱስ ራሱ መሆኑን በግልፅ ተናግሯል። ማቴ 22÷41-46 አዲስ ኪዳንም በብዙ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠው እየሱስ እንደሆነ ይነግረናል። ማር 16÷19 ፣ ሐዋ 1÷55 ፣ ዕብ 8÷1
እንዲሁም በ መዝ 40 ÷6 ላይ " መስዋዕትንና መባን አልፈለክም #ስጋን ግን አዘጋጀህልኝ " እያለ ወልድ ለ አብ የተናገረው እንደሆነ ያሳያል።
ኢሳ 48 ÷16 "ጌታ እግዚአብሔር እና መንፈሱ ልከውኛል " ይላል ይህ ደሞ ነብዩ ስለ አብ እና መንፈስ ቅዱስ የተናገረው ነው።
በተጨማሪም በብሉይ ኪዳን ከአንድ በላይ የሆኑ የስላሴ አካላት በአንድ ጊዜ ወይንም በአንድ ሁኔታ አብረው መገለፃቸው ከእነዚህ ጥቅሶች መረዳት ይቻላል።
ዘፍ 19 ÷24 መዝ 2÷7
መዝ 45 6-7 ሚል 3÷1-2

በአዲስ ኪዳን ላይም እግዚአብሔር በ 3 አካል ተገልፆል ፦
የስላሴ አስተምህሮ ከብሉይ ይልቅ በአዲስ ኪዳን በግልፅ ተቀምጧል። በብሉይ ኪዳን ሶስት መሆናቸውን ግልፅ አድርጎ አያሳየንም። በአዲስ ኪዳን ግን 3 መሆናቸው በግልፅ ተቀምጧል።
ማቴ 3÷16 " እየሱስ በውሀ በተጠመቀ ጊዜ እግዚአብሔር #አብ ከላይ በድምፅ #የምወደው_ልጄ በማለት ሰጠራ #ወልድ ደሞ በውሀ ሲጠመቅ #መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በርግብ አምሳል ሲወርድ " ሶስቱን የስላሴ አካላት በአንድ ላይ ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን።
በማቴ 28÷19 እየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ታላቁን ተልዕኮ ሲሰጣቸው #በአብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ትዕዛዙን ሰጥቷቸዋል። በዚህ ክፍል 3ቱም የስላሴ አካላት አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በእኩልነትና በአንድነት ተገልፀው እናያለን።
በዚህም ለሶስቱ አካላት እንደ ቋንቋ ህግ #ስሞች የሚለው ሳይሆን #ስም የሚለውን እንጠቀማለን። ይህም የእግዚአብሔር በሶስትነት አንድነት ማለትም በአካል 3 በስም 3 በባህሪ ግን አብድ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው።
1ቆሮ 12÷4-6 1ጴጥ 1÷2
ራዕይ 1÷4 2ቆሮ 13÷14

#አንዱ_ለሌላው በሰጠው ምስክርነት
1.አብ ለወልድ ተናግሯል (ማር 1÷11 ፣ሉቃ 3÷22 ፣ ዮሀ 12 ÷28)

2. ወልድ ለአብ ተናግሯል ( ማቴ 11÷25 ፣ ዮሀ 11÷41 )

3. መንፈስ ቅዱስ ስለ አብ ተናግሯል ( ዕብ 3÷7-10)

4. አብ ስለ መንፈስ ቅዱስ ተናግሯል (ዕብ 3÷7-10)

5. ወልድ ስለ መንፈስ ቅዱስ ተናግሯል ( ዮሐ 16 ÷13)

#ሶስቱም_በጥምረት_ተገልፀዋል

ሮሜ 15 ÷30 " ወደ እግዚአብሔር እየፀለያችሁ ... በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እለምናችኋለው። "

2ቆሮ 13 ÷14 " የጌታ የእየሱስ ክርስቶስ ፀጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ህብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን አሜን "

1ጴጥ 1÷1-2 "እግዚአብሔር አብ አስደድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ ይታዘዙና በእየሱስ ደም ይረጩ ዘንድ ..."

#ይቀጥላል

ይህንን መልእክት ለወዳጅዎ ያጋሩ!
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
@borforiconn @abenezzer
ወንጌል ይለውጣል።