🎤ቦርፎሪኮን🎸
2.11K subscribers
477 photos
103 videos
56 files
628 links
♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️
ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው።
ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ
ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ።
We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm
Download Telegram
#የቃል #ስንቅ

"እንደ ሥጋ ፊቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁ÷ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሼል ብትገድሉ በህይወት ትኖራላችሁ ። በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና "      ሮሜ 8:13-14

             🤔አስተውሉ ‼️
መጽሐፍ ቅዱስ ያለ እርሱ ፊቃድ የበላ ተድላንም የቀመሠው ማነው?ይለናል ።

⭕️እንዴት በመንፈስ ቅዱስ ድምፅ መመራት እንችላለን? በቀደመችው በጥንቷ ቤተክርስቲያን በብዙ ምሳሌ የሚሆኑ ሐዋርያት ያለ መንፈስ ቅዱስ መሪት አይወጡም ፣አይገቡም ነበር ! ሌላው ይቅርና ወንጌል ለመስበክ እንኳ በመራቸው መንገድ ነው።

⭕️ታዲያ ዛሬ ዛሬ የወንጌል አግልግሎት መልኩን ቀይሮ #ሶስት_በአራት በሆነ ክላስ እንትና እና እንትና አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በመባል አጠገብ ያለውን ወንድሙን እህቱን ሳያቅፍ አለምአቀፋዊ ስንል አናፍርም።

⭕️በሶሻል ሚዲያ #አምስቱን #ጣታችን በሞባይል እስክርናችን እየጫነን ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እያለን የምንተዳደር ብዙ ነው ።ይሁን ሰው ከተጠቀመበት ከተፈወሰበት ነፍሳት ከዳኑበት እና ክርስቶስ ከከበረበት !

     ⭕️ነገር ግን ጥያቄው እውነት እየተከበረ ነው? ራሳችን እንጠይቅ! በተሰጠን ምቹ ድረገጽ ነፍሳትን ከማዳን ለምድኑ ልድኑ ላሉ  እንቅፋት የሆንንበት ሁኔታ እንደሆነ ሁላችንም የሚናቀው እውነት ነው ።
    ✅እንድናገለግል እግዚአብሔር ጥሪ ስያደርግልን á
1. እንድንዘጋጅ (Let us prepare) ይፈልጋል ማለት ነው።
2. በፀሎት እንድንቆይ(devotion time ) እያሳሰበን ነው።
3. እግዚአብሔር የጊዜ አምላክ ስለሆነ ጊዜውን እስክናውቅ ጠብቅ እያለን ነው(God is the God of time).
4. ራሱ ጨርሶልን ጊዜው ነው ስል ስንወጣ ለተናገረው ነገር ራሱ provide ያደርጋል !! Gods provided your everything .

✅ማንኛውም የረጋ ወተት ቅቤን ያወጣል!🤔🤔🤔🤔🤔🤔🤔

ጆን እንደፃፈው t.me/yekal_sink