🎤ቦርፎሪኮን🎸
1.97K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
667 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
#በስራው

የወረቀት ሰሪ ተርብ

#የቀረቀት ሰሪ ተርቦች የተራቀቀ የምህንድስና ችሎታ እንዳላቸው ምሁራን ይናገራሉ።

#እስቲ_የሚከተለውን_አስብ

እነዚህ ነፍሳት ከግንድ ፣ከእንጨት አጥር እንዲሁም ከደረቁ የእንጨት ጭረቶች ይሰበስባሉ። ከዚያም ሴሊውለስ በተባለው ንጥረ ነገር የዳበረውን ጭረት ከፍተኛ ይዘት ካለውና ከሚያጣብቀው ምራቃቸው ጋር እያዋሀዱ ያላምጡታል። በዚህ መንገድ የተላመጠው ሊጥ የሚመስለው ነገር ሲደርቅ ግን ጠንካራ የሆነ ወረቀት ያስገኛል።

ከዚህም በላይ ምራቃቸው ሙቀት የመሳብ እና የተከማቸው ሙቀት የማስወጣት ልዩ ችሎታ እንዲኖረው ያደርጋል። በመሆኑም እንቁላሎቹ የሚቀመጡበት የቀፎው ክፍል በቀዝቃዛ ቀናት እንኳ ሳይቀር ተስማሚ የሙቀት መጠን ይኖረዋል።
የሚገርመው ደግሞ ከወረቀት ፋብሪካዎች በተቃራኒ እነዚህ ተርቦች ወረቀትን ሲሰሩ አየርን ፣ ውሀንና ምድርን አይበክሉም።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል_?
ከሁለት የአሸዋ ቅንጣቶች የማይበልጥ አንጎል ያላውቸ ነፍሳት ስለ ወረቀት እና ስለ ቀፎ አሰራር ያወቁት በራሳቸው ነው ?

ወይስ እነዚህ ነፍሳት የኬሚካል እና የመካኒካል ምህንድስና ጥበብ ያላቸው መሆኑ አንድ ሰሪ እንዳላቸው ግልጽ አይደለምን ?

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer

ወንጌል ይለውጣል። ቦርፎሪኮን ቻናልን ይከታተሉ።
#በስራው

እጅብ ብለው የሚዋኙ ዓሶች።

#በየአመቱ አንድ ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በመኪና አደጋ የሚሞቱ ሲሆን ወደ 50 ሚሊዮን ገደማ በሚሆኑም ላይ የአካል ጉዳት ይደርሳል።

በሌላ በኩል ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ #ዓሶች እጅብ ብለው የሚዋኙ ቢሆንም አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ፈጽሞ አይጋጩም። ዓሶች ይህንን ማድረግ የቻሉት እንዴት ነው ?

የሰው ልጆችስ የመኪና አደጋ ለመቀነስ ከእነርሱ ምን ልንማር እንችላለን ?

#እስቲ_የሚከተለውን_አስብ

አንድ ላይ እጅብ ብለው የሚዋኙ ዓሶች በአካባቢያቸው ስላለው ነገር የሚያውቁት በአይናቸው እና ላተራል ላይን በሚባል ልዩ የሆነ የስሜት ህዋስ አማካኝነት ነው። በዙርያቸው ያሉ አሶች የሚገኙበትን ቦታ ለማወቅ እነዚህን የስሜት ህዋሳት የሚጠቀሙ ሲሆን እነዚህንንም እርምጃዎችን ይወስዳሉ

1 ጎን ለጎን መዋኘት ፦ ይህንንም ሲያደርጉ ከጎናቸው ካለው አሳ ጋር ርቀታቸውን ጠብቀው በተመሳሳይ በሆነ ፍጥነት ይሄዳሉ።

2 ግጭት ማስቀረት ፦ ሲዋኙ ከሌሎች አሶች ጋር እንዳይነካኩ አቅጣጫቸውን ያስተካክላሉ።

3 መጠጋት ፦ ከነርሱ ርቆ ወደሚዋኘው አሳ ይጠጋሉ።

አንድ #የጃፓን መኪና አምራች ኩባንያ በእነዚህ አሶች ዙርያ ተመርኩዞ በርከት ያሉ የሮቦት መኪናዎችን ሰርቷል።

የሮቦት መኪኖቹ ፕሮጀክት ዋና መሀንዲስ የሆኑት #ቶሺ_ዩኪ_አንዶ እንዲህ ብለዋል "የተራራቁ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀማችን እጅብ ብለው ከሚዋኙ አሳዎች መኮረጅ ችለናል። በተጨማሪም ተሽከርካሪዎችን በማምረት መስክ የተሰማራን ሁሉ እጅብ ብለው ከሚዋኙ አሶች ብዙ ምንማረው ነገር አለ " በማለት ተናግረዋል።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል
እንደዚህ አይነት አሶችን ችሎታውን ያገኙት በአጋጣሚ ነው ወይንስ #ሰሪ_አለው ??

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer

ወንጌል ይለውጣል። ቦርፎሪኮን ቻናልን ይከታተሉ።
#በስራው

የእሳት ራት ዓይን

#አብዛኞቹ የእሳት ራቶች የሚበሩት ማታ ማታ ነው። አንዳንድ በማታ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታት አይናቸው ብርሀን ሲያርፍበት መልሶ ስለሚያንጸባርቅ ማንነታቸዉን እና መኖራቸው ይጋለጣል። #የእሳት ራት ግን ራሱን የሚሰውርበት መንገድ አለው ኮርኒያ የሚባለው የዓይኑ ክፍል ብርሀን እምብዛም አያንጸባርቅም።

#እስቲ_የሚከተለውን_አስብ ፦
የእሳት ራት አይን ለየት ያለ ኮርኒያ አለው ፤ ኮርኒያው 6 ጎኖች ያሏቸው እና በስርአት የተደረደሩ በዓይን የማይታዩ ጉብታዎች አሉት። በዩናይት ስቴት የፍሎሪዳ ዩንቨርስቲ የኬሚካል ምህንድስና ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት #ፔንግ_ጂያንግ ሲናገሩ " ጉብታዎቹ በአይናችን ልናየው የምንችለው ብርሀን ካለው የሞገድ ርዝመት ያነሱ ናቸው " ብለዋል። እነዚህም ጉብታዎች ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጡ ብርሀኖችን ውጦ ለማስቀረት ያስችሉታል።
ጥቃቅኖቹ ጉብታዎች ርዝመታቸው ከ200 እስከ 300 #ናኖ_ሜትር ብቻ ነው። ለማነጻጸር ያክል የአንድ ሰው ጸጉር በአማካይ 80,000 #ናኖ_ሜትር የሚያህል ውፍረት አለው።

መሀንዲሶች የእሳት ራትን ኮርኒያ አፈጣጠር በጥልቀት መረዳታቸው በብዙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እያገለገሉ ያሉትን ላይት ኤሚቲንግ ዳዮድ (LED) እንዲሁም ሊኩዊድ ክሪስታል ዲስፕሌል (LCD) አሰራር ለማሻሻል እንደሚረዳቸው ተስፋ ያደርጋሉ። ከዚህም በላይ የእሳት ራትን አይን ንድፍን የጸሀይ ሀይል ማመንጫዎች ላይ መጠቀም ይቻላል።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል ?
ይህ የእሳት ራት አይን እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይንስ ሰሪ አለው ??

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer
#በስራው

#የሀሚንግበርድ_ምላስ

ተመራማሪዎች መጠኑ በጣም አነስተኛ የሆነ የደም ወይንም የዲ ኤን ኤ ወይንም የሌላ ንጥረ ነገር ናሙና የእጅህን መዳፍ በሚያክል #መስታወት ላይ አድርገው ይመረምራሉ።

ተመራማሪዎቹ መጠናቸው በጣም አነስተኛ የሆኑ ነጠብጣቦችን ለማንቀሳቀስ በመምጠጫ ወይንም በመንፊያ የሚጠቀሙ ቢሆንም እነዚህ ዘዴዎች የሚፈለገውን ያክል ውጤታማ አይደሉም። በጣም ትናንሽ የሆኑ ጠብታዎችን ለማንቀሳቀስ የሚያስችል የተሻለ ዘዴ ይኖር ይሆን ??
#የማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ባልደረባ የሆኑት ዶክተር #ጆን_ቡሽ እንደተናገሩት #ተፈጥሮ ለዚህ ችግር መፍትሄ አለው። " ብለዋል።

#እስቲ_የሚከተለውን_አስብ ፦
ሀሚንግበርፍ የምትባለው ወፍ የአበቦች ማር በመምጠጥ ጉልበቷን አታባክንም። ከዚህ ይልቅ #ውሀ_በጠፍጣፋ_ነገር_ላይ_ሲያርፍ_ጠብታዎች_እንዲሰራ_እንዲሁም_ከስበት_ህግ_በተቃራኒ_እንዲሄድ የሚያደርገውን ሀይል ትጠቀማለች። የሀሚንግ በርድ ምላስ ከአበባው ማር ጋር በሚነካካበት ጊዜ ፈሳሹ ምላሷ እንዲጠቀለልና የአነስተኛ #ቀሰም ቅርጽ እንዲኖረው ያደርጋል።
በዚህ ጊዜ የአበባው ማር ወፏ ሳትመጠው በራሱ ወደ ላይ ይወጣል።
እነዚህ ወፎች በሚመገቡበት ጊዜ በሴኮንድ እስከ 20 ጊዜ በሚደርስ ፍጥነት ምላሳቸው በአበባ ማር መሙላት ይችላሉ።
እንደዚህ አይነት ውሀ ይመጠጣት ዘዴ አንዳንድ የውሀ ዳር ወፎች ይጠቀሙታል።
በዩናይትድ ስቴት ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኘው የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር #ማርክ_ዴኒ ይህን የወፏ ችሎታ አስመልክተው እንዲህ ብለዋል "በዚህ ዘዴ ላይ የሚታየው የምህንድስና ፣የፊዚክስና የሂሳብ ጥበብ ጥምረት በጣም አስደናቂ ነው። ....
ማንኛውም መሀንዲስ ወይም የሂሳብ ሊቅ አንድ ወፍ በምንቃሩ (በመንቁሩ) ወደ ጉሮሮው ውሀ የሚያስገባበት ዘዴ ፈልግ ብትሉት ፈፅሞ ይህን ዘዴ ሊያስብ አይችልም" ብለዋል።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል
ፈጣን በሆነ መንገድ የአበባ ማር የመሰብሰብ ችሎታ ያለው ይህ ወፍ በአጋጣሚ የተፈጠረ ነው ወይንስ ሰሪ አለው ?

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer

ወንጌል ይለውጣል።
#በስራው

የአሳ አመቴ ምንቃር(መንቆር)

በሰአት 300 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚጓዘው የጃፓን የመንገደኞች ባቡር በአለም ላይ ካሉት እጅግ ፈጣን ባቡሮች ውስጥ አንዱ ነው። ባቡሩ ይህን ያህል ፈጣን እንዲሆን አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አሳ አመቴ የምትባለው ትንሽ ወፍ ትገኝበታለች። እንዴት?

#እስቲ_ይህንን_አስብ

አሳ አመቴ የምትወደውን ምግብ ለማግኘት ቁልቁል ወደ ወሀ ውስጥ የምትገባው ምንም ሳታንቦጫርቅ ነው ማለት ይቻላል። ይህ ሁኔታ ፈጣኑን ባቡር የመሞከሩን ሂደት የሚመራው #ኤይጄ_ናካትሱ የሚባለውን መሀንዲስ ትኩረት ሳበው።
አየር ላይ ያለው ግፊት ከውሀ ያነሰ ሆኖ ሳለ ይህች ወፍ ይህንን ለውጥ ግምት ውስጥ በማስገባት ውሀው ሳይረበሽ ሰንጥቃ በመግባት የቻለችው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ጥረት አደረገ።

ይህ ሚስጥር መረዳቱ በፈጣኑ ባቡር አሰራር ላይ የገጠመው ለየት ያለ ችግር ለመፍታት የሚያስችል ቁልፍ ነበር። #ናካትሱ እንዲህ ብሏል " አንድ ባቡር በከፍተኛ ፍጥነት እየበረረ ጠባብ ወደ ሆነ የመሬት ክፍል ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲገባ በአየሩ ውስጥ ሀይለኛ ግፊት እንዲፈጠር የሚያደርግ ሲሆን ይህ ግፊት እየጨመረ ሲሄድ ከማእበል ሞገድ ጋር የሚመሳሰሉ ደምጾችን ይፈጥራል። እነዚህ ሞገዶችም በፍጥነት በመውጣት ነዋሪውን ይረብሻል " ሲሉ ገልፀዋል።

መፍትሄ
የፈጣኑ ባቡር የፊት ክፍል ከአሳ አመቴ ምንቃር ጋር በሚመሳሰል መንገድ እንዲሰራ ውሳኔ ተደረገ።
ታድያ ይህ ምብ ውጤት አስገኘ??

ፈጣኑ ባቡር በአሁኑ ጊዜ ፍጥነቱ 10 % የጨመረ ሲሆን የሀይል ፍጆታውም ከ15 % ቀንሷል።
በተጨማሪም ባቡሩ ወደ መሬት ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲገባ የሚፈጥረው የአየር ግፊት 30 % ቀንሷል። በመሆኑም ባቡሩ በመተላለፊያው ሲሄድ የነበረው ረብሻ ጠፍቷል።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል ?የአሳ አመቴ ምንቃር በድንገት ተሰራ ወይንስ ሰሪ አለው ??

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer
ወንጌል ይለውጣል።
#በስራው

ጄሊ ፊሽ የሚወነጨፍበት መንገድ።

♦ ጄሊ ፊሽ የሚባለው የአሳ ዝርያ ከአጠቃላይ ክብደቱ 95 % የሚሆነው #ውሀ ነው። ጄሊ ፊሾች የተለያየ መጠን ያላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ሰውነትልቸው ሲለካ ከ 3 ሴንቲ ሜትር ያነሰ ርዝመት ሲኖረው ሌሎቹ ደግሞ ከ 2 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት ሊኖራቸው ይችላል።
ብዙዎች የዚህ አሳ ዝርያዎች የሚጓዙት በጡንቻዎቻቸው አጋዥነት እየተወነጨፉ ነው። ይህንንም የሚያደርጉት የደወል ቅርፅ ያለውን አካላቸው ልክ እንደ ዣንጥላ እጥፍ ዘርጋ በማድረግ ነው።

#እስቲ_ይህንን_አስብ ?
ተመራማሪዎች ሀይል የሚቆጥቡ የባህር ሰርጓጅ መርከብ ለመስራት ሲሉ ጄሊ ፊሾች የሚወነጨፉበት መንገድን በማጥናት ላይ ናቸው። አንድ ተመራማሪ ከጄሊ ፊሽ ጋር በሚመሳሰል መንገድ የሚወነጨፍ 1.2 ሜትር ርዝመት ያለው የሙከራ የባህር ሰርጓጅ መርከብ ሰርቷል። ይህ ተሽከርካሪ የሚጠቀመው ሀይል በመደበኛው መቅዘፍያ የሚንቀሳቀሱ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች ከሚጠቀሙት ሀይል በ 30 በመቶ ያንሳል።
ከዚህም ሌላ ጄሊ ፊሾች የሚወነጨፉበትን መንገድ በማጥናት የሰው ልብ ስለሚመታበት መንገድ ተጨማሪ እውቀት ማግኘት ይችላል።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል ?
ይህንን የመሰለ ፍጥረት በዝግመተ ለውጥ የመጣ ነው ? ወይስ ሰሪ አለው ??

ቦርፎሪኮን ቻናል
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer
ወንጌል ይለውጣል።
#በስራው

የአዕዋፍ እንቁላል
#የአዕዋፍ እንቁላል "ተአምራዊ ማሸጊያ" በመባል ይጠራል። ለምን እንዲህ አይነት ስያሜ አገኘ??

#እስቲ_ይህንን_አስብ
በካልሲየም የበለፀገው የዶሮ እንቁላል ቅርፊት ሙሉ በሙሉ ድፍን ቢመስልም በአጉሊ መነፅር ብቻ ሊታዩ የሚችሉ እስከ 8,000 የሚደርሱ ቀዳዳዎች አሉት። እነዚህ ቀዳዳዎች ኦክስጅን ወደ ውስጥ እንዲገባ እና ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ውጭ እንዲወጣ የሚያስችሉ ሲሆን ይህ ደግሞ በእንቁላሉ ውስጥ የሚገኘው ሽል መተንፈስ እንዲችል በእጅጉ ይረዳዋል።
ከፍተኛ መጠን ያለው ውሀ የያዘው #አልቡሚን የተባለ ዝልግልግ ፈሳሽ እንቁሉለ ተንገጫግጮ አስኳሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ያደርጋል።

ተመራማሪዎች የእንቁላል አሰራርን በመኮረጅ ግጭትን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም የሚችሉ ነገሮችን እንዲሁም ፍራፍሬዎች በባክቴርያዎች እና በጥገኛ ተህዋሲያን እንዳይበከሉ የሚከላከሉ ማግጊያዎችን የመስራት ፍላጎት አላቸው።
ይሁን እንጂ #ማሪያን_ቦታ_ዲነ ፣ቪቫይ በተባለው መፅሄት ላይ እንደገለፁት "ተፈጥሮን መኮረጅ እንዲህ የዋዛ አይደለም። "
እኚህ ሴት እንደገለፁት እስከ አሁን የተደረጉት ሙከራዎች ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው።

#ታድያ_ምን_ይመስልሀል?
እንዲህ ያለው "ተአምራዊ ማሸጊያ "ወይም የአዕዋፍት እንቁልላ በአጋጣሚ የተገኘ ነው ወይንስ ሰሪ አለው ??