🎤ቦርፎሪኮን🎸
1.97K subscribers
478 photos
103 videos
56 files
667 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
🎤🎤ክፍል (6)🎤🎤
👋ሰላም የጌታ ቤተሰቦች🤝

ከባለፎ የቀጠለ....
።።።።።።።።።።።።።
እና ይህች ሴት #ውሃ ብቻ ሳይሆን እውነተኛ #የልብ #ፍቅር የተጠማች ናት።ስለዚህ ነበር ጌታ ኢየሱስ «#አምስት ባሎች ነበሩሽና አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም በዚህስ እውነት ተናግረሻል» በማለት ረሷን ለራሷ የገለጠላት።
#ጌታ በእጁ ውሃ ወይም መቅጃ ሳይዝ ለራሱ እየለመነ የሚጠጣ

🕎«እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ለዘላለም አይጠማም»🕎
ሲላት ግራ መጋባቷ አያስደንቅም? ጌታም ቢሆን የተጠማው ሳምራዊቷ
«አባታቻን ያዕቆብ የሰጠን»

ብላ የምትመካበትን የጉድጓድ ውሃ አልነበረም።ምክንያቱም እሱዋም ስትሰጠው እሱም ስጠጣ አላየንምና።ለደቀ መዛሙርቱ ግን እንደጠጣና፣ እንደረካ መሰከረ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ለካስ ያ የጉድጓድ ወሃ ለንግግር መነሻ ዋለ እንጂ ከተረሳ ቆይቷል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከጥቅት ንግግር በኃላ ጌታም ከውሃው ሳይጠጣ ረካ።ሴትቱም በፈንታው፣ ረክታ ርካታዋን ሊታካፍል እንስራዋን አስቀምጣ ወደ ከተማ ሮጠች። ልብ በሉ እኔነታችን (ማንነትን) የሚያስረሳ ፍቅር !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንግዲህ ልብ እንበል።
።።።።።።።።።።።።።።።
#ከህግ የተነሳ #አይሁድና #በሳምራዊያን መካከል ህብረት፣ እንዳልነበረ ሁሉ በእግዚአብሔርና በሰው መካከልም ያለው ህብረት ኢየሱስ በመስቀል ጥሉን ግድግዳ፣ እስካፈረሰበት ጊዜ ድረስ ለረዥም ዘመናት፣ ተቋረጦ ነበር።

✅ ታድያ ዛሬ በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ መንገዱ ከተዘረጋም በኃላ ራሳችንን የማንረባ፣ የማንጠቅም፣ የተጣለንና ዋጋ የሌለን አድርገን፣ እንድንቆጥር፣ ከሚሰማን ስሜት፣ ከጠላት ከስና ራሳችንንም ላይ ከምናየው ግልፅ ድካም የተነሳ እግዚአብሔር ከኛ ጋር የፍቅር ህብረት ሊኖረው እንደሚፈልግ እንዳናውቅ ከልክሎናል።

ስለዚህም ጌታ የልባችንን የፍቅር ምንጭ ተጠምቶ አጠጡኝ ሲል እንደ ሳምራዊቷ ሴት እንዳላት #እርካታን ለማግኘት በዓለም ያደረግነው መቅበዝበዝና፣ ክንቱ ድካም ሊያሳየንና ከእርሱ ጋር ህብረት በማድረግ የሚሰጠንን የቃሉ ውሃ ከእድፋችን ሊያነፃን ይወዳል።

ከእርሱ ጋር ያለን ህብረት ፈፅሞ የስጋ አይደለም። በመንፈስ የሆነ ህብረት እንጂ።ይህንን ለመግለፅ ነው ሴትቱን፦

#እግዚአብሔር መንፈስ ነው።የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋችኃል ያላት....
።።።።።።።።።።።።።።።።
ይቀጥላል
።።።።።።።።።።።።።።
#ላይክ👍 እና👉 #ሼር ያድርጉ

@borforiconn
@borforiconn
Via @like