Bole woreda 11 communication
181 subscribers
2.41K photos
22 videos
10 files
151 links
Bole Woreda 11 administration's communication office.
Download Telegram
የ3ኛ ሩብ ዓመት የብልፅግና ፓርቲ አባላት ኮንፍረንስ ተካሄደ ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ3ኛ ሩብ ዓመት የብልፅግና ህብረት ኮንፈረስ የቢሮ ማህበራዊ መሠረት ተካሄደ ።

የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቸርነት ለማ በጠንካራ የፓርቲ አባላት ተሳትፎ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ወሳኝ እንደሆነ ገልፀው አባላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማድረጋቸው ለብልፅግና ፓርቲ ተቋም ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳለው በመገንዘብ በጋራ አባላቱን በሀገራዊ ጉዳይ ፥ በሰላም ጉዳይ፥ በልማት ጉዳይ ግንባር ቀደም መሆን እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።

በመድረኩ የብልፅግና ህብረት አመራሮችም በዘጠኝ ወር ውስጥ የተሰሩትን በርካታ ስራዎችንም በሪፖርት በማቅረብ እንደተሞክሮ የሚወሰዱትን ጥንካሬዎች የማስቀጠልና ክፍተቶችን የማረም ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይም እንደሆነም ገልፀዋል ። በመጨረሻም የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን በ9 ወር የተሰሩ ስራዎችን በሪፖርት በማቅረብ ተጠናቋል ።

#ሚያዝያ_17_2017_ዓ_ም_
ተግባራቶችን አቀናጅቶ መምራት ለውጤታማ አፈጻጸም !!

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ከጠቅላላ አመራሩ ጋር ወቅታዊ እና መደበኛ ተግባራቶችን
ገመገመ

በመድረኩ ከስራ እድል ፈጠራ ፣ ከገቢ አሰባሰብ ፣ ከሰላምና ፀጥታ ስራዎች ከውስጠ ፓርቲ ስራዎች ፣ ከውጤታማ ለአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ሁሉንም ተግባራትን በአግባቡ በፍጥነት ፣በጥራት በማጠናቀቅ በጀት አመቱን በስኬት መጨረስ የሚገባ መሆኑን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አማን ሀምዳ እና የወረዳው የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ቸርነት ለማ በጋራ ገልፀው

በመጨረሻም በቀጣይም ልዩ ትኩረት በሚፈልጉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

#ሚያዝያ_17_2017_ዓ_ም_