🎤ቦርፎሪኮን🎸
1.97K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
667 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
#ሳይንስና_እግዚአብሔር

#የክዋክብት_ክብር

ጥርት ባለው ሰማይ ላይ ተረጭተው የሚታዩት ስፍርችቁጥር የሌላቸው ክዋክብትን በምሽት ስታይ አድናቄት ፈጥሮብህ ያውቃል ? ክዋክብት በሚፈነጥቁት ብርሀን ድምቀት ብቻ ሳይሆን በቀለማቸውም እንደሚለያዩ አስተውለህ ይሆናል። #መፅሀፍ_ቅዱስ በትክክል እንደሚገልፀው። "#የአንዱ_ኮኮብ_ክብር_ከሌላው_ይለያል። " 1ቆሮ 15 ÷14

የክዋክብት ክብር ወይንም የብርሀናቸው ድምቀት የሚለያየው ለምንድነው ?ለምሳሌ አንዳንዶቹ ክዋክብት ነጭ ሌሎቹ ሰማያዊ ፣ቢጫ ወይንም ቀይ ቀለም እንዳላቸው ሆነው የሚታዩን ለምንድነው ? ብልጭ ድርግም የሚሉ የሚመስሉትስ ለምንድነው?

ክዋክብት በውስጣቸው #እጅግ በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው ሀይል የሚያመነጭ የኑክሊዬር ማብሊያ አላቸው። ይህ ሀይል ወደ ኮከቡ ውጪኛ ክፍል ይሄድና በአብዛኛው #በኢንፍራሬድ ጨረርና በአይን በሚታይ ብርሀን መልክ ወደ ህዋ ይሰራጫል። #የሚገርመው ነገር በጣም
#ከፍተኛ ሙቀት ያላቸው ክዋክብት #ሰማያዊ ሲሆኑ #ቀዝቀዝ የሚሉት ደግሞ #ቀይ ቀለም አላቸው።

#የምድር_ከባቢ_አየር_የፀሀይን_ቀለም #ይለውጠዋል።

ከባቢ አየር በውስጡ ባሉት ነገሮች የተነሳ ወደ ምድር ከሚመጣው የፀሀይ ብርሀን ውስጥ ሰማያዊ እና ሀምራዊ የሆነውን ቀለም ስለሚበትነው ደመና በሌለበት ቀን ሰማዩ ውብ የሆነ ሰማያዊ ቀለም ይኖረዋል።

ሌላው ፀሀይ ከምትፈነጥቀው ብርሀን ውስጥ ሰማያዊው እና ሀምራዊው ቀለም በዚህ መንገድ ስለሚቀነስ እኩለ ቀን ላይ ፀሀይ ቢጫ ቀለም ይኖራታል። ጀንበሯ(ጸሀይዋ) ወደ አድማስ በምትጠጋበት ጊዜ ወይንም ልትጠልቅ ስትል ግን ብርሀኗ ከባቢ አየሩን በአግድሞሽ ስለሚያቋርጥ በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ረጅም ርቀት ይጓዛል፤ በዚህ ጊዜ የምድር ከባቢ አየር ሰማያዊውና አረንጓዴውን ብርሀን ይበልጥ ይበትነዋል። ስለሆነም የምትጠልቀው ፀሀይ በጣም የምታምር ቀይ ኳስ ሆና ትታያለች።

የስነፈለክ ተመራማሪዎች ጠፈርን በጥልቀት በመረመሩ መጠን ብዙ ከዋክብትንና ጋላክሲዎችን ያገኛሉ። ጠቅላላ ቁጥራቸው ምን ያህል ይሆናል ??? #ፈጣሪያችን_እግዚአብሔር_አምላክ_ግን_መገመት_አያስፈልገውም።

መዝሙረ ዳዊት 147÷4 "የክዋክብትን ብዛት ያውቃል ፤ እያንዳንዱንም በስሙ ይጠራዋል" ይላል።
ነብዩ ኢሳይያስም ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል።
"#አይናችሁን_አንሱ_ወደ_ሰማይ_ተመልከቱ_እነዚህን_ሁሉ_የፈጠረ_ማንነው_የክዋክብትን_ሰራዊት_አንድ_በአንድ_የሚያወጣቸው_በየስማቸው_የሚጠራቸው_እርሱ_ነው። #ከሀይሉ_ታላቅነት_እና_ከችሎታው_ብርታት_የተነሳ_አንዳቸውም_አይጠፉም። ኢሳይያስ 40÷26

ለክዋክብት ክብርን ያለበሰ አምላክ ከኛ አዕምሮ በላይ አይደለምን ???

"ይህች በፎቶው የምትመለከቷት ኮከብ V838 ሞኖሴሮቲስ ትባላለች. ራስዋ በምትፈነጥቀው ብርሀን ውስጥ #ሌሎችንም ከዋክብት ታኖራለች። ክርስቲያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ ከዚህች ኮኮብ ምን እንማራለን ?? ©abenezzer "

ይህንን ቻናል ተቀላቅለው ሳይንስና እግዚአብሔር ን ይከታተሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
@borforiconn
@borforiconn
@borforiconn
👆👆👆👆👆👆👆👆
ያላችሁን አስተያየት @abenezzer ላይ ያድርሱን።

ወንጌል ይለውጣል።
#ድባቴ/ዲፕረሽን ክፍል 2

ተፃፈ ፦ pasror d.r mualtu belayneh ( licensed marriage and family therapist )

ቀረበ ፦ ቦርፎሪኮን ቻናል ✝ ሀምሌ 2011

#ከፍተኛ ለሆነ ድብርት ተጋላጭ የሚያደርጉ ምክንያቶች

-የድባቴ አይነቶች የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የድባቴ መጠናቸው ፣ የጊዜ ገደባቸውና የሚያመጡት ተፅዕኖም የተለያየ ነው።
አንድ ሰው ለድባቴ ተጋላጭ የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶች አሉ ነገር ግን ዛሬ ዋና ዋና የተባሉትን እንቃኛለን።

1.ስነ-ህይወታዊ /biological / መንስኤዎች።

ለድብርት ህመም መንስኤ በመሆን ከሚጠቀሱይ ምክንያቶች የመጀመሪያው ስነ ህይወታዊ ምክንያት ነው።
ከዚህ ስነ ህይወታዊ ምክንያት ውስጥ ለድብርት ህመም መንስኤ በመሆን ተጠቃሽ የሆነው አዕምሮ ጤነኛ ሆኖ እንዲሰራ ከሚያደርጉ ኬሚካሎች መጠን ዝቅ ወይም ከፍ የማለት ሂደት ነው።
አዕምሮ ጤነኛ ሆኖ እንዲሰራ የሚያደርጉ ኬሚካሎች መጠን ዝቅ ወይንም ከፍ በማለት ለውጥ ሲያሳይ ይህ ያጋጠማቸው ሰዎች ለድብርት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
ከመጠን ያለፈ የአልኮል ተጠቃሚ መሆንና ሌሎች ተጠቃሽ ምክንያቶች የሚያሳድሩት የጎንዮሽ ተፅዕኖ ያስከተላቸው ችግሮች ስነ ህይወታዊ ምክንያቶች ሁነው ይጠቀሳሉ።

2. ስነ - ልቦናዊ መንስኤዎች

#በሰው ህይወት የሚከሰቱ ገጠመኞች የሚያመጡት አዎንታዊም አሉታዊ ተፅዕኖዎች መኖራቸው ግድ ነው።
አንዳንድ የህይወት ፈተና እና ገጠመኞች በስነ ልቦና ላይ ፈጥረውት የሚሄዱት ተፅዕኖ ቀላል ላይሆን ይችላል።

#ወጣቶች በድብርት ህመም ውስጥ የመውደቅ ስነ ልቦናዊ ምክንያት ከሚሆኑት ችግሮች መካከል ቅርብ የሆነ ፣ የሚወዱት እናም ተስፋ ሲያደርጉት የነበረ የቤተሰብ አባል ፣ ጓደኛ ፣ ዘመድ
በሞት መለየት ፣ ወላጆች ደስተኛ እና ጤነኛ የሆነ ትዳር ሳይኖራቸው እንዲሁም የቤተሰብ ትዳር በፍች መፍረስ እና መበተን ሌላም ደግሞ የቤተሰብን ኑሮ ችግር ውስጥ የሚከት የገንዘብ ችግር የስራ ማጣት የመሳሰሉት ምክንያቶች ናቸው ወደ ስነ ልቦናዊ ድብርት የሚከቱን።

3.የስነ ጤና የሆኑ መንስኤዎች

ጤነኛ ሆኖ የተወለደ ወይም ገና ሲወለድ የጤንነት እንከን የገጠመው ወጣት በአካሉ ላይ በገጠመው በሽታ ለድባቴ አልፎ ሊሰጥ ይችላል።

አንድ ወጣት በተለይ በአካሉ ላይ ጎልቶ የተቀመጠና በሌሎች ዘንድ በቀላሉ ሊታይ የሚችል የአካል ችግር ከተከሰተበት እናም በዚህ ምክንያት የት.ቤት እና የሰፈር ጓደኞቹ መጠቋቆሚያ እና መሳለቂያ ካደረጉት ወይም #እንዳደረጉት_ከገመተ ለድባቴ ህመም ተጋላጭ ይሆናል።

4.መንፈሳዊ መንስኤዎች

የእግዚአብሔር ቃል የህይወት መርህ በማድረግ የሚመራ ሰው የሚያደርገው ነገር መንፈሳዊ የድብርት ምክንያት ሊኖረው እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው።

በህይወታችን የሚገጥሙን የተለያዩ የክርስትና ፈተናዎች ፣ መከራዎች እና መንፈሳዊ ውጊያዎች ውስጥ ስናልፍ
መፍራት፣ ተስፋ መቁረጥ እናም ጥርጣሬ በውስጣችን ይፈጠራል። ይህም ለድብርት ተጋላጭ ሊያደርገን ይችላል።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን የጠላቱን ወሬ ሰምቶ በመደበቅ ፣ በመተኛት እና ለራሱ ሞትን በመለመን የሚታወቀው ነብዩ ኤልያስ ነው።

ሌላም ደግሞ ልጅ በማጣት ብዙ ስትፀልይ የነበረችው ሀና በላቅሶ ፣ ምግብ ባለመብላት ፣ ደስተኛ ባለመሆንና የልብ ሀዘንተኛ በመሆን ሰካራም ተብላ እስክትጠረጠር መድረሷ ለጊዜውም ቢሆን ማለትም እግዚአብሔር ፀሎቷን እስኪመልስ ድረስ ድባቴ ውስጥ እንደነበረች ምልክቶቹ ይናገራሉ (1ሳሙ 1÷7-8)

ሌላው በአዲስ ኪዳን ተጠቃሽ የሚሆኑት ክርስቶስ እየሱስ ሞቶ ከተነሳ በኋላ በኤማሁስ መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩት ደቀመዛሙርት ለዚህ የድብርት አይነት ምሳሌ ናቸው።(ሉቃስ 24÷13-32)

ስለዚህ የፀሎት መልስ ባላገኘን ወቅት ፣ ስለ እምነታችን የተሳሳተ ግምት ሲኖረንና ዲያቢሎስ በመንፈስ ሲዋጋን ለጊዜውም ቢሆን ለድብርት ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል።

5. ማህበራዊ መንስኤዎች

ይህ ማህበራዊ መንስኤ አንድ ሰው ከለመደው ባህል ፣ ከለመደው ፍቅር ፣ ከለመደው ጓደኛ ፣ ከለመደው አካባቢ ከነዚህ እና ከሌሎች ከተላመድናቸው ነገሮች ርቀን አዲስ ህይወት ለመጀመር ሲያስቡም ሆነ ሲጀምሩ ለድብርት ተጋላጭ ይሆናሉ።
ለምሳሌ ... ወደ ዩኒቨርሲቱ የሚቀላቀሉ ተማሪዎች
እንዲሁም ባህር አቋርጠው ለሚሄዱ ወጣቶች ነገሩን እስኪላመዱት ድረስ ለድብርት ህመም ተጋላጭ በመሆን ሊታመሙ ይችላሉ።

ይቀጥላል ....
በቀጣይ የድብርት ተፅዕኖ ምልክቶች በ @chariisma ቻናል።

ለማንኛውም አስተያየት @abenezzer መጠቀም ይችላሉ።

ቦርፎሪኮን ቻናል ✝
@borforiconn
@borforiconn @abenezzer